TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬇️

ፖሊስ በቡራዩ ከተማና አካባቢው ከተፈጸመው ወንጀል ጋር በተያያዘ የተለያዩ #መረጃዎችን መያዙን ገለጸ።

በቡራዩ ከተማና አካባቢው በተፈጸመ ወንጀል በማስተባበር፣ በማነሳሳት፣ ገንዘብ በማከፋፋል እና በመኪና በመሸኘት የተጠረጠሩ እነ #ሳምሶን_ጥላሁን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ ሃሰተኛ መታወቂያ፣ የመንግስት መሃተምና ቲተር እንዲሁም በቤት ውስጥ 74 #ገጀራና ቢላ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ በተጠረጠሩት ሳምሶን ጥላሁን፣ አለሙ ዋቅቶላ፣ ቡልቻ ታደሰ፣ ሃሺም አሚር፣ ሽፈራሁ ኢራና እና አሊ ዳንኤል አስተያየት እና መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራን አዳምጧል።

መርመሪ ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለ ጀምሮ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ባንኮች የገንዘብ ዝውውሩን እንዲገለጽ ደብዳቤ መላኩን ገልጿል።

1ኛ ተጠርጣሪ ሳምሶን ጥላሁን የነዋሪዎችን መሬት #በመቀማትና ለሌለች አሳልፎ በመስጠት ግጭት አንዲፈጠር ማድረጉን ፖሊስ መረጃ እንዳለው ገልጿል።

የበርካታ ወጣቶች ፎቶና ሃሰተኛ መታወቂያ የመንግስት #መሃተምና ቲተር በተጠርጣሪው እጅ መገኘቱንም አስረድቷል።

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አቀባበል ድጋፍ በወጡ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ፓስተር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሽጉጥ መተኮሱምን ነው ፖሊስ የገለጸው።

ሶስተኛ ተጠርጣሪም በቡራዩ በቤቱ ውስጥ ለወንጀሉ መፈጸሚያ የሚውል 74 ገጀራና ቢላ መያዙን የገለጸው። ፖሊስ የቀሩ ተጠርጣሪዎችም መስከረም 5 #በመንግስት_ተሽከርካሪዎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ማመላለሳቸውንና ገንዘብ ማከፋፈላቸውን ለችሎቱ አብራረቷል።

ለተጨማሪ መረጃ የሟቾችን አስከሬን ምርመራ ውጤት እና የተባባሪ ግብረሃይሎችን በቁጠጥር ስር ለማዋል የ28 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድቤቱን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ሳምሶን ጠበቃ በበኩላቸው ፖሊስ በተናጠል እና በዝርዝር የያንዳንዳቸውን ተሳትፎ አልገለጸም አሁን ሽብር ድርጊት ነው፣ የተባለውም ተጠርጣሪዎችን በእስር ለማቆየትና ዋስትና ለማስከልከል ነው፤ ፍርድ ቤቱ ይህን ከግምት አስገብቶ ዋስትና ይፍቀድና ክርክሩን በውጭ ሆነው ያካሂዱ ሲሉ ጠይቀዋል።

ተጠረጣሪዎቹ ሁሉም በተናጠል በአንደበታቸው ፖሊስ እያደረገው ያለው ምርመራ አኛን ለማሰር ነው ወንጀሉን አልፈጸምንም፣ አያያዛችንን በተመለከተ ከአይምሮ ህሙማን ጋር ታስረን #ስንሯሯጥ ነው የምናድር፣ ጨለማ ውስጥ ነው የታሰረነው ሰባዊ መብታቸን ይጠበቅ የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበው ምርመራ የሸብር ድርጊት መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን፥ ዋስትና አያሰጠም ሲል ለመርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አከናውኖ እንዲቀርብ ለጥቅምት 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የተጠርጣሪዎችን ሰባዊ አያያዝ በተመለከተም የአዲስ አበባ ፖሊስም ሆነ ፌዴራል ፖሊስ ማስተካከያ አንዲያደረግ ትዛዝ ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ወንጀል የተጠረጠሩ ከ250 በላይ ተጠርጣሪዎች ለዛሬ በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት በቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እየሰጡ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ፖሊስ እስካሁን በተሰጠው የ14 ቀን ጊዜ ከወንጀሉ ውስብስብና ሰፊ መሆን ጋር ተያይዞ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም የተጠርጣሪዎችን ቃል ተቀብሏል፤ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን የምስክርነት ቃል ለመቀበልና ዝርዝር ምርመራ ለማከናወን ተጨማሪ 14 ቀን ጊዜ ጠይቋል።

በዚህም የወረዳው ፍርድ ቤትም ለፖሊስ የስምንት ተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦቦ ለማ መገርሳ!

#በመንግስት ላይ የሚያያቸውን ጉድለቶች ሕዝቡ #በግልፅ በመናገር እንዲታረሙ ማድረግ አለበት ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ፡፡

Via Sheger FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሸዋሮቢት ውስጥ የሰውም ሆነ የባጃጅ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል። የከተማው አስተዳደር ፤ ለከተማው ሰላምና ጸጥታ ሲባል ማንኛውም የባጃጅና የሰው እንቅስቃሴ ከምሽቱ 12 ስዓት ጀምሮ የተከለከለ ነው ሲል አሳውቋል። ለተላለፈው ትዕዛዝ ሁሉም ትብብር እንዲያደርግ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል። ከሰሞኑን በዚሁ ቀጠና ዳግም ግጭት ተቀስቅሶ በርካቶች የደህንነት ስጋት ላይ ወድቀዋል። @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፤ " ሰሞኑን በሸዋሮቢት እና በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በተደረገ ጦርነት በርካታ የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረትም ውድሟል " ሲል አሳውቋል።

የንብረት ውድመት የደረሰባቸው የከተማው የ05 ቀበሌ ነዋሪዎች #በመንግስት_ቸልተኝነት እና #የላላ_ህግ የማስከበር ተግባሩ የተነሳ በየአመቱ ለሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት ውድመት ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ፤ ውፍጮ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ሙሉ በመሉ መውደማቸውን በመግለጽ መንግስት በዚህ ቀጠና ያለውን ጦርነትና የተደራጀ ቡድን ወይም  ኃይል በማጥራት የመንግስት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ከሰሞኑን በደረሰው ጥቃት በርካታ ሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን የህዝብ መገልገያ ትምህርት ቤቶች ፣ ወፍጮ ቤቶች ፣ የጤና ክሊኒኮች ፣ ሱቆች ፣ የቀበሌ አስተዳደር ቢሮዎች ፣ የግለሰብ ቤቶች ወድመዋል።

ነዋሪዎች የሚመለከተው የበላይ የመንግስት አካል ልዪ ትኩረት ሰጥቶ ህይወታችንን ሊታደግ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Photo Credit : የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዓድዋ በዓል በአዲስ አበባ ? ዛሬ የዓድዋ ድል በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ነው። በመዲናዋ በሚገኘው የአፄ ሚኒሊክ ሀውልት ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ እንዳልነበር ወደ ስፍራው የሄዱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የቤተሰባችን አባል እንዲህ ሲል ዛሬ ጥዋት የተመለከተው አስረድቷል፦ " በመጀመሪያ ከጥቁር አንበሳ ጀምሮ ቀይ ለባሾች፣ አድማ በታኞች እና የፌዴራል…
#ዓድዋ

ዛሬ በምኒሊክ አደባባይ አካባቢ ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያያዘ ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ሰሜን ሆቴል አካባቢ ወደ ምኒሊክ አደባባይ እና ወደ ቅዱስጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ማለፍ ተከልክሎ እንደነበር ገልጿል።

" አስለቃሽ ጭስ እና ድንጋይ ውርወራ ነበር " ያለው ይኸው ቤተሰባችን አባል አንዳንድ ወጣቶች ላይም ድብደባ ተፈፅሟል " ሲል አስረድቷል።

በተመሳሳይ ፤ ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ዛሬ የፌደራል ፖሊሶችና አድማ በታኞች ወደ ጊዮርጊስ መስመር የሚሄደውን ሰዉ ከሰሜን ሆቴል እና ከዮሀንስ ቤ/ክ አካባቢ ማለፍ አይቻልም በሚል እየመለሱ እንደነበር ገልጿል።

እስካሁን #በመንግስት_አካላት በኩል በምኒልክ አደባባይ ስለነበረው እና ስለተፈፀመው ሁኔታ ማብራሪያ አልተሰጠም።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የድል በዓሉ በአደባባዩ መከበሩን በስፋት ዘግበዋል።

#ዓድዋ127

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል። የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ…
#MoE #ይፋዊ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ #ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #የመውጫ_ፈተና ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በመገኝበት…
#MoE

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎችን አፈፃፀምን በተመለከተ ለህ/ተ/ም/ቤት ባቀረቡት ሪፖርት የ2015 የፈተና ዝግጅትን በተመለከተ አብራርተዋል።

ለ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፣ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በየትምህርት አይነቱ እራሱን የቻለ የፈተና ዝግጅት ቢጋር እንዲዘጋጅ ተደርጓል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ " የ12ኛ ክፍል ዋናና የሙከራ ፈተና በፈተና በቢጋሩ መሰረት ከተለኪ ባህሪያት አንፃር ተገቢና አስተማማኝ ጥያቄዎችን በጥንቃቄና #ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በተዘጋጀ የስራ መመሪያ ቼክ ሊስት መሰረት በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከቀናት በፊት ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የሬሜዲያል ተማሪዎች ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትላንት ይፋ በተደረገው የማካካሻ ትምህርት / ሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከተደረገላቸው በኃላ ለ4 ወራት የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ሲሆን ይህንን ተከታትለው በተቋማቸው እና በማዕከል የሚሰጣቸውን ፈተና ማለፍ ሲችሉ በቀጣይ መደበኛ ተማሪ ሆነው ወደ ፌሽማን ይቀላቀላሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የመቁረጫ ነጥብ በሁሉም አማራጮች ማለትም #በግል እና #በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ይህም ማለት 210 ከ700፣ 180 ከ600 እና 150 ከ500 ማስመዝገብ አለባቸው።

በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) በዩኒቨርሲቲ ተመድበው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ በ #ተፈጥሮ_ሳይንስ የመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች መቁረጫው 255 ከ700 ነው። የሴት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫው ደግሞ 234 ከ700 ነው።

በዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚማሩ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡ 218 ከ600 ሲሆን ፤ የሴት ተማሪዎች መቁረጫው 200 ከ600 ነው።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ዘንድሮ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው ይማራሉ።

#ማስታወሻ ፦ የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

በሌላ በኩል ፤ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ ከትላንት ጀምሮ ይፋ የተደረገ ሲሆን የምደባ መመልከቻው ፦በድረገፅ https://result.ethernet.edu.et/
የቴሌግራም ቦት @moestudentbot መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ለኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደብዳቤ ፃፈ።

ፓርቲው በዚህ ደብዳቤው ፤ " የፓርቲ አባል ያልሆኑ የመንግሥት ሰራተኞች በብልፅግና ፓርቲ ስልጠና እንዲሳተፉ የሚደረግበት አሰራር እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።

ነእፓ ፤ #የመንግስት እና #የፓርቲ መደበላለቅ በለውጡ ማግስት መጠነኛ መሻሻል አሳይቶ እንደነበር አስታውሷል።

ነገር ግን በተለይ ከ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ጀምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ብሏል።

ከቅርብ ወራት ጀምሮ ገዢው ፓርቲ እያካሄደ ባለው የአባላት ስልጠና፣ የፓርቲው አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች (Public servants) የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑ ለዚህ አንድ ማሳያ ነው ሲል አስረድቷል።

ፓርቲው አለኝ ባለው መረጃ የገዢው ፓርቲ አባላት ያልሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ስልጠናውን እንዲወስዱ በተለያየ መንገድ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጿል።

ይባስ ብሎ በየአካባቢው እየተካሄዱ ያሉ ስልጠናዎች ፦
- አበል፣
- ትራንስፖርት፣
- ሆቴል እና ሌሎች የስልጠና ወጪዎች የሚሸፈኑት #በመንግስት_በጀት መሆኑ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ብሏል።

በመሆኑም የፓርቲ አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች የገዢውን ፓርቲ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ ህገ መንግስቱን እና የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ስርአት አዋጃ ቁጥር 1162/2011 የሚቃረን በመሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ድርጊቱ ይቆም ዘንድ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

በቀጣይ ተመሳሳይ የህግ ጥሰቶች እንዳይፈጠሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድም አሳስቧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት፤ ገዢው ፓርቲ የስልጠናና ሌሎች ድርጅታዊ እንቅስቃሴውን በመንግስት ሀብት የሚሸፍንበት አሰራር ህግ እና ስርአትን ያልተከተለ ከመሆኑም ባሻገር የፖለቲካ ሜዳውን የሚያዛንፍ በመሆኑ፣ ድርጊቱ ይታረም ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

በተለይም ፦
- የምርጫ ቦርድ፣
- የገንዘብ ሚንስቴር
- የክልል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ቢሮዎች፣
- በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምከር ቤቶች አዋጁን በማስከበር ገዢው ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሩን ከመንግስት መዋቅር ለይቶ እንዲሰራ ኋላፈነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia