TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

"የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም" - አሜሪካ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ፤ ትላንት እሁድ በሰጡት ቃል አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ብቸኛው መፍትሄ ዲፕሎማሲ ነው ብላ ታምናለች ብለዋል።

ከTeN የሳተላይት ቻናል ቃለምልልስ የነበራቸው ዋርበርግ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ለአፍሪካ አህጉር እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ዓላም አቀፉ ማህበረሰብ የህዳሴው ግድይ ጉዳይ ለናልይ ተፋሰስ ቀጠና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ተገንዝቧል ብለዋል።

ዋርበርግ፥ የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው በማንሳት "በአፍሪካ አህጉር ምንም አዲስ ጦርነት ልንገምት አንችልም" ብለዋል።

የተፋሰሱ አገራት እና የ #አፍሪካ_ህብረት ድርድርን እንደገና መጀመር እንዳለባቸው ጠቁመው አሜሪካ ማንኛውንም የፖለቲካ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ዋርበርግ፥ "ውይይቱን ለመቀጠል አሜሪካ ሁሉም ወገኖች ከማንኛውም መግለጫ እንዲታቀቡ ጥሪ ታደርጋለች ፤ የሚደረገው ማንኛውም ውይይት ድርድሮችን ወደፊት ለማስቀጠል ያለመ መሆን ይገባዋል" ብለዋል።

አሜሪካ ድርድሩ ላይ የበለጠ ጊዜ እንዲያልፍ አትፈልግም ብለዋል።

@tikvahethiopia
#GoE

የፌዴራል መንግስት በቅርቡ ወደ ትግራይ ፣ መቐለ ተጉዞ የነበረው የዲፕሎማቶች የልዑካን ቡድን " የህወሃትን የውሽት ትርክት አስተጋብቷል፤ ይህም ስህተት ነው " ብሏል።

ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ላይ መንግሰት በራሱ ተነሳሽነት የተኩስ አቁም ስምምንት ለማድርግ ወሰኖ እንደነበር እና አሁንም #ለሰላም ውይይት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የምግብ ድጋፍ በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት ተደራሽ እየተደረገ ነው ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " መንግስት ወደ ትግራይ የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ ባላቋረጠበት እና ክልከላዎች ባላደረገበት ወደ መቐለ ተጉዞ የነበረው የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኞችን የያዘው የዲፕልማቶች ቡድን የህወሓት የውሽት ትርክት ማስተጋባቱ ስህተት ነው " ብለዋል።

መንግስት በ #አፍሪካ_ህብረት በኩል የሚካሄደው የሰላም ውይይት ሁሌም በማንኛውም ቦታ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት በህወሃት በኩል ከሰላም ድርድር ፍላጎት ይልቅ አሁንም የጦርነት ጉሰማዎችና ለሰላም ውይይት እንቅፋት የሚሆኑ ንግግሮች እየተሰሙ ነው ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ለዜጎች ሰላም እና ከጦርነት ጭንቀት እረፍት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተስፋ ጭላጭል " ሙሉ በሙሉ " ይከስም ይሆን ? የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ዛሬ ፤ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ " ህወሓት " በምስራቅ ግንባር በቢሶበር ፣ ዞብል ፣ እና ተኩለሽ በኩል ከለሊት 11 ሰዓት አንስቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል። በዚህ እርምጃውም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል ብሏል። ዜጎችን ከ "ህወሓት"…
#ተመድ #አፍሪካ_ህብረት

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ፤ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን በመስማታቸው ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ፤ ዛሬ ከሚካሄድ የፀጥታው ም/ ቤት ስብሰባ አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ በጣም ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን የገለፁት ጉተሬዥ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ተማፅነዋል።

" ኢትዮጵያውያን ትግራዋዮች፣ አማራዎች፣ ኦሮሞዎች ፣ አፋሮች ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

" አጠንክሬ የምጠይቀው በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግና የመንግስትና የህወሓት የሰላም ድርድር እንዲቀጥል ነው " ብለዋል።

ጉተሬዥ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሙሉ ዋስትና እንዲሰጠው ፤ በተጨማሪ የህዝብ አግልግሎቶች ተመልሰው እንዲቋቋሙ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በኢትዮጵያ እንደገና ወታደራዊ ግጭት መፈጠሩን የሚገልፁ ሪፖርቶች መስማታቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል፤ ሁኔታውን እየተከታተሉ መሆኑንም አመልክተዋል።

ሊቀመንበሩ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ንግግሩ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት #የሀገሪቱን_ጥቅም_ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ሂደትን ለመደገፍ ከሁሉም ወገን ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ ነው ሲሉ አረጋግጠዋል።

ለዚህም ሁሉም ወገኖች ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia