TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.6K photos
1.39K videos
200 files
3.74K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#LiveUpdate የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በጊዜ ሠሌዳው ቅደም ተከተል መሠረት በመከናወን ላይ ስላለው የመራጮች ድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት እና አጠቃላይ የቴክኒክ ሥራዎችን አስመልክቶ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ለሚዲያዎች መግለጫ ይሰጣል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሚገኙ ሲሆን በሚነሱ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃዎችን የምንለዋወጥ…
#BREAKING

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በገጠሙ የህትመት ችግር፣ የጸጥታ ሁኔታና የዳታ ችግር ምክንያት በሁለት ዙር እንደሚካሄድ አስታውቋል።

ሁለተኛው ዙር ምርጫም ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሆን ቦርዱ ወስኗል።

በሁለተኛ ዙር ምርጫ የተካተቱት አካባቢዎችን ዝርዝር ሲገለፅ እናሳውቃችኃለን።

በሌላ በኩል፥ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ መራዘሙን ቦርዱ አስታውቋል።

የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ይደረጋል ተብሏል።

PHOTO : Tikvah-Family
@tikvahethiopia
#Update

በተሻሻለው የምርጫ 2013 ተመዝጋቢዎች ቁጥር ሪፖርት መሰረት አጠቃላይ የመራጮች ቁጥር 37,408,600 መድረሱን ያሳያል።

ከነዚህ ውስጥ 20,317,472 ወንዶች ሲሆኑ 17,091,128 ሴቶች ናቸው።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የኢትዮጵያ ብሄራቂ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14/2013 የሚካሄደው 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ በሶማሌ ክልል እንደማይካሄድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ፥ ለምርጫው በተያዘለት ጊዜ አለመካሄድ የህትመት ችግር እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎችን በምክንያትነት አስቀምጠዋል።

የክልሉ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት እጩዎች ጷግሜ 1 ቀን 2013 ዓ/ም በሚካሄድ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይመረጣሉ መባሉን አል ዓይን ዘግቧል።

PHOTO: Tikvah-Family
@tikvahethiopia
#Update

ድምፅ መስጫ ወረቀቶች በድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው የምርጫ ክልሎች ከላይ በዝርዝር የተገለፁት ናቸው።

#ምርጫ2013 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 6,069 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 280 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 273,678 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 5 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,231 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,920,676 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማክሮን በስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ። ፕሬዚደንቱ በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ #ደሮም_ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ እያሉ ነው በጥፊ የተመቱት። ማክሮን በተከለለ አጥር ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ሰላም ለማለት ጠጋ ሲሉ ነው ክስተቱ የተፈፀመው። ፕሬዚዳንቱ በጥፊ ሲመቱ “ Down with Macron-ism ” የሚሉ ቃላት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዜዳንት ማክሮንን በጥፊ የመታው ግለሰብ ተፈረደበት።

የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በሥራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ የተማታው ግለሰብ 18 ወራት እስር ተፈርዶበታል።

ዳሚኤን ታሬል የተባለው ግለሰብ ፕሬዝደንቱን መማታቱን ለፍርድ ቤት በሰጠው ቃል አምኗል። ዐቃቤ ሕግ ግለሰቡ ሆነ ብሎ የኃይል እርምጃ ወስዶ ፕሬዝደንቱን ተማትቷል ሲል ከሶታል።

በጥፊ የተማታው ግለሰብ "ማክሮኒዝም ይውደም" እያለ ነው ፕሬዝዳንቱን በጥፊ የመታቸው።

ፍርድ ቤቱ ግለሰቡ ላይ የ18 ወራት እስር ቢፈርድበትም 14ቱ በይርጋ የሚታይ ይሆናል ብሏል።

ማክሮንን በጥፊ በመማታት ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ የ4 ወራት እስሩን የሚጀምር ሲሆን በቀጣዮቹ 18 ወራት ውስጥ ጥፋት አጥፍቶ ቢገኝ የ18 ወራት ፍርዱ የጸና ይሆናል።

ማክሮንን በጥፊ የተማታው ዳሚኤን ታሬል ፕሬዝደንቱን ለምን እንደተማታ ሲጠየቅ፤ ከጓደኛው ጋር የፕሬዝደንቱን ጉብኝት መኪናቸው ውስጥ ሆነው እየጠበቁ ሳለ በሁሉም ዘንድ የሚወሳ ተግባር ለመፈጸም ማቀዱን ተናግሯል።

ግለሰቡ ኃይል የመጠቀም ሃሳብ አልነበረኝም ብሏል።

ፕሬዝደንቱ ላይ እንቁላል ወይም ክሬም ኬክ ለመወርወር አቅዶ የነበረ ቢሆንም ፕሬዝደንቱ ቀርበውት "ድምጼን [የምርጫ] ልሰጠው እንደምችል ሲገምተኝ በጣም ተበሳጨሁ" በማለት ተናግሯል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

Video Credit : AlexpLille

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ልማት አመራሮች በትግራይ ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ተሰምቷል። ውይይቱ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ እንደሆነ ይጠበቃል። ስብሰባው በትግራይ ክልል ባለው የሰብዓዊ ቀውስና ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ማዕቀፍ ውስጥ አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ…
#Update

ዛሬ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብዓዊ ቀውስን በተመለከተ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት (EU) ከፍተኛ ባለስልጣናት በኦንላይን ውይይት አድርጋዋል።

የዛሬው ውይይት ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በቀጥታ ተላልፏል።

በውይይቱ እነማን ተሳተፉ ?

- በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ፣
- የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር፣
- የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ
- የአውሮፓ ሕብረት የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌነርቼክ
- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ተሳታፊ ሆነውበታል።

እነንማን ምን አሉ የሚለውን በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-06-10

በሌላ በኩል በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዛሬ በዚህ መድረክ ባሰሙት ንግግር ነገ የቡድን ሰባት (G7) አገራት ሰብሰባ እንደሚኖራው ገልጸው ፤ ከG7 አገራት አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጉዳይም የተባበሩት መንግሥታት (UN) የጸጥታ ም/ ቤት አጀንዳ መሆን አለበት ብለዋል። ፌልትማን ረሃብ የጦርነት መሳሪያ ተደርጎ መወሰዱ የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት አጀንዳ ያደርገዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

ተኩስ እንዲቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረስ እና የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ጫና ማድረጋችንን መቀጠል አለብን ብለዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
'የNISS ጥቆማ መቀበያ 910 '

ዜጎች ማንኛውም አይነት ለሀገርና ህዝቦች ሰላምና መረጋጋት እንቅፋት የሚሆኑና ከሀገራዊ ምርጫው ጋር በተያያዘ የደህንነት ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በአቅራቢያቸው ሲመለከቱ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አጭር የጥቆማ መስጪያ ቁጥር " 910 " በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ተገልጿል።

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ ብሄራቂ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14/2013 የሚካሄደው 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ በሶማሌ ክልል እንደማይካሄድ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ፥ ለምርጫው በተያዘለት ጊዜ አለመካሄድ የህትመት ችግር እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎችን በምክንያትነት አስቀምጠዋል። የክልሉ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት እጩዎች…
#UPDATE #ምርጫ2013

ከሶማሌ ክልል በተጨማሪ በሐረሪ ክልል ሰኔ 14 ቀን 2013 ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ እንደማይካሄድ ተገልጿል።

በሁለቱም ክልሎች ምርጫው ጳጉሜ 1 የሚካሄድ እንደሚሆን ተገልጿል።

በሶማሌ ክልል ምርጫው የተራዘመበት ምክንያት ከዚህ ቀደም በመራጮች ምዝገባ ላይ በታዩ ቅሬታዎች ምክንያት ምርጫው እንደማይደረግ ከተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች በተጨማሪ አሁን ላይ በተፈጠረው የህትመት ችግር መሆኑ ተጠቅሷል።

ቦርዱ በትላንትናው ዕለት 54 የምርጫ ክልሎች ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት እንደሚያስፈልጋቸው ገልጾ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በድጋሜ ህትመታቸው ተጠናቆ ለሰኔ 14ቱ ምርጫ የሚደርሱትን መለየቱን ዛሬ አስታውቋል።

በቀጣይም የህትመት ሁኔታው እየታየ ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፥ ቀጣይ ሂደቶችን በተከታታይ አሳውቃለሁ ብሏል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopia
#NewsAlert

የኦሮሚያ ፖሊስ ከሌሎች ፀጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር 95 የ "ኦነግ ሸኔ" ታጣቂ ቡድን አባላትን መደምሰሱን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳወቀ።

የምስራቅ ኦሮሚያ እና የደቡብ ኦሮሚያ ዞን ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ በመጣመር ከተለያዩ ጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ለተከታታይ 4 ቀናት በልዩ ሁኔታ ኦፕሬሽን ተካሂዷል ሲል ገልጿል።

በዚህ ኦፕሬሽን ህዝቡን በመዝረፍ፣ በማሰቃየት እና በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል የነበረ ያለውን የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ 95ቱ ተደምስሰዋል ብዙዎቹን ቁስለኛ ሆነዋል ብሏል።

ልዩ የነው የተባለው ኦፕሬሽን ስራ የተሰራው በደቡብ ኦሮሚያ በጉጂ ዞን እና በቦረና ዞን ሲሆን ግንቦት 24 ፣ ግንቦት 25 ፣ ግንቦት 26 ፣ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ነው ተብሏል።

በኦፕሬሽኑ ሙት እና ቁስለኛ ከሆኑት የታጣቂ ቡድኑ አባላት በተጨማሪ ብዛት ያላቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መማረኩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

ፖሊስ ማረኩኝ ካላቸው የጦር መሳሪያዎች መካከል ፦ ብሬን፣ ክላሽ ፣ SKS (ኤስ ኬ ኤስ) M14 (ኤም14) ይገኙበታል።

በተጨማሪም፦ ሞተር ሳይክሎች፣ የተለያዩ መድኃኒቶች፣ የምግብ ሬሽን ኮሾሮ፣ ፓስታ፣ እና የተለያዩ የምግብ እቃዎችን መማረኩን ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ኦፕሬሽኑ እንዲሳካ ላደረገው ህዝብ ምስጋና አቅርቧል።

በተጨማሪ የሶማሌ ክልል ፖሊስ በተለይ የዳዋ እና ሊበን ዞን ፖሊሶች ላደረጉት ትበብር ምስጋና አቅርቧል በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ።

@tikvahethiopia
የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ?

ወደ #ኤርትራ ለሥልጠና ተልከው የነበሩ በሺዎች ሚቆጠሩ የሶማልያ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ በተደረገው ውጊያ ተካፋይ ሆነዋል በሚል፣ በዚህ ሳምንት በወጣው ሪፖርት የተነሳ በሶማልያ መንግሥት ላይ የሚደረገው ግፊት እያየለ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

የልጆቻቸው አድራሻ የጠፋባቸው የወታደሮቹ ቤተሰቦች የሱማሊያ ፕሬዚዳንት የሆኑትን መሀመድ አብዱላሂ መሀመድን (ፈርማጆን) ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን እሳቸው ግን ሪፖርቱን አስተባብለዋል፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበው የተወካዮቹ ምክር ቤት ኮሚቴ የወታደሮችን አድራሻ በሚመለከት ምርመራ እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡

በተባበሩት መንግስታት (UN) የሰአብአዊ መብት ጉባኤ በዚህ ሳምንት የወጣው ዘገባ እንዳመለከተው “ለሥልጠና ወደ ኤርትራ ተልከው የነበሩ ወታደሮች በኢትዮጵያው የትግራይ ውጊያ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡”

የሶማልያ መንግሥት ግን ወታደሮቹ ትግራይ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን አስተባብሏል፡፡

የሱማሊያ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ኦስማን ዱቤ ትላንት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ከሱማሊያ ወታደሮች ጋር የሚወጡት መረጃዎች ሀሰተኛ፣ መሰረተቢስ አሉባልታ፣ እና ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ ነው ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/SOMALIA-06-11

@tikvahethiopia
#MarkLowcock

የተባበሩት መንግስታት (UN) የሰብአዊ ጉዳዮች ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ "በሰሜን ኢትዮጵያ ረሃብ አለ" አሉ።

ይህን ያሉት በተባበሩት መንግስታት የተደገፈ ጥናት ከተለቀቀ በኋላ ነው።

ሎውኮክ “አሁን ረሃብ አለ” ያሉ ሲሆን አክለው “ይህ በጣም የከፋ እየሆነ ነው” ብለዋል።

የተመድ ጥናቱ እንዳመለከተው በጦርነት በተጎዳው ትግራይ ክልል እንዲሁም በአጎራባች አማራና አፋር ውስጥ 350,000 ሰዎች “በከባድ ቀውስ” ውስጥ ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል ውስጥ በተደረገው ውጊያ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ፤ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

ያንብቡ : https://t.co/py8S8JgFjX?amp=1

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በUN የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ታዬ አፅቀስላሴ ተመድ (UN) "በትግራይ 350,000 ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል" ብሎ ይፋ ያደረገውን ሪፖርት ውድቅ አድርገዋል።

አምባሳደር ታዬ የተመድን ሪፖርት ውድቅ ያደረጉት ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ ተደራሽነትን እያገደ ነው በሚል የሚወጡትን ሪፖርቶችንም ውድቅ አድርገዋል።

@tikvahethiopia
ቻይና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውን ሙከራ ተቸች።

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ላይ አቶ ደመቀ ፥ መንግስት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች በተለይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላትን ለህግ እንዲቀርቡ፣ የሰብዓዊ ጥሰቶችን በተመለከ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት እንዲሰፋ መንግስት ተገቢ ምላሽ እየሰጠ ቢሆንም መሰረተ በመንግስት ላይ የሚሰነዘሩ መሰረተ ቢስ ትችቶች መቀጠላቸውን ለቻይናው አቻቸው አብራርተዋል።

ዋንግ ይ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያደርጋቸውን ጥረቶችን ማድነቃቸው ተነግሯል። በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውንም ሙከራ ተችተዋል።

አያይዘውም ቻይና በምትከተለው በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ መሆኑን ጠቅሰው ፣ አገራት የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው የመፍታት ልዑላዊ መብት ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በተደረገው ውይይት አቶ ደመቀ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እልባት እንደሚያገኝ ኢትዮጵያ እምነት ያላት መሆኑን ገልፀዋል።

ዋንግ ይ በበኩላቸው ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ አገራቸው ድጋፍ የምታደርግ መሆኑን ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/Ethio-China-06-11

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tikvahethiopia