TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት የስራ ሃላፊዎች ማድረሳቸው ተገልጿል።

አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት ያደረሱት ፦ ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን ነው።

አፈጉባኤው ከአውሮፓ ህብረት (EU) አመራሮች ጋር ኢትዮጵያ ሰላማዊ ፣ ነፃ ፣ እና ፍትሓዊ ምርጫ ለማድረግ እያደረገች ያለው ጥረት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር፣ በትግራይ እየተደረገ ያለው የሰብአዊ ድጋፎችና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የህብረቱ አመራሮች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እንዲደርሳቸው የሚደረገው ጥረት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

አመራሮቹ በትግራይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከመንግስታቱ ድርጅት ሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር የጀመረው የምርመራ ሂደት የሚበረታታ ስለማለታቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገልጿል።

@tikvahethiopia
ትላንት ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 አካባቢ ደራ ወረዳ ውስጥ በደረሰ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ከ11 በለይ ተጓዦችን ሞቱ ።

በደቡብ ጎንደር በደራ ወረዳ ከ "ሀሙሲት ከተማ" ወጣ ብሎ በመገኘው ወንጨጥ ቀበሌ ታች ቀረር በተባለ ጎጥ ወይም ቴሌ ታወሩ አካባቢ ከወረታ ወደ ባህር ዳር ሲጓዝ የነበረ አባዱላ ከ አይሱዚ እና ከሲኖ ትራክ ጋር በተከሰተ የግጭት አደጋ ከ11 በላይ ሰዎች መሞታቸውን በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች መግለፃቸውን የደራ ወረደ መ/ኮ ጽ/ቤት አሳውቋል።

በአደጋው ከባድ እና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ባ/ዳር ሆስፒታል መላካቸው ተሰምቷል ።

ስለ አደገው ተጨማሪ ምርመራ የተደረገ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

• "350 ሺ ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል" - ሮይተርስ ተመልከቱት ያለው የተመድ የውስጥ ሪፖርት

• "ኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ ተከስቷል ለማለት የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ፤ አሁን በትግራይ ባለው ሁኔታ ከ90 % በላይ የክልሉ ነዋሪ ሰብዓዊ ድጋፍ አግኝቷል" - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር


በሮይተርስ የተመለከትኩኝ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውስጥ ሰነድ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ወደ 350,000 ያህል ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተገምቷል።

በሰነዱ ላይ ትንታኔ የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና የእርዳታ ቡድኖች ናቸው።

ይህ ነው የሮይተርስ ዘገባ : https://www.reuters.com/world/africa/exclusive-some-350000-people-ethiopias-tigray-famine-un-document-2021-06-09/?rpc=401

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው ላይ "በትግራይ ክልል 350 ሺህ ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል" በሚል በተመድ የውስጥ ሰነድ ላይ ቀረበ የተባለውን ለህዝብ ይፋ ያልሆነ ሰነድ ምንጭ ተደርጎ የወጣውን መረጃ ትክክል እንዳልሆነ አሳውቀዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ "ኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ ተከስቷል ለማለት የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ፤ አሁን በትግራይ ባለው ሁኔታ ከ90 በመቶ በላይ የክልሉ ነዋሪ ሰብዓዊ ድጋፍ አግኝቷል" ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም ፥ በቀጣይ የእርሻ ስራም 70 በመቶ ለግብርና ስራ የሚውል መሬት ለእርሻ ስራ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው በዚህ ሁኔታ ረሃብ ይከሰታል የሚለው ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#EritreaTroops

ዛሬ ሳምታዊ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አማባሳደር ዲና ሙፍቲ "የኤርትራ ወታደሮች በምእራብ ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ዞኖች እና በደቡብ ኦሮሚያ ውስጥ አሉ" ስለሚባለው ጉዳይ ተጠይቀው ነበር።

አምባሳደር ዲና “መረጃ የለኝም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፥ የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል በተለይ በቦረና ዞን ነጌሌ ከተማ አካባቢ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባይ ጮመን በሚባል ስፍራ መታየታቸውን ገልፆ ነበር።

ኦነግ የኤርትራ ወታደሮች ናቸው ያላቸው ግለሰቦች “ሁሉም አፋን ኦሮሞ ቋንቋን የማይችሉ እና የተወሰኑት ብቻ አማርኛ ቋንቋ የሚችሉ ናቸው” ብሏል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ “የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ታይተዋል ስለመባሉ ምንም መረጃ የለኝም” ብለዋል።

በትግራይ ክልል ያሉት የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተም ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዌ።

አማባሳደር ዲና የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣት መጀመራቸውን ገልጸው ፣ ይህንንም መከላከያ ሚኒስቴር ማረጋገጡን አስታውሰዋል።

ትግራይ ክልል ከሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች ምን ያክሉ ወጡ? መቼ ሙሉ በሙሉ ይወጣሉ ? የሚለውን በተመለከተ “ሙሉ መረጃ የለኝም” ሲሉ መልሰዋል።

በሌላ በኩል የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር (NATO) በትግራይ ካለው ችግር ጋር በተያያዘ “ኢትዮጵያን ለመውረር ተዘጋጅቷል” እየተባለ ስለሚወራው ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ እንደሌለው ጠቁመዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ “ኢትዮጵያ ከሁሉም የኔቶ (NATO) አባላት ጋር መልካም ግንኙነት ነው ያላት፤ ይህንን ያደርጋሉ የሚል እምነት የለኝም” ሲሉ የግል አስተያየት ሰጥተዋል።

የዚህ ዘገባ ባለቤት "አል ዓይን ኒውስ" ነው።

@tikvahethiopia
' አዲስ ስርዓተ ትምህርት በአማራ ክልል '

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በቅርቡ ተግባራዊ የሚኾን አዲስ የሥርዓተ ትምህርት ይፋ አድርጓል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በቅርቡ ተግባራዊ የሚኾን አዲስ የሥርዓተ ትምህርት ይፋ አድርጓል፡፡

አዲሱን የሥርዓተ ትምህርት ይፋ ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) ናቸው፡፡

በዚህም፦

- አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በትምህርት ቤቶች አደረጃጀት ይለያል፦
° ከ1እስከ 6ኛ ያሉትን አንደኛ ደረጃ
° ከ7 እስከ 8 ያሉትን መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣
° ከ9 እስከ 12ኛ ያሉትን ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ በሚል ተደራጅቶ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን አብራርተዋል፡፡

- የመምህራን ስልጠና ሥርዓትን በተመለከተ ከምልመላ ጀምሮ የስልጠና አይነት እና ጊዜ እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል።

- ሥርዓተ ትምህርቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት እንዲኖረው የትምህርት ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ መደረጉን ጠቁመዋል።

- ሁለተኛ ደረጃ ላይ የትምህርት አሰጣጥ የቀለም ትምህርት እና የሙያ ትምህርት ተብሎ በሁለት መንገድ ሊሰጥ ታስቧል፥ ትግበራውም በቀጣይ ዓመት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በተመረጡ ትምህርት ቤቶች፣ ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉ ኹሉም ትምህርት ቤቶች ተግባዊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

- የማስተማሪያ ቋንቋን በተመለከተ በአማርኛ፣ በአዊኛ፣ በኽምጣና እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚኾን እና ሥርዓተ ትምህርቱም በዚሁ እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል።

- የአርጎበኛ ቋንቋን ለማካተት የማጥናት ሥራ እየተሰራ እንደሆነ አንስተዋል።

- የግእዝ ቋንቋን በሥርዓተ ትምህርቱ ለማካተት ዝግጅት እየተደረገ እንደኾነም ጠቁመዋል።

(አሚኮ)

@tikvahethiopia
"...ግድያው ለሰው ልጅ ሕይወት ያለን ቸልተኝነት ያሳያል" - ሂዩማን ራይትስ ዋች

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች በደምቢ ዶሎ ከተማ በአደባባይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተገድሏል ላለው ወጣት ተጠያቂ የሆኑ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቀ።

የ17 ዓመት ወጣት የነበረው አማኑኤል ወንድሙ ከበደ ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ ሕዝብ በተሰበሰበበት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መገደሉን የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታወቋል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች እንዳለው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ታዳጊውን በአደባባይ ከገደሉት በኋላ የታዳጊውን የቤተሰብ አባላት ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን በመግለጫው አስታውቋል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር የሆኑት ሌቲሻ ባደር ፥ "ባለስልጣንት ወጣቱን መግደላቸው ለሰው ልጅ ሕይወት ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል" ብለዋል።

የአካከባቢው ባለስልጣናትም ወጣቱን በአደባባይ መግደላቸው እና ቪዲዮ መቅረጻቸው ከሕግ በላይ እንደሆኑ እምነት እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት : https://www.hrw.org/news/2021/06/10/ethiopia-boy-publicly-executed-oromia

#ቢቢሲ
@tikvahethiopia
#LiveUpdate

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በጊዜ ሠሌዳው ቅደም ተከተል መሠረት በመከናወን ላይ ስላለው የመራጮች ድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት እና አጠቃላይ የቴክኒክ ሥራዎችን አስመልክቶ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ለሚዲያዎች መግለጫ ይሰጣል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሚገኙ ሲሆን በሚነሱ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃዎችን የምንለዋወጥ ይሆናል። መልካም ቆይታ !

@tikvahethiopia
ዛሬ ሰኔ 3 በፋግታ ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ፋግታ ወረዳ ዛሬ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በአንዳንድ አከባቢዎች ሰብል ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ፋግታ ኮሙዩኒኬሽን ሪፖርት አድርጓል።

ዝርዝር የጉዳቱ መጠን እንዲሁም አካባቢዎቹ አልተገለፁም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዛሬ ጥዋት የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን ማድረሳቸው መገለፁ ይታወሳል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን ስለማድረሳቸው ተሰምቷል።

ደብዳቤውን ለሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ ነው ያስረከቡት።

ወ/ሮ ዳግማዊት ደብዳቤውን ባስረከቡበት ወቅት ከሚኒስትሯ ጋር በተለያዩ ጉደዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር እና በኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

@tikvahethiopia
"...ቱርክ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን ትቆማለች" - አምባሳደር ያፕራክ አልፕ

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የህዳሴዉ ግድብ ሶስትዮሽ ድርድር እና የኢትዮ ሱዳን የድንበር ዉዝግብ በሠላማዊ መንገድ ሊፈታ ይገባል አሉ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጡት ቃለምልልስ ነው።

ቱርክ ከሱዳን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት ያላት አገር መሆኗን የገለፁት አምባሳደሩ ፥ ጦርነት ለሁለቱም አገራት ስለማይበጅ ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ያፕራክ አልፕ አገራቸዉ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆምም አስታዉቀዋል፡፡

አገራቸዉ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ልዉዉጥ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደምትሰራም ገልፀዋል።

ቱርክ እና ኢትዮጵያ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸዉ የገለፁት አምባሳደር ያፕረክ አልፕ፤ አሁን ላይ የአገራቱ አመታዊ የንግድ ልዉዉጥ 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

በሌላ መረጃ : ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከቱርኩ የትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር አዲል ካራይስማይሎግሉ ጋር ስምምነቱን መፈራረማቸውን በትዊተር ገጻቸው አሳውቀዋል።

#EthioFM #WeyzeroDagmawitMoges

@tikvahethiopia