TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.67K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AMHARA

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው ምርመራ 912 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

- 8 ሰዎች በምዕ/ጎንደር ዞን በሚገኘው መተማ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው

- 1 ሰው ከደሴ ከተማ አስተዳደር

- 3 ሰዎች ኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን በሚገኘው ከሚሴ ከተማ በተደረገ የአሰሳ ምርመራ የተገኙ ናቸው።

በፆታ አኳያ 9 ወንዶች እና 3 ሴቶች ናቸው ፤ የእድሜ ክልላቸው ከ15 እስከ 50 ዓመት ውስጥ ይገኛል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 155 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 7 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በቫይረሱ የተያዙት ግለሰቦች 6 ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ እድሜያቸው ከ19-70 ዓመት ያሉና ነዋሪነታቸው በድሬዳዋ ከተማ የሆኑ ናቸው።

አራቱ (4) ከዚህ ቀደም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ (ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው አንዱ ከጅቡቲ ተመላሽ) ሲሆኑና ሁለቱ ከማህበረሰቡ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው። አንደኛዋ ግለሰብ በሆስፒታል በተጓዳኝ ህመም ህክምና ላይ የነበሩ ናቸው።

#TIGRAY

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 283 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። 11 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፥ 1 ሰው በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው። በአጠቃላይ በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 179 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OROMIA

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 292 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

- 2 ሰዎች ከሰበታ (38 ዓመት ወንድና የ13 ዓመት ሴት) ሲሆኑ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ሁለቱም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው።

- 1 ሰው ከቡራዩ (የ33 ዓመት ሴት) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

- 1 ሰው ከሞጆ (የ39 ዓመት ወንድ) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

#AFAR

በአፋር ክልል በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 118 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 7 ሰው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

#HARARI

ባለፉት 24 ሰዓት በሐረሪ ክልል 94 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው። ሁለቱም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ የ38 ዓመት ወንድ (የጂኔላ ወረዳ)ና የ7 ህፃን ሴት (ሽንኮር ወረዳ) ነዋሪዎች ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሐረሪ ክልል 1 ሞት ተመዝግቧል!

የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉን በዛሬው ሪፖርት ላይ አሳውቋል።

ሟቹ የአራት (4) ወር ህፃን (የድሬጠያራ ነዋሪ) ሲሆን ሪፖርት ከተደረገበት ቀን ጀምሮ የህክምና እርዳት ሲደረግለት እንደቆየ ቢሮው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ በጤና ሚኒስቴር የወጣውን ሪፖርት መልሶ የተመለከተ ሲሆን የ4 ወር ህፃን መሞቱን የሚገልፅ መረጃ አላገኘም።

የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሪፖርት ያደረገው ሞት አጠቃላይ የሀገሪቱን የሟቾች ቁጥር ስልሳ ስድስት (66) ያደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
10ኛው የኢትዮጵያ ክልል 'ሲዳማ ክልል' !

የደቡብ ክልልና አዲሱ የሲዳማ ክልል በዛሬው ዕለት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ፊት ቀርበው የስልጣን ርክክብ አካሂደዋል።

ይህን ተከትሎ ሲዳማ በሀገሪቱ 10ኛው ክልል የሚሆን ሲሆን ፥ የምክር ቤቱ አባላት ለሲዳማ ክልል ህዝብ 'እንኳን ደስ አላችሁ' ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19AddisAbaba

ባለፉት 24 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው 144 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 3 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ 40 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የተቀሩት 101 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

5 ከፍተኛ የሰው ቁጥር በኮቪድ-19 የተያዘባቸው የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የሚከተሉት ናቸው ፦

• አዲስ ከተማ - 666 ሰዎች
• ቦሌ - 437 ሰዎች
• ጉለሌ - 308 ሰዎች
• ልደታ - 282 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራንዮ - 268 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ከሰኔ 6 - ሰኔ 11 በኢትዮጵያ!

ከሰኔ 6/2012 ዓ/ም እስከ ዛሬ ሰኔ 11/2012 ዓ/ም (6 ቀናት) ብቻ በሀገራችን ኢትዮጵያ 1,056 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በ6 ቀናት ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል (የዛሬውን የሐረሪ ክልል ሪፖርት ጨምሮ) እንዲሁም 383 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

ሁላችንም ከምንጊዜውም በላይ ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ነን፤ በየትኛውም ቦታ እና ከማንኛውም ሰው የኮሮና ቫይረስ ሊይዘን ስለሚችል ሁል ጊዜ ጥንቃቄ እናድርግ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
10ኛው የኢትዮጵያ ክልል 'ሲዳማ ክልል' ! የደቡብ ክልልና አዲሱ የሲዳማ ክልል በዛሬው ዕለት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ፊት ቀርበው የስልጣን ርክክብ አካሂደዋል። ይህን ተከትሎ ሲዳማ በሀገሪቱ 10ኛው ክልል የሚሆን ሲሆን ፥ የምክር ቤቱ አባላት ለሲዳማ ክልል ህዝብ 'እንኳን ደስ አላችሁ' ብለዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
10ኛው የኢትዮጵያ ክልል!

(በኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

በዛሬው የሲዳማ የስልጣን ርክክብ ስነ ስርዓት የታደሙ የሲዳማ ተወላጅ የዞን እና የፌደራል ባለስልጣናት ደስታቸውን በተለያዩ መልኩ ሲገልጹ እንደነበር ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በፎቶ ዘገባው አሳይቷል።

ባለስልጣናቱ እግዚያብሔርን ደጋግመው ሲያመሰግኑ መደመጣቸውንና፤ በይፋዊ ንግግራቸውም ሆነ በስልክ ቃለ ምልልሳቸው ይህንኑ ሲያስተጋቡ እንደነበር ተገልጿል።

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ደስታቸውን በመተቃቀፍ አሊያም በመጨባበጥ መግለጽ ያልቻሉት ባለስልጣናቱ፤ ክርኖቻቸውን በማጋጨት “የእንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት ሲለዋወጡ ታይተዋል።

በዛሬው ስነ ስርዓት ላይ የቀድሞዎቹ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ደሴ ዳልኬ እና ሚሊዮን ማቲዮስ፣ የቀድሞው እና የአሁኑ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪዎች ቃሬ ጫዊቻ እና ደስታ ሌዳሞ እንዲሁም የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ተገኝተዋል።

#EthiopiaInsider

@tikvahethtikvahethiopia @tikvahethiopia
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ-19 ምርመራ ተጀመረ!

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል ዛሬ ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ሥራ መጀመሩ ታውቋል፡፡ የምርመራ ማዕከሉ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ600 እስከ 700 ናሙናዎችን መመርመር ይችላል ማባሉን አብመድ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የሚጠበቀውን 'የፀሐይ ግርዶሽ' በማስመልከት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲና የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አዳራሽ ዛሬ 8፡00 ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እና የጥንቃቄ መልዕክቶች ይሰጣሉ፡፡ ተከታትለን እናሳውቃችኃለን! @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ኢትዮጵያ ከ3 ቀናት በኋላ በሚከሰተው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ከጎብኚዎች ልታገኝ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረረሽኝ የተነሳ የምታጣ መሆኑን የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል - https://telegra.ph/ENA-06-18

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የፒን-ሆል ሳጥን እንዴት አድርጌ ላዘጋጅ ?

(በአለምዬ ማሞ)

በባዶ አይናችን በቀጥታ ፀሐይን ስንመለከት ጉዳት የሚደርስብን ከሆነ ፤ ታዲያ እንዴት የፀሐይን ግርዶሽ ማየት እንችላለን ?

የአነስተኛ ሽንቁር ቀዳዳ ሳጥን (Pin-hole Box) ፦

ፒን-ሆል ወይም አነስተኛ ሽንቁር ቀዳዳ በርቀት ያለን አንድ አካል ገልብጦ እንደሚያሳይ ከብዙ ዘመናት በፊት ጀምሮ እናውቃለን፡፡

እንደውም በዝቅተኛ ክፍሎች ት/ቤት በነበርን ወቅት የፒን ሆል ሳጥን (አነስተኛ ሽንቁር ቀዳዳ ያለው ሳጥን) ሰርተን ፤ እርሱን ተጠቅመን የዛፎችን እና የጓደኞቻችንንም ምስሎች ተገልብጠው ያየን አንጠፋም፡፡ አሁንም ፀሐይዋን በግርዶሽ ወቅት ለማየት የምንጠቀመው ይህንኑ መርህ ነው፡፡

ይህንን 'የፒን ሆል ሳጥን' መስራት እጅግ ቀላል በመሆኑ ዛሬ በቤታችን ውስጥ በማዘጋጀት መጠቀም እንችላለን፡፡ ይህንንም ለመስራት የሚያስፈልገን ማንኛውም ልሙጥ ወረቀት ወይም የካርቶን ወረቀት ሲሆን ፤ ወደ ፀሐይ ስናዞረው ፤ በሌላኛው ጎን በኩል የፀሐይዋ ምስል ይታያል።

በተጨማሪ ይህ ተጭናችሁ አንብቡ https://telegra.ph/EASE2020-06-18 ከላይ ያስቃመጥነው ቪድዮ 12 MB ሲሆን ይበልጥ ስለ ፒን-ሆል አዘገጃጀት እንድታውቁት ስለሚያደርጋችሁ እሱንም ብትመለከቱት ጥሩ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ግርዶሹ ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ስንት ሰዓት ይፈጅበታል ?

በኢትዮጵያ የሚከሰተው ግርዶሽ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ዋናው "ቀለበታዊ ግርዶሽ" በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ውስጥ በተለያየ ሰዓት የሚታይ ሲሆን ለምሳሌ ወለጋ አካባቢ ከጥዋቱ 1:55 ሰዓት ላይ (ለ1 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ) ፣ ላልይበላ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ (ለ1 ደቂቃ ከ8 ሴኮንድ) እንዲሁም አፋር ላይ ከጥዋቱ 2:03 (ለ1 ደቂቃ ከ6 ሴኮንድ) ይታያል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#LiaTadesse

"ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል፡፡ የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል ። ህክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ ይወጣል።" - ዶ/ር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ጥብቅ ማስገንዘቢያ ስለ ዴክሳሜታሶን'

(ዶክተር ያቤፅ ከበደ-የጤና ባለሙያ)

ከብሪታንያ ተመራማሪዎች የወጣው የዚህ ዴክሳሜታሶን የተባለው ስቴሮይድ ዘር መድሀኒት በኮቪድ-19 በፅኑ ለታመሙ ያለው ተስፋ ሰጪ ውጤት ሁላችንም የሚያስደስት ነው፤ ነገር ግን መገንዘብ ያሉብን ነገሮች ይኖራሉ።

ይህ መድሀኒት (Dexamethasone) ልዩ የሆኑ የሆርሞን በሽታዎችን እንደ መመርመሪያነት አንስቶ እስከ ለተለያዩ የሰውነት አካላት መቆጣት ፣ በእናት ሆድ ውስጥ ላሉ ጨቅላ ህፃናት ሳንባ ማብሰያ (ያለ ጊዜው ከመጣ የነፍሰጡሮች ወሊድ ጋር በተያያዘ) ፤ ብሎም ከተለያዩ ፀረ-ካንሰር ተጓዳኝ መድሀኒቶች ጋር አብሮ ይሰጣል።

ይህ መድሀኒት በጣም ጥብቅ የሆነ የሀኪም ትእዛዝ እና ክትትል የሚጠይቅ ጭምር ነው። ይህን ዴክሳሜታሶን የተባለውን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ በራስ ፍቃድ እና ሀሳብ መውሰድ ከአለርጂክ ክስተት ጀምሮ እስከ ልብ እና ኩላሊት በሽታ ድረስ የጓንዮሽ ጉዳት (Side effects) ሊያደርስ ይችላል።

ህብረተሰቡ በሀይድሮክሲክሎሮኩዊን የተባለው የወባ መድሀኒት መረጃ በወጣበት ጊዜ ያደረገውን አለአግባብ ግዢ በዚህ መድሀኒት ላይ እንዳይደግመው እዲሁም መድሀኒት ሺያጮች ጥብቅ የሆነ አሰራርን ቢከተሉ የተሻለ ይሆናል።

ህክምና በአቦ-ሰጡኝ ሳይሆን በእውቀት ሲከናወን ነው ውጤታማ የሚሆነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia