TIKVAH-ETHIOPIA
1.42M subscribers
55.2K photos
1.38K videos
199 files
3.7K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም !

" ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ብለዋል።

ከንቲባዋ በመግለጫቸው የከተማ አስተዳደሩ በየ3 ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰዋል።

በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩ በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉን አስረድተዋል።

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ አይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም አይነተ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

#አከራዮችም ሆኑ #ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመው ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አሳስበዋል።

በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብት እና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
#ሐምሌ19

የፀጥታ ኃይሎች ዝግጅት ምን ይመስላል ?

(ቁልቢ ገብርኤል)

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ፤ በዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ላይ የሚታደሙ ምዕመናንን እና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አስተማማኝ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።

ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የምስራቅ እና የምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፣ የሐረሪ ክልል ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተቀናጅተው በቂ ዝግጅት አድርገዋል።

የንግስ በዓሉ ታዳሚዎች መጨናነቅ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ በተለይ የደብሩ መግቢያና መውጫ በሮች አካባቢ የኪስ ቦርሳቸውን ፣ ሞባይላቸውን እና ሌሎች ንብረቶቻቸውን በጥንቃቄ እንዲይዙ ፖሊስ አሳስቧል።

አሽከርካሪዎች ወደ ንግስ በዓሉ ሲመጡ #ከኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_መለያ ወይንም ከህጋዊው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በስተቀር ሌላ ለፖለቲካ ማራመጃ የሚሆን ዓርማና ምልክት ይዞ መገኘት እንደማይቻል አሳስቧል።

በንግስ በዓል ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ እና የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎች ሲያዙ ውሳኔ ለመስጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።

የበዓሉ ታዳሚዎች አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥማቸው በስልክ ቁጥር 0256665056 መጠቆም እንደሚችሉ ፖሊስ ገልጿል።

የአካባቢው የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ አክብረው በማሽከርከር ከአደጋ እንዲጠበቁ ተብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ ከባድ መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል።

#ENA

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ የ44 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው እና የልማት ባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ልማትና የቢዝነስ አቅርቦት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱል ካማራ ናቸው።

የመጀመሪያው የ40 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በምስራቅ አፍሪካ ፈተናዎችን በመቋቋም የምግብ ዋስትና ማረጋገጥን አላማ ላደረገ መርሃ ግብር ተፈጻሚነት የሚውል ነው።

የተቀረው 4. 4 ሚሊዮን ዶላር የማክሮኢኮኖሚ አስተዳደር አቅምን የማጠናከር ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ልጆቻችን እየመጡ ነው❤️ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረጉት ያስከበሩት የሀገራችን ልጆች ዛሬ ምሽት ኢትዮጵያ ይገባሉ። የአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድናችን ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በስካይ ላይት ሆቴልም ያርፋል። ነገ ሀሙስ ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ካረፈበት ስካይላይት…
" ጀግኖቻችን በሰላም ገብተዋል "

በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዋል።

ነገ በተመረጡ የመዲናችን አካባቢዎች ህዝቡ በዓለም መድረክ ሀገራችንን #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ከፍ ላደረገው የአትሌቲክስ ቡድን አድናቆቱን በመግለፅ አቀባበል ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia #SW ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ። የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ። ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው። በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን…
" አልሸባብ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል " - ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው

የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት እርምጃ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በሶማሌ ክልል በ5 ትናንሽ የጠረፍ አካባቢዎች ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራ በጸጥታ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሉ ተቆርጠው የቀሩትን የሽብር ቡድኑ አባላትን የማጽዳት ዘመቻ ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ባለፉት ቀን ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡ በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ጠቁመዋል፡፡

ነገር ግን የሽብር ቡድኑ #ዛሬ_ሌሊት ላይ የተበታተነ ኃይሉን በማሰባሰብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት አካባቢ ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም መሞከሮ ነበር።

ሆኖም የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ዳግም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራዎችን ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ነው ያብራሩት፡፡

እስካሁን ባለው መረጃም ከ150 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውንና የሽብር ቡድኑ ለአጥፍቶ መጥፋት ያዘጋጃቸው ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንደተማረኩ አመልክተዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia
#SNNPRS #SouthWestEthiopia

የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

👉 ለወንዶች 41፣
👉 ለሴቶች 40 እና
👉 ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

👉 ለወንዶች 39፣
👉 ለሴቶች 38 እና
👉 ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
"ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል"

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ያገረሸው ግጭት ተባብሶና ሰፍቶ እየቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት መሳሪያ ወርዶ ወደ ንግግር እንዲገባ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ቀጥለዋል።

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ" ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል" ሲል የሰላም ጥሪ አቅርቧል።

ጉኤው ምን አለ?

- ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊቆምና የሰላም ሂደቱ ሊቀጥል ይገባል።

- የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው።

- ከዚህ ቀደም የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል፤አሁንም የሰላም ጥሪ እናቀርባለን።

- የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሌሎችም ወገኖች ለዚህ ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል።

- የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል።

- ህፃናትን ለወታደራዊ ዘመቻ ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ ሊቆም ይገባል።

- በወቅታዊ ጉዳይ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።

- ትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች መሪዎች የትግራይ ክልል ወደ ሰላማዊ ድርድሩ እንዲመለስ በመምከር አባታዊና መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

- የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና የውጭ ሀገራት መንግሥታት፣አፍሪካ ሕብረት፣ ተመድና ሌሎች አካላት ሁሉ የሰላም ጥረቱ አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።

- የጳጉሜን 5ቱን ቀናት ምእመናን በፆምና ፀሎት እንዲያሳልፉ ጥሪ እናቀርባለን።

(የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ)

#ENA

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ያለውን ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (#ሀዋሳ እና #መቅደላ_አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
#Update

ዛሬ " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " አባላት ፤ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አጠቃላይ ሂደት እና ቀጣይ ስራዎችን በሚመለከት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ለሁለቱ ም/ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች ፣ ለክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች ፣ ለከፍተኛ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሀሴን የተናገሩት ፦

- ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቋል።

- በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችልና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- ከህገ-መንግስት ውጪ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቆመው በትግራይ ክልል በህገ-መንግስቱ መሰረት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ #ጊዜያዊ_አስተዳደር ይቋቋማል።

- ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ቀደመው ማህበራዊ ትስስር እንዲመለሱ በጋራ ይሰራል።

- የወደሙ ተቋማትን ጨምሮ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በጋራ ርብርብ ሊከናወኑ ይገባል። የትስስርና የተግባቦት ስራዎች የህዝቦችን መጻኢ የጋራ ጉዞ ታሳቢ ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል።

- በግጭቱ ምክንያት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እንዲሁም በሌሎች መስኮች የደረሰውን ጫና በማስተካካል ረገድ በትብብር መስራት ይጠበቃል።

- የመገናኛ ብዙሃን #ቁርሾዎችን ማባባስ ሳይሆን ዜጎች ከችግሩ ተምረው በቀጣይ አብሮነታቸውን አጠናክረው የሚሄዱበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ሊሰሩ ይገባል።

- #በማወቅም ሆነ #ባለማወቅ የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሰሩ ኣካላትን በጋራ ማስቆም ይገባል።

- ሁሉም ዜጋ ለሰላም ስምምነቱ #ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ  ይገባል።

#ENA

@tikvahethiopia