TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BeleteMolla

"የኦሮሞ ተማሪም ተጎድቷል፤ የአማራ ተማሪም ተጎድቷል። ይሄ እየለየን የምንሰራው ፖለቲካ የትም አያደርሰንም። ከእውነትም መሸሽ የለብንም። ኦሮሞና አማራ ብቻ አይደሉም ሌሎች ብሄር ተወላጅ ተማሪዎችም ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። ይሄ እንዲሆን አንፈልግም።" - አቶ በለጣ ሞላ(የአብን ምክትል ሊቀመንበር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BeleteMolla

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ ለአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች በተለይም ለወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት...

ለኦሮሞ እና አማራ ህዝቦች በተለይ ለወጣቶች ማድረስ የምፈልገው መልዕክት ሁለቱ ህዝቦች ብዙ ጉዳዮች በጋራ አሏቸው። ከፖለቲካም በላይ የሆኑ የጋራ ጉዳዮች አላቸው። ይሄንን ቀናውን እናበረታታው፣ እንመልከተው፣ እንየው ሩቅ አይደለም።

ልንመለከተው ከፈለግን፤ ፍቃደኛ ከሆንን ሁለቱ ህዝቦች ሰፊ የሆኑ የጋራ ጉዳዮች አሏቸው። ከፖለቲካ በላይ የሆኑና እነሱን በማጤን ስራዎቻችን በመተባበር የተቃኙ በጋራ መንፈስ፤ በታሪካችን የተጠፋፋንባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ እንሱ ላይ ብቻ ቆመን ነገን መናፈቅ የለብንም። ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁላችንም ትላንት ችግር ቢኖርም በሁሉም መልኩ ችግር ቢኖርም ያንን ተሻግረን ወደፊት የጋራ የሆነ የተሻለ ነገር ለመፍጠር የሁለቱ ህዝቦች መቻቻል፣ መግባባት፣ መቀራረብ፣ መነጋገር፣ መከራከር፣ የተሻለ እውነትን፤ ሚዛናዊ የሆነ እውነትን እዛ ላይ እንድንደርስ ስለሚያስችል ሁለቱ ህዝቦች የበለጠ ተቀራርበው መገኘት መቻል አለባቸው።

በተራራቁ ጊዜ ትላንት ምን እንደሆኑ ሁለቱ ህዝቦች ምናስታውሰው ነው፤ እስር ቤቶቻችን የአማራና ኦሮሞ ማጎሪያ ካምፕ ሆነው ቆይተዋል፤ ብዙ ወጣቶች የህይወት መስእዋትነት ከፍለዋል፣ ያ ሁሉ ድሃ ተከፍሏልና ይህን በማስታወስ ዛሬ ላይ ቆመን ነገን የተሻለ ለማድረግ የሁለቱ ህዝቦች መቀራረብ በታሪክ ትልቁ አጋጣሚ ሆኖ ምናስታውሰው ስለሚሆን ይሄን አጋጣሚ መጠቀም እንዳያመልጠን መጠንቀቅ እንዳለብን መልዕክት ማስተላለፍ ፈልጋለሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia