#DemekeMekonen #DrTedrosAdhanom
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ጄኔቫ በሚገኘው የድርጅቱ ፅ/ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በሁሉ አቀፍ የጤና ሽፋን፤ በቅድመ ጤና አጠባበቅ፤ በተመጣጠነ ምግብ፤ በፋማሲዮቲካል አቅርቦት እና በአቅም ግንባታ ዙሪያ በስፋት መክረዋል።
(Office of Deputy Prime Minister)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

“መጪው ምርጫ ሁከትን ሊያቀጣጥል ይችላል” - ክራይስስ ግሩፕ #Election2020
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘንድሮ ይደረጋል የተባለዉ ምርጫ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየውን ክፍፍል ሊያሰፋው እና ሁከትንም የበለጠ ሊያቀጣጥል እንደሚችል ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተሰኘው ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም አስጠነቀቀ። በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ከተባባሰ የኢትዮጵያ መንግስት መጪውን ምርጫ የሚያካሄድበትን ጊዜ እንዲያዘገይ ተቋሙ መክሯል።
ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ይህን ያለው የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 6 ባወጣው ዳሰሳ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ቀውስ አምጪ ሁነቶችን በመተንተን የሚታወቀው ይሄው ተቋም በኢትዮጵያ በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎችየሚታዩትን ሁከቶች የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል ተንብዩዋል።
https://telegra.ph/crisis-group-12-16
(Deutsche Welle)

#Boeing737MAX
ቦይንግ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርትን በጊዜያዊነት ሊያቋርጥ መሆኑን አስታውቋል። እንደ ኩባንያው ገለፃ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርት ከፊታችን ጥር ወር ጀምሮ በጊዜያዊነት የሚቆም መሆኑ ታውቋል።
የኩባንያው ቦርድ ለሁለት ቀናት በአሜሪካ ቺካጎ ከተወያየ በኋላ ነው የአውሮፕላን ምርት እንዲቆም ውሳኔ ያሳለፈው ተብሏል። ይህ የሆነውም የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር በአውሮፓውያኑ ከ2020 በፊት አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንዲገቡ ፍቃድ አልሰልጥም ማለቱን ተከትሎ ነው።
የቦይንግ ምርት የሆኑት 737 ማክስ አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ በደረሰ አደጋ በድምሩ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትትሎ ካሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ ከአገልግሎት ውጭ ተደርገው መቆማቸው ይታወሳል።
አደጋዎቹ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች መቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ በነበረ ችግር መፈጠሩ የተገለፀ ሲሆን፥ በዚህም ምክንያት ኩባንያው እስከ 9 ቢሊየን ዶላር አጥቷል ነው የተባለው።
ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላኖችን ምርት ቢያቋርጥም፤ ለወታደራዊ ግልጋሎት የሚውለውን የP8 ስሪት ምርቶችን ግን እንደሚቀጥል አስታውቋል። የቦይንግ አክሲዮን ገበያው እየተቀዛቀዘ ነው የተባለ ሲሆን፥ የ737 ማክስ አውሮፕላኖች ምርትን ለጊዜያዊነት አቋርጣለሁ ማለቱን ተከትሎ የአክሲዮን ገበያው በ4 በመቶ መቀነሱ ነው የተነገረው።
ምንጭ፦ አልጀዚራ(ኤፍ ቢ ሲ)

#OLF
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ 2012 በሰላም እንዲጠናቀቅ እንደሚሰራ የግንባሩ ሊቀ-መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ ከትናንት በስቲያ በአምቦ ከተማ ስታድዮም ለአምቦ ነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር ኦነግ ህብረ-ብሄራዊ ፌደሪሊዝም ወደኋላ እንዳይመለስ የበኩሉን አስተዋፆ እንደሚያደርግ ገልጿል።
PHOTO:VOA

#BarackObama
ሁሉንም የዓለም ሃገራት የሚመሩት ሴቶች ቢሆኑ ኖሮ የተሻለ የህይወት ዘይቤ ይኖረን ነበረ ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ተናገሩ። በሲንጋፖር በተካሄደ መድረክ ላይ ሴቶች ፍጹም ባይሆኑም "ያለምንም ጥርጥር ከወንዶች የተሻሉ ናቸው" ብለዋል።
ኦባማ ዓለማችን ከሚያጋጥሟት የአብዛኞቹ ችግሮች መነሾ ያረጁ ወንዶች በተለይ ስልጣን ላይ ያሉት ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ኦባማ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ዓለም በሴት መሪዎች ብትመራ ምን ልትመስል እንደምትችል ያልሙ እንደነበረ ተናግረዋል። "ሴቶች፣ አሁን እንድትረዱት የምፈልገው ፍጹም አይደላችሁም ግን ያለምንም ክርክር ከእኛ ትሻላላችሁ"ብለዋል።
"በጣም በእርግጠኝነት የምናገረው ሁሉም ሃገር ለሁለት ዓመታት በሴቶች ቢመራ፤ የተሻለ የኑሮ ዘይቤ እና ደረጃ ይኖረናል። በሁሉም ዘርፍ ለውጥ እንመለከታለን" ብለዋል።
ወደፊት ወደ ፖለቲካ መድረኩ የመመለስ ዕቅድ ካላቸው የተጠየቁት የቀድሞ ፕሬዝደንት፤ ይልቁንም ለሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ቦታ መልቀቅ እንደሚያሳምናቸው አስረድተዋል። "ዓለምን በትኩረት ከተመለከትናት የችግሮቿ ምንጮች ብዙ ጊዜ ያረጁ ስልጣን ያለመልቀቅ አባዜ ያላቸው እምቢተኛ ወንዶች ናቸው" ብለዋል።
(BBC)

አምባሳደር ጥሩነህ ዜና...
"አማራና ኦሮሞ እንዳይነጣጠሉ ሆነው በደምና ስጋ የተሳሳሩና በርካታ እሴቶችን የሚጋሩ ሕዝቦች ናቸው። ሁለቱ ሕዝቦች ለአገር ግንባታ በጋራ ዋጋ እንደከፈሉ ሁሉ በሂደቱ ቁርሾ የፈጠሩ ክስተቶች ነበሩ፤ የበርካታ አገራት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደት መሰል ታሪክ ማስተናገዱ ይታወሳል። ሕዝብን በማንቃት ደረጃ ቀዳሚ የሚባሉት የፖለቲካ ኃይሎች የሚጠበቅባቸውን ሚና ቀድመው ባለመወጣታቸው ችግሩ ተባብሶ ለሰው ሕይወት መጥፋት መንስኤ እየሆነ መጥቷል። የነገ አገር ተረካቢ ወጣቶች በጥላቻ አዙሪት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል። በመሆኑም ፖለቲከኞች የእነዚህን ሕዝቦች ልዩነት እየለቀሙ ከመነታረክ ወጥተው በጋራ መስተጋብሮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።"

የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ...
"በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በተለይ ወጣቶችን የማጋጨቱ ስራ እየሰፋ ነው። ማንኛውም የፖለቲካ ቡድን ሕዝብን ከማጋጨት ወጥቶ ወደ ሰለጠነ የሃሳብ የበላይነት ትግል መሸጋገር አለበት። አሁን ላይ እየተከሰቱ ያሉ አብዛኞቹ የፀጥታ ችግሮች በሁለቱ(አማራና ኦሮሚያ) ክልሎች ነውጪ እየተካሄደ ያለው መድረክ (የአማራና የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ) በዋናነት እነዚህን ችግሮች መፍታት ላይ አቅጣጫ ያቀምጣል። መድረኩ ከአማራና ኦሮሞ በተጨማሪ ሌሎች ሕዝቦችን ያቀፈ አገራዊ ውይይት የመፍጠር ሚናው የጎላ ነው።"

3ተኛው የሪልስቴት ኤክስፖ...
3ተኛው አመታዊ የሪልስቴት ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑን ሰምተናል፡፡ የዚህ ኤክስፓ አላማ ሁሉንም የሪልስቴት አልሚዎችንና በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በአንድ ቦታ በማገናኘት ተገልጋዩ ሳይጉላላ ግዢ የሚፈጽምበት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነውም ተብሎለታል፡፡ ኤክስፓው የፊታችን ቅዳሜና እሁድ በስካይላይት ሆቴል ይዘጋጃል፡፡

ጄኔራል ፐርቬዝ ሙሻራፍ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው!
የፓኪስታኑ የቀድሞ መሪ ጄኔራል ፐርቬዝ ሙሻራፍ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው። የቀድሞው ወታደራዊ መሪ በዛሬው እለት በመዲናዋ ኢስላማባድ በተሰየመው ልዩ ችሎት ነው ፍርዱ የተላለፈባቸው።
በፈረንጆቹ 1999 በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት ሙሻራፍ፥ ከፈረንጆቹ 2001 እስከ 2008 ድረስ ሃገራቸውን በፕሬዚዳንት መምራታቸው ይታወሳል።
ጄነራል ፐርፌዝ ሙሻራፍ ስልጣናቸውን ለማራዘም ህገ መንግስታዊ ጥሰት ፈጽመዋል በሚል መወንጀላቸው የሚታወስ ነው። ሙሻራፍ ከሶስት አመት በፊት ህክምናቸውን እንዲከታተሉ ተፈቅዶላቸው ከሃገር ከወጡ በኋላ ዱባይ ውስጥ ይገኛሉ።
(አልጀዚራ-ኤፍቢሲ)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፌደራል ፖሊስ በዩኒቨርሲቲዎች...
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የፀጥታ ሃይሎችን በልዩ ሁኔታ መድቤአለሁ ብሏል፡፡ የፀጥታ ኃይሎች በሌሎችም ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ይመደባሉ ተብሏል፡፡
(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

#ProsperityParty #TPLF
"ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያቋቋሙት ብልፅግና የሚባለው ፓርቲ የውሸት ፓርቲ ነው፡፡ እስካሁንዋ ደቂቃ በህግ የሚታወቅ ብልፅግና የሚባል ፓርቲ የለም፡፡ ግን በየቦታው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ የሚባሉ ሰዎች እየሰማን ነው፡፡ እንደ ትግራይ ሳወራ የትግራይ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚነካ ውሳኔ ከአራት ኪሎ ይምጣ ፣ ከዋይት ሃውስ ይምጣ ፣ ከባንኪንግሃም ፓላስ ይምጣ ፣ ከዌስት ሚኒስትር አብይ ይምጣ ማንም ሰው ሊቀበለው አይችልም፡፡ እኔ ይሄንን አልቀበልም ፤ እኔ በማውቀው ልክ ይህንን የሚቀበል የትግራት ተወላጅ የለም፡፡ እኔ እንደማውቀው ይህንን የሚቀበል የአማራ ተወላጅ አለ አልልም ፤ መኖርም የለበትም፡፡ ከአራት ኪሎ በሚመጣው ትእዛዝ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትህ ለጊዜው ታጥፈዋል የሚባል ኦሮሞ ይኖራል ብየ አላምንም ፤ የሚኖርም አይመስለኝም፡፡”- አቶ ጌታቸው ረዳ (የህወሓት/ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባል)
#TMH

ድሬዳዋ...
ድሬዳዋ ወደቀድሞ ሰላሟና ህብራዊነቷ እየተመለሰች ነው። በከተማዋ ይስተዋል የነበረው ግጭት ከቆመ ሦስት ሳምንት ሆኖታል። የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ የድሬዳዋ ሁኔታን በተመለከተ ከላይ የምትመለከቱትን የቪድዮ ዘገባ ሰርቶ አሰራጭቷል።
(📹9 MB WiFi ብትጠቀሙ)

የአማራና የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር በዛሬው ዕለት ለሁለተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው!
በዛሬው ውይይትም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግ/ መሪዎች ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ በጥናታዊ ጽሁፉ በአማራና በኦሮሞ ህዝቦች መካከል ቁርኝት እንዳለ ተነስቷል፡፡
በታሪክ አጋጣሚ የተሰሩ መልካም ነገሮችና ጥፋቶች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ከተቻለ ለመጪው ትውልድ የተሻለ አጋጣሚ መፍጠር እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡ ሁለቱ ህዝቦች በታሪክ ላይ ያሉ ችግሮችን ብቻ በማንሳት የታሪክ እስረኛ መሆን እንዳሌለባቸው ተገልጿል፡፡
እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም የዳበረ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት የጋራ መግባባት ሊፈጠር እንደሚገባ የጥናት ጽሁፍ አቅራቢዎቹ አንስተዋል፡፡ ውይይቱ በሁለቱ ህዝቦች መካከል አንድነትንና አብሮነት ለማጠናከር በፖለተካ ልህቃን መካከል የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
(EBC)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

አሳሳቢው የትራፊክ አደጋ...
ባለፉት ሁለት 3 ቀናት ብቻ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በደረሱ የትራፍሪክ አደጋዎች የ19 ሰዎች ሂወት አልፏል። በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ እና በጃዊ ወረዳ በደረሱ ሁለት የትራፍሪክ አደጋዎች ነው የ19 ሰዎች ሂወት ያለፈው፡፡ በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ትላንት በ06/04/2012 ዓ.ም በደረሰው አደጋ የ13 ሰዎች ሂወት እንዳለፈ ትላንት መዘገቡ ይታወቃል። በጃዊ ወረዳ በ04/04/2012 እና በ06/04/2012 ዓ.ም በደረሱ አደጋዎች የ6 ሰዎች ሂወት አልፏል፡፡
@tikvahethiopia @tikvahethiopiabot

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኞች ማኅበር ”አባላቱን ለማደራጀትና ለመንቀሳቀስ በአሰሪው ድርጅት ጫና እየተደረገብኝ ነው” በሚል ቅሬታ አሰምቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በበኩሉ ”ቅሬታው የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ነው” ብሏል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-12-17-3
(ENA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
More👇
https://telegra.ph/ETH-12-17-3
(ENA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በዚህ ዓመት የሚሰጠው 12ኛ ክፍል ላይ ብቻ ነው!
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ አስቀድሞ ቢነገርም አንዳንድ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለ10ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎችን እያዘጋጁ መሆኑን መረጃ እየደረሰው ነው፡፡
የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ለኢቲቪ እንደገለፁት ለአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ዝግጅት ማድረግ እንደማይገባ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች መደበኛ የክፍል ፈተና ብቻ እንደሚፈተኑ ለማስታወስ ለሁሉም ክልሎች ተቋሙ ድብዳቤ ፅፏል ብለዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ብሄራዊ ፈተና የሚወስደው 12ኛ ክፍል ላይ መሆኑን ተማሪዎችም ወላጆችም ሆነ ትምህርት ቤቶች ሊያውቁት እንደሚገባ አቶ አርአያ ተናግረዋል።
(ኢቲቪ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ አስቀድሞ ቢነገርም አንዳንድ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለ10ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎችን እያዘጋጁ መሆኑን መረጃ እየደረሰው ነው፡፡
የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ለኢቲቪ እንደገለፁት ለአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ዝግጅት ማድረግ እንደማይገባ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች መደበኛ የክፍል ፈተና ብቻ እንደሚፈተኑ ለማስታወስ ለሁሉም ክልሎች ተቋሙ ድብዳቤ ፅፏል ብለዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ብሄራዊ ፈተና የሚወስደው 12ኛ ክፍል ላይ መሆኑን ተማሪዎችም ወላጆችም ሆነ ትምህርት ቤቶች ሊያውቁት እንደሚገባ አቶ አርአያ ተናግረዋል።
(ኢቲቪ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"...ግልፅ ለመናገር መከላከያም ጭምር፤ትግራዋይ በመሆናቸው የተባረሩ አሉ!" - ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ህዳር 23/2012 ዓ/ም - መቐለ)
"አንድም ወታደር ቢሆን የትግራይ ተወላጅ በመሆኑ ከመከላከያ የተቀነሰ የወጣ የለም!"-ጀነራል ብርሃኑ ጁላ
የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ(ታህሳስ 6/2012 ዓ/ም) ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተከታዩን ተናግረዋል፦
በሠራዊታችን ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ሀገራቸውን በቅንነትና ታማኝነት እያገለገሉ ይገኛሉ። ትግርኛ ተናጋሪውም ቢሆን እንደሌሎቹ ሁሉ ፕሮፌሽናል ወታደር ነኝ፣ፖለቲካ አያገባኝም ወደነፈሰበት አልነፍስም ብሎ ሀገሩን እያገለገለ ነው። አንድም በትግርኛ ተናጋሪነቱ ከሠራዊቱ የወጣ ሰው አላውቅም። አላወጣንም። መውጣትም የለበትም። አባባሉም ትክክል አይደለም።
ሠራዊቱ የጋራ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠራዊት ነው።የትግራይም ሕዝብ ሠራዊት ነው። ትግራይ በመሆኑ ልጅህን ከሰራዊቱ እያስወጡብህ ነው ማለት ምን ማለት ነው። ትክክል አይደለም። ባለን አሰራርና ሕገ ደንብ መሰረት ሰው ይቀጠራል ያገለግላል። ጡረታ መውጪያ ግዜ ገደብና የእድሜ ጣሪያ አለው። በዚህ የወጡ ሰዎች አሉ። ይሄ ለሁሉም የሠራዊቱ አባሎች ላይ የሚሰራ ነውና ይቀጥላል። ከዚህ ውጭ በሌላ መንገድ የወጣ እኔ የማውቀው አንድም ሰው የለም።
ከፍተኛ አመራር ከሆነ እኛ ነን የምናውቀው። ታች ከሆነ ደግሞ በጡረታ፤ በሕክምና፤ በዲስፒሊን የሚባረር ሰው ከሆነ እዛው ተወስኖ ሪፖርት ተደርጎ ነው የሚወጣው። የማይታወቅ ነገር የለም። እኔ እውነት ዶ/ር ደብረጽዮን እንደዛ ብለዋል ወይ የሚል ጥያቄ አለኝ። ለሠራዊቱም ቅርብ ስለሆኑ መረጃ አጥተው እንዴት እንደዛ እንዳሉ አላወቅኩም።

ዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ እንዲንሆኑ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የኦሮሚያና አማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ!
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ እንዲንሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።
በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ ቆይቷል።
የውይይት መድረኩ በሁለቱም ክልሎች ባሉ ዩኒቨርስቲዎች በሚከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ በመምከር የመፍትሄ ሃሳብ ለመጠቆም ያለመ ነው።
ከዚህ ባለፈም ውይይቱ በሁለቱ ክልሎች ህዝቦች መካከል ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነትና ትስስር ይበልጥ በማጠናከር ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።
እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተቀራርበው በቅንጅት እንዲሰሩ እና የፖለቲካ ዓላማቸውን እና ተግባራቸውን በተለያዩ አካባቢዎች ለደጋፊዎችቻው እንዲያሳውቁ የሚያስችል መሆኑም ታውቋል። ለሁለት ቀናት ሲካሄደ የቆየው ውይይትም በዛሬው እለት የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለው ግጭጥ እንዲቆም እና የመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ እንዲንሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ።
መንግስትም በተማሪዎች መካከል ግጭት የሚፈጥሩ አካላት ተጠያቂ እንዲያደርግ በመግለጫቸው ጠይቀዋል። የከፍተኛ ተቋማት ጥበቃ እንዲጠናከርም አሳስበዋል።
(ኤፍ ቢ ሲ)

#DrDesalgnChane
በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚፈጠሩት ግጭቶች የአብን እጅ አለበት ስለሚባለው ጉዳይ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የሰጡት ምላሽ...
አብን ሰላማዊ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ነው። የኦሮሞ ወንድሞቻችን፤ እኔ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነኝ፤ ኦሮሞ ተማሪዎች አሉኝ አስተምራቸዋለሁ እኩል እንደ አማራ ልጆቼ አያቸዋለሁ፤ ያንን የመፍጠር ዓላማ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም። መንግስት ግን አይደለም ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚፈጠር ግጭት ሀገር ውስጥ በሚፈጠሩ ትልልቅ የፖለቲካ ግድያዎች አብንንም ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን እየወነጀለ የሚያስርበት ሁኔታ ነው ያለው።
ለኦሮሞ ወንድሞቻችን ማስተለፍ የምፈልገው የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደህንነታቸው እንዲከበር አማራ ክልል ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ተማሪዎችም ሰላማቸው ተጠብቆ እንዲማሩ አብን የሚችለው የሚሰራ እንጂ ከነዚህ ግጭቶች ጀርባ የለም።
ከእነዚህ ግጭቶች ከጀርባ ያለውን አካል በአግባቡ ፈትሾ ወደህግ የማቅረቡ ኃላፊነት የመንግስት ነው። ለኛም ብዙዎቹን ነገሮችን አንገነዘባቸውም። በእርግጠኝነት መናገር የምችለው አብን በእንደዚህ አይነት የወረደ ና የአማራን ህዝብ ክብር በማይመጥን ድርጊት ውስጥ የሚሳተፍ ድርጅት እንዳልሆነ ነው።

ለአማራ እና ኦሮሞ ህዝብ...
ከአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ የተላለፈ መልዕክት...
"ለሁለቱም ወንድማማች ህዝቦቻችን (አማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች) ማስተላለፍ የምፈልገው፤ ዕጣፈንታችን የተሳሰረ ነው። የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ተከባብረው በሰላም መኖር የመጨረሻ አማራጫቸው ነው። ከዚህ ውጪ ያለው አማራጭ ሁለታችንንም የሚጎዳ ነውና መከባበር፣ መደማመጥ፣ እርስ በእርሳችን ወንድማማችነታችንን ማጎልበት አለብን የሚል መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።" - ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ (የአብን ሊቀመንበር)

#BeleteMolla
"የኦሮሞ ተማሪም ተጎድቷል፤ የአማራ ተማሪም ተጎድቷል። ይሄ እየለየን የምንሰራው ፖለቲካ የትም አያደርሰንም። ከእውነትም መሸሽ የለብንም። ኦሮሞና አማራ ብቻ አይደሉም ሌሎች ብሄር ተወላጅ ተማሪዎችም ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። ይሄ እንዲሆን አንፈልግም።" - አቶ በለጣ ሞላ(የአብን ምክትል ሊቀመንበር)