TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን እንደደረሰበትና ከፈፃሚዎቹ ጥቂቶቹን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው እንደገለጹት፥ በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተደርሶበታል።

በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ ከተሳተፉት ውስጥም ጥቂቶቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸወን አስታውቀዋል።

የወንጀሉ ፈፃሚዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በተለያየ መንገድ በእጃቸው እንደሚያስገቡ የጠቆሙት ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው፥ የወንጀሉ ተሳታፊዎችን በማጋለጥ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ዩንፎርም ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው የጎረቤት አገራትም የደንብ ልብሱ ለወንጀል መፈፀሚያነት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ እየሰሩ ያሉ ጥቂት ግለሰቦችም በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

ፖሊስ በተያዘው ወር ለሚካሔዱት የጥምቀት በዓልና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል።
ለዚህም ስኬት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩንና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያሳይ በማለት ኮሚሽነሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ #ሰባራ_ባቡር አካባቢ እንጀራ በመጋገር የሚተዳደሩ ግለሰቦች #ባእድ ነገር #በመቀላቀል ለአመታት ለምግብ ቤት በማከፋፈል የቆዩ ሲሆን በአካባቢው ህብረተሰብ ጥቆማ #በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ሲል የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮምዩኒኬሽ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በጅግጅጋና አካባቢው #ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው #ወንጀል ዙሪያ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች #በቁጥጥር ስር የሚውሉ አካለትም መኖራቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ከሀምሌ 28 እሰከ 30 በሶማሌ ክልል በጅግጅግናና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ በጋራ ሲያደርጉት የቆዩትን የምርመራ ስራ አጠናቀዋል።

ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ከሀምሌ 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት በጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሄርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ዙሪያ የድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት ተጨማሪ ትልልቅ ወንጀሎች እንደተገኙ የታወቀ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም በቁጥጥር ስር የሚውሉ ተጨማሪ ግለሰቦች መኖራቸውም ታውቋል።

የምርመራው ውጤት በመጠናቀቁም በቁጥጥር ስር ያሉትን የክልሉን የቀድሞ ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ሌሎች አካላት ላይ ክስ መመስረቱ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

የምርመራ ሂደትንና ውጤቱን በተመለከተም አርብ (ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም) በጠቅላይ ቃቤ ህግ ለጋዜጠኞች #መግለጫ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነጭ ሳር🔝

በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት ተነስቶ የነበረው እሳት #በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ #ሽመልስ_ዘነበ እንደገለፁት #የሀገር_መከላከያ_ሠራዊት እና #የፖሊስ_አባለት ባደረጉት ጥረት የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ እሳቱ የተነሳው "አርፋይዴ" ተብሎ በሚታወቀው የፓርኩ ክፍል ሲሆን 1ሺህ ሄክታር ያህል መውደሙን አቶ ሽመልስ ገልፀዋል ፡፡ #ጂቲዜድ የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር እንዲውል የቁሳቁስ አቅርቦት እና አስፈለገውን ወጪ መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ Gamo Zone Adminstration office public Relation unit
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬደዋ‼️

በድሬዳዋ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት የጸጥታ ማስከበር ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ እንዲረከብ መደረጉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በሰሞኑ ሁከት የተጠረጠሩ 200 ሰዎች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ድሬዳዋ እንዲገባ የተደረገው ባለፉት ቀናት በከተማይቱ የነበረው ሁኔታ ከአስተዳደሩ እና ከፌደራል ፖሊስ አቅም በላይ ስለነበር ነው።

የመከላከያ ሰራዊት ከተማይቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን ኮማንድ ፖስቶች በተለያዩ አካባቢዎች ማቋቁሙንም ጽህፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል።

የጀርመን ራድዮ የድሬዳዋ ዘጋቢ #መሳይ_ተክሉ እንደገለጸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በከተማይቱ ተሰማርተዋል። በመኪና ላይ ሆነው ከሚዘዋወሩት በተጨማሪ በየአካባቢው በተጠንቀቅ ቆመው የሚታዩ እንዳሉ ዘጋቢው ተናግሯል። የሰራዊቱ አባላት ለአደጋ ይጋለጣሉ ለተባሉ የመንግስት ተቋማት እና ድርጅቶችም #ጥበቃ እያደረጉ ነው ብሏል።

በከተማይቱ ያለው ዘጋቢያችን የመንግስት ወታደሮቹ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በድምጽ ማጉያ ሲያስጠንቅቁ ተመልክቷል። በድሬዳዋ ሰሞኑን ሲደረጉ የነበሩ የህዝቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ከሚያውኩ ድርጊቶች እንዲታቀቡም ተቃዋሚዎችን ሲያስቡም ታዝቧል።

በድሬዳዋ ላለፉት ሶስት ቀናት ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ጎማዎች በማቃጠል እና ድንጋይ በመደርደር መንገዶችን ዘግተው ነበር። በዛሬው ዕለት በከተማይቱ እንቅስቃሴዎች እንደሚታዩ የገለጸው ዘጋቢያችን መንገዶች መከፈታቸውን እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ስራ መመለሳቸውን ተናግሯል።

በድሬዳዋ ከሰሞኑ በተከሰተው ሁከት ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተጠየቁት የከተማይቱ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እና ፖሊስ “የተደራጀ መረጃ የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ:- DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬ ፖሊስ‼️

#ብሄሬን መሰረት ተደርጎ ጥቃት ተፈፅሞብኛል በሚል በሀሰት የሽንት መሽኛ #ብልቱን በፋሻና ፕላስተር በመጠቅለል ግጭት ለመቀስቀስ የሞከረው ግለስብ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ተጠርጣሪ #ኢብራሂም_ደደፎ_አብደላ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት ሆን ብሎ ብሄሬን መሰረት አድርገው በቢላዋ የሽንት መሽኛ ብልቴን ቆርጠው ጉዳት አድርሰውብኛል በሚል ድርጊቱን ያልፈፀሙ ግለሰቦችን ስም በመጥቀስ ለፖሊስ አቤቱታ ያቀረበው።

ፖሊስ የቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ ሁኔታውን ለማጣራት ተከሳሽን ወደ ህክምና የላከ ሲሆን በተደረገ የህክምና ምርመራ ግለሰቡ ላይ ምንም አይነት ጥቃት #እንዳልተፈፀመበት ማረጋገጥ መቻሉን ተናግሯል።

#ተጠርጣሪው አሁን ላይ #በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ጨምሮ ገልፆ ማንኛውም ሰው በዜጎች መካከል ግጭቶችና አለመግባባቶች እንዲፈጠሩ ከሚያደርጉ ተግባራት ሊቆጠብና ሊርቅ እንደሚገባ አሳስቧል::

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ዞን ፖሊስ‼️

የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር #ኤፌሶን¥ላካይቶ እንደገለጹት በዞኑ የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት በተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀል የተጠረጠሩና እጅ ከፍንጅ የተያዙ በቁጥር 50 የሚሆኑ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ለማድረግና የህግ የበላይነት እንዲከበር ለማስቻል መምሪያው ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሀገሪቱ በለውጥ ጎዳና ላይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ለውጡን የማይቀበሉ አንዳንድ አካላት በሚፈጥሩት የፀጥታ መደፍረስ የተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀሎች እየተበራከቱ በመሆናቸው ችግሮችን ለመቅረፍ የፀጥታ አካላትን ያሳተፈ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል መቋቋሙንም ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የሚፈጸሙ #የስርቆትና #የንጥቂያ ወንጀል #በዘላቂነት ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማወያየትና በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በጉኑኖ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ሌሊት ባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር ፖሊስ ያደረገውን ጥረት ጥቂት የሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ‹‹እኛን መቆጣጠር አትችሉም›› በማለት ሁከት ፈጥረው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ሁከት ፖሊስ ከከተማው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት #በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በከተማው ሁከት የፈጠሩ፣ የተሳታፉና የመሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ህጋዊ የምርመራ ሂደት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

በሶዶ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ በቡድን ተደራጅተው #በስርቆት ወንጀል የተሰማሩ 9 ግለሰቦች ለህግ ቀርበው ተገቢ ውሳኔ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በዋዱ አከባቢም በተመሳሳይ ወንጀል ተሰማርተው የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በተለይ የባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ማሽከርከር እንደሌለባቸው ያሳሰቡት ምክትል ኮማንደር ኤፌሶን ሌሊት ማሽከርከር ለተለያዩ አደጋዎች የሚያጋልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በየአካባቢው ህብረተሰቡ ከወትሮው የተለየ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም ለዞኑ ፖሊስ በ046-551-21-26፣ ለሶዶ ከተማ ፖሊስ 046-551-01-46፣ ለሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ 046-551-00-22 የስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ሰባት ኪሎግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ሃገራት ገንዘብ #መያዙን ገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ። አራት ተጠርጣሪዎችም #በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር #ቶጎ_ውጫሌ ኬላ ላይ ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጪ አገር ገንዘብ መያዙን ገልጿል።

የአሜሪካ፣ የካናዳና የአውስትራሊያ ዶላር፣ ዩሮ፣ ድርሃምና የሌሎች ሃገራት ገንዘብ ነው የተያዘው ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።

ትናንት ምሽት ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የውጪ አገር ገንዘብ ከአራት ተጠርጣሪ ኮንትሮባንዲስቶች ጋር በቶጎ ዉጫሌ ኬላ በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ🔝ቶጎ ውጫሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ #በቁጥጥር ስር የዋለው 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የውጭ አገራት ገንዘብና 7 ኪ.ግ ወርቅ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር‼️

ግምታዊ ዋጋቸው 1 ሚሊየን 300 ሺህ ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃች በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያዎች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ባዛሬው ዕለት በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያዎች ላይ በተደረገ ክትትል ግምታዊ ዋጋቸው 1 ሚሊየን 315 ሺህ 310 ብር የሚሆኑ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም በወልዲያ የጉምሩክ ፍተሻ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ጊዜው ያለፈበት የፋፋ ዱቄት እና ግምታዊ ዋጋቸው 385 ሺህ 50 ብር የሆኑ 369 ሞባይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለፀው።

በተመሳሳይ በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ዋጋቸው 76 ሺህ 500 ብር የሚገመቱ የመኪና ጎማዎችና የተለያዩ መድሃኒቶች በግለሰቦች ቤት ውስጥ በፌዴራል ፖሊስ፣ ጉሙሩክ ሠራተኞች እና ህብረተሰቡ ባደረገው ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከዚህ ባለፈም በህገ ወጥ መንገድ ከመተማ ወደ መሀል ሀገር ሊገቡ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው 167 ሺህ 760 ብር የሆኑ 1 ሺህ 997 የብሬን ጥይቶችና 100 የክላሽ ጥይቶች በሠራባ ኬላ ላይ በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia