الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.3K subscribers
389 photos
19 videos
8 files
921 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
🚫:::::::::::እህቶቼ እባካቹን::::::::🚫

🚫ፎቶዋቸውን የሚለቁ ሴቶች ደህንነት ያሰጋኛል! ሃቂቃ የእናንተ ጉዳይ ሰላሜን ነስቶኛለል።📌📌
ብዬ ስጀምር … ያ ሰላም ልባችሁ ቀጥጥጥ… አላለም አይደል?! አብሽር ቀጥ አይበል ጣጣ የለውም! 

ርዕሱን ቀየርኩት

የማን እጣ ፈንታ እስኪደርሳችሁ ነው??

#ሴቶች ሆይ እንደው ፊታችሁ ላይ በሆነ አጋጣሚ የደረሰ ጫን ያለ ጠባሳ ቢኖር አልያ አንዳንዶች "ብል የበላው ፊት" የሚሉት አይነት "ጯ ፣ ቋ ፣ ሟ ፣ጧ " ፊት ቢኖራችሁ FB ላይ ትፖስቱ ነበር? ??

መልሱን ለናንተ!📌

ውበት እንደተመልካቹ ነው። በኪሎ አይመዘንም ፣ በሊትር አይለካም ፣ በኪሎ ሜትር አይመተርም። ስለዚህም ሁሉም ለራሱ ቆንጆ ነው። አንዳንዶች ደግሞ ከራሳቸው አልፈው በሌሎችም እይታ ቆንጆ ናቸው።
ሁሉም ግን የአላህ ፍጥረት ነው። ማን የቆዳውን ቀለም ፣ ቁመቱን ክብደቱን መርጦ የተፈጠረ አለ? ??📌

እናማ በሌሎች እይታ ቆንጆ ተብላችሁም ይሁን ለእናታችሁ ቆንጆ ሆናችሁ የምትፖስቱ ሴቶች ሆይ!

በርቱ ተበራቱ … ፎቷቹን በአዶቤ "ኤዲቱ"
የፊታቹን ጠባሳና … ቡጉሩን ደልቱ
ራሳቹን በሞናሊዛ ሂሳብ … እያሰባችሁ አክቱ ፖስቱ … ላይክና አድናቆት ሸምቱ
ብዙ አባዙ … ፎሎወር አካብቱ
ይለናል ብላችሁ እንደማትጠብቁ ተስፋ አለኝ።

"ኤዲቱ" ዘመኑ የኤዲቲንግ ነው!
አይ "ፋጤ" ስሜ አይመስጥም ይሸክካል ኤዲት አርጉና አቆላምጣችሁ "F" በሉኝ አልሽ አሉ።

አይ በማንነት የማፈርና ማንነትን የማጣት ቀውስ።
Original ስምሽ የተወዳጁ ነብይ ተወዳጅ ልጅ ተወዳጅ ስም ፋጢማ መሆኑን አላረፍሽም ማለት ነው።
ማንነቱን የማያውቅ በማንነቱ ያፍራል!
ይቅርታ! የስፖንሰር ማስታወቂያ ገብቶብን ነው።

ከማስታወቂያ ተመለስናል…

እንደው አያምጣውና ቢሆንስ ማለት ደግ ነውና ቢሆንስ አልኩና አዕምሮዬ ላይ የተመላለሰውን ግላዊ ስጋት "ፎቶዋቸውን የሚለቁ ሴቶች ደህንነት ያሰጋኛል!" ብዬ ከተብኩት!
እውነቴን ነው ያሳስበኛል …በጣም ያስጨንቀኛል
የእህቶቼ ጉዳይ ያገባኛል … እኔም ይመለከተኛል
ስለዚህ ቅድመ ማስጠንቀቂያ … መስጠት ይገባኛል
አዕምሮዬን ቆርቁሮኛል … ጣቶቼም ክተብ ይሉኛል።ስለዚህም ከተብኩ!

#እህቶች ሆይ! የምትለቁት ፎቶ ሁል ጊዜ Like , Share , Friend Request & Follower ብቻ ይዞ ይመጣል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ብዬ አስባለሁ!

እንዴት? ለምን? ማለት ጥሩ ነው!📌

ሽቅርቅር ብላችሁ ያዙኝ ጋብዙኝ እያላችሁ የምትነሱት ፎቶ ላይ wow wow እያሉ ኮሜንት ላይ የሚጮሁ የመንደር ወጠጤዎች በመልካችሁ ተማርከውና ከመጮህ አልፈው ፎንቃ ጠብ አደረገኝ በሚል ክፉ መንፈስ ተነሳስተው ቅድመ አያቶቻቸው ሂሮሺማ ናጋሳኪ ላይ ያደረሱትን አይነት ከባድ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርጉስ?📌
ምን ዋስትና አላችሁ?📌

ቆይ እናንተ አደጋ ካልደረሰባችሁና የሌሎችን እጣ ፈንታ ካልተቃመሳችሁ ምክር አልሰማም አላችሁ ማለት ነው? ተው ብትባሉ እንቢ አላችሁ አይደል?? "ፋት ከሆኑ ማን አይፈሩ " አለች እህቴ "ከወፈሩ ሰው አይፈሩ" ለማለት ፈልጋ ነው።

ሂሮሺማ ናጋሳኪ ያልኩት ካሚላትና ሔርሜላ ነው።
እንደሚታወቀው ወንዶች ስንባል ጥሎብን በሴት ጉዳይ ደካማ ነን! ደካማ! ² በዚህ ደካማነት ላይ ደግሞ ዱዝ ደነዝነት ሲደመርበት አስቡት በእንቅርት ላይ ጆር ደግፍ! እዛው መንደፋደፍ ነው።

📌ፎንቃ ጠለፈን የሚሉ ወንዶች አብዛኞቹ ፦
አስተሳሰባቸው የተናጋ …
ጆሯቸው ላይሰማ የተዘጋ
ልባቸው እዝነትን የዘነጋ
ቆም ብሎ ማሰላሰል የተሳናቸው
ከራሳቸው ውጪ የሰው ስሜት የማይታያቸው
ከነሱ ፍላጎት በቀር የሌላ የማይሰማቸው
ካልተሳካላቸው ቡጢ እርግጫ ተንኮል ብቀላ የሚቀናቸው ናቸው።
በዚህም ምክንያት በተለያየ አጋጣሚ በእንደዚህ አይነት ግለሰቦች ምክንያት ለከፍተኛ አዳጋ የተጋለጡ እንስቶች እጅግ ብዙ ናቸው። ከነዚህ መካከል ስለ ሁለቱ ሀገር በሰፊው አውርቷል። ወሬውን ተቀባብሎ አራግቧል።

እና እነሱ በFB አይደል የደረሰባቸው የሚል ጥያቄ እንዳታነሱ! በFB ሁሉ ነገራችሁን እየለጠፋችሁ የዚህ አይነት ደነዝ አፍቃሪ ነን ባይ ጎረምሶችን አንፈጥርም ማለት ዘበት ነው። በተለይ ይህች አመርቃኝ Chat እያለች።
የተከሰተውን አስታውሱ የደረሰባቸውን ከፍተኛ አደጋ አትርሱ።

ካሚላት አሲድ ተደፋባት ፊቷን እንዳይሆን አድርጎ ለስቃይ ዳረጋት ፣ ሔርሜላ ከሷም አልፎ ቤተሰቦቿ ላይም የደረሰው ከባድ ጥቃት ማንም የማይረሳው ነው።
አደጋ ከደረሰ በኃላ ፊልም ቢሰራላችሁ ፣ ፕሮግራም ላይ ብትቀርቡ ለሌሎች የስራ ፈጠራ ሀሳብ ከማመንጫነት የዘለለ ለእናንተ ትርፍ ያለው አይመስለኝም።

እናም ሴቶች ሆይ! Follower እናበዛለን እያላችሁ በምትለቁት ፎቶ ተከታይ ማብዛታችሁን ብቻ እያሰባችሁ ህይወታችሁን ሊያመሰቃቅሉና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ወጠጤዎችን በራሳችሁ ላይ በየ ቦታው ከተወሸቁበት እየፈለፈላችሁ በግድ ፎሎው አድርጉኝ ተከተሉኝ ብላችሁ እየጠራችሁ መሆኑን አትርሱ። "አያ በሬ ሆይ! አያ በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ" እንዳይሆን ነገራችሁ።
ኮሜንት ላይ የሚፃፉ ፀያፍ ቃላትን ተመልከቱ!
በጊዜ ራሳችህን ከዚህ አደጋ መክቱ!
ካልሆነ ግን እንዲህ ነው ተረቱ!

"ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል ድስጥ ጥዶ ማልቀስ።"
ሴቶች ሆይ! የወንድማችሁን ምክር ስሙ! እንደ ኩራተኞች ምክር አትናቁ! ከአላህና ከመልዕክተኛው ትዕዛዝ አትራቁ! ከአመፅ ርቃቹ የተቅዋን ስንቅ ሰንቁ! ከዚህች አንቀፅ ዛቻ ራሳችሁን ጠብቁ ተጠንቀቁ!
"እነዚያ ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።"
#(አን_ኑር:63)

አሁንም ፎቶዋቸውን የሚለቁ ሴቶች ደህንነት ያሰጋኛል!
የማን እጣ ፈንታ እስኪደርሳችሁ ነው የምትጠብቁት?! ኧረ #እህቴ ተይ
ይቅርብሽ 📌 ( ሀይደር ኸዲር)

ፁሁፉን አስመልክቶ ጥያቄ ከለ

👉 t.me/Hayatbintkedir

👆ለይ ይላኩልን #ሼር ማድረጉን አይርሱ

💍:::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::::💍

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam