الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
923 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
⁉️ እኛ ግን የት ነን::::::

ነብያችን ሞት አፋፍ ላይ ሁነው አደራ ያሉለት ትልቁ ኢባዳ…
አ…………………ሰላት  ።
እኛ ልብ ገዛን አወቅን ላልን አዎቂዎች በጀነት የተበሸርንበት ከጀሃነም ቅጣት እንተርፍ ዘንዳ አደራችሁን  የተባልንበት ትልቁ አጀንዳ ……… አ…………………ሰላት።
በግብር ይውጣ አቋቋም በቸልተኝነት እና በተለያዩ የሃሳብ ጭነቶች ተዳክመን ዝለን ሰልችቶን በሰግደናል ስሜት ተለብጠን አላህ ፊት የምንቆምለትን አብዩ የሰላት ጉዳያችንን ከዚህች ህመመተኛ ጨቅላ ህፃን ሰላት ጋር ስንመዝነው ምን ያህል ሚዛን ይደፋል ኢባዳችን? …
                                
“ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ።ሰላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ።ሰላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና። አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል።” (
አል-አንከቡት፤ 45)
                            *
መልእክተኛው በነበሩበት ዘመን እንኳን ሙናፊቆች ሰላት ይሰግዱ ነበር። ነገር ግን የሚፈለገውን ሰላት አልነበረም የሚሰግዱት ። ሶላታቸው የይዩልኝ ሰላት ነበር ። ሶላታቸው ማታለያና ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ጊዜ ጠበቂያ ነበር። በርግጥ ራሳቸውን ነው ያታለሉት ፡-
إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا

“መናፍቃን አላህን ያታልላሉ። እርሱም አታላያቸው ነው። (ይቀጣቸዋል)። ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ። አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም።” (
#አል_ኒሳእ፤ 142)

                          *
فَذَٰلِكَ الَّذِي يَدُعُّ الْيَتِيمَ وَلَا يَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ الْمِسْكِينِ فَوَيْلٌ لِلْمُصَلِّينَ الَّذِينَ هُمْ عَنْ صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ الَّذِينَ هُمْ يُرَاءُونَ وَيَمْنَعُونَ الْمَاعُونَ

“ወዮላቸው ለሰጋጆች። ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)። ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት። የዕቃ ትውስትንም (ሰዎችን) የሚከለክሉ ለኾኑት (ወዮላቸው)።” (
#አል-ማዑን፤ 4-7)

         ❗️እኛ የቱ ጋር ነን? …………
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam