الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.3K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
924 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
💍:::::::::::የትዳር ትልቁ አላማ:::::::::💍

#የትዳር ትልቁ አላማ ራስህን ወደ አላህ የሚያቃርብ
አጋዥ ማግኘት ነው።
☞ዐልይ ረዐ እና ፋጥማ ረዐ በተጋቡ ማግስት የአላህ
መልእክተኛ ወደቤታቸው በመሄድ ዐልይን ባለቤትህን
እንዴት አገኘሀት? ሲሉ ጠየቁት እርሱም "አላህን
ለመገዛት ጥሩ ረዳት ሆና አገኘዃት" ብለው መለሱ።

#ትዳርን አላህን የማመፅ ሳይሆን እርሱን የማፍቀርና
የመገዛት ምርጡ መንገድ መሆኑን ተገንዘብ!!!!
ዱንያ የተንጣለለች የእርሻ ቦታ ናት።

የዱንያ ደስታ አለያም ቅመሙ
አሏህን በብቸኝነት ማምለክ እና
ጥሩ #ትዳር መስርተው ያማረ ህይወት
መኖር ሲቻል ነው ___

#ኒካህ/ጋብቻ የእምነት ግማሽ ነው።👌

📌ባልነት ወይም ሚስት መሆን የሚከተሉትን ጠቀሜታዎች ያጎናፅፋል👇

☞አካላችን ከሩሃችን ጋ ሳይጣላእርካታ ያገኛል

☞በብቸኝነት ውስጥ የሚያጋጥሙ በርካታ ስነ-ልቦናዊ ውጥረቶች ይቀንሳል

☞ማህበራዊይነት ያበረታታል

☞ተስፋማ ያደርጋል

☞ፅኑ እና ጠንካራ የሰራተኝነት ስሜት ያጎለብታል

☞ መረጋጋት እና መተጋገዝን ይሰጣል ወዘተ……………👌👌#ሼር

💌::::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
💍:::::::::::::ትዳር በኢስላማ:::::::::::::💍

አንች ሙስሊም #ወጣት ሆይ #አላህን ፍሪ ፦ ለስራ ወይም ለትምህርት ብለሽ #ትዳርን አትተይ፡፡

ትምህርትሽም ሆነ ስራሽ የማይተካልሽ የሆነን ኪሳራ ትከስሪና ትለድሚያለሽ፡፡

#በትዳር_ግን_ኪሳራ_የለም
الخطب المنبرية في المناسبة العصرية
الجزء رابع 400/322
#ሸህፈውዛን_ሀፊዞሁሏህ

💌:::::::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
🚫:::ዝሙት አፀያፊ ነው አትቅረቡት:::🚫

🚫#(ዚና)_ዝሙትን_አትቅረቡ 🚫

ክፍል 2⃣

የዝሙት አኼራዊ ቅጣት እዚህ ዓለም ላይ ከሚያስከትለው ከባድ ቅጣት የባሰ የከፋ! ነው።ለዚህም ነው አላህ (ተባረከወተዓላ) ከሌሎች ሀራም ነገሮች በተለየ መልኩ “ዝሙትን አትቅረቡት” በማለት ገና በርቀት ያስጠነቀቀው፣ ይህ ከመሆኑም ጋር ግን በአሁን ጊዜ አብዘሃኛው ማለት በሚያስችል መልኩ ወጣቱ ዘንድ እንደ ሀላል ይታያል! ሴቱ በግልፅ ዝሙትን ፍለጋ ተራቁቶ ተጋግጦ ከቤቱ ይወጣል!
ወንዱ ብሷል፣ ህልሙም ቅዠቱም ሴትን በሀራም ማደን ነው፣

ለሊቱን ሙሉ #በማህበራዊ_ሚዲያ የማያውቃትን ሴት ሲያማልልና ለብልግና ሲያታልላት ከሷ ጋር ሲቸካቸክ ያድራል፣ ሊነጋጋ ሲል ይተኛል፣ 📌ሱብሂ ሶላት በጀመዓ መስገድ የለ፣ በጊዜ መስገድ የለ፣ ምናልባትም ከሰገደው ፀሃይ ከወጣች በኋላ ነው፣ ጭራሹን ላይሰግደውም ይችላል፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተጠቀማቸው አይቀር ስለ ዲኑ የተወሰነች ነገር እንኳን አንብቦ ከማወቅ ይልቅ በአጅነቢይ ሴት ፎቶ ላይ ስያፈጥና ከሷ ጋር ሲቸካቸክ ጊዜውን ያቃጥላል፣

ዲን አለው ትንሽ ሻል ይላል የሚባለውም ሳይቀር ለትዳር ነው የማናግራት ምን ችግር አለው? በማለት ራሱን እያታለለ በዚያው ቀልጦ ይቀራል! ወንድሜ ሆይ! ያየሃትን ሁሉ ሴት አታገባትም/ የአንተ ልትሆን አትችልም፣ ትዳር አካሄዱ በማህበራዊ ሚዲያም አይደለም! ማህበራዊ ሚዲያ ከመምጣቱ በፊት በስርዓቱ እንደሚፈለገው አላህ በፈቀደው መንገድ ብቻ ለትዳር የምትሆነዋን ሷሊህ የሆነችዋን የልጆችህ እናት፣ ልጆችህን ሸሪዓ በሚፈልገው መልካም አስተዳደግ የምታሳድግልህን፣ አንተንም በዲንህ ላይ የምታበረታህን ሴት ፈልግ፣ "ቤቱን በበሩ በኩል ግቡት" ነው የተባለውና ትዳርን በትክክለኛ መንገድ ፈልጉት፣ በእየ ማህበራዊ ሚዲያው ሁሉ ጥሩ መልእክት ያላቸው የደዕዋ ፅሁፎችና ድምፆችን ሼር ያደረገ ወይም ያደረገች ሁሉ ጥሩ ሷሊህ ናቸው ማለት አይደለም!።
ምናልባትም ሌሎች ነገሮች ላይ ጥሩ ሆኖ ትዳር ላይ ባለው ነገር ስለ ትዳር ካለው የእውቀት ማነስ አንፃርም ይሁን ሌላ… ጥሩ ላይሆን/ላትሆን ይችላሉ።

"ቤቱን በበሩ በኩል ግቡት" ነው የተባለውና #ትዳርን በትክክለኛው መንገድ ያውም ለማግባት ሙሉ በሙሉ በተዘጋጁበት ጊዜ መፈለግ ነው። በየ መንገዱ ያየሃት ሴት ሁሉ የአንተ ሚስት አትሆንምና ያየሃት ሴት ላይ ሁሉ አታፍጥ፣ ይህ አንዱ የዝሙት አካል ሲሆን ለቀጣዩና ለዋናው ዝሙት ራስህን እያዘጋጀህ መሆኑን አትዘንጋ! በዚህ መልኩ በዝሙት የወደቁት በርካቶች ናቸው፣ 🚫ዝሙትን የቀመሰ አላህ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር ለመመለስ እጅግ በጣም ይከብደዋል!!

አላህ ይጠብቀንና! በዚህ ወንጀል የተፈተኑ ወንዶች አግብተው እንኳን የማይተዋቸውና ሚስታቸውን እቤት አስቀምጠው ለብልግና ራሳቸውን አዘጋጅተው የሚወጡ ሴቶችን የሚያድኑ ወንዶች በርካቶች ናቸው።

አዑዙ ቢላህ! ሚስቱ በምታረግዝበት ጊዜና በምትወልድበት ጊዜ ከሰራተኛው ጋር የሚያማግጥ ስንቱ ነው?? ስንቱ ነው ቤተሰቤን እረዳለሁ ኑሮዬን አሻሽላለሁ ብላ ቤቱ ውስጥ ተቀጥራ የምትሰራዋን ሰራተኛ የሚያባልገው?? ከተሳካለት በጥቅማጥቅም አታሎ ካልተሳካለትም በጉልበት አስገድዶ የሙስሊም እህቱን ህይወት ምስቅልቅ የሚያደርጉት ስንትና ስንት ወንዶች ናቸው??

ሴቷም እንዲሁ አግብታም የማታርፍ ከሌላ ወንድ ጋር ስታማግጥ ትዳሯን ልጆችዋን እስከመበት የምትደርስ አለች፣ በተለይ ባሏ ለስራና ለተለያዩ ጉዳዮች ወጣ በሚልበት ጊዜ ከጎረቤት ወንዶች አልያም የሆነ ጊዜ ላይ በምላሱ ካታለላት የመንደር ቦዘኔ ወንዶች ጋር፣ ከራሱ ከባል ወንድም ጋር እንኳን ሳይቀር ይህን እጅግ በጣም ከባድ የሆነን ወንጀል ላይ የሚወድቁ ሴቶች አሉ።

«ልብ በሉ ባሳለፍኩት ክፍል ሴቶች ላይ ይበልጥ ትኩረት አድርጌ
በዚህ ክፍል ደግሞ ይበልጥ ወንዶች ላይ ትኩረት አድርጌ የፃፍኩትና በፅሁፌም ላይ የጠቀስኩዋቸው ነገሮች ልበ ወለድና ግምት እንዳይመስላችሁ በተጨባጭ እየተከሰተና እየባሰበት ያለ ነገር ነው

📌እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! አላህን (ተባረከወተዓላ) እንፍራ!! ከሰዎች ተደብቀን የምንፈፅመውን ወንጀል ሁሉ ከአላህ አይሸሸግምና ወደ አላህ ከልባችን ተፀፅተን ሞት በድንገት መጥቶ ሳይወስደን አልያም አላህ በዚህች ዓለም እያለን ቅጣቱን ሳያከናንበንና ሳያዋርደን እንመለስ
የወጣትነት እድሜም ያልቃል፣ ዛሬ ላይ እህቶችህን የምታባልግበት ሀብት ንብረትህም እንዳልነበራ ይሆናል! አንዳንድ ትልልቅ ለትዳር የሚበቁ ልጆችን አድርሰው፣ የደረሱ ሴት ልጆቻቸውን የሚያክሉ ሴቶችን ስራዬ ብለው እያደኑ የሚያባልጉ የሽማግሌ ዝሙተኞች አሉ፣ ልጆቻቸው እንኳን አውቀው ይህን የአባቶቻቸውን ተግባር ላለ ማየት የራሳቸውን ህይወት ማጥፋት የሚመኙበት ደረጃ "አባቴ የሚሰራውን ከማየት ራሴን ላጥፋ" እስከማለት ደርሰዋል፣ ይህ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ወንጀል ሲሆን ቅጣቱም የተለየ ነው፣ «በአላህ ፈቃድ በሌላ ፅሁፌ እመለስበታለሁ»
📌ዝሙት ከዱኒያዊ ቅጣቱ በተጨማሪ አኼራዊ ቅጣቱ የከፋ ነው!! አላህ (ተባረከወተዓላ) በተከበረው ቃሉ የአማኞችን ባህሪ ከገለፀ በኋላ አማኞች በጭራሽ የማይፈፅሟቸውንና በጣም የሚጠነቀቁዋቸውን ነገሮችን ደግሞ በዝርዝር ስያስቀምጥ እንዲህ ብሏል:–
﴿وَالَّذينَ لا يَدعونَ مَعَ اللَّهِ إِلهًا آخَرَ وَلا يَقتُلونَ النَّفسَ الَّتي حَرَّمَ اللَّهُ إِلّا بِالحَقِّ وَلا يَزنونَ وَمَن يَفعَل ذلِكَ يَلقَ أَثامًا★يُضاعَف لَهُ العَذابُ يَومَ القِيامَةِ وَيَخلُد فيهِ مُهانًا★إِلّا مَن تابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صالِحًا﴾ الفرقان ٦٨-٧٠
“እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉት፣

🚫ዝሙት የማይሰሩትም ናቸው፣ ይህንንም የሚሰራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። በትንሳኤ ቀን ቅጣቱ ለርሱ ይደራርባል፣ በርሷ ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል። ተፀፅቶ (ወደ አላህ) የተመለሰና ያመነ መልካም ስራንም የሰራ ሰው ሲቀር፣” #አል_ፉርቃን_ 68_70
እናንተ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ስሜትና ሸይጧን አይሸነግሉዋችሁ!! የዝሙትን ከባድነት ልብ በሉ! አላህ (ተባረከወተዓላ) ከባእድ አምልኮና ህይወትን ከማጥፋት ጋር ነው አያይዞ ያስቀመጠው፣ ቅጣቱም የተደራረበ ቅጣት እንደሆነ ነው ያስጠነቀቀው!።
የነቢያቶች ህልም ወህይ ነውና ነቢዩ ﷺ በህልማቸው ያዩትን እንዲህ በማለት ተናግረዋል:
እንደ ምድጃ ያለ ከላይ ጠባብና ከታች ሰፊ የሆነን ነገር በውስጡም ጫጫታና ድምፅ ያለበት ሲሆን አየሁ፣ በውስጡም እርቃናቸው የሆኑ ሴትና ወንዶችን አየሁ፣ የእሳት ነበልባል ከታቻቸው በኩል ወደ ላይ እየወጣ (ያሰቃያቸዋል) ስለነሱም ጠየኩ፣ እነሱ እኮ ዝሙተኞች ናቸው ተባልኩ አሉ፣ ሀዲሱ ቡኻሪይ ውስጥ ያለ ረዥም ሀዲስ ሲሆን አጠር ባለ መልኩ ነው ያቀረብኩት።
ዝሙት ኢማንን ከልብ ውልቅ ያደርጋልና እምነት የለሽ ከሀዲ ሆነህ እንዳትሞት ፍራ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
(ዝሙተኛ ዝሙት በሚሰራበት ጊዜ አማኝ ሆኖ ዝሙት አይሰራም!…) ኢማሙ አህመድ 1/276 ቡኻሪይ 2475 ሙስሊም 57 ላይ ከአቢ ሁረይራ ዘግበውታል።በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል…ኢንሻአላህ

💍:::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w