الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.5K subscribers
359 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
📌እህቶች ግን ሚድያ ላይ ለምንድነው የምትወጡት???

የተገላለጠችዋን ሲመክሩ ጭራሽ ሙተነቂቦችም መውጣት ጀመሩ።ኒቋቧን ለብሳ ወጥታ ቁርኣን ትቀራለች፣ኪታቦችን ታስቀራለች፣የኒቋብ style ታሳያለች አረ ስንቱን ወል ዒያዙ ቢላህ!   አስለን የመሰተር አላማው ምንድነው??!  ከሙተበሪጃዋ በምን ተለየሽ አንቺም ወጥተሽ ያዙኝ ልቀቁኝ ካልሽ???  ለምን ዲናችንን እናሰድባለን???
ለሙሃዶራህ 👈 ነውኮ ካልሽ አንቺ አታስፈልጊም ሚድያ ላይ ወጥተሽ ለማስተማር   ጀግና የሱናህ ወንድሞች አሉን እነሱ ይበቃሉ።       ማስተማርና ማቅራት ከፈለግሽ እህቶችሽን ብቻ ወንዶች የማያዩሽን ቦታና ጊዜ መርጠሽ አስተምሪ።  ሚድያ ላይ በምንም መልኩ መውጣትሽ አያስፈልግም።  
አሁን አሁን ላይ ሙተነቂቦች በጣም እየበዙ ነው ሚድያ ላይ መውጣት።
    ወንዶች ፊት የተለያዩ የሚስቡ ድርጊቶችን ወጥታ ታሳያለች።
ቆይ ወንዶች የተሸፈነችዋም ሴት ጭምር እንደምትፈትናቸው አታውቂምን???????
ከሙተበሪጃዋ ባላነሰ መልኩ ሙተነቂቧም የምትፈትነው እንዳለ ዘነጋሽው????
የመሸፈንሽ አላማ ምንድነው??????  አይደለም ቪድዮሽን ድምፅሽ ራሱ አያስፈልግም በምንም በቃ አንቺ ተሰተሪ የውጩንም የውስጡንም ኒቋብ/ሂጃብ ተላበሺ።
ሀያዕ ሊኖረን ይገባል    ሀያዕ ከሌለን እመኚኝ አንከበርም። ሀያኣችን ነው ከፍ ዝቅ የሚያደርገን።
         አሁንም የምልሽ፦ለማስቀራትና ለማስተማር በሚል ሰበብ ሚድያ ላይ ወጥተሽ ወንዶች ፊት አታውሪ። አያስፈልግም።   ከቻልሽ በፅሁፍ ካልቻልሽ ሁሉን መተው።        እህቶችሽን ብቻ አቅሪ።    ብዙ የሱና አንበሶች አሉ እነሱ ይሸፍናሉ ቀሪውን።
ንግግር አላብዛ  እናም እህቴ እስካሁን ለፖሰትሽው ተፀፅተሽ ቪድዮሽን አጥፊ ለሚቀጥለው ደግሞ ላለ መስራት ለረቡና ቃል ግቢለት!
ሀያዕ 👈ከኢማን ነው።  ኒቋብ ከሀያዕ ጋር ነው የሚሄደው።
ወሏሁ አዕለም

#ሼር_አድርጉልኝ_ለሁሉም_ይድረስ

👉#ቴሌግራማችን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam