الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.3K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
924 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
→ክፍል አራት←

🌻🥀🍁🌹🍁🥀🌻
↝የሒጃብ ድንጋጌዎች↜

አላህ(ﷻ)ሒጃብን በበርካታ የቁርኣን አንቀጾች አዟል፡፡ የዚህም
ዋናው ምክንያቱ ሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን ለብሰው ወንዶችን እንዳይፈታተኑ ነው፡፡ ከነዚህም አንቀጾች መካከል ቀዳሚዎቹ በወንዶች የሚጀምሩትና ሱረቱን ኑር ላይ ያሉት ሁለት ተከታታይ አንቀጾች ናቸው፡፡
አላህ(ﷻ)እንዲህ ይላል፡-

↝Surah An-Nur (النّور), verses: 30 ⇩

قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا۟ مِنْ أَبْصَٰرِهِمْ وَيَحْفَظُوا۟ فُرُوجَهُمْ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا يَصْنَعُونَ

ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡

↝Surah An-Nur (النّور), verses: 31 ⇩

ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡(የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት(ባሪያ)ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡

↝Surah Al-Ahzab (الْأحزاب), verses: 33 ↷

وَقَرْنَ فِى بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ ٱلْأُولَىٰ

በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ፡፡

↝Surah Al-Ahzab (الْأحزاب), verses: 53 ↷
وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَٰعًا فَسْـَٔلُوهُنَّ مِن وَرَآءِ حِجَابٍ ذَٰلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ

ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው፡፡ ይህ ለልቦቻችሁ፤ ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው፡፡

ሒጃብ ያስፈለገው ሴቷ ለመሠረታዊ ጉዳዮች ከቤቷ ስትወጣ እንድትታወቅበት፣ ገላዋን እንድትሸፍነት፣ ከወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ እንድትርቅ፣ ውበቷንና ጌጣጌጦቿን ከባዳ ወንዶች እንድትደብቅበት፣ ጨዋነቷን እንድታስመሰክርበት፣ ለባዳ ወንዶች
የተከለከለች መሆኗን እንድታሳይበትና ከባለጌዎች ተንኮል እንድትጠበቅበት ነው፡፡
ይህንኑ አስመልክቶ አላህ (ﷻ) እንዲህ ይላል፡-
↝Surah Al-Ahzab (الْأحزاب), verses: 59 ↷
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَٰجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَآءِ ٱلْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَٰبِيبِهِنَّ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና(በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ (ረድየላሁ አንሀ) «ምርጥ ሴት ማለት ያቺ ወንዶችን የማታይና ወንዶችም እርሷን እንዲያዩዋት የማታደርግ ናት» ብላለች፡፡ ይህም ማለት ወንዱ ዓይነስውር ቢሆን እንኳን፣ ልከ እርሱ እንደማያያት ሁሉ እርሷም እርሱን ማየት የለባትም ማለት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ጊዜ ዓእሻ እና ሀፍሳ (ረድየላሁ አንሁማ) ከነብዩ (ﷺ) ጋር ተቀምጠው ሳሉ ዓይነስውሩ ዐብደሏህ ኡም መክቱም (ረድየላሁ አንሁ)መጣ፡፡
ከዚያም ነብዩ (ﷺ) ለሚስቶቻቸውም፡-
እራሳችሁን ከርሱ ሸፍኑ አሏቸው፡፡ እነርሱም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ታዘናል አሉና (ግን) እርሱ ዓይነስውር ነው፡፡ እናም እኛን ለይቶ ሊያውቀን አይችልም እኮ› በማለት ጠየቋቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ነብዩ(ﷺ እናንተ ግን ዓይነስውሮች አይደላችሁም፤ እናም እርሱን ማየት ትችላላችሁ» አሏቸው፡፡»
(ቲርሚዚ፣ አሕመድና አቡ ዳዉድ)
🍁 🍁 🍁
ያ ኡኽቲ እነዚህ የአላህ ቃላቶች ለኛ ናቸው አጥብቀን ከያዝናቸው በአላህ ፍቃድ ውዷን ጀነትን እንወርስበታለን።
ግን አብዛሃኞቻችን እውነታውን እያወቅን ተዘናግተናል በዚች ዝቅተኛ በሆች ዱንያ ተታለናል ቂያማንም እሩቅ አድርግን አስበናል ይችን አጭር ህይወትም ረጅም አድርገን እያሰብናት አብዛሃኞቻችን ተዘናግተናል።
አላህ ካዘነላቸው ውጭ።

ያ ኡኽቲ የህይወት ዋጋው ምንድን ነው አላህን በመታዘዝና እርሱን ለማግኜት መዘጋጀት ላይ ካልሆነ እ
↝የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) አላሉምንዕ ከናንተ በላጩ አድሜው የረዘመና ስራው ያማረ ነው ከናንተ መጥፎው እድሜው የረዘመና ስራው የከፋ ነው።

እናስተንትን እንጂ ወላሂ ይህች ህይወት ረጅም ብትመስለንም አጭር ናት ባጭር ጊዜ ውስጥ ትጠፋለች።

የምተነፍሽው ትንፋሽም ሊወጣና ላይመለስ ይችላል አይንሽም ትርገበገባለች ዳግም አላህ ፊት ካልሆነ ላትርገበገብ ትችላለች።
ምንአለ ካንቺ በፊት የሞቱትን ብታስታውሽና ከነሱ ትምህርት ብትወስጂ።
ውድ እህቴ ቀድሞ ከሞተው ትምህርት ያልወሰደ ሌላ በምን ትምህርት ሊወስድ ይችላል። ኧረ እንቃ እህቶቼ ይመሻል ይነጋል ጭንቀታችን ዱንያ ብቻ ናት እስከመቼ ነው? ጊዜው ቆሞ ይጠብቀናል እንዴ ወደ ሞት እየተቃረብንኮ ነው።
አትፈሪም በዚህ ሁኔታሽ መሞት።❗️

እንመለስ ወደ አላህ ባረከላሁ ፊኩም።

#አላህ_የበለጠ_ያውቃል
አላህ እኔንም እናንተንም በሰማነው ይጥቀመን።
اللهم صل وسلم على سيدنا محمد
በዱዓችሁ አትርሱኝ
አላህ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን።
☞ኢንሻ አላህ በቀጣይ↓
#የትክክለኛ_ሒጃብ_መስፈርቶች በሚል ርዕስ አጭር በጣም አስተማሪ በሆነ ፁሁፍ እንገናኛለን።

መልዕክቱን
ሼር እንድታደርጉት ማስታወስ ሚጠበቅብኝ አይመስለኝም ምክንያቱም ሃላፊነት እንደሚሰማችሁ አምናለሁ።
እና ለአላህ ብላችሁ
ሼር አድርጉት።
የኡመትሽ ሒጃብ አለመልበስ ካሳሰበሽ/ካሳሰበህ፣ የኡመትሽ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ መልበስ ካመመህ ካመመሽ፣ የኡመታችን ወደ ዚና አብዝቶ መሳብ ካስጨነቀን አሁኑኑ
ሼር እናድርገው። ❗️
#ሼር_ሼር_ሼር_ሼር

ማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ ጀዛከላህ በሚለው ሊንክ አናግሩኝ።
@Jezakellah @Jezakellah

https://t.me/latekrebu_zina
የማይጠገበውን ምክሮቻችንን ይግቡና ያምብቡ
አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑን
Join JOIN join
👇 👇 👇 👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
👍 👆 👍
አሰላሙዓልኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ

ለእህቶቻችን መልስ
ሁላችንም ከዚህ መጥፎ ተግባራት መራቅ አለብን

አንዲት ሙሰሊም እህትህን ለምን አጅ ነብይ ወንድ ታወሪያለሽ ለምን ፎቶሽን ትልኪለታለሽ ለምን ከሱ ጋር በሃራም ታወሪያለሽ ብለህ ስጠይቃት እንዲሀ ብላ ትመልስልሃለች
ከቤተሰቦቸ የሚረዳኝ ማንም ሰው የለም አባቴም በእድሜ የገፋ ስለሆነ በጣም ያካብዳል አናቴም እንደዛው
ወንድሞቸም በጣም መቆጣጠርን ያበዛሉ
ስለዚህ የኔን ስሜት የሚረዳኝ የኔን ንግግር የሚረዳኝ ወጣት ፈልጌ ስወጣ አገኘሁ ለዚሀ ብየ ነው ሌላ አማራጭ ስላጣሁ ነው ትልሃለች።
#ሱብሃናላህ
የሰራችውን ከባድ ወንጀል በማይሆን ምክንያት ለመሸፋፈን ትሞክራለች ግን እህቴ አልገባሽም እንጂ ግዜሸን እድሜሽን ወጣትነተሽን እና ክብረ ንፅህናሽን ሀላል ላልሆነና ለማይገባው ወንድ አሳልፈሽ እየሰጠሽ ነው
የሚገርመው ይህን ሁሉ ነገር እያወቀች ምክንያት እየፈጠረች እራሷን ትሸውዳለች።

ስሚ አንች እህቴ ስማ አንተ ወንድሜ
ታላቁ ነብዩላህ ዮሱፍን ወንድሞቻቸው ጉድጓድ ውስጥ ወርውረዋቸው ይህ ሁሉ በደል በወንድሞቻቸው ከደረሰባቸው በኋላ ከጉድጓዱም ከወጡን በኋላም የገዛ ወንድሞቻቸው በረከሰ ዋጋ ባሪያ አደርገው ሸጧቸው
ከዛም ይህ ሁሉ በደል ከደረሰባቸው በኋላ ባሪያ ሁነው በተሸጡበት ንጉስ ቤት ውስጥ የንጉሱ ሚስት ባቀረበችላቸው አስፀያፊ ሀራም የዚና ግብዣ
ምን እንዳሏት ታውቃላችሁ
ውስጣቸው ባለው ትልቅ ኢማን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው
#አላህን_እፈራለሁ በአላህም ካንች እጠበቃለሁ። ነው ያሉት
#አላሁ_አክበር
ይህ ታላቅ ነብይ ለወጣቱ አርአያ ሆኖ ተቀምጦ ሳለ ግን የኛ ወጣቶች ወንዶችም ሴቶችም ለምን ይመስላችኋል በሃራም ዙሪያ የሚሽከረከሩት
የአላህ ፍቅርና የአላህ ፍራቻ ከብዙ ወጣቶቻችን ልብ ውስጥ ስለጠፋ ነው።
አላህን እንፈራ❗️ አላህን እንፍራ❗️ ከማይፈቀድልን ሰው ጋ በማንኛውም አጋጣሚ ወሬ አናውራ በጋብቻ በሚል ሰበብ ቢሆን እንኳ ጠንቃቄ እናድርግ።
ከኒካህ በኋላ ነው እንደፈለግን ማውራት የምንችለው።
ልታገባት ከፈለክ ቀርበህ አንዴ ብቻ ፊቷንና እግሯን እንድታያት ተፈቅዶልሃል።
ከዛ ውጭ አላህ ቃል ገብቶልሃል በመሃከላችሁ መዋደድንና እዝነትን እንደሚያደርግላችሁ እና ከዚሀ በላይ ምን ትፈልጋላችሁ።
አንተ ውድ ወንድሜ አንች ውድ እህቴ ጋብቻ ትልቅ ነገር ነው አግብተን ደስተኛ መሆን ከፈለግን በሃራም ነገር አናነካካው በሃላል ነገር ብቻ እናጥራው።

ባረከላሁ ፊኩም

አላህ ሆይ ልባችንን ባንተ ፍቅር ብቻ ሙላው
ወጣቶቻችንንም አንተው ጠብቅልን።



ለመልካም ነገር እንሽቀዳደም
☞ አይታወቅም ባንተ ባንች ምክንያት ብዙ ሰው ከዚህ ሃራም ተግባር እንዲርቁ ሰበብ ልንሆን እንችላልን ከኛ ሚጠበቀው
ሼር ማድረግ ነው።


#ሼር_ሼር_ሼር


Join us On
TelegraM Channel
👇 👇 👇 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
→ክፍል አንድ←

↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶቹ↜

አነስ ቢን ማሊክ ባወሩት ሐዲሥ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
↝«የሃይማኖታዊ ዕውቀት መነሳት (በዑለሞች ሞት ምክንያት)፣ የመሃይምነት መንሰራፋት፣ የኸምር (በስፋት) መጠጣትና የዝሙት ይፋ መውጣት ከቂያም
ምልክቶች መካከል ናቸው፡፡» (ቡኻሪና ሙስሊም)

ይህ ከላይ የተጠቀሰው ሐዲሥ ነብዩ (ﷺ) ከዛሬ 1400 ዓመታት በፊት ስለመጪው ጊዜያት ክስተቶች ከተናገሩት ትንቢቶች መካከል ነው፡፡ እነዚህ ትንቢቶችም ከበቂው በላይ በገቢር ተፈጽመው የርሳቸውን ነብይነት ይበልጡኑ የሚያረጋግጡ መረጃዎች ሆነው ቀርበዋል፡፡ ያለ ምንም ጥርጥር ዛሬ ዛሬ ዝሙት በዓለም ማህበረሰብ ዘንድ እንደ መደበኛ የሕይወት ዘዬ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ ዝሙት
የበለጠ በተስፋፋ ቁጥርም ጉዳቱም የዛኑ ያህል አብሮ ሥር ይሰዳል፡፡

ከጌታው ጋር መገናኘትን ተስፋ የሚያደርግ ሰው፣ የጌታውን ምሕረትና እዝነቱን የሚከጅል ሰው፣ እንዲሁም ነገ በኣኼራ የጀነት በሮች ተከፋፍተው እንዲጠብቁት የሚሻና እንኳን ደህና መጣ መባልን የሚፈልግ ሙስሊም ሁሉ የዝሙትን ጉዳቶች ጠንቅቆ ማወቅና ከርሱም መራቅ አለበት፤ ምክንያቱም ብልትን ከሐራም መጠበቅ ከመዳኛ መንገዶች አንዱ ነውና፡፡ ሙስሊሙ በሕይወቱ እስካለ ድረስም የዝሙትን መዘዞች በሚገባ ማወቅና ከዚህ ጸያፍ ነገር በመራቅ የጌታውን ትዕዛዝ አጥብቆ መከተል ይጠበቅበታል፡፡

በዚህ ርዕስ ሥር እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ በርካታ የዝሙት መዘዞች በዝርዝር ይቀርባሉ፡፡ ከዚህም በመነሳት እያንዳንዱ ሙስሊም እራሱን ከዝሙት ይበልጥ አርቆ ለመጠበቅ ይቻለው ዘንድ እነዚህን ጉዳቶች
በቅድሚያ ለራሱ በሚገባ ማወቅ አለበት፡፡ በመቀጠልም አንዱ ሙስሊም ሌላውን በተደጋጋሚ በዚህ ነገር መገሰጽና መምከር አለበት፡፡ የዝሙትን ጉዳት ማወቅ ከርሱ ለመራቅ ትልቁ መንገድ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ነጥብ ላይ የበዛ ትኩረት ሰጥተን ግንዛቤያችንን ማዳበር ይጠበቅብናል፡፡ በተለይ ዛሬ ዛሬ ዝሙትን መሥራት ውሃን የመጠጣት ያህል በቀለለበት ዘመንና የዝሙት ማጥመጃዎች በየቦታው በተዘረጉበት ጊዜ ሙስሊሙ የዝሙትን ጉዳቶች በሚገባ ካልተረዳ ሰቀላሉ ዝሙት ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችን አብዛኛውን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በዝሙት መዳረሻ መንገዶች ዙሪያ ለማንበብና እዚያም እዚህም በመዋለል ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የዝሙትን ጉዳቶች በዝርዝር ማወቁ አንገቢጋቢና ወቅታዊ ነው፡፡


የዝሙት ዋና ዋና ጉዳቶች በየፈርጁ

በዚህ ርዕስ ሥር ወደ 15 የሚሆኑ የዝሙት ጉዳቶች በምድብ ተከፋፍለው ይቀርባሉ፡፡ ነገር ግን የዝሙት ጉዳቶች እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም፤
ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚሁ በየፈርጁ ተከፋፍለው የሚብራራ የዝሙት ጉዳቶችም ሥነ-ልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ጤና ነክ ጠንቆችና መንፈሳዊ ጉዳቶ ናቸው፡፡ ከዝሙት ሥነ-ልቦና ጉዳቶችም እንጀምራለን፡፡

ኢንሻ አላህ በቀጣይ ከዝሙት ስነ ልቦናዊ ጉዳቶቹ እንጀምራለን።

👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

👉በጣም ወሳኝና ትልቅ ትምህርት ያለው ማስታዎሻ ነው። ሁላችንም ልናውቀው ይገባል ምክንያቱም አብዛሃኞቻን አለማወቃችን ነው ወንጀልን እንደቀላል እንድንዳፈረው ሚያደርገን።
👉 እናም ከእናንተ ያለውን በረካ ለሌሎችም ማድረስ አትርሱ ለራሳችን ብቻ ምንኖር ከሆነ የኢማንን ጥፍጥና አናገኝም።
👉 #ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር👈


JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
Audio
🚫:::::::ዝሙት::::::::🚫

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላህ ጥያቄዬ
"አንድ ሴት #ከዚና ፀንሳ ኒካህ ማሰር ይበቃላታል(ከዚና ጓደኛዋም ቢሆን)?

#ሼር_ሼር_ሼር👆
☞ኡስታዝ አቡ ዐብዱራህማን

💍:::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::💍

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam