الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.5K subscribers
359 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም:::☜ #ክፍል_ሀያ_ሶስተ /②③ት 2/ #እናታችን_ሰውዳ     ነብዩ ﷺ ከኸዲጃ ሞት በኃላ ወደ ፈታኝ የህይወት ምእራፍ ተሸጋግረዋል።ነብዩ  ﷺ እናታችን ሰውዳን ረአ ሲያገቡ የሰውዳ እድሜ 55 አመት ነበር።ሚስቶቻቸው አብዛኞቹ ሀምሳዎቹ ውስጥ ከመሆናቸው የተነሳ የነብዩን ﷺ_ ባለቤቶች እድሜ ማወቁ የኢስላም ጠላቶች በነብዩ  ﷺ ላይ የሚቀጥፉት ቅጥፈት በትክክል ለማወቁና ለእነርሱ…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_አራት/②④ት

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች
6/
#እናታችን_ኡሙ_ሰለማህ

    እነኚህ እናታችንም እንደሌሎቹ የነብዩ ﷺ ባለቤቶች ተመሳሳይ ችግር ነበረባቸው። ከባለቤታቸው 
#ከአብዱላህ_ኢብኑ_አብድ_አል_አሰድ ጋር ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ ናቸው። ከሀበሻ ከተመለሱ በኃላ ባለቤታቸው አራት ልጆች ትተው በድር ላይ ሸሂድ ሆኑ። እናታችን ኡም ሰለማህ በዚያን ጊዜ እድሜያቸው ወደ ስልሳ አመት እየተቃረበ ነበር።ነብዩ ﷺ ይቺን ችግረኛ ሴት የሚረዳቸው መከራቸውን የሚያቃልል ሰው አሰቡ አላገኙም። በመጨረሻም ራሳቸው ሀላፊነቱን ለመውሰድ ማግባትን ወሰኑ።የትዳር ጥያቄ አቀረቡላቸው ። እናታችን ኡም ሰለማህ እንዲህ አሉ፣ "በእድሜዬ የገፋሁ፣የቲሞች ያሉብኛ እና ቀናተኛ ሴት   ስለሆንኩ ለአላህ መልእክተኛ አልሆናቸውም" ብላ ላከች። የአላህ መልእክተኛም መልሰው "አብሽሪ አትጨነቂ የእድሜሽ መግፋት ጉዳዬ አይደለም የቲሞቹንም ተንከባካቢያቸው እኔ ነኝ።ለቅናትሽ ዱአ አደርግልሻለሁ አላህ ያነሳልሻል።" ብለው ላኩባቸው እሺ አሉ ወትሮውንም ያንገራገሩት ለነብዩ በመጨነቅ እንዴት ይህን ሁሉ የቲም ሀላፊነት እጥልባቸዋለሁ በሚል ለነብዩ ካላቸው ታላቅ ክብር ነበር።እኒህ ሴት ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ ከእናታችን አኢሻ ጋር ሆነው አቡ ሁረይራህ ሲሳሳቱ ያርሙ ነበር።

7/
#እናታችን_ዘይነብ_ቢንት_ጀህሽ
       ይቺ እናት የነብዩ የአጎት ልጅ እና  የታላቁ ሰሀባ የአብደላህ ኢብኑ ጀህሽ እህት ናቸው። ነብዩ  ﷺ ለዘይድ ኢብኑ ሀሪሳህ ድረዋቸው ነበር።በዘይድ እና ዘይነብ መካከል ከረር ያለ አለመግባባት  ተከሰተ።ዘይድ ረአ ወደ ነብዩ ﷺ ወጥቶ ጉዳዩን ነገራቸው።ነብዩም ﷺ ለማረጋጋት ሲሉ ዘይዲን እንዲታገስ መከሩት። ሊሆን አልቻለም።የፀባቸውም መነሻ ዘይድ ለዘይነብ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘት ይመስላል። ዘይነብ ረአ ከአረብ ጎሳዎች  ሁሉ ታላቅ የሆነው የቁረይሽ ዘር መሆኗ እና ዘይድ ደግሞ ነብዩ ሰአወ ነፃ አውጥተው እስኪድሩት ጊዜ ድረስ ባሪያ መሆኑ ሳይሆን አይቀርም። ነብዩ ﷺ ይህን ሲሰሙ ለማስማማት ብዙ ጥረት አደረጉ ነገር ግን አልተሳካም። ፀቡ እያየለ ሂዶ ለመፋታት በቁ።ምን አልባት አንባቢ "ሁለቱ ምርጥ ሰሀቦች ተግባብተው በትዳር ለመቀጠል መስማማት ለምን ተሳናቸው?" የሚል ሀሳብ በአእምሮ ሊመጣ ይችላል።ከክስተቱ በስተኃላ አላህ ለሙስሊሞች አንድ ሊያስተምር የፈለገው ነገር መኖሩ ከዚያ በኃላ የተከሰቱትን ክስተቶች  ማወቅ ለጥያቄው መልስ ያገኛል።

   
#ዘይድ_ኢብን_ሀሪስ ከነብዩ  ﷺጋር የነበራቸው ቁርኝት የጠበቀ መሆን እና ያሳለፉት ጊዜ ረዘም ያለ በመሆኑ በሰዎች ዘንድ የነብዩ ልጅ ተደርገው #ዘይድ_ኢብን_ሙሀመድ እየተባሉ ይጠሩ ነበር።በአረቦች ባህል አንድ ሰው ባእድ የሆነን ሰው አስጠግቶ እያገለገለው ለረጅም ጊዜ ከቆየ እንደልጁ በቁጠር በስሙ ይጠራል።ሁሉ ነገሩ ከስጋ ልጅ ተለይቶ አይታይም ነበር። በዚህም የተነሳ እሱ ያገባትን ሴት አሳዳሪው የነበረው ሰው ማግባትም እርም ነበር።ይህን  መሰል አጉል የጃሂሊያ አስተሳሰብ አላስፈላጊ መሆኑን አላህ በቁርአኑ አውግዞታል። ከዘይድ የተፋቱትን እናታችን #ዘይነብን እንዲያገቡ ነብዩን ﷺ አዘዛቸው።

☞ ዘይድ ኢብን ሙሀመድ የሚለው አጠራር ትክክል እንዳልሆነ አላህ በቁርአኑ እንዲህ ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ادْعُوهُمْ لِآبَائِهِمْ هُوَ أَقْسَطُ عِندَ اللَّهِ ۚ فَإِن لَّمْ تَعْلَمُوا آبَاءَهُمْ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ وَمَوَالِيكُمْ ۚ وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ فِيمَا أَخْطَأْتُم بِهِ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

ለአባቶቻቸው (በማስጠጋት) ጥሯቸው፡፡ እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛ ነው፡፡ አባቶቻቸውንም ባታውቁ በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው፡፡ በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ኀጢአት  አለባችሁ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 5)

   ☞የመሀመድ ልጅ እየተባለ ይጠራ የነበረውን ሰሀቢይ የፈታትን ሚስት አግባ በማለት አላህ (سبحانه وتعالى) እንዲህ ሲል አዟቸዋል፣

وَإِذْ تَقُولُ لِلَّذِي أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِ وَأَنْعَمْتَ عَلَيْهِ أَمْسِكْ عَلَيْكَ زَوْجَكَ وَاتَّقِ اللَّهَ وَتُخْفِي فِي نَفْسِكَ مَا اللَّهُ مُبْدِيهِ وَتَخْشَى النَّاسَ وَاللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَاهُ ۖ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيْدٌ مِّنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَاكَهَا لِكَيْ لَا يَكُونَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ حَرَجٌ فِي أَزْوَاجِ أَدْعِيَائِهِمْ إِذَا قَضَوْا مِنْهُنَّ وَطَرًا ۚ وَكَانَ أَمْرُ اللَّهِ مَفْعُولًا
ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ) አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 37)
ነብዩ  ﷺ የሰው ምላስ ፈርተው ሀቁን ከማሰረተማር ወደ ኃላ እንደማይሉ አላህ በተደጋጋሚ በቁርአኑ ውስጥ መስክሮላቸዋል። በዚህ ጉዳይ የሰዎች ቀልብ ይሰበራል በማለት ወፈ ኃላ ለማለት ሲሞክሩ አላህ በግልፅ ትዛዝ አስተላለፈባቸው።እሳቸው ማንንም ሳይፈሩ የኢስላምን ድንጋጌ ማስተማር ነበረባቸው። ምክንያቱም ከሳቸው በኃላ ሌላ ነብይ መጥቶ ሊያስተካክል አይችልም።እርሳቸው የመጨረሻ ነብይ ናቸውና።ከዚህ ጋር በተያያዘ ነበር አላህም የመጨረሻ ነብይ እንደሆኑ በቁርአኑ በግልፅ ያወጀው።ይህንንም በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፤
مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡።(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 40)
    እውነታው እና በቁርአን የተመሰከረለት የነብዩ ﷺ እና የእናታችን ዘይነብ ቢንት ጀህሽ ጋብቻ ያሳለፍነውን ይመስል ነበር።ነገር ግን አንዳንድ ሙናፊቆች የሚያወሩት ያልተጨበጠ እና ከሀቅ የራቀ ቅጥፈት በስፋት ሲናፈስ ይስተዋላል። መፅሀፏ አጭር ከመሆኗ አንፃር  ለእያንዳንዱ ውሸት አጥጋቢ መልስ እንዳልፅፍ ይረዝማል የሚል ፍራቻ አደረብኝ በጥቅሉ የሚያወሩት ወሬ እዚህ ግባ የማይባል እና ውሃ ቀጠነ የማይቋረጥ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ
@Tidar_Be_Islam👈👈