الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.6K subscribers
359 photos
16 videos
7 files
912 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
❥::::::::::::::::ሀያዕ::::::::::::::❥

☞☞ሀያዕ ከኢማን ነው!! ሀያዕ ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም ሀያዕ ነው!!

#እህቴ__ሆይ!👇👇

☞ሰላት የጋብቻ ዋነኛ መስፈርትሽ ይሁን!!
ለፈጠረው አምላክ ያልተናነሰ፣ ለነብሱ ያላዘነና ትእዛዝን ያላከበረ ሰው ላንቺ የሚያስብና የሚራራ አይሆንም!!

አላህን ከወደድሽ ወዳጆቹን ትወጃለሽ ለትእዛዛቱ እጅ የማይሰጡ ፋሲቆችን ትጠያለሽ፣ ትርቂያለሽም!! ሰው እንደውሎው ነው!!

📐::::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::📐

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
❥::::::::::::::::ሂጃብ:::::::::::::❥

በዉስጥ መስመር ስለ ሂጃብ ለጠየቃቹት ጥያቄ አጠቀላይ መልስ

🚫ሂጃብ አንለብስም ልባችን ንጹህ ነው ብለው ለሚከራከሩ እህቶች :- 🚫

🚫ሂጃብን ለብሰዉ መልሰዉ ለወለቁ እህቶች አሪፍ መላሽ ።#እህቴ ልብ በይ ሂጃብሽ ክብርሽ አንጂ እፍረትሽ አይደለም።

🚫አንደኛ ልብ ውስጥ ያለ ኢማን ግዴታ አካል ሊተገብረው ይገባል፡፡ምክንያቱም ኢማን ማለት፡-በልብ የሚታመን በምላስ ሚነገር በአካል ሚተገበር ነው:: ☜☜
ሌላው ደግሞ ያለምንም ሙግትና ክርክር አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) በሂጃብና በጨዋነት ያዘዛቸው የንጽህና ተምሳሌት ሰሃቦችን ነው:: እንዲህ ብሏል:-

وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ ۚ ذَٰلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ [٣٣:٥٣]
|ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው፡፡ ይህ ለልቦቻችሁ፤ ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው፡፡´
(ምእራፍ #አል_አህዛብ_አንቀጽ_53)

ታዲያ እኛ ከእነርሱ የተሻልን ሆነን ነው ይህንን የምንለው? መልሱን ለአስተንታኞች::
በእርግጥ ስለ ኒቃብ ፊት ስለመሸፈን የሚናገሩ መረጃዎችን በጭሩም ቢሆን ለመዳሰስ ብንሞክር የሚዘለቅ አደለም:: ለማንኛውም ግን ሴት ልጅ ፊቷን መሸፈነ ግዴታ እንደሆነ ተከታዩ አንቀጽም በማያሻማ መልኩ አስቀምጦታል:: አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል:-

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا [٣٣:٥٩]
|አንተ ነብይ ሆይ ለሚስቶችህ ለሴት ለጆችህም ለምእመናንም ሚስቶችም ከመከናነቢያቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው ፡፡

ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው አላህም መሃሪ አዛኝ ነው´
(ምእራፍ #አል_አህዛብ_አንቀጽ_59)☜☜

📌 ሸይኽ አብድራህማን ቢን ናስር አስሳዕዲ አላህ ይዘንላቸውና ይህን አንቀጽ አስመልክተው እንዲህ ብለዋል ፡- ማለትም “ከልብስ በላይ የሚሆን እንደ መቅለሚያ ጉፍታ ኩታና የመሳሰሉት ሲሆን በእርሱ ፊቶቻቸውንና ደረታቸውን ይሸፍኑ ማለት ነው”::

በእውነቱ የውበት ዋናው መገለጫ ፊት ነው::አንድ ሰው ስለሚወዳት አሊያም ስለሚመኛት ሴት ሲያስብ ከሁሉ በፊት ፊቷን ነው ሚቀርጸው:: ለማየትም ሚቌምጠው ዳሌ ፣ሽንጥ፣ ወገብ እግር ሌላም ሌላም ከፊት በኃላ የሚመጡ ነገሮች ናቸው::
ታዲያ ይህ የውበት መገለጫ ፣ሳቢ መግነጢስ ከሆነ እንዴት መሸፈን የለባትም ይባላል??? መልሱ ለማንም ግልጽ ነው አላህ ሁላችንንም በውስጣዊም በውጫዊም ሂጃብ ያስጊጠን:: አንቺ ውዲቷ እህቴ ኒቃብሽን በመልበስ ደረጃሽን የበለጠ ከፍ ልታደርጊው ይገባል::

ኒቃብ መልበስ ከነገር አለሙ የሚያሰናብት አድርገው ለሚመለከቱ እንዲሁም ለሚሰብኩ ለውጪም ይሁን ለውስጥ ጠላቶችሽ ኒቃብሽን ለብሰሽ ለራስሽም ይሁን ለሌሎች መልካም ነገርን በማበርከት ላይ ፍጹም እንደማያቅብሽ በተግባር አሳያቸው አዎ! ኒቃቤ ውበቴን እንጂ አይምሮዩን አልሸፈነውም በያቸው ውዷ እህቴ👌

📐:::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::::📐

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
🚫:::::::::::እህቶቼ እባካቹን::::::::🚫

🚫ፎቶዋቸውን የሚለቁ ሴቶች ደህንነት ያሰጋኛል! ሃቂቃ የእናንተ ጉዳይ ሰላሜን ነስቶኛለል።📌📌
ብዬ ስጀምር … ያ ሰላም ልባችሁ ቀጥጥጥ… አላለም አይደል?! አብሽር ቀጥ አይበል ጣጣ የለውም! 

ርዕሱን ቀየርኩት

የማን እጣ ፈንታ እስኪደርሳችሁ ነው??

#ሴቶች ሆይ እንደው ፊታችሁ ላይ በሆነ አጋጣሚ የደረሰ ጫን ያለ ጠባሳ ቢኖር አልያ አንዳንዶች "ብል የበላው ፊት" የሚሉት አይነት "ጯ ፣ ቋ ፣ ሟ ፣ጧ " ፊት ቢኖራችሁ FB ላይ ትፖስቱ ነበር? ??

መልሱን ለናንተ!📌

ውበት እንደተመልካቹ ነው። በኪሎ አይመዘንም ፣ በሊትር አይለካም ፣ በኪሎ ሜትር አይመተርም። ስለዚህም ሁሉም ለራሱ ቆንጆ ነው። አንዳንዶች ደግሞ ከራሳቸው አልፈው በሌሎችም እይታ ቆንጆ ናቸው።
ሁሉም ግን የአላህ ፍጥረት ነው። ማን የቆዳውን ቀለም ፣ ቁመቱን ክብደቱን መርጦ የተፈጠረ አለ? ??📌

እናማ በሌሎች እይታ ቆንጆ ተብላችሁም ይሁን ለእናታችሁ ቆንጆ ሆናችሁ የምትፖስቱ ሴቶች ሆይ!

በርቱ ተበራቱ … ፎቷቹን በአዶቤ "ኤዲቱ"
የፊታቹን ጠባሳና … ቡጉሩን ደልቱ
ራሳቹን በሞናሊዛ ሂሳብ … እያሰባችሁ አክቱ ፖስቱ … ላይክና አድናቆት ሸምቱ
ብዙ አባዙ … ፎሎወር አካብቱ
ይለናል ብላችሁ እንደማትጠብቁ ተስፋ አለኝ።

"ኤዲቱ" ዘመኑ የኤዲቲንግ ነው!
አይ "ፋጤ" ስሜ አይመስጥም ይሸክካል ኤዲት አርጉና አቆላምጣችሁ "F" በሉኝ አልሽ አሉ።

አይ በማንነት የማፈርና ማንነትን የማጣት ቀውስ።
Original ስምሽ የተወዳጁ ነብይ ተወዳጅ ልጅ ተወዳጅ ስም ፋጢማ መሆኑን አላረፍሽም ማለት ነው።
ማንነቱን የማያውቅ በማንነቱ ያፍራል!
ይቅርታ! የስፖንሰር ማስታወቂያ ገብቶብን ነው።

ከማስታወቂያ ተመለስናል…

እንደው አያምጣውና ቢሆንስ ማለት ደግ ነውና ቢሆንስ አልኩና አዕምሮዬ ላይ የተመላለሰውን ግላዊ ስጋት "ፎቶዋቸውን የሚለቁ ሴቶች ደህንነት ያሰጋኛል!" ብዬ ከተብኩት!
እውነቴን ነው ያሳስበኛል …በጣም ያስጨንቀኛል
የእህቶቼ ጉዳይ ያገባኛል … እኔም ይመለከተኛል
ስለዚህ ቅድመ ማስጠንቀቂያ … መስጠት ይገባኛል
አዕምሮዬን ቆርቁሮኛል … ጣቶቼም ክተብ ይሉኛል።ስለዚህም ከተብኩ!

#እህቶች ሆይ! የምትለቁት ፎቶ ሁል ጊዜ Like , Share , Friend Request & Follower ብቻ ይዞ ይመጣል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ብዬ አስባለሁ!

እንዴት? ለምን? ማለት ጥሩ ነው!📌

ሽቅርቅር ብላችሁ ያዙኝ ጋብዙኝ እያላችሁ የምትነሱት ፎቶ ላይ wow wow እያሉ ኮሜንት ላይ የሚጮሁ የመንደር ወጠጤዎች በመልካችሁ ተማርከውና ከመጮህ አልፈው ፎንቃ ጠብ አደረገኝ በሚል ክፉ መንፈስ ተነሳስተው ቅድመ አያቶቻቸው ሂሮሺማ ናጋሳኪ ላይ ያደረሱትን አይነት ከባድ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርጉስ?📌
ምን ዋስትና አላችሁ?📌

ቆይ እናንተ አደጋ ካልደረሰባችሁና የሌሎችን እጣ ፈንታ ካልተቃመሳችሁ ምክር አልሰማም አላችሁ ማለት ነው? ተው ብትባሉ እንቢ አላችሁ አይደል?? "ፋት ከሆኑ ማን አይፈሩ " አለች እህቴ "ከወፈሩ ሰው አይፈሩ" ለማለት ፈልጋ ነው።

ሂሮሺማ ናጋሳኪ ያልኩት ካሚላትና ሔርሜላ ነው።
እንደሚታወቀው ወንዶች ስንባል ጥሎብን በሴት ጉዳይ ደካማ ነን! ደካማ! ² በዚህ ደካማነት ላይ ደግሞ ዱዝ ደነዝነት ሲደመርበት አስቡት በእንቅርት ላይ ጆር ደግፍ! እዛው መንደፋደፍ ነው።

📌ፎንቃ ጠለፈን የሚሉ ወንዶች አብዛኞቹ ፦
አስተሳሰባቸው የተናጋ …
ጆሯቸው ላይሰማ የተዘጋ
ልባቸው እዝነትን የዘነጋ
ቆም ብሎ ማሰላሰል የተሳናቸው
ከራሳቸው ውጪ የሰው ስሜት የማይታያቸው
ከነሱ ፍላጎት በቀር የሌላ የማይሰማቸው
ካልተሳካላቸው ቡጢ እርግጫ ተንኮል ብቀላ የሚቀናቸው ናቸው።
በዚህም ምክንያት በተለያየ አጋጣሚ በእንደዚህ አይነት ግለሰቦች ምክንያት ለከፍተኛ አዳጋ የተጋለጡ እንስቶች እጅግ ብዙ ናቸው። ከነዚህ መካከል ስለ ሁለቱ ሀገር በሰፊው አውርቷል። ወሬውን ተቀባብሎ አራግቧል።

እና እነሱ በFB አይደል የደረሰባቸው የሚል ጥያቄ እንዳታነሱ! በFB ሁሉ ነገራችሁን እየለጠፋችሁ የዚህ አይነት ደነዝ አፍቃሪ ነን ባይ ጎረምሶችን አንፈጥርም ማለት ዘበት ነው። በተለይ ይህች አመርቃኝ Chat እያለች።
የተከሰተውን አስታውሱ የደረሰባቸውን ከፍተኛ አደጋ አትርሱ።

ካሚላት አሲድ ተደፋባት ፊቷን እንዳይሆን አድርጎ ለስቃይ ዳረጋት ፣ ሔርሜላ ከሷም አልፎ ቤተሰቦቿ ላይም የደረሰው ከባድ ጥቃት ማንም የማይረሳው ነው።
አደጋ ከደረሰ በኃላ ፊልም ቢሰራላችሁ ፣ ፕሮግራም ላይ ብትቀርቡ ለሌሎች የስራ ፈጠራ ሀሳብ ከማመንጫነት የዘለለ ለእናንተ ትርፍ ያለው አይመስለኝም።

እናም ሴቶች ሆይ! Follower እናበዛለን እያላችሁ በምትለቁት ፎቶ ተከታይ ማብዛታችሁን ብቻ እያሰባችሁ ህይወታችሁን ሊያመሰቃቅሉና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ወጠጤዎችን በራሳችሁ ላይ በየ ቦታው ከተወሸቁበት እየፈለፈላችሁ በግድ ፎሎው አድርጉኝ ተከተሉኝ ብላችሁ እየጠራችሁ መሆኑን አትርሱ። "አያ በሬ ሆይ! አያ በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ" እንዳይሆን ነገራችሁ።
ኮሜንት ላይ የሚፃፉ ፀያፍ ቃላትን ተመልከቱ!
በጊዜ ራሳችህን ከዚህ አደጋ መክቱ!
ካልሆነ ግን እንዲህ ነው ተረቱ!

"ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል ድስጥ ጥዶ ማልቀስ።"
ሴቶች ሆይ! የወንድማችሁን ምክር ስሙ! እንደ ኩራተኞች ምክር አትናቁ! ከአላህና ከመልዕክተኛው ትዕዛዝ አትራቁ! ከአመፅ ርቃቹ የተቅዋን ስንቅ ሰንቁ! ከዚህች አንቀፅ ዛቻ ራሳችሁን ጠብቁ ተጠንቀቁ!
"እነዚያ ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።"
#(አን_ኑር:63)

አሁንም ፎቶዋቸውን የሚለቁ ሴቶች ደህንነት ያሰጋኛል!
የማን እጣ ፈንታ እስኪደርሳችሁ ነው የምትጠብቁት?! ኧረ #እህቴ ተይ
ይቅርብሽ 📌 ( ሀይደር ኸዲር)

ፁሁፉን አስመልክቶ ጥያቄ ከለ

👉 t.me/Hayatbintkedir

👆ለይ ይላኩልን #ሼር ማድረጉን አይርሱ

💍:::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::::💍

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
☞ ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ
" ማንኛዋም ሽቶ ተቅብታ ወደ መስጂድ የወጣች ሴት መልሳ እስክትታጠብ ድረስ ሰላቷ ተቀባይነት የለውም "

📚 [ አልባኒ ሰሂህ ብለውታል ]

👉 ልብ በይ #እህቴ መስጂድ ለሰላት ብለሽ ወጥተሽ ሽቶ በመቀባትሽ ሰላትሽ ተቀባይነት አያገኝም ከተባለ ፤ ለሌላ ሀጃሽ ሽቶ ተቀባብተሽ ስትወጪ እንዴት ሊሆን ነው ቅጣቱ ?! አስቢበት !!! አስቡበት።📌

💍:::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::💍


https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
❥::::ህይወት ከስልምና ጋር::::❥

እህቴ☞➩ውጫዊ ውበትሽን
#በሂጃብ እንዳስዋብሽው ,,,,,

☞ውስጣዊ ማንነትሽንም
አሏህን በመፍራት አስውቢው 🌹

#እህቴ_በዲንሽ_ጠንካራ_ሁኚ

ቢንት ኸዲር

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::::💍

t.me/Tidar_Be_Islam
t.me/Tidar_Be_Islam
#እህቴ! "ጋብቻ የአላህ ሪዝቅ(ሲሳይ) አይደለምን?ኒቃብ(መልበስ)አላህን መታዘዝ አይደለምን?ኧረ እንደት አላህን መታዘዝ የአላህን ሪዝቅ ትከለክላለች?!"<አላህን የሚጠነቀቅ(የሚፈራ)(ከችግሩ) መዋጫን ያደርግለታል፣ካላሰበው ቦታም ሪዝቅን ይለግሰዋል> መታሰቢያነቱ→በኒቃብ ፊቴን ከተሸፈንኩ ባል አላገኝም ለሚሉ እህቶች!

ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
አቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- አንድ ሰው #ሚስቱን_ወደ አልጋው ቢጠራት እሷም እምቢ ብትል፣ እሱም ቢያሳልፍ።
በእርሷ የተናደዱ ሌሊት መላአክቶች እስከ ማለዳ ድረስ ይረግሟታል፣ ተስማሙ። ባለቤቷ ወደ ፍላጎቱ ቢጠራት ማዳመጥ እና መታዘዝ የሴቲቱ ግዴታ ነው, ከትክክለኛ ሰበብ በስተቀር.ስለዚህ
#እህቴ_የባልሽን ትዕዛዝ አክባሪ ሁኚ ። ነገ ለአኼራሽም ይጠቀምሽ ዘንድ

        ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞ትዳር_በኢስላም☜

 
#ክፍል_አንድ/①

  
#ኹልዕን_በተመለከተ_በባል_እና_ሚስትመካከል_የሚፈፀሙ_ስህተቶች!!!!!

❗️
#በወንዶች_ላይ_የሚስተዋሉ_ጥፋቶች

    ኹልዕ በሸሪዓችን የተፈቀደ እና ሁሉም ሰው ያለጥላቻና ያለማመንታት ሊቀበለው ግድ ይለዋል።አንዳንድ ወንዶች በዚህ ላይ የተለያዩ ስህተቶችን ሲፈፅሙ ይስተዋላሉ።ከፊሉ ስለዚህ ነገር ምንም እውቀቱ እና ግንዛቤው ስለሌለው ለሚስቱ ሳይመቻት ቀርቶ ሸሪዓው በሚፈቅደው መሰረት ማስለቀቂያ ከፍላ ኹልዕ ስትጠይቅ የታባሽ ብሎ ጨቁኖ ለማኖር የሚፈልግ አለ። ይቺ ሴት ችግር ኑሮባት ፍታኝ ብላ ብትጠይቀው ሸሪዓ እንደሚደግፋት ማወቅ ግድ ይለው ነበር። እያስፈራራ ሳትፈልግ በግዴታ ከኔ ጋር ኑሪ ማለት ከየት የተገኘ ሸሪዓ ነው? ይህን ቢያደርግ አላህ ፊት ተጠያቂ ነው።

     ☞ ሴቷ ወዳው እና አፍቅራው እንጂ ተገዳ እንድትኖር ኢስላም አያዝም።የሚሰራ ጉልበት አለኝ የሚናገር አንደበት አለኝ ብሎ ይቺን የአላህን ሴት ባሪያ ቢበድላት ነገ ሃያሉ ጌታችን ዚህ ትፋረደዋለች። ዛሬ ሰሚ አጥታ ብትጨቆን ነገ የፍትህ ባለቤት ናት።

    ከነብዩ( صلى الله عليه وسلم) ዘመን ጀምሮ ኢስላም ለሴቶች የሰጠው ክብር እና ዋስትና ከዚህ በፊት በነበሩት ሀይማኖቶች ያልተጠቀሰ ሆኖ እናገኘዋለን። ከነዚህ አንዱ ሴት ልጅ የማይመቻትን እና የማትወደውን ባል እርሷ  ከፈለገች ሸሪዓውን ሳትፃረር መፍታት መቻሏ ነው። ለዚህም ማስረጃው የሚከተለው አንቀፅ ነው፣

فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ اللَّهِ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا فِيمَا افْتَدَتْ بِهِ ۗ

የአላህንም ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብታውቁ በእርሱ (ነፍሷን) በተበዠችበት ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለም፡፡ (አል በቀራህ 229)

    ቡኻሪ ላይ በተዘገበው ሀዲስ የሳቢት ኢብኑ ቀይም ሚስት በማለዳ ወደ ነብዩ ሰአወ ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች፣ "የአላህ መልክተኛ ሆይ ሳቢት በዲንም ሆነ ፀባዩ ሳካ አላወጣለትም ነገር ግን በራሴ ላይ ክህደትን እፈራለሁ(ስለምጠላው ሀቁን ባለመጠበቄ ዝቅተኛው ኩፍር ላይ ልወድቅ ስለምችል ይፍታኝ) አለች፣ የአላህ መልእክተኛ( صلى الله عليه وسلم)"
የአትክልት ቦታውን ተመልሽለታለች?" አሏት እሷም "አዎ" አለች ፣የአትክልቱንም ቦታ መለሰች።እንዲፈታትም አዘዙት።

     የቁርአን አንቀፁ እና ሀዲሱ እንደሚያስረዳው አንዲት ሴት ከባሏ ጋር እንዳትኖር የሚያግዳት በቂ ምክንያት ካላት በጉልበት አፍኖና ጨቁኖ ማኖር እንደማይቻል አበክሮ ያስተምራል።

    ☞ ❗️
#ወንዶች_አላህንፍሩ!! ኢስላም ለሰው ልጆች ሁሉ በቂ መፍትሄ የሚሰጠውን በእናንተ የግንዛቤ ችግር ሴት ልጅን የበታች አድርጎ እንደሚጨቁን አታስመስሉት።ከኢስላም ውጭ ያለው አካል ኢስላምን አያውቅም ኢስላምን የሚመዝነው በተከታዮቹ ነው። ወንዶች ሆይ፣ ዱኒያም አኼራም የተስተካከለ ይሆን ዘንድ #የነብዩ_(ሰለላሁ_ዓሌይሂ_ወሰለም) ፈለግ እግር በእግር በመከታተል ጥሩ ሞዴል ለመሆን ሞክሩ ።

ለ/
#በሴቶች_ላይ_የሚስተዋሉ ጥፋቶች❗️
   ❗️
#የሴት_ልጅ_ፍቺ_መጠየቅ የተፈቀደ ነው ሲባል ገደብ የሌለው አስመስለው እንደፈለጉ እየተነሱ #ፍታኝ_እሄደዳብላ እያሉ ባሎቻቸውን እና ቤታቸውን የሚያምሱ ሴት እህቶቻችን ቁጥራቸው እየተበራከተ መጥቷል።ከዚህም በባሰ ሁኔታ ኢስላም መፍትሄን አስቀምጦ እያለ በቁርአን መዳኘት ሲገባት አሻፈረኝ ብላ ባሏን በሌላ ህግ ለመዳኘት የማታደርገው ጥረት የለም።ለዚህ ተግባር  አላህ ፊት መልስ የለውም። ባልሽን መፍታት ስትፈልጊ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት የአላህ መልክተኛ አሳምረው አስተካክለውልሽ አልፈዋል።ይህን አልፈሽ በሰው ሰራሽ ህግ እዳኛለሁ ብለሽ የምትፈልጊ ከሆነ የአላህ ቅጣት ከባድ መሆኑን ማወቅ ግድ ይልሻል። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ብሏል፣👇

ۚ فَلَا تَخْشَوُا النَّاسَ وَاخْشَوْنِ وَلَا تَشْتَرُوا بِآيَاتِي ثَمَنًا قَلِيلًا ۚ وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ
ሰዎችንም አትፍሩ፡፡ ፍሩኝም፡፡ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፡፡ አላህም ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡(ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 44)

    የቁርአኑ አንቀፅ እንደሚያስረዳው የአላህ ህግጋት እያለ ወደ ሌላ ሰው ሰራሽ ህግ ለመሄድ አስገዳ ጅ ነገር ሳይኖር በሸሪዓ ከመዳኘት ሰው ሰራሽ ህግ የበለጠ ይጠቅመኛል ብሎ አስበልጦ የሄደ በአላህ የካደ ነው ሲል አስግጧል።

#እህቴ_ሆይ_ኢስላም ያስቀመጠልሽን ፍትህ ትተሽ በሰው ሰራሽ ህግ ለጊዜው የተጠቀምሽ ሊመስልሽ ይችል ይሆናል በኃላ ግን ፀፀት ውስጥ ትወድቂያለሽ ለዱኒያም ሆነ ለአኼራ ትክክለኛ ፍትህ እና ጥቅም ያለው በኢስላም ውስጥ ብቻ ነው።
    አንዳንድ እህቶች በሰላም እየኖሩ በቤተሰብ ወይም በጓደኛ ግፊት ከሜዳ ተነስተው አምባጓሮ ፈጥረው ባላቸውን ፍቺ የሚጠይቁ አሉ።በጣም ይገርማል!! መጀመሪያ እነዚህ ቤተሰቦች በቅናተወ ወይም እሷ የምታመጣውን ሀብት ለመቀራመት በመፈለግ ወይም ባሏን በመጥላት እንዲፈታት ያግባቧታል።ይቺ የዋህ ሴት በሰላም ከምትኖርበት ቤት በክብር ከያዛት ባሏ ለመፈታት ዉሳኔ ላይ ትደርሳለች።ይህን ስትፈፅም ለህይወቷ ባታስብ እንኳን የነብዩ (ሰአወን) ሀዲስ ማክበር ግዴታ ይሆንባት ነበር። ይህን የነብዩን (ሰአወ) ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በመተው የምትጓዝ ከሆነ የሚጠብቃት ቅጣት ከባድ ለመሆኑ  የሚከተለው ሀዲስ ይጠቁማል ።

  ሶውባን ከነብዩ ሰአወ ሰምተው ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ አሉ፣
#ማንኛዋም ሴት አስቸጋሪ ነገር ሳይገጥማት ባሏን ፍቺ የጠየቀች ከሆነ የጀነት ሽታ በእርሷ ላይ እርም ይሆናል። (አቡ ዳውድ፣ቲርሙዚይና ሌሎችም ዘግበውታል) #ይቀጥላል_ኢንሻአላህ_ቴሌግራማችን_ሼር_ያድርጉ👇👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
#እህቴ ሆይ!
ብዙ ጊዜ ነገሮች ሁሉ ተስተካከሉ ስትይ!
ባላሰብሽው መንገድ ሰዎች
በአንች ላይ! ክፋት አስበው ሊጎዱሽ ይነሱ ይሆናል!
#ነገርግን! አትፍሪ ሁሌም ልብሽን  ዕምነትሽን ተወኩልሽን…………በአላህ ላይ አድርጊ!
ምክንያቱም! እርሱ (አላህ) ከወሰነው ውጪ የሚሆን ነገር የለምና!!!
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam

#እስኪ #ስሚ #እህቴ......

መንገድ ከጀመረ በተውሒድ ጎዳና
በነብያት መንገድ በሩሱሉ ፋና

በሽሪአ ልጓም መኖር ከጀመረ
የተውሒድ ቀለበት አጥብቆ ካሰረ

የእለት ተግባሩ ካረገ በሱና
ለዲኑ ታታሪ ማይበገር ጀግና

አኽላቁ ካማረሽ እንዲሁም ምግባሩ
ምርጫሽ ይሁን እሱ።
ምን አለሽ ከዘሩ!!❗️

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☀️ነገሮችን ባላየ ማለፍን ልመጂ...... የማይጠቅሙሽን ነገሮች!
ህይወትሽ ላይ ምንም የማይጨምርና ...የማይቀንሱን ነገሮች በመዝለል ላይ በርቺ .....ትተሽ ያለፍሻቸውን ነገሮች ዞረሽ ባለማየት ላይ ጀግኚ ......ላልሆንሻቸው ስያሜዎችሽ መልስ በመስጠት ላይ አትገኚ .......በቀኖችሽ ውስጥ የሚጠቅምሽን ብቻ ዝገኚ!!!!!

#እህቴ ትኩረት አልባ ሁኚ ማለቴ አይደለም ነገር ግን መርጠሽ ትኩረት ስጪ የማይጠቅምሽን እያሰብሽ እንቅልፍ አጥተሽ አትደሪ ነቃ በይ። 
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam