الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
23.1K subscribers
351 photos
14 videos
7 files
905 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
#አደራ_አደራ_የምለው_ነገር_ቢኖር _በፅናት_ጉዳይ_ነው። ❗️

በተለይ በዚህ የሚገለባበጥ በበዛበት ወቅት የፅናት ጉዳይ እጅግ አንገብጋቢ ነው❗️!! በዚህን ጊዜ
#በሐቅ ላይ #በኢኽላስ መፅናት የተሰጠው ሰው አላህ ከሚሰጡ ነገሮች ትልቁን ስጦታ ሰጥቶታልና አላህን ሊያመሰግንና ፅናቱን አላህ እንዲያዞትርለት አላህን ሊለምን ይገበዋል!!።

ታላቁ ዓሊም ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“የሰው ልጅ ነፍሱ ከሰውነቱ እስከቆየች ድረስ ለፊትና የተጋለጠች ናት። በመሆኑም እራሴንም እናንተንም የምመክረው ዘውትር አላህን ፅናት እንዲሰጠን በመለመን ላይ ነው። ልትፈሩ ይገባል!፣ ምክንያቱም ከእግራቹ ስር የሚያዳልጡ ነገሮች አሉ። የላቀው አላህ ፅናቱን ካልሰጣችሁ ጥፋት ላይ ልትወድቁ ትችላላቹ።
አላህ ለመልክተኛው ﷺ የተናገረውን ስሙ:-

وَلَوْلَا أَن ثَبَّتْنَاكَ لَقَدْ كِدتَّ تَرْكَنُ إِلَيْهِمْ شَيْئًا قَلِيلًا

«ባላረጋንህም ኖሮ ወደነሱ ጥቂትን (ዝንባሌ) ልትዘነበል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር፡፡» አል-ኢስራእ 74

ይህ የተባለው ለመልእክተኛው ﷺ ከሆነ የኛ ጉዳይስ እንዴት ይሆን?፣ እኛ በኢማናችንም በየቂናችንም ደካሞች ነን፣ ብዥታዎችና ስሜቶች ይቀጣጩናል። እኛ ከባድ የሆነ አደጋ ላይ ነን፣ የላቀውን አላህን ልባችንን ከቅኑ እንዳያዘነብልብን፣ በሐቅ ላይ ፅናት እንዲሰጠን ልንጠይቀው ይገባል፣ ይህ ነው የማስተዋል (የአዕምሮ) ባለ ቤቶች ዱዓ ማለት።

رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْوَهَّابُ

«እነሱም ይላሉ፡- "ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራሀን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፡፡ ከአንተ ዘንድ የሆነን ችሮታም ለኛ ስጠን፡፡ አንተ በጣም ለጋስ ነህና፡፡» ኣል-ዒምራን 8
[ሸርህ አልሙምቲዕ 5/388]

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam