الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.5K subscribers
359 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::እህቴ::::::☜ ክፍል ሶስት/ ③ ..ከዕለታት በአንዱ ቀን አንዲት እህትሽ ወደ ተወዳጁ ነብይ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመምጣት.. «አዉድቅ አለብኝ፣ (አዉድቁ በሚጥለኝ ወቅት ደግሞ) ሰዉነቴ ይገለጣል። ዱዓ አድርጉልኝ!» አለች። ያ የነፍስና የልብ ሀኪም የሆኑት ተወዳጁ ነብይም ሁለት ምርጫ ሰጧት፣ አንድም ዱዓ አድርገዉላት መዳን፣ አልያም ታግሳ ጀነትን ማግኘት። አማኞች ዘንድ ከጀነት በላይ…
☞::::::እህቴ!::::::::☜

ክፍል አራት/④

ይህ ታሪክ ትዝ ባለኝ ቁጥር ሰዉነቴን ከእግሬ እስከ ፀጉሬ ይነዝረኛል። ገና ሳልፅፈዉ ዐይኔን በእንባ ይሞላዋል። ወላሂ ደስታ ይሁን ሀዘን እንጃ አላዉቀዉም.. ግን ልቤን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይወርሰዋል።

ዛሬ የማወራዉ ስለዚያች.. በረሱል ምስክርነት የሷ ተዉባ ለሰባ ሰዎች ቢከፋፈል ይበቃ ነበር ስለተባለላት ሴት ነዉ።

ያ አላህ!! ያ ረሱላችን ምስክር በሰጡት በኢማኗ ታላቅነት ልገረም?! ወይስ ያለ አንዳች ግፊት የሰራችዉን በግልፅ ተናግራ ሀድ እንዲቆምባት ረሱሉን በጠየቀቺዉ እዉነተኝነቷ ልገረም?!

ይህ ወሬ በማሰማመር ምናልፈዉና ዝምብለን እንባ ተራጭተን ምናወራዉ ተራ ወሬ አይደለም። ይህ የአላህን ዒቃብ ለሚፈሩት ይገሰፁ ዘንድ የተፃፈ ታሪክ ነዉና ጥሞና ይፈልጋል። እዚች ሴት ላይ ከየትኛዉ ጊዜ በላይ ሙሉ የሆነን ትኩረትን እፈልጋለሁ።

እቺ ታላቅ ሴት አንድ ቀን ወደ ረሱሉ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመምጣት.. «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! ዝሙት ሰርቻለሁ አጥሩኝ!» አለች። ረሱሉም መለሷት። በነገታዉም መጣችና «ለምንድን ነዉ ምትመልሱኝ?! ምናልባትም ማዒዝን እንደመለሳችሁት ልትመልሱኝ ፈልጋችሁ ይሆናል። ወላሂ እኔ እርጉዝ ነኝ!» አለች። «(እንደዚያ ከሆነ) ስትወልጂ ተመልሰሽ ነይ!» አሏት። በወለደችም ጊዜ ልጁን ይዛዉ መጣችና «ይሄ እሱ ነዉ! ወልጃለሁ!» አለቻቸዉ። ረሱሉም «ይዘሺዉ ሂጂና (ጡት እስኪጥል) አጥቢዉ!» አሏት። አጥባታዉ በጨረሰች ጊዜ በእጁ ዳቦ አስይዛዉ መጣችና «ይሀዉ የአላህ ነብይ! (ጡት ጥሏል!) እንደምታዩትም ምግብ ጀምሯል።» አለቻቸዉ።

ረሱሉም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለአንዱ ሰሀባ ልጁን ሰጡና ጉድጓድ ቆፍረዉ አዘጋጇት። ‛ረጅም’ እንድትደረግ አዘዙ። ኻሊድም መጣና (በትልቅ) ድንጋይ ራሷን ፈነከታት። ደም በደም አደረጋት። ደሟ ኻሊድን ሳይቀር አለበሰዉ። ኻሊድ ሰደባት። ረሱላችንም ኻሊድ መሳደቡን በሰሙ ጊዜ እንዲህ አሉት.. «ኻሊድ ሆይ ተረጋጋ! ያ ነፍሴ በእጁ ባለችዉ ጌታ ይሁንብኝ! እሷ ኮ (ያ ቀረጥ ሚቀበለዉ) ሰዉ ቢቶብት እንኳን አላህ ይቅር የሚለዉን ተዉባ ነዉ የቶበተችዉ።»

በሌላ ዘገባ ሊሰግዱባት ሲዘጋጁ ዑመር ዝሙት ሰርታ ሳለ እንዴት ትሰግድባታለህ?! ሲሏቸዉ እንዲህ አሉት.. «በእርግጥም እቺ ሴት ለ70 የመዲና ሰዎች ተዉባዋ ቢከፋፈል የሚበቃን ተዉባ ነዉ የቶበተችዉ። አንዲትን ነፍሷን ለአላህ ከሰጠች ሴት በላይ ትልቅ ደረጃ ያለዉን ሰዉ አግኝተሃልን?!»

ሱብሀነላህ!
እቺ ሴት ኮ ከአላህ ዉጪ ማንም ባላያት ሁኔታ ላይ ሁና ነዉ ሸይጣን ወስዉሷት ለዝሙት የተዳረገችዉ። ወደ አላህ አልቅሳ፣ ተመልሳ ብትለምነዉና ትክክለኛ ተዉባን ወደሱ ብትመለስ ይበቃት ነበር። ግን የኢማን ለዛ ልብን ሲቆጣጠር እንዲህ ነዉ። በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተራ ሚመስለዉ ወንጀል ኢማን ልባቸዉን ለተቆጣጠረ ሰዎች ቀንና ማታ ሀዘንና ቁጭትን ሚያወርስ ነዉ።

አይገርምም! ሲመልሷት እንኳን ተመልሳ ትመጣለች ኮ! እስክትወልድ ብዙ ወራት ነበራት። ከወለደች ብኃላ ጡት እስኪጥል ሁለት አመት ገደማ ያቆያል። ግን በዚህ ሁላ መሃል አንድም ቀን የአላህ ሀድ እንዳይቆምባት ወደኃላ ማለትን አልመረጠችም። በወደቀ ማንነት ጌታዋን መገናኘትን አልፈለገችም።

እቺ ሴት ወደ አላህ ቁርጥን የሆነን መመለስን ለሚሹት ምርጥ ምሳሌ ናት። እርግዝናዋ፣ ዉልደቷ፣ ማጥባቷ አንድኛቸዉም ከተዉባ አላገዷትም። የልጇ ዉብ ዐይኖች እሷ እንደዚያ ስትቀጠቀጥ በእንባ መሞላቱ ከተዉባ አላገዳትም። ልጇን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታ በጠራ ልብ አምላኳን ተገናኘች።

በአላህ ዉዴታ ተፅናንታ የዚያን የድንጋዩን ህመም ተቋቋመች። ወንጀሏን እንዲያፀዳላት በመሻት ልብሷኗ መላዉ ሰዉነቷ ደም እስኪለብስ ፀናች።

ይህ ሁላ ለአላህ ዉዴታ የተከፈለ ዋጋ ነዉ።
:
ይህ ሁላ
#ለጀነት የተከፈለ ዋጋ ነዉ።

እህቴ! ልክ እንደዚች እህትሽ ቁርጠኛ ሁኚ! በተራ ነፍስ አላህን መገናኘትን አትሺ! ከሱ ብኋላ መንሸራተት የሌለዉን ትክክለኛ መመለስን መደ አላህ ተመለሺ!!

[[አንዲት ነፍሷን ለጌታዋ ከሰጠች (ነፍስ) በላይ አላህ ዝንድ ትልቅ ደረጃ ያለዉን ሰዉ ታገኛላችሁ?!]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

     ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam