الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
924 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
☞ትዳር_በኢስላም☜

 
#ክፍል_አንድ/①

  
#ኹልዕን_በተመለከተ_በባል_እና_ሚስትመካከል_የሚፈፀሙ_ስህተቶች!!!!!

❗️
#በወንዶች_ላይ_የሚስተዋሉ_ጥፋቶች

    ኹልዕ በሸሪዓችን የተፈቀደ እና ሁሉም ሰው ያለጥላቻና ያለማመንታት ሊቀበለው ግድ ይለዋል።አንዳንድ ወንዶች በዚህ ላይ የተለያዩ ስህተቶችን ሲፈፅሙ ይስተዋላሉ።ከፊሉ ስለዚህ ነገር ምንም እውቀቱ እና ግንዛቤው ስለሌለው ለሚስቱ ሳይመቻት ቀርቶ ሸሪዓው በሚፈቅደው መሰረት ማስለቀቂያ ከፍላ ኹልዕ ስትጠይቅ የታባሽ ብሎ ጨቁኖ ለማኖር የሚፈልግ አለ። ይቺ ሴት ችግር ኑሮባት ፍታኝ ብላ ብትጠይቀው ሸሪዓ እንደሚደግፋት ማወቅ ግድ ይለው ነበር። እያስፈራራ ሳትፈልግ በግዴታ ከኔ ጋር ኑሪ ማለት ከየት የተገኘ ሸሪዓ ነው? ይህን ቢያደርግ አላህ ፊት ተጠያቂ ነው።

     ☞ ሴቷ ወዳው እና አፍቅራው እንጂ ተገዳ እንድትኖር ኢስላም አያዝም።የሚሰራ ጉልበት አለኝ የሚናገር አንደበት አለኝ ብሎ ይቺን የአላህን ሴት ባሪያ ቢበድላት ነገ ሃያሉ ጌታችን ዚህ ትፋረደዋለች። ዛሬ ሰሚ አጥታ ብትጨቆን ነገ የፍትህ ባለቤት ናት።

    ከነብዩ( صلى الله عليه وسلم) ዘመን ጀምሮ ኢስላም ለሴቶች የሰጠው ክብር እና ዋስትና ከዚህ በፊት በነበሩት ሀይማኖቶች ያልተጠቀሰ ሆኖ እናገኘዋለን። ከነዚህ አንዱ ሴት ልጅ የማይመቻትን እና የማትወደውን ባል እርሷ  ከፈለገች ሸሪዓውን ሳትፃረር መፍታት መቻሏ ነው። ለዚህም ማስረጃው የሚከተለው አንቀፅ ነው፣

فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ اللَّهِ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا فِيمَا افْتَدَتْ بِهِ ۗ

የአላህንም ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብታውቁ በእርሱ (ነፍሷን) በተበዠችበት ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለም፡፡ (አል በቀራህ 229)

    ቡኻሪ ላይ በተዘገበው ሀዲስ የሳቢት ኢብኑ ቀይም ሚስት በማለዳ ወደ ነብዩ ሰአወ ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች፣ "የአላህ መልክተኛ ሆይ ሳቢት በዲንም ሆነ ፀባዩ ሳካ አላወጣለትም ነገር ግን በራሴ ላይ ክህደትን እፈራለሁ(ስለምጠላው ሀቁን ባለመጠበቄ ዝቅተኛው ኩፍር ላይ ልወድቅ ስለምችል ይፍታኝ) አለች፣ የአላህ መልእክተኛ( صلى الله عليه وسلم)"
የአትክልት ቦታውን ተመልሽለታለች?" አሏት እሷም "አዎ" አለች ፣የአትክልቱንም ቦታ መለሰች።እንዲፈታትም አዘዙት።

     የቁርአን አንቀፁ እና ሀዲሱ እንደሚያስረዳው አንዲት ሴት ከባሏ ጋር እንዳትኖር የሚያግዳት በቂ ምክንያት ካላት በጉልበት አፍኖና ጨቁኖ ማኖር እንደማይቻል አበክሮ ያስተምራል።

    ☞ ❗️
#ወንዶች_አላህንፍሩ!! ኢስላም ለሰው ልጆች ሁሉ በቂ መፍትሄ የሚሰጠውን በእናንተ የግንዛቤ ችግር ሴት ልጅን የበታች አድርጎ እንደሚጨቁን አታስመስሉት።ከኢስላም ውጭ ያለው አካል ኢስላምን አያውቅም ኢስላምን የሚመዝነው በተከታዮቹ ነው። ወንዶች ሆይ፣ ዱኒያም አኼራም የተስተካከለ ይሆን ዘንድ #የነብዩ_(ሰለላሁ_ዓሌይሂ_ወሰለም) ፈለግ እግር በእግር በመከታተል ጥሩ ሞዴል ለመሆን ሞክሩ ።

ለ/
#በሴቶች_ላይ_የሚስተዋሉ ጥፋቶች❗️
   ❗️
#የሴት_ልጅ_ፍቺ_መጠየቅ የተፈቀደ ነው ሲባል ገደብ የሌለው አስመስለው እንደፈለጉ እየተነሱ #ፍታኝ_እሄደዳብላ እያሉ ባሎቻቸውን እና ቤታቸውን የሚያምሱ ሴት እህቶቻችን ቁጥራቸው እየተበራከተ መጥቷል።ከዚህም በባሰ ሁኔታ ኢስላም መፍትሄን አስቀምጦ እያለ በቁርአን መዳኘት ሲገባት አሻፈረኝ ብላ ባሏን በሌላ ህግ ለመዳኘት የማታደርገው ጥረት የለም።ለዚህ ተግባር  አላህ ፊት መልስ የለውም። ባልሽን መፍታት ስትፈልጊ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት የአላህ መልክተኛ አሳምረው አስተካክለውልሽ አልፈዋል።ይህን አልፈሽ በሰው ሰራሽ ህግ እዳኛለሁ ብለሽ የምትፈልጊ ከሆነ የአላህ ቅጣት ከባድ መሆኑን ማወቅ ግድ ይልሻል። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ብሏል፣👇

ۚ فَلَا تَخْشَوُا النَّاسَ وَاخْشَوْنِ وَلَا تَشْتَرُوا بِآيَاتِي ثَمَنًا قَلِيلًا ۚ وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ
ሰዎችንም አትፍሩ፡፡ ፍሩኝም፡፡ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፡፡ አላህም ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡(ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 44)

    የቁርአኑ አንቀፅ እንደሚያስረዳው የአላህ ህግጋት እያለ ወደ ሌላ ሰው ሰራሽ ህግ ለመሄድ አስገዳ ጅ ነገር ሳይኖር በሸሪዓ ከመዳኘት ሰው ሰራሽ ህግ የበለጠ ይጠቅመኛል ብሎ አስበልጦ የሄደ በአላህ የካደ ነው ሲል አስግጧል።

#እህቴ_ሆይ_ኢስላም ያስቀመጠልሽን ፍትህ ትተሽ በሰው ሰራሽ ህግ ለጊዜው የተጠቀምሽ ሊመስልሽ ይችል ይሆናል በኃላ ግን ፀፀት ውስጥ ትወድቂያለሽ ለዱኒያም ሆነ ለአኼራ ትክክለኛ ፍትህ እና ጥቅም ያለው በኢስላም ውስጥ ብቻ ነው።
    አንዳንድ እህቶች በሰላም እየኖሩ በቤተሰብ ወይም በጓደኛ ግፊት ከሜዳ ተነስተው አምባጓሮ ፈጥረው ባላቸውን ፍቺ የሚጠይቁ አሉ።በጣም ይገርማል!! መጀመሪያ እነዚህ ቤተሰቦች በቅናተወ ወይም እሷ የምታመጣውን ሀብት ለመቀራመት በመፈለግ ወይም ባሏን በመጥላት እንዲፈታት ያግባቧታል።ይቺ የዋህ ሴት በሰላም ከምትኖርበት ቤት በክብር ከያዛት ባሏ ለመፈታት ዉሳኔ ላይ ትደርሳለች።ይህን ስትፈፅም ለህይወቷ ባታስብ እንኳን
የነብዩ (ሰአወን) ሀዲስ ማክበር ግዴታ ይሆንባት ነበር። ይህን የነብዩን (ሰአወ) ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በመተው የምትጓዝ ከሆነ የሚጠብቃት ቅጣት ከባድ ለመሆኑ  የሚከተለው ሀዲስ ይጠቁማል ።

  ሶውባን ከነብዩ ሰአወ ሰምተው ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ አሉ፣
#ማንኛዋም ሴት አስቸጋሪ ነገር ሳይገጥማት ባሏን ፍቺ የጠየቀች ከሆነ የጀነት ሽታ በእርሷ ላይ እርም ይሆናል። (አቡ ዳውድ፣ቲርሙዚይና ሌሎችም ዘግበውታል) #ይቀጥላል_ኢንሻአላህ_ቴሌግራማችን_ሼር_ያድርጉ👇👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞ትዳር በኢስላም☜ ክፍል ሶስት/ ③ =>ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ነብያት..      ....በዚህም ምክንያት ሳራም ነብዩላህ ኢብራሂም አሰ ልጅ ይወልዱ ዘንድ #ሀጀርን ዳረቻቸው።ሀጀርን አግብተው ነብዩላህ ኢስማኢልን አሰ ከወለዱ በኃላ #ሳራ የቅናት_መንፈስ አደረባት። ኢብራሂም አሰ ሚስታቸውን ሀጀርን እና ልጃቸውን ኢስማኢልን ከአጠገቧ እንዲያርቁላት ሳራ ጠየቀች። ይግን ጉዳይ ኢብራሂም አሰ ወደ #አላህ…
☞ትዳር_በኢስላም.☜

  ክፍል~አራት /④ት

=>ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ነብያት..

 
#ነብዩላህ_ያዕቁብ_እና_ሌሎችም

   ነብዩ ያዕቁብ አሰ በአንድ ጊዜ 4 ሚስቶች ያገቡ ሲሆን እንደመፅሀፍ ቅዱስ ገለፃ ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፣

1/
#ሊያ
2/
#ራሄል
3/
#ባላ
4/
#ዘለፋ ናቸው።

  ☞ ከእነዚህ አራት ሴቶች 12 ልጆችን ያገኙ ሲሆን ከሚስቶቻቸው በጣም ተወዳጅ የነበረችው
#የነብዩ_ዩሱፍ_እናት_ራሄል ነበረች።
እሷም ነብዩ ዩሱፍን እና ታላቅ ወንድማቸውን ቢኒያሚኒን ወልዳላቸዋለች ይላል መፅሀፍ ቅዱስ

     
#ነብዩ ሙሳ..

    ሙሳ 4 ሚስቶች እንደነበሯቸው የቀደምት መፅሀፍት ያረጋግጣሉ።ስማቸውም እንደሚከተለው ተጠቅሷል..
1/
#ሰፉራህ ይቺ ሚስታቸው ከእሳቸው 2 ልጆች ያላት ሲሆን ስማቸውም #ጀሱንና_አዚር ናቸው።

2/
#ጀብሻህ
3/
#የቀይኑይ_ልጅ
4/
#የሃባብ_ልጅ ናቸው።
     ይህ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረ ነው።

        /ነብዩ.ዳውድ

     እንደቀደምት መፅሀፍት(መፅሀፍ ቅዱስ እና ሌሎችም)
የነብዩ ዳውድ ሚስቶች በርካታ ከመሆናቸው አንፃር ቁጥራቸው በትክክል ለማወቅ ያዳግታል።በአንዳንድ ዘገባዎች #29 ሚስቶች እና #40 ሴት ባሮች እንደነበራቸው ይነገራል። ቁጥራቸው  ብዙ ስለሆነ ስማቸው በውል አይታወቅም ይላል።በሌሎች ዘገባዎች ደግሞ የዳውድ ሚስቶች ዘጠኝ ብቻ ናቸው የሚልም አለ..

☞ነብዩ ሱለይማን..

   በመፅሀፍ ቅዱስ እንደተጠቀሰው ከሆነ ነብዩ ሱለይማን
#ከ1000 በላይ ሴቶች እንዳላቸው እና ከእነዚህ ውስጥ 700 ጨዋ ሚስቶቻቸው ሲሆኑ 300 ደግሞ ሴት ባሮቻቸው እንደነበሩ ተነግሯል።ከብዛታቸው የተነሳ ስማቸውን በውል ለማወቅ አልተቻለም ይላሉ የመፅሀፉ ባለቤቶች።ነገር ግን እኛ ሙስሊሞች የምናምነው በቁርአን እና በሀዲስ የተረጋገጠውን ብቻ ነው። በኢስላም የሚታወቀው የነብዩላህ ሱለይማን  ሚስቶች #100 ብቻ ናቸው የሚለው ነው። መቀበልም ያለብን ይህን ብቻ ነው። ምክንያቱም ይህ እውነታ በነብዩ ሰአወ የተነገረ ነው..
   
#ያላገቡ.ነብያት
☞ መልእክተኛ ሆነው ከተላኩ ነብያቶች ውስጥ ያገቡ  ነብያቶች እንዳሉ ከላይ አሳልፈና። 1 ሚስት ብቻ ያገቡም ነበሩ ለምሳሌ
#ዩሱፍ ያገቡት አንድ ብቻ ነበር፣በአንፃሩ ምንም ያላገቡ የአላህ መልእክተኞች የነበሩ ሲሆን በውል የሚታወቁት ሁለት ብቻ ነበሩ፣ እነሱም #ነብዩላህ የህያ እና ነብዩላህ ኢሳ ናቸው..

   ☞እዚህ ጋር ማስታወስ የምፈልገው ነገር አለማግባት የታላቅነት መገለጫ እንዳልሆነ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነው። አንዳንድ የሌላ እምነት ተከታይዎች ነብዩላህ ኢሳ ባለማግባታቸው አንዱ የታላቅነት መገለጫ አድርገው ሲቆጥሩት ይስተዋላሉ።ጉዳዩ ሴት አለማግባት ከሆነ ታዲያ ነብዩላህ የህያ የንግስናው እና የገድሉ ባለቤት ለምን አላደረጓቸውም..
   ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በነብዩ ሰአወ ጊዜ የተደነገገ አስመስለው እሱንም እንደታላቅ ነውር በመቁጠር ሲያራግቡት እና ጥላሸት ሲቀቡ እስልምና ሃቅ ፈላጊ በሆኑ ሰዎች ተቀባይነት እንዳያገኝ በር ላይ ቁመው ሰዎችን ሲያስበረግጉ ይስተዋላሉ። ከዚህም በከፋ ሁኔታ መፅሀፍ ቁዱስ ከአንድ በላይ አግብተዋል ያላቸውን ነብያቶች በተመለከተ የተፃፈውን ነገር መሰረዝ ስለማይችሉ በምትኩ እንደእነሱ አባባል የኦሪት እና የመዝሙር ባለቤት የሆኑትን ነብዩ ሱለይማንን እና ነብዩ ዳውድን መናፍቃን ሆነው ነው ብዙ ሚስት ያገቡት እያሉ ሲጠሯቸው የያዙትን እምነት እየተቹ  መሆናቸው ያልገባቸው ሊሆኑ ይችላሉ ብለን ድምዳሜ ለመስጠት ተገደናል። እነዚህ ነብያቶች ከአንድ በላይ ያገቡት መናፍቅ ሆነው ፣ተሳስተው ወይም ተገደው ነው ብለው ያስባሉ።
#እውነታው ግን ነብይ መናፍቅ ፈፅሞ ሊሆን አይችልም.

     ☞ እውነታው ኢስላም ከአንድ በላይ ሚስት እንደ አዲስ የደነገገ ሳይሆን ገደብ ያጣውን የሴቶችን ያለገደብ በአንድ ወንድ ቁጥጥር ስር የመሆንን ጭቆና ከላያቸው ላይ ገፎ በፍትህ ማኖር የሚችል ሰው ከአራት በላይ እንደማይፈቀድለት አጥብቆ እርምት የሰጠ ሀይማኖት ነው.።

      ከአንድ በላይ ሚስት በገደብ መሆን እንዳለበት ከሰማይ ወርዶ የተደነገገበት ብቸኛው ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነው..
        የአይሁዳውያን ሀይማኖት ከአንድ በላይ ሚስት የሚፈቀድበት ሆነ ነገር ግን የቁጥር ገደብ ያልተቀመጠለትና ስለፍትህ ያልተወራበት ሆኖ እናገኘዋለን።የኃላ ኃላ የአይሁድ እምነት አዋቂነን ባይዎች በራሳቸው ስልጣን የሚስትን ቁጥር #4 እንዲሆን ተስማሙ።ይህ ስምምነት ሰው ሰራሽ እንጂ በተውራት ያልወረደ እና ያላስተማሩት ስለሴቶች መብትና ፍትህ ያልተወራበት ጎደሎ ድንጋጌ ነው።

#ከአንድ_በላይ_ሚስት_በቀደምት_ሀይማኖቶች

⇡ይቀጥላል ..

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳር በኢስላም::::👈 ክፍል ሀያ/⑳ #የኢስላም_ጠላቶች_ከአንድ_በላይ_ሚስትን_አስመልክተው_የሚያነሱት_ትችቶችና_መልሶቻቸው    ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ ድንጋጌ ሲሆን ከፊቱም ሆነ ከኃላው መጥፎ ነገር  የማይመጣበት ነው። በቁርአን እና በሀዲስ  ተደግፎ የሚመጣ ማንኛውም ድንጋጌ ለሰው ልጆች በአጠቃላይ በሁሉም ዘመን ትልቅ ጥቅም ያዘለ እንጅ የሚጎዳ ነገር ፈፅሞ አይቀላቀለውም።…
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜

#ክፍል_ሀያ_አንድ/②①

2#አንድ_ወንድ_ከአንድ_በላይ_የሚያገባ_ከሆነ_በእያንዳንዱ_ቤት_ያለው_ቤተሰብ_አንዱ_ለሌላው_የጠላትነት_ስሜት_እንድኖር_ያደርጋል_ይላሉ

#መልስ፣ በመሰረቱ ይህን ሙስሊም የሚባሉትም ሰዎች እንደሚያነሱ አሳልፈናል። ይህ ሁሉ ፈር የለቀቀ አስተሳሰብ ኢስላምን በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው።በመካከላቸው አንድ የሚያደርጋቸው አባት መኖሩ በሁሉም ቤተሰብ ውስጥ የስጋ ዝምድና ተቀላቅሎ እያለ እንዴት ስለጠላትነት ሊነሳ ይችላል??ነገሩማ ሰው የሚገምተው ካለበት ነባራዊ ሁኔታ ተነስቶ ስለሆነ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የለመዱት መጠጥ ቤት ገብተው አንድ ሴት ለአራት ወይም ለአምስት ይዘው በዝሙት ሲጨማለቁ አድረው ጠዋት ላይ ተፈነካክተው ይለታያሉ ፣የለመዱት ይህን ስለሆነ ይህ ቆሻሻ ተግባራቸው ኢስላም ውስጥ የሚከሰት ይመስላቸዋል።ሲቀጥል እኛ ሙስሊሞች ለሁሉም የማያዳላ በፍትህ የሚፈርድ ኢስላም አለን።ሁሉም የራሱን ሀቅ ጠብቆ ሌላ ሰው ሳይጎዳና ሳይጨቁን እንዲኖር ያስገድደናል።ይህን ሁሉ አልፎ እንዴት ስለመጨቃጨቅ ይወራል??? ቅሬታ እንኳ የሚኖር ከሆነ ሊከሰት የሚችለው በባላቸው ስር ባሉ ሚስቶች ወይም እናቶችቻቸው በአባቶቻቸው ስር ባሉ ልጆች ሳይሆን ሁለተኛ ሚስት ባለመቀበል ምክንያት በተፈታችው ሴት ወይም ልጆችና እናታቸወ ቤት ባሉ ልጆች መካከል ነው። #የእኛን_እናት_ፈቶ_የናንተን_እናት_ይዟል፣ የእኛ እናት ተቸግራ የእናንተ እናት ከባሏ ጋር ትኖራለች በማለት በተፈታችውና አዲስ በተገባችው ሚስት ቤተሰብ መካከል መጨቃጨቅ ሊኖር ይችላል። ይህ መጨቃጨቅ ራስን በኢስላም ካለማስገዛት የመነጨ ነው።ምክንያቱም #ሁለተኛ_ሆኖ_መኖርን_ብትቀበል ይህ ሁሉ ንትርክ ከየት ይመጣል።

3/
#ከአንድ_በላይ_ሴቶችን_ማግባት_ክብራቸውን_የሚነካና_የመበደል_ተግባር_ነው_ይላሉ

#መልስ፣ ሴቶችን ክብር አልባ የሚያደርገው በተለያየ ምክንያት ባል ሳታገባ ቀርታ ወይም ለመጀመሪያ ሚስትነት ለመመረጥ ያልታደለች ሆና የሚንከባከባትና ቁጥብነቷን የሚያረጋግጥላት ሀላፊነቱን የሚወስድ ባል ባለማግኘቷ ክብሯ ተነክቶ የወንድም የሴቱን ስራ ራሷ ተሸክማ ኑሮን መግፋት ለክብሯ የማይበጀውና ፍትሀዊያልሆነው ስርአት ይህ ነው።
።ሴት ልጅ ለመጀመሪያ ሚስትነት መስፈርት ሳታሟላ ቅ ታ የሚፈልጓት ወንዶች ባየወገኙ ያገኘ ባለጌ ከሚደፍራት ሁለተኛ ሆና በማግባት ክብሯን ማስጠበቅ የተከበረች የሙስሊም ሴት መገለጫ እንጂ የአላህ እርግማን የወረደባቸው ጋጠወጥ ሴቶች  መገለጫ አይደለም።

4
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_ማግባት_ለህዝብ_ብዛት_ዋና_መንስኤው_ሲሆን_ለአንድ_ሀገር_ደሀ_ የመሆን_ዋና_ምክንያት_ነው_ይላሉ፣

#መልስ፣ ይህ አባባል መመዘኛው የተንጋደደ ሰው አስተሳሰብ እንጂ የሌላ አይደለም።የህዝብ ብዛት ለድህነት መንስኤ ቢሆን #ቻይና የመጨረሻዋ ደሀ አገር ትሆን ነበር።ነገር ግን ያለው ነባራዊ ሁኔታ በተቃራኒው ነው።በርካተሰ መውለድ በኢስላም የሚበረታታ የሚደገፍ ከመሆኑም ባሻጋር የሁሉም ሰው የሲሳይ አዳይ አላህ ብቻ ነው።ሲሳይ በሰው እጅ ቢሆን እማ ስንት ብልጥ ድሆች ነበሩ ሁለየንም ቀድመው ትልቅ ሀብት በያዙ ነበር።

   ☞ እነዚህ የኢስላም ጠላቶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ለመቃወም የሚያመጧቸው በርካታ ተልካሻ ምክንያቶች አሉ።ሁሉንም እያነሱ መልስ መስጠት ጊዜው አይበቃም።በጥቅሉ ሁሉም መቃወሚያዎቻቸው እዚህ ግባ የማይባሉ ተልካሻ ሀሳቦች ናቸው።ሙስሊም ላደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው።

5/
#የኢስላም_ጠላቶች_ድብቅ_አላማቸውን_ለማስፈፀም

   ሙስሊም ሴቶች አላህ የዋለላቸው ታላቅ ኒእማ(ፀጋ) ማስተዋል አቅቷቸው ለምእራባዊያን እጅ ሲሰጡ ይስተዋላሉ።ምእራባዊያን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ሲቃወሙ ከበስተጀርባው የሚፈልጉት አላማ ለሙስሊም ሴቶች ብቻ ተደብቆባቸዋል።የሙስሊም ሴቶች ቁጥብነት ያስቆጫቸው ምእራባዊያን የእነሱ የእርቃን እና የአደባባይ የዝሙት አባል ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድናጋይ የለም።አንዳንድ የዋህ የሙስሊም ሴቶች ለጥሪያቸው አቤት ብለው እጅ ሰጥተው ኢስላም የሰጣቸውን ክብር ጥለው እንደ እነርሱ የውርደትን ህይወት ተቀላቅለዋል።በኢስላም ጥላ ስር ስትኖር እንዴት ሁለተኛ የክብር ሚስት ትሆኛለሽ ሲሏት የነበሩት እነሱን ስትቀላቀል እንደ ረከሰ ሸቀጥ በጅምላ አንድ ለአስር ወይም አንድ ለአምስት ካልሆነ አንድ ለመቶ የረከሰ የዝሙት ወንድ ተጋሪ ትሆናለች።የሚያሳዝነው ሰላሳ አርባ ሴት በዝሙት የሚያንጋጋ ወንድ ጋር ስትማግጥ (ሙስሊም ሴቶችን አላህ ይጠብቅልን) የማይሰማት ሴት ወደ ኢስላም ተመለሽ ባል ከጠፋ በክብር ሁለተኛ ሚስት ሁኚ ስትባል እምቧ ከረዩ ስትል ትስተዋላለች።ይህ የጤነኝነት አይመስለኝም። "አላሁል ሙስተአን ወኢላሂቱክላን" ትርጉሙን ፀሀፊውን ጠትቁልኝ!!!!!

#የነብዩ_(صلى الله عليه وسلم)_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ..
#ኢንሻአላህ_ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜ #ክፍል_ሀያ_አንድ/②① 2#አንድ_ወንድ_ከአንድ_በላይ_የሚያገባ_ከሆነ_በእያንዳንዱ_ቤት_ያለው_ቤተሰብ_አንዱ_ለሌላው_የጠላትነት_ስሜት_እንድኖር_ያደርጋል_ይላሉ #መልስ፣ በመሰረቱ ይህን ሙስሊም የሚባሉትም ሰዎች እንደሚያነሱ አሳልፈናል። ይህ ሁሉ ፈር የለቀቀ አስተሳሰብ ኢስላምን በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው።በመካከላቸው አንድ የሚያደርጋቸው አባት መኖሩ በሁሉም ቤተሰብ ውስጥ…
=>ትዳር~በኢስላም

    
#ክፍል_ሀያ_ሁለት/②②ት

#የነብዩ_ሰአወ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ

    ነብዩ ﷺ ቁጥብ እና ንፁህ ሆነው ለሀያ አምስት አመታት ከቆዩ በኃላ በ15 አመት የምትበልጣቸውን እናታችን ኸዲጃን አግብተው በርካታ ልጆችን ከእናታችን ለመውለድ የቻሉ ሲሆን ሌላ ተጨማሪ ሚስት ሳያገቡ ከኸዲጃ ጋር የወጣትነት ጊዜያቸውን በማሳለፍ ለ23 አመት በፍቅር እና በሰመረ ህይወት አብረው ቆይተዋል።ማለትም እድሜያቸው 48 አመት እስኪሆን ድረስ ሌላ ባል ፈታ ከአገቧት እናታችን ኸዲጃ ጋር ታላቅ የሆነ የትዳር ህይወትን ኑረዋል። የአላህ ውሳኔ ደረሰና ከተጋቡ ከ23 አመት በኃላ ያቺ የኢስላም ታላቅ ባለውለታ የነብዩﷺየጭንቅ ቀን ጓደኛ የሆኑት እናታችን ኸዲጃ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ! ኸዲጃ በመሞታቸው ነብዩ ሰአወ በጣም አዘኑ።

   እናታችን ኸዲጃ  ከሞቱ በኃላ ነብዩ ﷺ ልጆቻቸውን እንደልጅ አድርጋ የምትይዝ በእድሜያቸው የገፉትን እና ባላቸውን በሁለተኛው የሀበሻ ስደት በሞት ያጡ እና ያለታዛቢ የቀሩትን የ55 አመት አዛውንት እናታችን ሰውዳን  አገቡ።አንድ መረሳት የሌለበት መሰረታዊ ነጥብ
የነብዩ ﷺእድሜ 53 በሆነበት ጊዜ ታላላቅ የኢስላም ህግጋቶች የተደነገጉበት ሰአት ነበር።ልብ በሉ ነብዩ ﷺ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በታዘዙበት ሰአት ሶስት ወሳኝ ነገሮች አብረው በተጓዳኝ ነበሩ።

1) በጊዜው ሙስሊም ወንዶች ወደ ጀሀድ እንዲሄዱ የታዘዙበት፣
2) ነብዩ ﷺአብዛኛውን ሌሊት በመቆም እንድያሳልፉ የታዘዙበት ነበር።
3) ከሚስቶች ጋር ቁጭ ብሎ ለመጫወት ብዙ ረፍት የማያገኙበት እና የወጣትነት ጊዜያቸውን ካለፈ ወይም እድሜያቸው 53 ከሆነ በኃላ ነው።

     ☞ በዚህ ሰአት ነብዩ ﷺ የተወሰኑ ሚስቶችን አግብተዋል ነገር ግን ሙስሊሞች ከነበረባቸው ኢስላምን የበላይ የማድረግ ስራ ግቡን ከመታና የሙስሊሞች ሰራዊት ተጠናክሮ የወንዶች ሞት ከቀነሰ በኃላ ሌላ አዲስ ሚስት እንዳያገቡ አላህ በእርሳቸው ላይ እርም አደረገ። በቁርአኑም እንዲህ ይላል፣

لَّا يَحِلُّ لَكَ النِّسَاءُ مِن بَعْدُ وَلَا أَن تَبَدَّلَ بِهِنَّ مِنْ أَزْوَاجٍ وَلَوْ أَعْجَبَكَ حُسْنُهُنَّ إِلَّا مَا مَلَكَتْ يَمِينُكَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ رَّقِيبًا

ከእነዚህ በኋላ እጅህ ከጨበጠቻቸው (ባሮች) በስተቀር ሴቶች ለአንተ አይፈቀዱልህም፡፡ ከሚስቶችም መልካቸው ቢደንቅህም እንኳ በእነርሱ ልታላውጥ (አይፈቀደልህም)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 52)

    ይህን የቁርአን አንቀፅ ልብ ብሎ ያስተዋለ ሰው
የነብዩ  ﷺ ከአንድ በላይ #የማግባታቸው_ጥበብ በትክክል ይረዳል። ነገር ግን የኢስላም ጠላቶች ከእውነት የራቀ ቅጥፈት በነብዩ  ﷺ ላይ ሲቀጥፉ መስማት ከህመም በላይ ህመም ነው።ከአንድ በላይ የሆኑ ሚስቶችን እንደ እነርሱ ቅጥፈት "ያገባው ስሜት ለመወጣት እንጂ ለሌላ አይደለም… ………"
እና ሌላም ሌላም በጣም አፀያፊ ዘለፋ መዘለፋቸው የተለመደ ነው።እነርሱ እንደሚሉት አይነት ሰው ቢሆኑ ኖሮ ያረጀች እና በ15 አመት የምትበልጣቸውን የአርባ አመት ሴት ማግባት ለምን አስፈለጋቸው??ከእናታችን ኸዲጃ ጋር 23 አመት አብረው ሲኖሩ ለምንስ ሌላ ወጣት ሴት አላገቡባትም?? ብዙ የማግባት ሱስ ያለበት ወንድ እድሜው እርጅና ደረጃ እስከሚደርስ ድረስ እንዴት ሊያስችለው ይችላል?? እናታችን ኸዲጃ  ሲሞቱ እርጅና ውስጥ ገብተው 63 አመት  ሞልቷቸው ነበር ።ነብዩ  ﷺ ያገቧቸውን ሴቶች ስንመለከት ከዘጠኙ ስምንቱ
#አግብተው_የፈቱ እና በእድሜ የገፉ አብዛኞቹ ከሀምሳ አመት በላይ የሆናቸው ነበሩ፣ ለስሜታቸው ብለው የሚያገቡ ቢሆኑ ኖሮ በእድሜ ወጣት እና አግብተው የማያውቁ ልጃ አገረዶችን ለምን ምርጫቸው አላደረጉም?? የሚስቶቻቸውን ዝርዝር ማንነት እና እያንዳዳቸውን በምን ምክንያት እንዳገቧቸው እንዲሁም የእድሜ ክልላቸውን እና መሰል ቁም ነገሮችን አላህ ከፈቀደው ወደፊት በሰፊው ይመጣል።

    ይህ በእንዲህ እንዳለ የቁረይሽ አለቆች ተሰብስበው ለነብዩ ሰአወ እንዲህ አሏቸው፣ "ንግስናን እናንግስህ ከሴቶች ቆንጆዎችን እየመረጥን እንዳርህ ይህን ወደኢስላም የምታደርገውን ጥሪህን ተው"ብለው ሲማፀኗቸው አላማቸው ሴቶችን መሰብሰብ ቢሆን ኖሮ ወይም ብዙ ሴቶች የማግባት ሱስ ያለባቸው ሰው ቢሆኑ በቀረበላቸው ግብዣ ተደስተው ከአንድ በላይ ቆነጃጅቶችን በሰበሰቡ ነበር!!!

     ⇧ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት
የነብዩ ﷺ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ኡስላምን ከማስፋፋት ቀጥታ ቁርኝት ያለው #ሂክማ_ጥበብ  ነበር።እያንዳዷ  ያገቧቸውን ሚስቶች የኒካህ አጋጣሚ ማንሳት ለግንዛቤ የሚበጅ ስለመሰለኝ በአጭሩ ለማንሳት ወደድኩ።አንባቢያንም ከታሪኩ በርካታ ትምህርቶችን እንደምታገኙ ተስፋ አለኝ።

1/
#እናታችን_ኸዲጃ_ረአ

     የእርሳቸው የትዳር አጋጣሚ ከላይ ለመጥቀስ ሞክሪያለሁ። እናታችን ኸዲጃ ሲያገቡ እድሜያቸው 40 አመት ቢሞላቸውም በእድሜ መለያየታቸው በፍቅር እና በመተሳሰብ ከመኖረወ አንዳችም ተፅዕኖ አልፈጠረባቸውም። ኸዲጃ ረአ ከዚህ አከም በሞት እስከተለዩ ድረስ በመካከላቸው አንዳችም እንከን ሳየከሰት ወርቃማ ጊዜን አሳልፈዋል።በዚህ የትዳር ህይወታቸው ነብዩ ሰአወ በኸዲጃ ላየወ አንዲትም ሴት ተጨማሪ አላገቡም!! እናታችን ኸዲጃ በሞቱበት አመት ትልቅ ድጋፍ እና እርዳታ ሲያደርጉላቸው የነበሩ አጎታቸው አቡ ጧሊብ የሞቱበት ነበር።ይህ ለነብዩ ሰአወ ትልቅ ፈተና ነበር።ያለረዳት እና አማካሪ ብቻቸውን ቀሩ።አመቱ የሀዘን አመት እየተባለ ይታወቃል።እናት የሌላቸውን ልጆች ታቅፈው ኸዲጃን ከጊናቸው አጡ።ከኢብራሂም በስተቀር ሁሉንም ልጆቻቸውን ያገኙት ከዚች ታላቅ ባለቤታቸው ነበር።

#ኢንሻአላህ_ይቀጥላል
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም:::☜ #ክፍል_ሀያ_ሶስተ /②③ት 2/ #እናታችን_ሰውዳ     ነብዩ ﷺ ከኸዲጃ ሞት በኃላ ወደ ፈታኝ የህይወት ምእራፍ ተሸጋግረዋል።ነብዩ  ﷺ እናታችን ሰውዳን ረአ ሲያገቡ የሰውዳ እድሜ 55 አመት ነበር።ሚስቶቻቸው አብዛኞቹ ሀምሳዎቹ ውስጥ ከመሆናቸው የተነሳ የነብዩን ﷺ_ ባለቤቶች እድሜ ማወቁ የኢስላም ጠላቶች በነብዩ  ﷺ ላይ የሚቀጥፉት ቅጥፈት በትክክል ለማወቁና ለእነርሱ…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_አራት/②④ት

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች
6/
#እናታችን_ኡሙ_ሰለማህ

    እነኚህ እናታችንም እንደሌሎቹ
የነብዩ ﷺ ባለቤቶች ተመሳሳይ ችግር ነበረባቸው። ከባለቤታቸው  #ከአብዱላህ_ኢብኑ_አብድ_አል_አሰድ ጋር ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ ናቸው። ከሀበሻ ከተመለሱ በኃላ ባለቤታቸው አራት ልጆች ትተው በድር ላይ ሸሂድ ሆኑ። እናታችን ኡም ሰለማህ በዚያን ጊዜ እድሜያቸው ወደ ስልሳ አመት እየተቃረበ ነበር።ነብዩ ﷺ ይቺን ችግረኛ ሴት የሚረዳቸው መከራቸውን የሚያቃልል ሰው አሰቡ አላገኙም። በመጨረሻም ራሳቸው ሀላፊነቱን ለመውሰድ ማግባትን ወሰኑ።የትዳር ጥያቄ አቀረቡላቸው ። እናታችን ኡም ሰለማህ እንዲህ አሉ፣ "በእድሜዬ የገፋሁ፣የቲሞች ያሉብኛ እና ቀናተኛ ሴት   ስለሆንኩ ለአላህ መልእክተኛ አልሆናቸውም" ብላ ላከች። የአላህ መልእክተኛም መልሰው "አብሽሪ አትጨነቂ የእድሜሽ መግፋት ጉዳዬ አይደለም የቲሞቹንም ተንከባካቢያቸው እኔ ነኝ።ለቅናትሽ ዱአ አደርግልሻለሁ አላህ ያነሳልሻል።" ብለው ላኩባቸው እሺ አሉ ወትሮውንም ያንገራገሩት ለነብዩ በመጨነቅ እንዴት ይህን ሁሉ የቲም ሀላፊነት እጥልባቸዋለሁ በሚል ለነብዩ ካላቸው ታላቅ ክብር ነበር።እኒህ ሴት ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ ከእናታችን አኢሻ ጋር ሆነው አቡ ሁረይራህ ሲሳሳቱ ያርሙ ነበር።

7/
#እናታችን_ዘይነብ_ቢንት_ጀህሽ
       ይቺ እናት
የነብዩ የአጎት ልጅ እና  የታላቁ ሰሀባ የአብደላህ ኢብኑ ጀህሽ እህት ናቸው። ነብዩ  ﷺ ለዘይድ ኢብኑ ሀሪሳህ ድረዋቸው ነበር።በዘይድ እና ዘይነብ መካከል ከረር ያለ አለመግባባት  ተከሰተ።ዘይድ ረአ ወደ ነብዩ ﷺ ወጥቶ ጉዳዩን ነገራቸው።ነብዩም ﷺ ለማረጋጋት ሲሉ ዘይዲን እንዲታገስ መከሩት። ሊሆን አልቻለም።የፀባቸውም መነሻ ዘይድ ለዘይነብ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘት ይመስላል። ዘይነብ ረአ ከአረብ ጎሳዎች  ሁሉ ታላቅ የሆነው የቁረይሽ ዘር መሆኗ እና ዘይድ ደግሞ ነብዩ ሰአወ ነፃ አውጥተው እስኪድሩት ጊዜ ድረስ ባሪያ መሆኑ ሳይሆን አይቀርም። ነብዩ ﷺ ይህን ሲሰሙ ለማስማማት ብዙ ጥረት አደረጉ ነገር ግን አልተሳካም። ፀቡ እያየለ ሂዶ ለመፋታት በቁ።ምን አልባት አንባቢ "ሁለቱ ምርጥ ሰሀቦች ተግባብተው በትዳር ለመቀጠል መስማማት ለምን ተሳናቸው?" የሚል ሀሳብ በአእምሮ ሊመጣ ይችላል።ከክስተቱ በስተኃላ አላህ ለሙስሊሞች አንድ ሊያስተምር የፈለገው ነገር መኖሩ ከዚያ በኃላ የተከሰቱትን ክስተቶች  ማወቅ ለጥያቄው መልስ ያገኛል።

   
#ዘይድ_ኢብን_ሀሪስ ከነብዩ  ﷺጋር የነበራቸው ቁርኝት የጠበቀ መሆን እና ያሳለፉት ጊዜ ረዘም ያለ በመሆኑ በሰዎች ዘንድ የነብዩ ልጅ ተደርገው #ዘይድ_ኢብን_ሙሀመድ እየተባሉ ይጠሩ ነበር።በአረቦች ባህል አንድ ሰው ባእድ የሆነን ሰው አስጠግቶ እያገለገለው ለረጅም ጊዜ ከቆየ እንደልጁ በቁጠር በስሙ ይጠራል።ሁሉ ነገሩ ከስጋ ልጅ ተለይቶ አይታይም ነበር። በዚህም የተነሳ እሱ ያገባትን ሴት አሳዳሪው የነበረው ሰው ማግባትም እርም ነበር።ይህን  መሰል አጉል የጃሂሊያ አስተሳሰብ አላስፈላጊ መሆኑን አላህ በቁርአኑ አውግዞታል። ከዘይድ የተፋቱትን እናታችን #ዘይነብን እንዲያገቡ ነብዩን ﷺ አዘዛቸው።

☞ ዘይድ ኢብን ሙሀመድ የሚለው አጠራር ትክክል እንዳልሆነ አላህ በቁርአኑ እንዲህ ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ادْعُوهُمْ لِآبَائِهِمْ هُوَ أَقْسَطُ عِندَ اللَّهِ ۚ فَإِن لَّمْ تَعْلَمُوا آبَاءَهُمْ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ وَمَوَالِيكُمْ ۚ وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ فِيمَا أَخْطَأْتُم بِهِ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

ለአባቶቻቸው (በማስጠጋት) ጥሯቸው፡፡ እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛ ነው፡፡ አባቶቻቸውንም ባታውቁ በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው፡፡ በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ኀጢአት  አለባችሁ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 5)

   ☞የመሀመድ ልጅ እየተባለ ይጠራ የነበረውን ሰሀቢይ የፈታትን ሚስት አግባ በማለት አላህ (سبحانه وتعالى) እንዲህ ሲል አዟቸዋል፣

وَإِذْ تَقُولُ لِلَّذِي أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِ وَأَنْعَمْتَ عَلَيْهِ أَمْسِكْ عَلَيْكَ زَوْجَكَ وَاتَّقِ اللَّهَ وَتُخْفِي فِي نَفْسِكَ مَا اللَّهُ مُبْدِيهِ وَتَخْشَى النَّاسَ وَاللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَاهُ ۖ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيْدٌ مِّنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَاكَهَا لِكَيْ لَا يَكُونَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ حَرَجٌ فِي أَزْوَاجِ أَدْعِيَائِهِمْ إِذَا قَضَوْا مِنْهُنَّ وَطَرًا ۚ وَكَانَ أَمْرُ اللَّهِ مَفْعُولًا
ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ) አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 37)
ነብዩ  ﷺ የሰው ምላስ ፈርተው ሀቁን ከማሰረተማር ወደ ኃላ እንደማይሉ አላህ በተደጋጋሚ በቁርአኑ ውስጥ መስክሮላቸዋል። በዚህ ጉዳይ የሰዎች ቀልብ ይሰበራል በማለት ወፈ ኃላ ለማለት ሲሞክሩ አላህ በግልፅ ትዛዝ አስተላለፈባቸው።እሳቸው ማንንም ሳይፈሩ የኢስላምን ድንጋጌ ማስተማር ነበረባቸው። ምክንያቱም ከሳቸው በኃላ ሌላ ነብይ መጥቶ ሊያስተካክል አይችልም።እርሳቸው የመጨረሻ ነብይ ናቸውና።ከዚህ ጋር በተያያዘ ነበር አላህም የመጨረሻ ነብይ እንደሆኑ በቁርአኑ በግልፅ ያወጀው።ይህንንም በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፤
مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡።(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 40)
    እውነታው እና በቁርአን የተመሰከረለት
የነብዩ ﷺ እና የእናታችን ዘይነብ ቢንት ጀህሽ ጋብቻ ያሳለፍነውን ይመስል ነበር።ነገር ግን አንዳንድ ሙናፊቆች የሚያወሩት ያልተጨበጠ እና ከሀቅ የራቀ ቅጥፈት በስፋት ሲናፈስ ይስተዋላል። መፅሀፏ አጭር ከመሆኗ አንፃር  ለእያንዳንዱ ውሸት አጥጋቢ መልስ እንዳልፅፍ ይረዝማል የሚል ፍራቻ አደረብኝ በጥቅሉ የሚያወሩት ወሬ እዚህ ግባ የማይባል እና ውሃ ቀጠነ የማይቋረጥ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ
@Tidar_Be_Islam👈👈
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜      #ክፍል_ሀያ_አራት/②④ት #የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች 6/ #እናታችን_ኡሙ_ሰለማህ     እነኚህ እናታችንም እንደሌሎቹ የነብዩ ﷺ ባለቤቶች ተመሳሳይ ችግር ነበረባቸው። ከባለቤታቸው  #ከአብዱላህ_ኢብኑ_አብድ_አል_አሰድ ጋር ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ ናቸው። ከሀበሻ ከተመለሱ በኃላ ባለቤታቸው አራት…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_አምስት/②⑤ት

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች።

8/
#እናታችን_ጁወይሪያህ_ቢንትሀሪስ

      ጁወይሪያህ  የሙረይሲእ ቀን በበኒል ሙስጠሊቅ ጦርነት የተገደለው እና የኢስላም ታላቅ ጠላት የነበረው የማ ቲዕ ኢብን ሶፍዋን ባለቤት ነበሩ። አባታቸው ሀሪስ ኢብኑ አዶራር የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃቸው ሲሆን ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ እንዲደርስ ትእዛዝ ያስተላልፍ ነበር።
የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ ሲፈፅሙ የነበሩ ጎሳዎች ነበሩ።ጁወይሪያህ ባላቸው ማቲእን ኢብን ዶፍዋን በጦርነቱ ከተገደለ በኃላ ከበርካታ ሴቶች ጋር ተማርከው በሙስሊሞች እጅ ወደቁ። ጦርነቱ ተጠናቆ ነብዩ  ﷺ የተማረከውን የምርኮ ገንዘብ(ገኒማህ) በፈረስ ለተዋጉ ሁለት እጅ በእግር ለተዋጉ አንድ እጅ እያደረጉ በእጣ ሲያከፋፍሉ ጁወይሪያህ ለሳቢት ኢብኑ ቀይስ ረአ ድርሻ ሆኑ ገንዘብ ከፍለው ከሳቢት ኢብን ቀይስ ነፃ ለመውጣት ተስማሙ፣አምጪ የተባሉት ገንዘብ ስላልሞላቸው ወደ ነብዩ ሰአወ ቀርበው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ ፣እኔ የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃ ልጅ ነኝ ።ዛሬ እንደምታዩኝ በዚህ ችግር ውስጥ ገብቻለሁ፣እናም ለሳቢት ገንዘብ ከፍዬ ነፃ እንዲያወጣኝ ተስማምተን ነበር፣የምከፍለው ገንዘብ ይስጡኝ" ብለው ሲጠይቋቸው  "ከዚህም  የተሻለ ላደርግልሽ እችላለሁ" አሏቸው። "እሱ ምንድነው?" አሉ ጁወይሪያህ "ገንዘቡን ከፍየልሽ ከፈለግሽ ከእኔ ጋር ትኖሪያለሽ ከፈለግሽ ወደ አባትሽ ትመለሻለሽ" አሏቸው። ጁወይሪያም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እርሰዎን አግኝቼ እንዴት ቤተሰብ ያምረኛል? እርሰዎን መርጫለሁ"አሉ። ነብዩ   ﷺ  ጁወይሪያን ካገቡ በኃላ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የበኒሙስጠሊቅ ህዝብ እስልምናን ተቀበለ።እስልምናን ያልተቀበሉትም ቢሆኑ በሙስሊሞች በየመንገዱ  ላይ የሚደርስባቸውን ስቃይ ትተው በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ፈቀዱላቸው።

9/
#እናታችን_ኡሙ_ሀቢባ

      እናታችን ኡሙ ሀቢባ  እስልምናን ከመቀበሉ በፊት ከአቡ ጀህል በመቀጠል ነብዩን እና ሙስሊሞችን እጅግ ሲበዛ ያሰቃይ የነበረው የአቡ ሱፍያን ልጅ ናቸው።ኡሙ ሀቢባ በጊዜው ኢስላምን ተቀብለው መካ ውስጥ ስቃዩ ሲበረታ ባቸው ከባላቸው ጋር በመሆን ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ አንዷ ነበሩ። ሀበሻ ከደረሱ በኃላ ባላቸውን በድንገት በሞት አጡ።በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት እና መከራ በላያቸው ላይ አጠላባቸው።ወደመካ አይመለሱ የሚጠብቃቸው ኩፍር ነው ይህን የማይቀበሉ ከሆነ የሚጠብቃቸው እስራት እና ግርፋት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። አባታቸው እንኳን የገዛ ልጁን መካ ውስጥ ለምን ኢስልምና ይኖራል ብሎ በቁጭት ሙስሊሞችን የሚያሰቃይ ሰው ነው።ይህ ጭንቀታቸው እና ችግራቸው ወደ አላህ መልእክተኛ ዘንድ ደረሰ። በሁኔታው ነብዩ አዘኑ በወቅቱ አባታቸው ሀይለኛ የኢስላም ጠላት መሆን ያልበገራቸው ይቺ ለኢስላም ብለው ውቅያኖሱን አቋርጠው የተሰደዱት እንስት የሚረዱበት እና የተሰበረውን ልባቸውን የሚጠግኑበት ነገር እሷን ወደርሳቸው አስጠግተው በቅርበት መንከባከብ ነበር። ይህም ሀሳባቸው በተባረከው የሀበሻ ንጉስ ድጋፍ ተሳካ።
የነብዩ   ﷺ  ወኪል ሆኖ ኡሙ ሀቢባን ኒካህ አስሮ በክብር ወደ መዲና እንዲልክላቸው ወደ ሀበሻው ንጉስ መልእክተኛ ላኩ። ንጉሱም በታዘዘው መሰረት 400 ዲናር ጥሎሽ በመጣል እና በጣም የሚያስደስት ስጦታ በመጨመር ኒካሁን አስሮ ለነብዩ   ﷺ  ላከላቸው።ኡሙ ሀቢባ የነብዩን መልእክት በሰሙ ጊዜ ሀዘናቸው እና ትካዜያቸው ጠፍቶ በጣም ተደሰቱ። በሰላም ከነብዩ ዘንድ መዲና ደረሱ። ከነብዩ ጋር የደስታ ህይወትን መኖርም ጀመሩ። ለአላህ ብሎ የተሰደደ ሰው ሁሉንም ነገር የተሻለ ያደርግለታል።

    ☞ ነብዩ   ﷺ  ሀቢባን ካገቡ በኃላ የአቡ ሱፍያን ተንኮል እና ጫና በሙስሊሞች ላይ እየቀነሰ መጣ።ከዛ በኃላ አቡ ሱፍያን ሙስሊሞችን ለመውጋት ወደ መዲና ተንቀሳቅሶ አያውቅም።የተጀመረውን የሰላም ድርድር ለማደስ ወደ መዲና የመጣውም ልጁ የአላህን መልእክተኛ በማግባታቸው ምክንያት ነበር። ወደ መዲና በመጣበት ሰአት ልጁን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸው  ሲያቀና ከልጁ ያገኘው መልስ እንዲህ የሚል ነበር፣
#የሰው_ልጅ_የትልቅነት_የመገለጫ_ኢስልምናን_ሲቀበል_ብቻ_ነው_እናም_እስልምናን_ተቀበል
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አቡ ሱፍያን ቀልቡ እየተለሳለሰ ይመጣ ጀመር።በስተመጨረሻም  ኢስልምናን ሊቀበል ችሏል።

#የመጨረሻዉ_ክፍል_ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜      #ክፍል_ሀያ_አምስት/②⑤ት #የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች። 8/#እናታችን_ጁወይሪያህ_ቢንትሀሪስ       ጁወይሪያህ  የሙረይሲእ ቀን በበኒል ሙስጠሊቅ ጦርነት የተገደለው እና የኢስላም ታላቅ ጠላት የነበረው የማ ቲዕ ኢብን ሶፍዋን ባለቤት ነበሩ። አባታቸው ሀሪስ ኢብኑ አዶራር የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃቸው…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_ስድት/②⑥ት_የመጨረሻዉ_ክፍል

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች

10/
#እናታችን_ሶፍያ_رضي الله عنها

     የአላህ መልእክተኛ ሶፍያን የማግባታቸው ምክንያት የኢስላም ጠላቶች እንደሚቀጥፉት የተለያየ ቅጥፈት ሳይሆን እውነታው እንደሚከተለው ነው።በኸይበር ዘመቻ ወቅት ለጦርነት ከተሳተፉት አይሁዶች ውስጥ አዲስ ተጋብተው በጫጉላ ቤት የነበሩት ሶፊያ ከእነባለቤታቸው ይገኙበታል። በሙስሊሞች እና በአይሁዶች መካከል በተካሄደው ጦርነት የሶፍያ ባለቤት ይገደላል፣ሶፍያም በሙስሊሞች ይማረካሉ። በዚህ መካከል ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ዲህየት አል ከልቢ የሚባል ሶሀቢይ ወደ ነብዩﷺ  መጥቶ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ ከተማረኩ እንስቶች መካከል አንድ ባሪያ ይስጡኝ" ብሎ ይጠይቃቸዋል፣ነብዩም ﷺ "የመረጥካትን እንስት ባሪያ ውሰድ" የሚል ምላሽ ይሰጡታል፣ወደ ተማረኩት እንስቶች ዘንድ በመሄድ ሶፍያን ሲመርጥ ሶሀቦች ያዩታል።የሶፍያን በአይሁዶች ዘንድ ያላቸውን ታላቅ ደረጃ የሚያውቁት ወደ ነብዩ ሰአወ ዘንድ መጥተው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሶፍያ እና የሶፍያ ቤተሰቦች በአይሁዶች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ንጉሶች ናቸው። እናም ሶፍያ የምትገባው ለእርሰዎ ነው!! ከእርሰዎ ውጭ ለሌላ የምትሰጥ ከሆነ ቅሬታ ሊመጣ ይችላል። ህዝቦቿም የሚያመጡት ሀሳብ አይታወቅም።"
የሚል ሀሳብ ሰጧቸው ነብዩም በሀሳቡ ተስማሙ። አስጠሯቸው እና ለሶፍያ እንዲህ አሏቸው፣ "ሁለት አማራጮችን አቀርብልሻለሁ፣የፈለግሽውን መምረጥ ትችያለሽ ይኸውም እስልምናን የማትፈልጊ ከሆነ ነፃ አውጥቼሽ ወደ ቤተሰቦችሽ  መቀላቀል ትችያለሽ፣እስልምናን የምትቀበይ ከሆነ ህይወትሽ ከእኔ ጋር ይሆናል(ኒካህ አደርግልሻለሁ)" በማለት ምርጫ ሰጧት ።እሷ ግን የመለሰችላቸው እጅግ አስገራሚ መልስ ነበር።እንዲህም አለቻቸው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እንዴት ክህደትን እና እስልምናን ባማራጭነት ያቀርቡልኛል።እኔ እኮ እስልምናን የተቀበልኩት ወደ ርሰዎ ከመምጣቴ በፊት ነው።ሞቴም ህይወቴም ኢስላም ነው።እኔ ለአይሁድ ቤተሰቦቼ ጉዳይ የለኝም" ብለው መለሱላቸው።

     ☞ ነብዩም ﷺ በተናገሩት መሰረት ኒካህ አሰሩላቸው።በዚህ ኒካህ ምክንያት በርካታ የአይሁድ ታላላቅ ሰዎች ጭምር እስልምናን ተቀበሉ።ያልሰለሙትም ቢሆኑ ነብዩን እና ሰሀቦችን አዛ ማድጋቸውን በእጅጉ ቀነሱ። ይህ ጋብቻ ለኢስላም ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው።

11/
#እናታችን_መይሙናህ( رضي الله عنها)

      እናታችን መይሙናህ ከነብዩ ﷺ በፊት 2 ባል አግብተው የፈቱ ሲሆን የአንድ የአረቦች ንጉስ የነበረ ሰው ሚስት እህት ናቸው። ይህ ሰው ያስተዳድራቸው የነበሩ ሰዎች እጅግ በጣም ሀይለኛ አስቸጋሪ የሚባሉ ጎሳዎች ነበሩ። የዲን አስተማሪ እንፈልጋለን በማለት ከነብዩ ሰአወ የተላኩላቸውን
#ሰባ_ሰሀቦች ገለዋል። በዚህ የተነሳ ከነብዩ ሰአወ ጋር ከፍተኛ የሆነ ጠላትነት ነበራቸው።
ሙስሊሞችን በአገኙት አጋጣሚ ለማጥቃት ወደኃላ አይሉም ነበርበአረቦች የተለመደው እና ኢስላምም ያልተቃወመው አንድ ቆንጆ ልምድ አላቸው።ይኸውም ሁለት የተለያዩ ጎሳዎች ከፍተኛ የሆነ ጥላትነት በመካከላቸው ሲፈጠር በአማችነት ትስስር ውስጥ ይገቡ እና ወደ ወዳጅነት ይቀይሩታልይህን ጠላትነት ለማርገብ ሲባል የአላህ መልእክተኛ እናታችን መይሙናን አገቡ።ነብዩ ﷺእንዳሰቡትም የእነዚህ ሰዎች ተንኮል ለመቀነስ እና ወደ ኢስላም የሚያደርጉትን ጥሪ ከመስተጓጎል ተቆጥበዋል።

☞ ነብዩ  ባለቤቶቻቸውን ያገቡበት መንገድ በአጠቃላይ ሲታይ በቀጥታ የጌታቸውን ትዛዝ ከመፈፀም ጋር የተያያዘ ነበር።እኛ ሙስሊሞች ሴቶችም ሆናችሁ ወንዶች ለጠላ ት ወሬ ጆሮ ሳንሰጥ የነብዩን ሱና ለመከተል ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። አንዳንድ ሙስሊም ወንድሞችን ሳይ በጣም አዝናለሁ። መስፈርቱን ሳያሟሉ እና ነገሮችን ሚስጥር ሳያወጡ የየዋህ እህቶቻችንን ህይወት አበላሽተው ወረታቸው ካለቀ በኃላ ወደ መጀመሪያዋ ሚስታቸው ይጠቃለላሉ።ይህ ታላቅ ክህደት ነው።ሴት እህቶቻችን ይህን በማየት ሁለተኛ ሲነሳ ልባቸው ላይ ጥላቻ እስከ ማሳደር ደርሷል።በእርግጥም ይህ ተራ ወንበዴ በሰራው ተነስቶ በአጠቃላይ ሁለተኛ የሚለውን መጥላት ወይም ሁለተኛ መሆን ውርደት ነው ብሎ ማሰብ ከአቂዳ ጋር የሚጋጭ አስተሳሰብ ነው። የሴቶች ሁሉ አይነቶች ተብለው የተመሰከረላቸውን እነ እናታችን ኢሻን እንደ የበታች መቁጠር ነው

❗️የነቢያች የትዳር ሕይዎት ይሄንን ይመስላል ከዚህ ፁሁፍ ብዙ ነገር እና እዉቀት እደገኛችሁ ተስፋ አለኝ።

እስኪህ ከመጀመሪያዉ እስከመጨረሻዉ ያነበባችሁ አስተያየት ፀፉልኝ بارك الله فيكم

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam