ቴዎፍሎስ theophilus
212 subscribers
145 photos
7 files
7 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
ቅድስና
ክፍል 9
ከፀደቀ
ያለክን መስጠት እንጂ ካለህክ ላይ መስጠት አይከብድም
(ከፀደቀ)
ዮሐ 14:6 ኢየሱስ እኔ መንገድ እዉነት ህይወት ነኝ
ኢየሱስ መንገድ ነዉ ሄድበታለዉ
እዉነት ነዉ እታመንበታለዉ
ህይወት ነዉ እኖርበታለዉ
መፅሐፍ ቅዱስ የሚለዉ አንድም ወይም ሁለትም በስሜ በተሰበሰባችሁበት እኔ እገኛለዉ ሳይሆን ያለዉ ሁለትም ሶስትም ነዉ በተሰበሰባችሁበት እኔ እገኛለዉ ነዉ ያለዉ ማቴ 18:20
ኢየሱስ እንኳን ለሰዉ አገልግሎት አህያዋን ፈታቹ አምጡልኝ ያለዉ ሁለት ሰዉ ነዉ
ቅድስና
ክፍል 10
ከፀደቀ
ፍፁም የሆነ ቤተክርስቲያን በመፈለግ ዘመንክን ባትጨርስ ይሻልሀል ምክንያቱም ፍፁም የሆነች ቤተክርስቲያን ስለሌለ ፍፁም የሆነች ቤተክርስቲያን አግኝተህ ብትገባ እንኳን አንተ ስለገባህ ፍፁምነቷን ትለቃለች
ቅድስና
ክፍል 11
ከፀደቀ
ሰላም ተወዳጆች ሁለት ጉዋደኛማቾች ለመዝናናት ወደ ሀይቅ በሄዱበት አንደኛዉ ሌላዉን ጉዋደኛዉን ገፍትሮ ወደ ሀይቅ ዉስጥ ቢከተዉ ሀይቅ ዉስጥ የገባዉ ቢሞትና እንደገና ከሞት የመነሳት እድል ቢሰጠዉ እርግጠኛ ነኝ ወደ ሀይቅ ከከተተዉ ጉዋደኛዉ ጋር ለመዝናናትም ሆነ ከእርሱ ጋር ለመዋል አይፈልግም። ተወዳጆች ዲያቢሎስ እኮ በኤደን ገነት አታሎ ገድሎናል እንደገና በክርስቶስ ህይወት ተሰጥቶናል አሁን ታዲያ ዲያብሎስን መበቀል እንጂ መቀበል እኮ የለብንም የምንበቀለዉም የፅድቅን ህይወት በመኖር መንፈሳዊ ፍሬን በማፍራት ነዉ
(ተባርካቿል ፀደቀ ነኝ)
ቅድስና
ክፍል 12
ከፀደቀ
ብዙዎቻችን ንስሀ የመግባት ችግር የለብንም ተመልሰን ወደ ሀጢአት የመግባት እንጂ በልጅነታችን በጭቃ ተጫዉተን ልብሳችን ከቆሸሸ ቡሀላ እናቶቻችን በደንብ አድርገዉ ያጥቡናል በመቀጠልም ልብስ ይቀይሩልናል ካሰማመሩን ቡሀላ ግን በድጋሚ በዛ ጭቃ እየተጫወትን ብታየን ምን ያክል እንደምታዝን መገመት አይከብደንም እግዚአብሄር ንስሀ ስንገባ የልጁ የክርስቶስ ደም ዛሬም ትኩስ ነዉና ከሀጢአታችን ያነፃናል እኛ ግን በድጋሚ ከወደቀዉ አዳም ጋር በሀጢአት ስንቦራጨቅ ሲያይ እግዚአብሄር ምን ያክል እያዘነብን ይሁን። እግዚአብሄር ይበልጥ የሚደሰተዉ ንስሀ መግባታችን ላይ ብቻ ሳይሆን ተመልሰን ወደ ሀጢአት አለመግባታችን ላይ ነዉ።
#ፀደቀ #መንፈሰ
ቅድስና
ክፍል 13
ከፀደቀ
ሰላም ተወዳጆች ፃዲቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል ወደ እግዚአበሐር የምንሮጠዉ የሚከበንን ሀጢአት ስናስወግድ ነዉ ዕብ 12 ሩዋጮች በሚሮጡበት ጊዜ ብዙ ደጋፊ ቢያያቸዉም ዘንጠዉ አይደለም የሚገቡት ቁንጣ አድርገዉ እንጂ የሚዘንጡት ዉድድሩን ከጨረሱ ቡሀላ ነዉ በዚህ ምድር በፅድቅ ስንኖር ላይመቸን ይችላል የምንዘንጠዉ ሰማይ ነዉ የመጨረሻዉ ደዉል ሲደወል ፍጥነት እንደሚጨምሩ አሁን የምንሰማቸዉ። እና የምናያቸዉ ክፍት ዘረኝነት ጥላቻ እና የመሳሰሉት የዘመን መጨረሻ ደዉሎች ናቸዉ ፍጥነታችንን ከቀድሞዉ መጨመር አለብን( ተባርካቿል ፀደቀ ነኝ)
እንኳን ተወለዳችሁ ይህ ያልኩበት ምክንያት የእየሱስ መወለድ የእኛ መወለድ ስለሆነ ነዉ ኢየሱስ በበረት ዉስጥ ሲወለድ የበረቱ ሽታ ለነማርያም ሆነ ለህፃኑ እየሱስ የሚስማማ አይደለም ሰዉ እንኳን በረትን ምርጫዉ ሊያደርግ አይደለም በዛን ለማለፍ እራሱ አፍንጫዉን ይዞ ነዉ የሚያልፈዉ እየሱስም እኛን መምረጡ ልክ እንደዚህ ይገርማል በበደላችንና በሀጢአታችን ሙታን ስለነበርን ከበረቱ ሽታ የበለጠ የእኛ ሽታ ይበልጥ ነበር ሰብአ ሰገዶቹ ለተወለደዉ ህፃን ይዘዉ የመጡት እጣን ከርቤና ወርቅ ነዉ መርጠዉ የሰገዱትም ለሱ ነዉ የእኛ እየሱስ እኮ እንኳን በዙፍኑ ተቀምጦ አይደለም በበረት ተኝቶ እንኳን ተሰግዶለታል እርሱ እንኳን በመላእክት ታጅቦ አይደለም በከብቶች ታጅቦ እንኳን ተሰግዶለታል ወገቡን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቆ አይደለም በጨርቅ መጠቅለያ ተጠቅልሎ እንኳን ተሰግዶለታል እኔን በጣም የገረመኝ ለወደቀዉ አዳም ያማረዉን ኤደን ገነት ለመኖሪያዉ ሰጠዉ ለራሱ ግን የመረጠዉ የከብቶች ማደሪያን በረትን ነዉ ኢየሱስ በከብቶች ማደሪያ መወለዱ ሳይሆን የሚገርመኝ ከእኔ ጋር መኖሩ ነዉ በድጋሚ ልበላችሁ እንኳን ተወለዳችሁ። መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ ይህንን መልእክት ለሌላዉ ያስተላልፉ
ተባርካቿል #ፀደቀ ነኝ
ህብረትን አትጥሉ ኢየሱስ እንኳን ለሰዉ አገልግሎት አይደለም ለ donky ministry እራሱ ሁለት ሰዉ ነዉ የላከ ፈታችሁ አምጡልኝ ነዉ ያላቸዉ( ከፀደቀ)
ቤቱ በጣም የሚያምር ምግብ ቤት ገብታችሁ ነገር ግን ምግቡ ምንም የማይጣፍጥ ከሆነ እርግጠኛ ነኝ እዛ ቤት ተመልሳችሁ አትሄዱም አንዳንዱ ቤት ደግሞ በጣም ትንሽ ናቸዉ ምግቡ ግን የሚጣፍጥ ከሆነ ሰዉ በሰልፍ ነዉ የሚበላዉ ቤተክርስቲያንም ለኔ ልክ እንደዚህ ነች የማምለኪያ አዳራሹ (ቤቱ) በጣም አምሮበት ክርስቲያኑ ደግሞ እንደ እግዚአብሄር ቃል ካልተሰራ ፍጥረታዊ ሰዉ(ያላመነ) መምጣት አይፈልግም ያሉትም ክርስቲያን ወደዛች ቸርች መሄድ አይፈልጉትም ነገር ግን ቤቱ ብዙም ባያምር ክርስቲያኑ ግን እንደ እግዚአብሄር ቃል ከተሰራ ብዙ ያላመኑት መጥተዉ ይድናሉ ያመኑትም እዛዉ ይቀራሉ አንዳንድ አገልጋዮች በአሁን ጊዜ ክርስቲያኑ የሚገነባበት ቃሉን ይዘዉ እነርሱ ግን የሚጨንቃቸዉ የቤቱን መገንቢያ ብር ነዉ ክርስቲያኑን በእግዚአብሄር ቃል ገንቡት እነርሱ ቤቱን ይገነቡታል (ተባርካቿል ፀደቀ ነኝ)
👉በገና በአል ስጦታ ከሚሰጠን ሰዉ በላይ ህይወቱን ለሰጠን ኢየሱስ የምናመሰግንበት ቀን ይሁን በገና በአል በግ ከማረዳችን በፊት ስለ እኛ እንደ በግ ሊታረድ የተወለደዉን ኢየሱስን እናስበዉ የገና በአል የኛ ከሌላዉ የሚለየዉ የምንበላዉ ምግቡ ላይ ሳይሆን ተቆርሶ የማያልቀዉን የህይወት እንጀራ የሆነዉን እየሱስን የተቀበልንበት ቀን ስለሆነ ነዉ ልደት ተጠርታችሁ ስጦታ ምን ይዤ ልሂድ እያላችሁ እንደምትጨነቁት ሁሉ ዛሬ ደግሞ የክርስቶስ ልደት ነዉ ክርስቶስ ደግሞ ተወልዶ ሙት የነበርነዉን እኛን ደግሞ ህይወት ሰጥቶናል ስለዚህ አዲስ የተወድኩት እኔም ጭምር ነኝ ታዲያ ለሱ የሚመጥን ስጦታ የት አገኛለዉ አለም ላይ ካለዉ አንዱን ብሰጠዉ አለም ሁሉ ደግሞ የሱ ነች ለስጦታዉ ብዙም አታስቡ ተገኝቷል እራስህን/ሽን ስጠዉ/ጪዉ ምክንያቱም በዚህ ምድር ካንተ/ቺ በላይ ዉድ ነገር ኢየሱስ ስለሌለዉ በድጋሚ ልበላችሁ የገና ድምቀቱ ኢየሱስ ነዉ መልካም በአል ይህንን መልእክት ለሌላዉ ያስተላልፍ (ተባርካቿል ፀደቀ ነኝ)
ህጉ 623 ነዉ ሁሉንም ፈፅመን በአንዱ ከወደቅን የሚያስበዉ 623×1 =623 ሀጢአት ሰርቷል የእስራኤል ህዝቦች ህግ እንደተሰጣቸዉ በመጀመሪያዉ ቀን ነዉ የወደቁት ለዛዉም በመጀመሪያዉ ትእዛዝ የመጀመሪያዉ ትእዛዝ ከኔ በቀር ሌላ አማልክት አይኑሩክ የሚል ነዉ ሙሴ ከሲና ተራራ ህጉን ይዞ ሲወርድ ጣኦት ሰርተዉ እያመለኩ ነበር ህጉ በተሰጠበት ቀን ጣኦት ስላመለኩ 3000 ሰዎች ሞቱ ፀጋዉ ደግሞ በጴጥሮስ 3000 ነብሳትን በማዳን ጀመረ (ተባርካቿል ፀደቀ ነኝ)
በገና በአል አካባቢ አንድ የተለመደ ነገር ቢኖር እኛ ክርስቲያኖች የ telegram profile ወይምየ Facebook profile ላይ የምንቀይረዉ ገናን ይገልፁልናል ብለን የምናስባቸዉን ፎቶ ነዉ አብዛኛዉ ሰዉ profile የሚያደርገዉ ክርስቶስን የሚገልፅ ሳይሆን ሳንታ ክላዉስን የሚያስታዉስ ፎቶ ነዉ ልደቱ የሳንታ ክላዉስ ሳይሆን የክርስቶስ ነዉ እንደዉም ይህ ክርስቶስን የሚያደበዝዝ ነዉ እኛ ክርስቲያኖች መንቃት መቻል አለብን ከ profile ከመቀየር አንስቶ እየሱስን ኢየሱስን የሚሸት መሆን አለበት (ተባርካቿል ፀደቀ ነኝ)
ቅድስና
ክፍል 14
ከፀደቀ
" ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።"
(2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 3:5)