አላዋቂ ሳሚ…
አንዳንድ የሰንበት ትምህርት እንኳ በቅጡ ያልተማሩና በካህናቱ ዘንድ ‹‹ጨዋ›› የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሰዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን እንደ አዋቂ በመቊጠር ‹‹አለን›› የሚሉትን መልስ ለመስጠት ያደረጉትን መንደፋደፍ አይተን ‹‹የልጅ ነገር›› ብለን ብንተዋቸውም እነርሱ ግን አዋራ በማስነሣት አላዊቂነታቸውን አደባባይ ላይ ማስጣታቸውን ማቆም አልቻሉም፡፡ ስለዚህም አንድ መልስ ሲሠራ 1) በጉዳዩ ላይ ትንሽም ቢሆን ማንበብ እንደሚገባ 2) በውይይቱ ወቅት የተነሣው ሐሳብ ትክክል ነው ወይ? የሚለውን በሚገባ መመልከት ግድ እንደሚል ለማሳየት ይህ ጽሑፍ ተዘጋጅቷል፡፡
እግረ መንገድም መልእከት በመተላለፉ ደስተኞች ነን፡፡
ለዚህ ጽሑፍ መዘጋጃት ምክንያት የሆነው የ‹‹ጨዋዎቹ›› የመጨረሻ መልእክት ነው፡፡ በዚህ መልእክታቸው ከኪዳነ ምሕረት ቊጥር 21 ላይ ያገኘነው ሐሳብ ነው በማለት ‹‹ድንግል ማርያም ለእኛ መዳን ድርሻ አላት ብለን የምናምነው #ከመስቀሉ #ስር #ስለተገኘች #እንደ #ሆነ #አስመስለው #አቀርበውታል!! ይህ ነው እንግዲህ የተሐድሶዎች #የማታለያ #ስለት፡፡… ለማንኛውም ይህ #ውሸታቸው በእውነተኛው ሚዛን ሲመዘን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነጥሮ ይወጣል›› የሚል ትችት አቅርበዋል፡፡
በዚህ ሐሳባቸውም ኪዳነ ምሕረት ላይ የተጻፈው ነገር ፈጽሞ የሌለና ውሸት የሆነ ነገር እንደ ሆነ ነው ማሳየት የፈለጉት፡፡ ከዚህ ጽሑፍ ጋር አብሮ ያለው ፎቶ እንደሚያሳየው ግን የተነሣው ርዕሰ ጉዳይ ከሜዳ የተነሣ (እነርሱ እንዳሉት ውሸት የሆነ) ሳይሆን ሄኖክ የተባለ አንድ ሰባኪ ‹‹የማርያም መንገድ›› በሚል ርዕስ በሰበከው ስብከት 23፡20-23-50 ደቂቃ ድረስ ያቀረበውን ስብከት መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በዚያ ስብከቱ ‹‹#ኢየሱስ #ሲሰቀል #መስቀል #ላይ #ቆማ #የእኛን #መዳን #አስፈጽማለች…›› ይላል (‹‹መስቀል ላይ #ቆማ›› ማለቱን ልብ ይበሉ!!!)
ጨዋው እንዲህ የሚል ትምህርት የለም ከሚል ሄኖክ ኦርቶዶክስን አይወክልም ቢል የተሻለ አቀራረብ ይሆን ነበር፡፡ ነገር ግን ኪዳነ ምሕረትን በተሻለ ሐሳብ መተቸት ስለከበደው ውሸት ነው ወደ ማለቱ አዘንብሏል፡፡
ለመሆኑ ሄኖክ የሚባለው ሰው ያለው ምንድን ነበር? የተሰጠውስ መልስ እንዲት ያለ ነው? የሚለውን በራስዎ እንዲያገናዝቡት ፎቶውን ይመልከቱ፡፡