እውነት አርነት ያወጣል
2.78K subscribers
371 photos
69 videos
37 files
365 links
እውነት አርነት ያወጣል!!!
Download Telegram
ለ2017 ዓ.ም. ሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት፣ በነገረ መለኮት ዘርፍ ለመጨረሻው ዙር ዕጩ ኾነው የቀረቡት የመጻሕፍት ዝርዝር በምስሉ ላይ የተመለከቱት ናቸው። በመኾኑም፣ ርስዎ ያነበቡትንና ዕውቅና ይገባዋል የሚሉትን አንድ መጽሐፍ፣ ዕጩ ከተደረገበት ዘርፍ ለመምረጥ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦


https://docs.google.com/forms/d/1YDUXGpLnx-mlnK1ipGyhkQeiEtjx-Al10rYepswpdjI/
እግዚአብሔርን ማስረሳት

ክርስቲያን የሆነ ሁሉ አንድ የመመሪያ መጽሐፍ አለው፡፡ እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ይባላል፡፡ በዚህ ቅዱስ መጽሐፍ በኩል የመጽሐፉ ባለቤት እግዚአብሔር አምላክ ሊያሳውቀን የወደደውን ሁሉ እንድናውቅ አድርጎናል፡፡ በመሆኑም ክርስቲያኖች ከዚህ መጽሐፍ አልፈው በራሳቸው መንገድ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን መቀጠል አይችሉም፡፡
በዚህ መንገድ ውስጥ ከሄዱት መካከል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንዱ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ‹‹እንዚራ ስብሐት›› በተሰኘው መጽሐፉ በኩል ወደ ቤተ ክርስቲያን ባስገባው ጽሑፉ እግዚአብሔርን ትተን በፍጡር እንድንታመን የሚያደርግ መልእክት አስተላልፏል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በሚኖሩን ተከታታይ ጽሑፎች ‹‹በርግጥም እግዚአብሔር ምን ይሠራልናል?›› የሚል ጥያቄ የሚያጭሩ ሐሳቦችን ከመጽሐፉ ውስጥ እናሳያለን፡፡

ይቅርታን የምታጎናጽፈዋ ማርያም

የቅዱሳንንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት በተመለከተ አንድ ሐሳብ በተደጋጋሚ ሲነገር ሰምተናል፡፡ እሱም፤ ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡን ናቸው፣ እነሱ ይቅርታ የሚያሰጡ እንጂ በራሳቸው ይቅርታ የሚያደርጉ ናቸው ብለን አናምንም የሚል ነው፡፡ በዚህ ሐሳብ ውስጥ ከሚቀርቡት አንዱ ማርያም ናት፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በዚህ ሐሳብ የሚስማማ አይመስልም ምክንያቱም ከዚህ በታች በቀረበው ጽሑፉ በኩል ማርያም በራስዋ ይቅርታ የምታደርግ ናት የሚል ሐሳብ አቅርቧል፡፡

‹‹ምሳሌ የሌለሽ ንግሥት ሆይ ዛሬም ልመናን በማብዛት እማጸንሻለሁ፡፡ መፍራትን ይቅርታን አጎናጽፊኝ፡፡… ይቅርታሽም ዘመኑን ሁሉ ይከተለኝ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 9)፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ ላይ ሦስት ችግሮችን የምናገኝ ቢሆንም ‹‹እማጸንሻለሁ›› የሚለውን በሌላ ጽሑፍ የምንመለከተው በመሆኑ ሁለቱን ችግሮች ብቻ ከዚህ በታች አሳያለሁ፤

1. ‹‹ምሳሌ የሌለሽ››፤ የመጽሐፉ አዘጋጅ አባ ጊዮርጊስ መጽሐፍ ቅዱስን የተማረ ነው ተብሎ የሚታመን በመሆኑ በቅዱሱ መጽሐፍ ውስጥ ምሳሌ የሌለው ተብሎ የተገለጸው እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን አይረሳም ተብሎ ተስፋ ይደረጋል፡፡ ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም›› ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳይያስ 46÷9)፡፡ በዚህም ምክንያት ታላቁ ነቢይ ኤርምያስ ‹‹አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው›› ይላል፡፡ በርግጥም እንደርሱ ያለ ማንም የለም (ኤርምያስ 10÷6)፡፡

ከዚህ አልፎ ለሚመጣ ሰው ‹‹እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?... እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ›› ተብሎ ተጽፏልና እርሱን እንዲያነብ ይመከራል (ኢሳይያስ 40÷18፡ 25)፡፡ በዚህም ደግሞ አባ ጊዮርጊስ የተሳሳተ ጽሑፍ የጻፈ መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ለማርያም በዚህ ልክ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በታች በሆነ ሁኔታ ምሳሌ የሌላት ተብሎ ስላልተጻፈ ጸሐፊው የልቡን መሻት ነውና የጻፈው፡፡

2. ‹‹መፍራትን ይቅርታን አጎናጽፊኝ፡፡… ይቅርታሽ››፤ ቀደም ሲል እንደተባለው ማርያም ወደ እግዚአብሔር የምታደርስ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር የምታስታርቅ ናት የሚል እምነት እንዳላቸው በአንደበት ይነግሩናል፡፡ ይሄ ግን ውሸት ነው፡፡ ምክንያቱም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት መካከል የሆነው አባ ጊዮርጊስ ማርያም የራሷ የኾነ ይቅርታ እንዳላት (ይቅርታሽ ነውና የሚለው) በመጻፍ በዚህ ይቅርታዋን እንደምታጎናጽፍ ሊያሳይ እየሞከረ ነው፡፡

ይሄ የአባ ጊዮርጊስ ጽሑፍ አሁን አሁን በውሸት ከሚናገሩት ንግግር ጋር ብቻ ሳይሆን ከታላቁ መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋርም አይስማማም፡፡ ምክንያቱም ቅዱሱ መጽሐፍ ይቅርታን የምናገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያስተምራል፡፡ ‹‹አቤቱ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል?›› የሚል ጥያቄ ይጠይቅና ራሱ መልሱን ሲሰጥ ‹‹ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና›› ይላል (መዝሙር 130÷3-4)፡፡ በርግጥም ከእርሱ ውጪ ይቅርታ ሊያደርግ የሚችል አካል የለም፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው›› የሚል ምክር ካቀረበ በኋላ ‹‹ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ›› በማለት ያበረታታል (ኢሳይያስ 55÷7)፡፡ ኢሳይያስ ይቅርታው የእግዚአብሔር መሆኑን ‹‹ይቅርታውም›› በማለት የጻፈ ሲኾን የእንዚራ ስብአት መጽሐፍ አዘጋጅ ደግሞ ‹‹ይቅርታሽ›› በማለት ይቅርታን ለፍጡር ሲሰጥ ይታያል፡፡

ወገኖቼ ይቅርታን ያገኘነው እንዲሁ በጸሎት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ ዋጋ ተከፍሎልን፣ ደም ፈሶልን ነው፡፡ ይኼን የይቅርታን መንገድ ደግሞ ጌታችን እንዲህ ብሎ ነግሮናል፤ ‹‹ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው›› (ማቴዎስ 26÷28)፡፡ ስለዚህ በሌላ አካል ይቅርታ ይገኛል እያሉ ዓይንህን ወደ ፍጡራን እንድታማትር የሚያደርጉህን ሰዎች አትስማቸው፡፡፡፡
እናንትዬ የእኔ ወዳጆች

በዚህች ሊንክ ገብታችሁ ይሄን መጽሐፍ በመምረጥ የበለጠ እንድትጋ እንድታበረታቱኝ እጠይቃለሁ



https://docs.google.com/forms/d/1YDUXGpLnx-mlnK1ipGyhkQeiEtjx-Al10rYepswpdjI/
የዛሬ ገጠመኜን እንካችሁ

በዘርዐ ያዕቆብ ላይ የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ እጄ እንደገባ ጉዞዬ ወደ ቤት ነበርና ባስ ውስጥ ገባሁ። ባሱ ባዶ ስለነበር ለንባብ የሚመች መቀመጫ መርጬ መጽሐፉን ጀመርኩ። ዘግይቶ በመምጣት አጠገቤ የተቀመጠው ሰው አብሮኝ እያነበበ እንደ ነበረ ግን አላወኩም ነበር።

ጎረቤቴ የመጽሐፉን ርዕስና አዘጋጅ ጠየቀኝ፤ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ሲገጥመኝ የመጽሐፋን የፊት ሽፋን ማሳየትን እመርጣለሁ። ምክንያቱም ወሬ ተጀምሮ ንባቤ እንዳይቋረጥብኝ ነበር። ሰውየው ግን በጥሩ ሞራልና ጎላ ባለ ድምጽ ወሬ ጀመረ። ወደ ንባቤ እንደማልመለስ ሲገባኝ መጽሐፉን ከድኜ ለወሬ ተመቻቸሁ።

ከጎረቤቴ ረዘም ያለ ንግግር ጸሐፊ መሆኑ ገባኝና ጠየኩ። አዎ ጽፌያለሁ ብሎ የመጽሐፉን ሽፋን በስልኩ አሳየኝና እሱ ግን ሁለት መጻሕፍት እንደሚወድ ነገረኝ።

የመጀመሪያ የጠቀሰልኝ "ወልታ ጽድቅ" የተሰኘውን መጽሐፍ ነው። መጽሐፉን በጣም እያደናነቀ በዚህ ጉዳይ ሁነኛ መጽሐፍ መሆኑን እንደቀበል ደጋግሞ ነገረኝ። የወዳጄን የዲያቆን አግዛቸውን መጽሐፍ ሽፋን ከፌስ ቡክ በማውጣት ይሄን መጽሐፍ አንብበኸዋል? አልኩት። የመጽሐፉን ሽፋን በጥንቃቄ ተመልክቶ የት እንደሚያገኘው ሲጠይቀኝ ፊቱ ላይ መጓጓት ይታይበታል። የመጽሐፉን ይዘት ስነግረው ቀደም ሲል ሲያደንቀው የነበረውን መጽሐፍ ደግሞም አላነሣውም።

ወደ ሁለተኛው መጽሐፍ የገባው በእኔ ጠያቂነት ነበር። "ሁለት መጻሕፍት እንደምትወድ ነግረኸኝ ነበር፤ ሁለተኛው ማነው?"። እሱም "መድሎተ ጽድቅ ነው" ብሎ እንደስሙ ነው በማለት ደጋግሞ ሲያወራ የስሙን ትርጉም ጠየኩት። ጎረቤቴም "የእውነት ሚዛን" አለኝ። "እኔ ግን አልስማማም ምክንያቱም ጸሐፊው ሐሰተኛ ክስ ያቀርባልና" አልኩት።

ጎረቤቴም ቆፎጠን ባለ ድምጽ "በፍጹም" አለኝ። እኔም "እንግዲያውስ መጽሐፉን አላነበብከውም" አልኩት። ጎረቤቴም መልሶ "እሺ ያነበብከውን ሐሰተኛ ክስ ንገረኝ" አለኝ።

"የመጀመሪያውን ቅጽ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመጀመሪያውን ንዑስ ርዕስ መመልከቱ ብቻ ጸሐፊው ሐሰተኛ ከሳሽ መሆኑን ለመረዳት ያግዛል። ገና ሲጀምር በውሸት ዓይኑን የከፈተ ጸሐፊ በቀጣይ እውነት ይናገራል ብሎ ማለት ይከብዳል። ይሄም ሐሳብ በዚህ ጽሑፍ ላይ ተገልጿል" በማለት በቅርቡ ለንባብ የሚበቃውን የ"መዛኙ ሲመዘን ቅጽ ፪"ን ሽፋን በማሳየት የመጽሐፉን ሐሳቡ ነገርኩት።

ቅድም የነበረው ወኔ ጠፍቶ ቀዝቀዝ በማለት ቤቱ እንደገባ የነገርኩትን ክፍል እንደሚመለከተው ቃል ገባልኝ። አያይዞም አንተ ያልከው ሐሳብ በመጽሐፉ ላይ ከተገኘ የመጽሐፉ አዘጋጅ ቀጣፊ ነው ማለት ነው" አለኝ። በሚገባ ቀጣፊ እንጂ ብዬው እጄ ላይ ወደያዝኩትና ለዚህ ውይይት መነሻ ወደሆነን መጽሐፍ ተመልሶ ጠየቀኝ። እኔም መጽሐፉ ገና አሁን እጄ እንደገባና እንዳላነበብኩት ነግሬው ስለራሱ መጽሐፍ (የእሱ መጽሐፍ ከዘመን ቆጠራ ጋር የተያያዘ ሐሳብ ያለው ነው) ሲወራኝ መውረጃችን ደረሶ ተሰነባበትን።
ታሪክን የኋሊት

"አንድ ልበ ብሩህ ያበሻ ሰው መሬት ትዞራለች ብሎ ቢያስተምር አሁን በቅርቡ በሀረርጌ በዳኛ ተይዞ አልነበረምን? አሁን 19 መቶ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በኋላ አልፈን ሃያኛውን መቶ ዓመት ስንጀምር #አንድ_ሰው_የተዋሕዶን_ሃይማኖት_ቢነቅፍ_ካዲስ_አበባ_ገበያ_ላይ_በድንጋይ_አልተቀጠቀጠምን? እስከ ዛሬ ድረስሳ ወደሩቅ ሀገር ተሰደው ወይም ወደ አበሻችን ከሚመጡት ፈረንጆች ጥቂት ጥበብ ተምረው ያገራቸውን መንግሥት ሊጠቅሙ የሚፈልጉ #ወንድሞቻችን_ጵሮቴስታንት፣_ካቶሊክም_መናፍቃን_የሌላ_መንግሥት_ሰላዮች_እየተባሉ_ሲራቡ_ሲከሰሱ_እናይ_የለምን። የነዚያን መከረኞች ስም #ስንት_ብለን_እንቁጠር? የሚከተሉት ሁለቱ ሰዎች ስም ግን እንዲወሱ የግድ ነው። እነሱም ከንቲባ ገብሩና አለቃ ታዬ ናቸው" (ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች ገጽ 14-15)
"ባገራችን አንድ የድንቁርና ነገር አለ። ሃይማኖቱ ተዋሕዶ ያልሆነ ሰው ሁሉ እንደርኩስ ይቆጠራል። ይህም እጅግ ያስቃል። አእምሮ የሌለው ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ሳያውቅ የእግዚአብሔር ጠበቃ ሊሆን ይወዳል" (ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች ገጽ 28)።

https://t.me/tewoderosdemelash/1041
ተኣምረ ማርያም፤ ‹‹በሥዕሏም ፊት ስገዱ፤ ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ፤ ስም አጠራሩም አይታወቅ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ›› በማለት ሐሳቡን አስቀምጧል፡፡

ይሄን ምንባብ ተኣምረ ማርያም ላይ ብቻ ሳይሆን ግብረ ሕማማትም ላይ እናገኘዋለን፤ ‹‹በሥዕሏም ፊት ስገዱ፤ ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ፤ ስም አጠራሩም አይታወቅ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ››፡፡

ለሥዕሏ አለመስገድ ብቻ ሳይኾን ሥዕሏን አለማክበር ተግሣጽ የሚያስከትል መኾኑን ተኣምረ ማርያም ይተርካል፡፡ ‹‹የሮም ሰዎች፣ የግብጽም ሰዎች ሁሉ የአፍንጅም የእስክንድርያ፣ የሶርያም፣ የገላትያም ሰዎች›› የሚሰግዱበት ቦታ የነበረ አንድ የማርያም ነው ተብሎ የሚታመን ሥዕል ነበር፡፡

እነዚህ ሰዎች ወደዚህ ጸሎት ቤት ሲገቡ የእግራቸውን ጫማ ሳያወልቁ በመግባታቸው፤ ‹‹የእመቤታችን ልቡናዋ አዘነ ከኢትዮጵያም ለሔዱ ሰዎች በሥዕሏ ላይ አድራ ተገልጣ ተነጋገረቻቸው››፡፡ በንግግሯም እናንተ ኢትዮጵያውያን ዐሥራት ተደርጋችሁ ተሰጥታችሁኝ እያለ ‹‹ወደኔ ሥዕል ጫማ ተጫምታችሁ የምትገቡ መራራ ትምህርትና ክፉ ምግባር እንደ ምን አበቀላችሁ አለቻቸው››፡፡

ይሄን ምክር የሰሙት የኢትዮጵያ ሰዎች ከዚያች ቀን ጀምሮ ለሥዕሏ ክብር በመስጠት ‹‹… በትዕቢት አካሔድ በጫማ ወደዚች ሥዕል አልገቡም››፡፡ የኢትዮጵያ ሰዎች ብቻም ሳይኾኑ ‹‹ከእስክንድርያና ከሮም ከግብጽም ሰዎች ቢኾን ከዚያች ቀን ወዲህ በጫማ ኾኖ የገባ የለም››፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ለማርያም ሥዕል ክብር መስጠት በማርያም ዘንድ ዋጋ የሚያስገኝ፤ ክብር አለመስጠት ደግሞ እንደሚያስገስጽ ማሳየት ነው፡፡ ነገሩን ከዚህ ከፍ ስናደርገው፤ ‹‹ለእመቤታችን ሥዕል ስላለስገደ መናፍቅ ሞት›› በሚል ርዕስ ወደተጻፈው ጽሑፍ እንሄዳለን፡፡

በአባ ጽጌ ድንግል የተጻፈው ‹‹ማኅሌተ ጽጌ›› የተሰኘው መጽሐፍ ለሥዕለ ማርያም ለመስገድ አለመፍቀድ ሞት ያስከትላል የሚለውን እንደሚከተለው ይተርካል፤
እስክንድርያ አገር ቀልሞን በሚባል ቦታ በማርያም ስም የተሠራ ቤተ ክርስቲያን ነበር ብሎ ይጀምርና፤ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ያለው ሥዕል ብዙ ተኣምር ያደርግ ነበር፡፡ ከእነዚህ ተኣምራት መካከል አንዱን ሲያስነብብ የሚከተለውን ይላል፡፡

ሰሎሞን የሚባለው የገዳሙ አስተዳዳሪ ከአራት ሰዎች ጋር ሆኖ የማርያም ተብሎ ለሚታመነው ሥዕል ሲሰግድ አብረውት ከነበሩት አራት ሰዎች መካከል ሦስቱ ከእርሱ ጋር አብረው ሲሰግዱ አንደኛው ግን ‹‹የሰው እጅ ለሠራው እንዴት እሰግዳለሁ?›› በማለት ለመስገድ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡

ባለመስገዱ የተከተለውን ነገር መጽሐፉ እንዳስቀመጠው ላሰነብባችሁ፤
በዚያችም ሰዓት ምላሱ ተጎልጉሎ ከከንፈሮቹ አንድ ስንዝር ያህል ወጣ፡፡ ወደ ላይ ወደ ታች ወደ ቀኝና ወደ ግራ እያለ ጥርሶቹንም ያፋጭ ነበር፡፡ ያንጊዜም የገዳሙ አስተዳዳሪ እግዚአብሔርን ይለምንለት ጀመር እመቤታችንም ለገዳሙ አስተዳዳሪ አትጸልይለት በእኔና በልጄ ላይ ስድብን ፈጽሟልና ከልጄ የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል አለችው፡፡ ወዲያውኑ በክፉ ሞት ሞቷልና ወደ ሲኦልም ወርዷልና እፎ የሐዩ እመአምላክ እንኪያኪ ጸአለ የአምላክ እናት ማርያም ሆይ አንቺን የሰደበ እንዴት ይድናል? አለ፡፡

ለማርያም ነው ተብሎ ለሚታመነው ሥዕል ያልሰገደው ሰው አሟሟቱ አስፈሪ እንዲሆን የተፈለገበት ምክንያት ለሥዕሏ አለመስገድ ውጤቱ ምን ያህል ከባድ እንደኾነ በሰዎች አእምሮ ላይ መሳል ስለተፈለገ ነው፡፡ ይኼም ደግሞ ቀደም ሲል ከተመለከትነውና በተኣምረ ማርያም ላይ ከተጻፈው ጋር ተመጋጋቢ ነው፡፡ በተኣምሩ ላይ ‹‹ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ፤ ስም አጠራሩም አይታወቅ›› የሚል እርግማን ሲያስቀምጥ የተኣምረ ማርያም ማብራሪያ እንዲሆን በግጥም መልክ በተዘጋጀው በማኅሌተ ጽጌ ደግሞ በአስፈሪ መንገድ በሞት መቀጣቱን በመንገር ያጸናልናል፡፡ የሞት ፍርዱ ደግሞ የመጣው ከኢየሱስ ነው በሚል ኢየሱስም የዚህ ድርጊት ተሳታፊ እንደ ኾነ በማስመሰል ሰፍሯል፡፡

ያልሰገደው ሰው በሞት መቀጣት ብቻም ሳይኾን መጨረሻው ሲኦል መሆኑም ተጽፏል፡፡ በዚህም ማስተላለፍ የተፈለገው በምድር ብቻም ሳይኾን በሰማይም እድል ፈንታ የላችሁም የሚለውን ነው፡፡ አስገራሚው ነገር የጭንቅ አማላጅ እንደሆነች የሚትታመነዋ እና ‹‹ሠአሊተ ምሕረት›› እየተባለች የምትጠራዋ ማርያም ለሥዕሌ አልሰገደም በሚል መዓት እንዲመጣና በርግማን እንዲሞት የምታደርግ ከሆነ ምሕረትን የምትለምነው ለማን ነው?
እንዲሞት ያደረገችው ማርያም ሳትሆን ኢየሱስ ነው ከተባለ በመጀመሪያ ነጻ ፈቃዳችንን የማያከበርና ለሥዕል ባለመስገድ በጭካኔ የሚገድል ከሆነ እግዚአብሔር የለም ብለው የካዱትን በትእግስት ዝም ማለቱ ምነው? መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ምሕረቱ የበዛ›› ከሚለውስ ጋር በምን ይስማማል? አምላካችንስ እንዲህ ባሉ መናኛ ምክንያቶች ወደሲኦል የሚጠለን ጨካኝ አምላክ ሳይሆን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲመጡ ወዶ የሚታገስ የምሕረት አምላክ ነው (2ኛ ጴጥሮስ 3÷9)፡፡


https://t.me/tewoderosdemelash/1042
ርሷ አፈራችው ወይስ ርሱ ለማደሪያ አዘጋጃት?


ጌታችን ከማርያም መወለዱን መሠረት በማድረግ ከሚቀርቡት ሐሳቦች ውስጥ አንዱ እግዚአብሔር በፈቀደ ሳይኾን በእርሷ ኃይልና ችሎታ እንደ ወለደች የሚናገረው ነው፡፡ ይሄን ሐሳብ ቅዳሴ ማርያም በሚከተለው መንገድ ሐሳቡን ግልጽ ያደርግልናል፤ ‹‹ድንግል ሆይ የሚበላውን ያፈራሽልን የሚጠጣውንም ያስገኘሽልን…››፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ ጕልሕ ገጽ 203)፡፡ አንድምታው ይኼን ሐሳብ እንደሚከተለው አስቀምጦታል፤ ‹‹የሚበላውን ሥጋውን የሚጠጣውን ደሙን ያስገኘሽልን…›› (መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው ገጽ 253)፡፡ በዚህ ሐሳብ መሠረት የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ያስገኘችው ማርያም ናት እንጂ እርሱ ራሱ አይደለም፡፡

ድርሳነ ማርያምም የሚከተለውን ይዟል፤ ‹‹ፍጥረትን ሁሉ መግዛት የሚቻለውን ትወሰኚዋለሽ፡፡… የተቀደሰ ሥጋሽን ይዋሐዳል፤ እናመሰግንሽ ዘንድ እርሱን ለመወሰን ለአንቺ ተገባ›› (ድርሳነ ማርያም ገጽ 191)፡፡ በዚህ ጽሑፍ መሠረት ፍጥረትን የሚገዛውን እርሷ እንደምትወስነው ቀድሞ ይንገረንና ምስጋና የሚገባት መሆኑን በመጠቈም ምክንያቱ ደግሞ እርሱን በመወሰኗ መሆኑ ላይ ያጸናል፡፡

ወደ ውዳሴ ማርያም ስንሄድ ‹‹ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ ቃልን ወሰነችው›› የሚለውን እናገኛለን (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ)፡፡ መጋቤ ሐዲስ ድምፀ አንበርብር ለዚህ ምንባብ በሠሩት ትርጓሜ የሚከተለውን ጽፈዋል፤ ‹‹ሰማይና ምድር የአብ አካላዊ ቃልን ወሰነችው ይህ ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ ምን ይደንቅ ኦ ወዮ እንደምን ያለ ረቂቅ ነው ለዚህ አንክሮ ይገባል›› (ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ጸሎተ ሃይማኖትና አቡነ ዘበሰማያት ገጽ 118)፡፡ ሁሉን ቻዩን አምላክ የምትወስን አንዲት ሴት መገኘቷ በርግጥም የሚደንቅ ነው፡፡

ይኼን ሐሳብ የእንዚራ ስብሐት መጽሐፍ አዘጋጅ ከዚህ በታች በሰፈረው መልኩ ጽፎታል፤ ‹‹አስፈሪ የኾነ መለኮታዊ ግለትን /እሳትን/ የወሰነች ማኅፀንም አመሰግናለሁ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 2)፡፡

ይሄ ብቻ ሳይኾን ‹‹የሚናገር በግን ያፈራሽ ቦታ ሆይ በትከሻዬ ላይ ጥበበኛ የሚያደርግ የልቡና መንፈስን አሳድሪልኝ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 66)፡፡

የመጽሐፉ አዘጋጅ አስፈሪ የኾነውን መለኮታዊ እሳት ተሸክማ እንደነበረችና በጉን ያፈራችው እሷ እንደሆነች እየነገረን ይገኛል፡፡ የሚገርመው ግን በአንድ አቋም የመጽናት ችግር ስላለበት ቀደም ሲል የጻፈውን ትቶ ከዚህ በታች የተጻፈውን ደግሞ ጽፏል፤ ‹‹እንደ ርግብም የዋሕ ነሽ አብም ለአንድ ልጁ ማደሪያ አዘጋጀሽ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 67)፡፡ በዚህ ጽሑፍ መሠረት ለጌታችን ማደሪያ ትሆን ዘንድ ያዘጋጃት አብ ነው፡፡ ሐሳቡን ከዚህ ከፍ ስናደርገው ‹‹አስገራሚውን ነገርም የፈጠረው በማሕፀንሽ አደረ፤ እናቱም ሆንሽ፡፡… በቀላዩ መኖሪያም የሚያጸናው እርሱ በአንቺ አደረ ማደሪያውም ኾንሽ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 29)፡፡ በዚህ ጽሑፍ መሠረት ደግሞ በማሕፀኗ ያደረው እሱ እንደ ኾነ ይነግረናል፡፡

በዚህ ላይ አንድ ስንጨምር ምንም እንኳ ቅድመ ኹኔታ ለማስቀመጥ የሚዳዳ ቢኾንም እርሷ ወሰነችው የሚለውን እያፈረሰ የሚከተለውን ይዟል፤ ‹‹ንጽሕናሽን ደም ግባትሽን ደስ ባሰኘው ጊዜ አምላክ ከአንቺ ሰው ሊሆን ወድዶ በማሕፀንሽ ሰው መሆንን አፈጠነ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 137)፡፡ በዚህ ጽሑፍ መሠረት ደግሞ ምንም እንኳ ንጽሕናሽን ወድዶ የሚል ማግባቢያ ቢያስቀምጥም በእርሷ ሰው መሆን የፈቀደው እሱ እንጂ እሷ አይደለችም፡፡

በዚህም ደግሞ በአንድ ጉዳይ ላይ ወጥ የሆነ ትምህርት የሌለ መሆኑን ለመመለከት እንችላለን፡፡ ከዚህም አለፍ ስንል ማርያም ‹‹ወሰነችው››፣ ‹‹አፈራችልን››፣ ‹‹አሰገኘችልን›› የሚለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የራቀና የጌታችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ እንደዚህ ካለው ትምህርት መራቅ ከእውነተኛ ክርስቲያኖች ይጠበቃል፡፡


https://t.me/tewoderosdemelash/1043
ስንቶቹን ታውቋቸዋላችሁ?


ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥ ጭላት፥ ጭልፊት በየወገኑ፥ ቁራ ሁሉ በየወገኑ፥ ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየወገኑ፥ ጕጕት፥ እርኩም፥ ጋጋኖ፥ የውኀ ዶሮ፥ ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞራ፥ ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጁላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ - ዘሌዋውያን 11÷14_19።
ይሄ የወንድሜ የመሐመድ አበባው ሦስተኛው መጽሐፉ ነው።

ለማሳተም እናግዘው 🙏🙏🙏
የእንዚራ ስብሐት ነገረ ድኅነት
ሰዎቻችን በቤተ ክርስቲያን ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ አዳኝ የለም የሚል ውሸት ይዋሻሉ፡፡ ይኼን ውሸታቸውን ግን መጻሕፍቶቻቸውን ገልበጥ ገልበጥ ያደረገ ሰው ሳይቸገር ያገኘዋል፡፡
ድኅነት በፍጡር በኩል እንደሚገኝ በማስመሰል አጉል ተስፋ ከሚሰጡት መጻሕፍት መካከል አንዱ እንዚራ ስብሐት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በተከታታይ ይኼን ለማሳየት ጥረት አደርጋለኹ፡፡ ለዛሬ ወደ ብሉይ ኪዳን በመሄድ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ሰዎች የዳኑት በማርያም በኩል እንደኾነ የሚናገሩትን ክፍሎች እንመለከታለን፡፡

አዳም

እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን መልካም አድርጎ ከፈጠረ በኋላ ሰውን በመልካሚቱ ስፍራ በገነት ሲያኖረው ከአንዲት ትእዛዝ በቀር ምንም ሸክም አይጠበቅበትም ነበር፡፡ አዳም ግን ያንን አንድ ትአዛዝ ለመጠበቅ ስላልቻለ ከመልካሚቱ ስፍራ ከገነት ወጣ፡፡
አዳም ወደ ገነት ተመልሶ እንዴት ገባ? የሚለውን ጥያቄ ለእንዚራ ስብሐት መጽሐፍ አዘጋጆች ብትጠይቋቸው በሁለት ዓይነት መንገድ ይመልሳሉ፡፡ የመጀመሪያው ቀጣዩን ይመስላል፤

"በመጀመሪያ የገነት በር በሔዋን በደል ምክንያት ተዘጋ፡፡ በመሸ ጊዜም በአንቺ ጽድቅ በአንቺ ተከፈተ፡፡ በሰይጣን ጦር የቆሰለውም የድኅነት መድኀኒትን በአንቺ ተሰጠ፡፡ በኃጢአት የሞተውም በአንቺ ጽድቅ ዳነ" - እንዚራ ስብሐት ገጽ 127፡፡

በዚህ ምንባብ መሠረት በገነት የተዘጋው የገነት በር በማርያም ጽድቅ ተከፈተ፡፡ በመጀመሪያ ሔዋንንና ማርያምን ማነጻጸር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልኾነና በሐዋርያት ዘመን ያልነበረ በኋላ ዘመን ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን አሾልከው ያስገቡት እንግዳ ትምህርት ነው፡፡ የውዳሴ ማርያም አንድምታ እና ተኣምረ ማርያም ይኼ ትምህርት የተጀመረው በሶርያዊው ሊቅ በቅዱስ ኤፍሬም ነው ሲሉ፤ ‹‹የብርሃን እናት›› መጽሐፍ አዘጋጅ ግን በዚህ ሐሳብ አይስማሙም፤ ሰማዕቱ ዮስጦስ ነው የሚለውን እንደሚከተለው ጽፈዋልና፤ ‹‹ለመጀመሪያ ጊዜ ሔዋንና ማርያምን በማነጻጸር ውድቀታችንን ከመዳናችን ጋር አስተያይቶ የጻፈው ሰማዕቱ ዮስጦስ…›› ነው፡፡ የዚህ ትምህርት ጀማሪ ማንም ይሁን ማን በኋላ ዘመን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ እንጂ ሐዋርያዊ አይደለም፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ነው ያስተማረው፤ ‹‹ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ኾኖአልና። ኹሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ኹሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና›› (1ኛ ቆሮንቶስ 15÷21-22)። ከዚህም የምንረዳው በሴት የመጣ ሞት በሴት ድል ተመታ የሚለው አባባል የሰው ብቻ ትምህርት እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡

ሰዎቻችን ይሄን ምንባብ ትክክል ነው ለማለት የሚያነሡት ሐሳብ ከማርያም መወለዱን ለማሳየት ነው በሚል ነው፡፡ ምንባቡ የሚናገረው ከአንቺ በመወለዱ ሳይኾን ‹‹በአንቺ ጽድቅ በአንቺ ተከፈተ›› ነው፡፡ ይሄም ደግሞ ገነት የተከፈተው በኢየሱስ ሳይኾን በማርያም ጽድቅ ነው የሚለው፡፡ ይሄ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው እንግዳ ትምህርት ነው፡፡

ከዚህም ሌላ ምንባቡ የሚከተለውን ይላል፤ ‹‹በሰይጣን ጦር የቆሰለውም የድኅነት መድኀኒትን በአንቺ ተሰጠ›› በዚህ ምንባብ ደግሞ የድኅነት መድኀኒት በእርሷ የተሰጠ በማስመሰል ቀርቧል፡፡ አንባቢው ልብ እንዲልልን የምፈልገው መድኀኒቱ ከእርሷ ተወለደ አላለም፡፡ ይልቁንስ እርሷ ራሷ መድኀኒት እንደኾነች በማስመሰል ‹‹በአንቺ›› በማለት ነው የተቀመጠው፡፡

ነገሩ በዚህ ቢያበቃ መልካም ነበር፤ በቀጣይ ደግሞ እንደዚህ ይላል፤ ‹‹በኃጢአት የሞተውም በአንቺ ጽድቅ ዳነ››፡፡ በዚህ ሐሳብ ደግሞ በኃጢአት ምክንያት የሞተውም በእርሷ ጽድቅ እንደሚድን የተገለጸው ማርያም አዳኝ ተደርጋ የተሳለች መኾኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ...

https://t.me/tewoderosdemelash/1047
ለማሳተም አግዙን
ከዚህ በፊት በነበረን ጸሑፍ አዳም ወደ ገነት ተመልሶ እንዴት ገባ? የሚለውን የመጀመሪያ ነጥብ ተመልክተን ነበር፡፡ ዛሬም ከዚህ ሐሳብ ሳንርቅ የእንዚራ ስብሐት መጽሐፍ አዘጋጆች የሚከተለውን ጽፈዋል፤ ‹‹የዓለሙ አባት /አዳም/ በአንቺ የተድላ ቦታ ገነትን ወረሰ›› (ገጽ 42-43)፡፡
በዚህ ጽሑፍ መሠረት የሁሉ አባት አዳም በበደለው በደል ምክንያት ከወጣበት ገነት ተመልሶ የገባው በማርያም ነው የሚል ሐሳብ ነው የምናገኘው፡፡ ለዚህ የሚረዳ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምንባብ የሌለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የክርስቶስን ሞት ከንቱ የሚያደርግ ሐሳብ ነው፡፡
የክርስቶስን ሞት ከንቱ የሚያደርገው አዳም ይቅርታን ያገኘውና ከእግዚአብር ጋር የታረቀው ጌታ ኢየሱስ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱና በመስቀል ሞት በመሞቱ ምክንያት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደም ሳይፈስ ስርየት እንደሌለ አስረግጦ ይናገራል (ዕብራውያን 9÷22)፡፡ ደሙን ያፈሰሰው ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ብቻ በመሆኑ ስርየት ያገኘው በእርሱ ሞት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አዳም በማርያም ወደ ገነት ገባ የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው ከሰዎች ልብ የወጣ ትምህርት ነው ማለት ነው፡፡


https://t.me/tewoderosdemelash/1049
የራሷን መቀመጫ ያላየችው ዝንጀሮ በሌሎቹ እንደ ተሣለቀችው÷ ከሳሻችንም በቤቱ ያለውን ሳይመለከት ወደ ሰው ቤት ዐይኑን ያማተረው ሰው÷ ‹‹ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ግን ይህን አውግስጢኖሳዊ ወለድ የኾነ ሉተራዊና ካልቪናዊ አስተምህሮ በፍጹም አትቀበልም›› በማለት ራሱን አዋድዶና ወደ ሌላው ጣቱን ጠቍሞ የሚከተለውን ይላል፤

በካልቪን አስተምህሮ መሠረት ሰው ነጻ ፈቃድ ስለሌለውና ውሳኔውና ድርጊቱ ለመዳኑ አንዳችም ሚና ስለሌለው÷ ሕገ ወጥነትንና ሥርዐት አልበኛነትን የማበረታታት ዐቅም ነበረው። ምክንያቱም ሰው መልካምም አደረገ ክፉም አደረገ ውጤቱ ያው አስቀድሞ የተወሰነበ(ለ)ት ከኾነ÷ ለምን ከኀጢአት ጋራ ይጋደላል? ለምን ከክፋት ይርቃል? መልካም ለማድረግስ ለምን ያተጋዋል?
በዚህ በከሳሻችን ጽሑፍ መሠረት÷ የቅድመ ውሳኔን ትምህርት የሚያስተምሩ ሰዎች ሕገ ወጥነትንና ሥርዐት አልበኛነትን የሚያበረታቱ ናቸው። በዚህም የተነሣ ከክፋት ለመራቅና መልካም ለማድረግ የሚበረታታበት ምክንያት የለም። ምክንያቱም ‹‹መልካምም አደረገ ክፉም አደረገ ውጤቱ ያው አስቀድሞ…›› ተወስኖበታልና ይላል።

ከሳሹ ወደ ሌሎች ጣቱን ጠቍሞ በከሰሰበት በዚህ ክስ÷ ርሱም ኾነ የሚመራው ተቋም የሚከሰሱ መኾናቸውን ዘንግቶታል። ምክንያቱም በመጻሕፍታቸው ከዚህ በታች ያሉትን ሐሳቦች እናገኛለንና፤

ከመጽሐፉ የተወሰደ

🕯💡🕯💡🕯💡🕯

ይሄን መጽሐፍ በማሳተም አግዙን