ትዕዛዝ ቢጤ ለወንድሞች
》ከፍቅር አጋርህ ጋር ያለህ ቅርርብ መልካም እንዲሆን እነዚህን የፍቅር ዘዴ ለአጋርክ አሳይ!!
1: እንድትለወጥ በምትነግራት ጊዜ ሁሉ የምትጠቀምባቸውን ቃላት ለስለስና ይቅር ባይነት የሞላባቸው መሆናቸውን አረጋግጥ::
°°° እጮኛህ ቁጣ በተሞላባቸው ቃላት ከጮህክባት አትለወጥም:: "እጮኛዬ አይወደኝም::" በማለት ራሷን ታሳምናለች:: እንዴት ልትለወጥ እንደምትችልና የተሻለች የፍቅር አጋር እንደምትሆን ልታስብ አትፈልግም:: በዛ ፈንታ ታለቅሳለች ወይም መልሳ ትጮህብሀለች::
》ቃሎችህ ለስለስና ይቅር ባይነት የሞላባቸው ከሆኑ ግን ፍቅርህ ይሰማታልና ለመለወጥ ዝግጁ ትሆናለች::
" የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች ሸካራ ቃል ግን ቍጣን ታስነሣለች። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 15:1)
2: ለመናገር ቁጣህ እስኪበርድ ጠብቅ::
ለምሳሌ የሆነ ነገር ተነጋግራቹ በተባባላቹበት ጊዜ አላከናወነችውም እንበል:: ወዲያው ስለሁኔታው እንደሰማክ አትናገራት:: እንዴት መለወጥ እንዳለባት ልትነግራት ይህ ጥሩ ጊዜ አይደለም:: ቁጣህ እስኪበርድ ድረስ ጠብቅ ተቆጥተህ እያለህ ብትናገር ቃሎችህ ለስላሳና ይቅርታን የተሞሉ ሊሆኑ አይችሉም::
3: በምትናገርበት ጊዜ "አንቺ" እንዲህ አደረግሽ ወዘተ... ከማለት "ይሰማኛል" በል::
》ቀጥሎ በዚህ መንገድ እንዴት እንደምትናገር የሚያሳይ ምሳሌዎች ተጠቀም::
》 "በተቀጣጠርንበት ቦታ በጊዜ አትገኚም(ትቀርያለሽ) ምክንያቱም ትዝ አልልሽም::" ከማለት ይልቅ በመጀመርያ አንተ ራስህ ቀጠሮ አክባሪ ሁን ከዛ " በተቀጣጠርንበት ቦታ በጊዜ ስትገኚ ለእኔ ያለሽ ፍቅር እና ክብር ትልቅ እንደሆነ ይሰማኛል::" ብትል መልካም ነው::
》 "እኔን ስታናግሪ ትህትና የለሽም ምክንያቱም አስተዳደግሽ ልክ ያልሆነ ጋጠወጥ እና ባለጌ ነሽ:: "አትበል ይህ ነቀፋ ነው:: ይህ ይጎዳታል እንጂ እንድትለወጥ አያደርጋትም:: በዚህ ምትክ " ረጋ ብለሽ ስታወሪኝ እና ነገሮችን ሰከን ባለ መንገድ ስታስረጂኝ እጅግ እንደምታፈቅሪኝ እና ለእኔ ያለሽን መልካም ስሜት የሚያሳይ ይመስለኛል::" ብትል እጅግ የተሻለ ነው::
ጌታ ዘመናቹን ይባርክ!!!
ፍቅራቹ ያለገደብ ይባረክ!!
✅ ይቀላቀሉን ⤵️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
[ https://t.me/sozo_purity ]

👍28❤25
ከእንቅልፋችን እንንቃ
" ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" (ሮሜ 13:11 )
》ከእንቅልፍ እንንቃ ሲባል ባጭሩ እንቅልፍ አራት ደረጃዎች እንዳሉት ሳይንሳዊ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር በማየት የኛን ሁኔታ ስንመለከት:-
ደረጃ_1: አይን መጨፈን የሚጀመርበት
》ንቁ ሆነን ስናከናውናቸው የነበሩ ነገሮችን ማከናወን የምናቆምበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ጊዜ በቀላሉ ለመንቃት የሚቻልበት ደረጃ የመሆኑን ያህል በፍጥነት ወደ ቀጣዩ እንቅልፍ ደረጃ የሚታለፍበት በመሆኑ ብዙ በዚህ ደረጃ የመቆየት እድል የለውም፡፡ ይህን ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር ስናየው በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ አማኝ ቀደም ሲል በንቃት የሚጸልየውን ጸሎት በፍቅር ለእግዚአብሄር የሚያቀርበውን አምልኮ እንዲሁም በመሰጠት ያነበው የነበረውን የእግዚአብሄር ቃል ለማንበብ ሃይል የሚያጣበት እና በሃጢያት ላይ ማመቻመች የሚጀምርበት ደረጃ ነው፡፡ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?( ገላ.3፡1 )
ደረጃ_2: ቀላል እንቅልፍ
》 በዚህ ደረጃ አይንን ከመጨፈን ባለፈ ወደ ቀላል እንቅልፍ የሚገባበት ደረጃ ሲሆን በዚህም የልብ ምት እና ሰውነት ሙቀት የሚቀንስበት ወቅት ሲሆን በዚህም ሰውነታችን ወደ ጥልቅ እንቅልፍ ለመግባት ዝግጅት የሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ልባችን ለክርስቶስ የነበረውን መቃጠል (ፍቅር) የሚያጣበት እና ያለን መንፈሳዊ መነቃቃት የሚቀዘቅዝበት ደረጃ ነው፡፡ …የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና። እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፡፡ (ራእ.2፡4-5)
ደረጃ_3_እና_4: ከባድ እንቅልፍ
》 በዚህ ወቅት ሰውነታችን ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ የሚገባበት በመሆኑ በዙሪችን እየተከናወኑ ያሉ ነገሮችን ማስተዋል አንችልም፡፡ ንቁ በሆንበት ጊዜ የሚታዘዙን ጡንቻዎቻችን ፓራላይዝድ የሚሆኑበት የእንቅልፍ ደረጃ ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ከመንፈሳዊ አለም ያለን ቁርኝት የሚቋረጥበት እና ለመንፈሳዊ ነገር ባዳ የምንሆንበት ይልቁንም ስንጸየፋቸው የነበሩ አለማዊ ልምምዶች ምንም እንዳለሆኑ ተቆጥረው በቤተ ክርስቲያን ስፍራ የሚይዙበት ፣ ከአለም ጋር መዳቀልና መቀላቀል የተለመደ የሚሆንበት ደረጃ ነው፡፡ ወገኞች ሆይ በየትኛውም የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ እንገኝ ያው እንቅልፍ ላይ በመሆናችን እንንቃ እንመለስ! ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ (ሮሜ.13፡11)
✍ አገልጋይ Alex
መልካም ምሽት!

👍25❤10
ለፍቅር ያሰብኩት የቸርች ሰው ጎዳኝ
》ሰላም ቤተሰቦቼ ዛሬ ይዤ የመጣሁት ርዕስ ከብዙ ክርስቲያን እህቶች እና ወንድሞች በተደጋጋሚ የሚደርሰኝ ጥያቄ ነው። ትንሽ ለማመን ቢከብድም ብዙ ክርስቲያን ወጣቶች ልባቸው የሚጎዳው አብሯቸው ከሚያመልኩ ወጣት አቻቸው ጋር ሊጀምሩ ባሰቡት የፍቅር ግንኙነት ነው። የፍቅር ጥያቄ አቅርበው እምቢ የሚባሉ እንዳሉ ሆነው እሺ ተብለው የፍቅር ግንኙነት የጀመሩ ወጣቶች በጣም በሚገርም ሁኔታ በማማረር እና በከባድ ፈተና ያሳልፋሉ።[ሁሉም ባይሆኑ አብዛኛዎቹ ማለት ነው]
》አንድ አመት ሙሉ እጮኛሽ ነኝ ብሎ አብሯት ቆይቶ ስለ ሰርግ እና አንዳንድ ነገሮች ማውራት እና ማቀድ ከጀመሩ በኋላ ግንገት በነጋታው "ግንኙነታችን እዚህ ጋር ይብቃ" ብሎ ጥሏት የሚሄድ ሰው ቸርች ውስጥ አለ።[ሁሉም እንዲህ አይነት ባህርይ አላቸው እያልኩ አይደለም።]
》ሌላው በጣም ያስተዋልኩት ነገር ከየቸርቹ[ሙሉወንጌል፣ቃለህይወት፣ህይወት ብርሀን፣መሰረተክርስቶስ. . .] አንዳንድ ወንድ ይዛ/ይዞ ፍቅረኛዬ ነው የሚል ሰው ቸርች ውስጥ አለ።[ይታያችሁ ይህ ሰው የአንድነት ፕሮግራም ሊያዘጋጅ ነው ወይስ ትዳር ሊመሰርት?]
》ምን እያልኩ እንደሆነ በዚህ ምክንያት የተጎዳችሁ በደንብ ይገባችኋል ብዬ አስባለሁ። እና በቸርች ልጅ ተጎዳችሁ ማለት ሁሉም የቸርች ልጅ እንደዛ መጥፎ ይሆናል ማለት አይደለም። ስለዚህ ለምን ከዚህ ሁሉ አንደኛዬን ክርስቲያን ካልሆነ ሰው ጋር ግንኙነት አልጀምርም እነሱ እንደሆኑ እንክብካቤውን እና ማፍቀሩን ተክነውበታል የሚል አቋም ላይ ከመድረሳችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁን ነገር ልነግራችሁ እወዳለሁ።
1. ትክክል አይደለም በሉ
》በምታመልኩበት ቸርች ውስጥ የተጎዳችሁ እናንተ ብቻ አይደላችሁም ልክ እንደ እናንተ በተመሳሳይ ሁኔታ ብሎም በተመሳሳይ ሰው የሚጎዱ እንደሚኖሩ አትርሱ። ስለዚህ ዝም ማለቱ አማራጭ ስለማይሆን ስለጉዳዩ በደንብ ብትጮኹ መልካም ነው ወይም ለምታምኑት ወጣት መሪዎች በዚህ ጉዳይ ግንዛቤ እንዲሰጡ፣ ሆን ብለው ከግንኙነት ወደ ግንኙነት የሚዘሉ ወጣቶችን ቸርች እንድታስጠነቅቅ እና ይዛ እንድትመክራቸው አሳውቁ። [ይህ ሀሳቤ ይቀልዳል እንዴ ሊያስብል ይችላል። ግን እመኑኝ ሞክሩት አውቃለው አንዳንድ ቦታ ወጣት መሪዎች ናቸው ጎጂዎቹ።]
2. ምሬታችሁን ለጌታ አሳውቁ
》መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት በቆዩበት ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን የላከላቸው እንዴት ይመስላችኋል? በምሬት ወደ እግዚአብሔር መጮኸ ሲጀምሩ ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ በቁጥቋጦው ውስጥ ተገልጦ "የህዝቤን ጩኸት ሰምቻለው" ነበር ያለው። ስለዚህ ተጎድታችሁ ዝም ማለቱ ተገቢ አይደለምና ምሬታችሁን ለእግዚአብሔር አሰሙ።[እንደሰው ስላልሆነ ባልጠበቃችሁት መንገድ ያክማችኋል።]
》ደግሞ ሰይጣን በበቀል እንድትነሱ እና ሰው እንድትጎዱ ሊያሳስባችሁ ይችላል። ይህን ጊዜ በቀል የእናንተ ሳይሆን የእግዚአብሔር እንደሆነ አውቃችሁ ለእርሱ አሳልፋችሁ መስጠት መልካም ነው።
3. ብቁ ማንነት አትጠብቁ
》ቀጥሎ ወደ ህይወታችሁ የሚመጣው ሰው መልዐክ እንዲሆን አትጠብቁ። ሰው ነው እና አንዳንድ ጉድለቶች ይኖሩታል። አንዳንዴ ታዲያ ይህን ጉድለቱን ስታዪ ሊጎዳኝ ነው የመጣው እያልሽ መጥፎ ሀሳብ ወደ ውስጥሽ ካስተናገድሽ በጣም ልትጎጂ ትችያለሽ። ስለዚህ በጎ በሆነ አመለካከት ራሳችሁን አስታጥቁ።

👍35❤17👎1
📖በእግዚአብሔር ወይስ በሰው እንታመን?
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።
በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።
በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።
በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል። " - ኤር17፥5-8

❤27👍20
ኢየሱስ-አዳኝ!
“ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” — ማቴዎስ 1፥21

❤8👍3
በወጣቶች የሚነሱ ጥያቄዎች-1.pdf
4.9 MB
በወጣቶች የሚነሱ ጥያቄዎች
በሚል እርስ ብሩስ እና ካሮል ብሪትን ተፅፎ በአለማየሁ ማሞ የተተረጎመው መፀሀፍ በወጣቶች ተዘውትረው የሚነሱ ርዕሶችን ስለትዳር ፣ ስለትጭጭት(ፍቅር) ፣ ቅድመ-ጋብቻ ግብረ-ስጋ ግኑኝነት ፣ እንዲሁም የብዙ ወጣቶች ጥያቄዎችና ከክርትያናዊ መልሶቻቸው ጋር ይዞ ቀርቧል ፣ ትማሩበታላችሁ። አንቡት!
✅ ይቀላቀሉን ⤵️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
[ https://t.me/sozo_purity ]
በሚል እርስ ብሩስ እና ካሮል ብሪትን ተፅፎ በአለማየሁ ማሞ የተተረጎመው መፀሀፍ በወጣቶች ተዘውትረው የሚነሱ ርዕሶችን ስለትዳር ፣ ስለትጭጭት(ፍቅር) ፣ ቅድመ-ጋብቻ ግብረ-ስጋ ግኑኝነት ፣ እንዲሁም የብዙ ወጣቶች ጥያቄዎችና ከክርትያናዊ መልሶቻቸው ጋር ይዞ ቀርቧል ፣ ትማሩበታላችሁ። አንቡት!
✅ ይቀላቀሉን ⤵️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
[ https://t.me/sozo_purity ]
👍33❤14🔥1
የተወደዳችሁ
💡 ዛሬን እየኖሩበት ነው?
--> ትናንት ላትመለስ ነጉዳለች:: አመኑም አላመኑም ትናንት ከዛሬ በፊት ከነበሩ ሺህ አመታት ተርታ ተሰልፋለች:: አዎ ታሪክ ሆናለች!! አይጠራጠሩ ይህን ፅሑፍ ያነበቡበት ጥቂት ሴከንዶች እንኳን ከትናንት ጋር ተመድበዋል::አዎ ታሪክ ሆነዋል!!
* ያስተውሉ !!!
ከታሪክ ትምህርት ብቻ ነው የሚወሰደው::
---> ታዲያ ለምን በትናንት ታሪክ ዛሬን ይኖራሉ?
---> ለምን ተመሳሳይ ታሪክ ይደግማሉ?
* ከኖሩ አይቀር አዲስ ታሪክ ለትናንት ያስረክቡ !! አሮጌ ታሪክ ለነገ ከማቆየት የተሻለ ነውና::
⏰🕰 ዛሬ ወደ ህይወት ግባችሁ እንዳትደርሱ ካሰራቹ የማይታይ ሰንሰለት እራሳቹን ነፃ የምታወጡበት ነው::
⏰🕰 ዛሬ ለራሳቹ ከሰጣቹት የውሸት ማንነት ወጥታቹ ኦርጂናል ማንነትዎን የሚገናኙበት ድልድይ ነው::
⏰🕰 ዛሬ ከምቾት ክልላችሁ ወጥታቹ አለምን በተለየ እይታ የምትመለከቱባት መነፅር ናት::
⏰🕰 ዛሬ አንድ የተለየ ነገር የሚያገኙባት የህይወት ቤተ-ሙከራ ናት::
** ፈፅመው እወድቃለው ብለው አይስጉ!!
* መውደቅ ሊያስፈራ የሚችለው መነሳት ባይኖር ነበር::
💪💪 አይዞን!!!
💪💪 አይፍሩ!!
💪💪 አይደንግጡ!!
🧔[ወንድማችሁ ነኝ]🧔
#ሼር
⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgnjWczaPdu0FwA
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🚀🚀 @sozo_purity
🚻🚻 @sozo_family

👍16❤12
ደስታን ፍለጋ
በግምት ወደ 50 ሰው የሚይዝ ህብረት በአንድ አዳራሽ ለጥብቅ ጉዳይ ይሰባሰባሉ::ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት መድረክ መሪው ታዳሚዎችን አንድ ጫወታ ሊያጫውት ይወስናል::በአዳራሹ ለተሰበሰቡ ሰዎች አንዳንድ ፊኛ ሰጥቷቸው ስማቸውን በእስክሪብቶ ፊኛው ላይ እንዲፅፉበት ያዛቸዋል:: ሁሉም ፅፈው ከጨረሱ በሁዋላ ፊኛው ተሰብስቦ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ተበታትኖ እንዲቀመጥ ያደርጋል::
በመቀጠል ጫወታው በ5 ደቂቃ ጠባቧ ክፍል ውስጥ ተበታትኖ ከተቀመጠው ፊኛ እያንዳንዳቸው ስማቸው የተፃፈበትን ፊኛ አግኝቶ መመለስ ነው ተባለ::በቅፅበት ያቺ ክፍል ስማቸውን በሚፈልጉ ታዳሚዎች ትርምስምስዋ ወጣ::ነገር ግን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ትዕዛዙን ተግብሮ ስሙን ያገኘ አንድ እንኳን አልነበረም::የጫወታው አስተባባሪም ከመድረክ ወጥቶ 1 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሀምሳዎቹም ፊኛቸው ስማቸውን እየጠራ መለሰ::
ደስታም እንዲህ ናት::በዚህች ጠባብ እና በማይሞላላት አለም ትውልድ ከሌላው ይልቅ የራሱን ደስታ ፍለጋ ይተራመሳል!!
ነገር የደስታን መገኛ በቅጡ አላወቀም::
አትጠራጠሩ በክፍሉ ውስጥ መጀመርያ ያገኙትን ፊኛ ለስሙ ባለቤት እየጠሩ ቢሰጣጡ ልክ እንደመድረኩ 1 ደቂቃ አይፈጅባቸውም ነበር::
ስለዚህ የእርሶን ደስታ ማግኘት ይሻሉ ??
የሌላ ሰው ደስታ በእጅዎ ነውና ይመልሱ ያን ጊዜ የእርሶ የሆነ ነገር ወደ እጅዎ ለመግባ ጊዜ አይፈጅም!!!
. ⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgnjWczaPdu0FwA
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🚀🚀 @sozo_purity 🚻🚻 @sozo_family

❤15👍12
ምን አይነት ወንድ ለመሆን ታስባለክ?
》እግዚአብሔር ለአብርሀምም የወደፊት ህይወቱን በተለያየ መንገድ ሲገልፅለትና ሲያሳየው ነበር:: ከምንም በላይ አብርሀም ሁሉን ነገር ትቶ እግዚአብሔር ወደተናገረው ስፍራ ጨርቄን ማቄን ሳይል ወቷል::
》እግዚአብሔር በህይወትህ ይሆናል የሚልክ ነገር ልክ እንደ አብርሀም ቢዘገይብህ ምን አይነት አባት የምትሆን ይመስልሀል?
》አብርሀም ከአምላኩ ጋር እለት እለት ይነጋገር እና ይፀልይ ነበር:: በዚህ ፀሎት ስፍራው ከእግዚአብሔር ጋር የማይቋረጥ ህብረት ያደርግ ነበር:: ከእግዚአብሔር ብዙ ትዕዛዝ ተቀብሏል:: እግዚአብሔር የሚስቱን ስም የአብርሀምን ስም ቀይሯል በአጠቃላይ ቤተሰቡን ከመሀንነት እና ፍሬ ከሌለው ማንነት አንስቶ ለብዙዎች አባትና ፍሬያማ አድርጓቸዋል::
ወደፊት ምን አይነት አባት መሆን ትፈልጋለህ?
》ይስሀቅም እንደ አባቱ አብርሀም የፀሎት ህይወት ነበረው:: እለት እለት ከእግዜአብሔር ትዕዛዝን ይቀበል ነበር::በዛ የፀሎት ስፍራ አምላክ ይስሀቅን እና ቤተሰቡን ጎብኝቷል::
》ይስሀቅ ታጋሽ ነበር:: ልጅ ለመውለድ ዘግይታ ለነበረችው ሚስቱ ከምንም በላይ ክብርና ትልቅ ፍቅር ነበረው:: አንዳች መጥፎ ነገር አልተናገራትም:: ከሌላ ሰው እንድትወልድ አልመከራትም:: አላንቋሸሻትም:: አልፈታትም:: ነገር ግን በእግዜአብሔር ቃል ላይ ታምኖ በፅናት ይጠብቅ ነበር::
እግዜአብሔር የሰጣችሁ ተስፋ ሲዘገይ ምን ታደርጋላችሁ?
》ይስሀቅ አብዝቶ ወደ እግዚአብሔር ይቀርብ ነበር::

❤11👍11
" ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" (ሮሜ 13:11 )
》ከእንቅልፍ እንንቃ ሲባል ባጭሩ እንቅልፍ አራት ደረጃዎች እንዳሉት ሳይንሳዊ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር በማየት የኛን ሁኔታ ስንመለከት:-
ደረጃ_1: አይን መጨፈን የሚጀመርበት
》ንቁ ሆነን ስናከናውናቸው የነበሩ ነገሮችን ማከናወን የምናቆምበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ጊዜ በቀላሉ ለመንቃት የሚቻልበት ደረጃ የመሆኑን ያህል በፍጥነት ወደ ቀጣዩ እንቅልፍ ደረጃ የሚታለፍበት በመሆኑ ብዙ በዚህ ደረጃ የመቆየት እድል የለውም፡፡ ይህን ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር ስናየው በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ አማኝ ቀደም ሲል በንቃት የሚጸልየውን ጸሎት በፍቅር ለእግዚአብሄር የሚያቀርበውን አምልኮ እንዲሁም በመሰጠት ያነበው የነበረውን የእግዚአብሄር ቃል ለማንበብ ሃይል የሚያጣበት እና በሃጢያት ላይ ማመቻመች የሚጀምርበት ደረጃ ነው፡፡ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?( ገላ.3፡1 )
ደረጃ_2: ቀላል እንቅልፍ
》 በዚህ ደረጃ አይንን ከመጨፈን ባለፈ ወደ ቀላል እንቅልፍ የሚገባበት ደረጃ ሲሆን በዚህም የልብ ምት እና ሰውነት ሙቀት የሚቀንስበት ወቅት ሲሆን በዚህም ሰውነታችን ወደ ጥልቅ እንቅልፍ ለመግባት ዝግጅት የሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ልባችን ለክርስቶስ የነበረውን መቃጠል (ፍቅር) የሚያጣበት እና ያለን መንፈሳዊ መነቃቃት የሚቀዘቅዝበት ደረጃ ነው፡፡ …የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና። እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፡፡ (ራእ.2፡4-5)
ደረጃ_3_እና_4: ከባድ እንቅልፍ
》 በዚህ ወቅት ሰውነታችን ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ የሚገባበት በመሆኑ በዙሪችን እየተከናወኑ ያሉ ነገሮችን ማስተዋል አንችልም፡፡ ንቁ በሆንበት ጊዜ የሚታዘዙን ጡንቻዎቻችን ፓራላይዝድ የሚሆኑበት የእንቅልፍ ደረጃ ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ከመንፈሳዊ አለም ያለን ቁርኝት የሚቋረጥበት እና ለመንፈሳዊ ነገር ባዳ የምንሆንበት ይልቁንም ስንጸየፋቸው የነበሩ አለማዊ ልምምዶች ምንም እንዳለሆኑ ተቆጥረው በቤተ ክርስቲያን ስፍራ የሚይዙበት ፣ ከአለም ጋር መዳቀልና መቀላቀል የተለመደ የሚሆንበት ደረጃ ነው፡፡ ወገኞች ሆይ በየትኛውም የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ እንገኝ ያው እንቅልፍ ላይ በመሆናችን እንንቃ እንመለስ! ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ (ሮሜ.13፡11)
. ⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgnjWczaPdu0FwA
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🚀🚀 @sozo_purity 🚻🚻 @sozo_family
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍18❤9
ቅዳሜ አመሻሽ ላይ ነው ድብርቴ ከሌላው ቀን ይልቅ እጅጉን ልቋል:: ከጊቢያችን ውስጥ ከዋናው መኖርያ ራቅ ብላ በምትገኘው ክፍሌ ከቴሌቪዥናችን ፊትለፊት ሪሞተር ጨብጬ ከስጋዬ ጋር እየታገልኩ ነው:: ብቻዬን ስሆን እንዲህ አይነት ፈተና ብዙ ጊዜ ይገጥመኛል::ለእኔ ይህ አዲስ አይደለም ብዙ ጊዜ ተሸንፌበታለሁ አምላኬንም አሳዝኜበታለሁ::በዚህ ችግሬ ምክንያት ውሎዬ እና አዳሬ በሰው የታጀበ እንዲሆን ጥብቅ መሻቴ ነው:: በእጄ ከፍርሀቴ የተነሳ የሙጥኝ ብዬ የያዝኩት የቴሌቪዥን መቆጣጠርያ ሪሞት አንደበት ኖሮት ቢናገር የእኔን ጉድ ከማንም በላይ ያወራችሁ ነበር:: ብዙ የሚስጢር ኮዶችን እንዳስገባሁባት ከእኔ እና ከሪሞተሯ በስተቀር ማንም የሚያውቅ የለም:: ብዙ ስጋዊ ነገሬን የሚያነሳሱ የተሌቪዥን ቻናሎችን ሞልቼበታለሁ:: ታድያ ዛሬ ቤት ማንም ስለሌለ ይህን ቻናል ከፍቼ ልመልከት አልመልከት በሚል እሰጣ ገባ ውስጥ እያለሁ ከመቅፀብት ጣቶቼ ከቁጥጥሬ ውጭ በመሆን የሪሞተሩን ቁልፎች ተጫኑ:: ወዲያው በስክሪኑ ላይ በብዥታ ምስል ፊታቸው ተሸፍኖ ልቅ የሆነ ወሲብ የሚፈፅሙ ጥንዶችን ተመለከትኩ :: ምስላቸውን መመልከት ስጀምር አንዳች ነገር ሊሰርቅ እንዳቀደ ሰው ግራ እና ቀኜን ዞር ዞር ብዬ አየሁ:: ረዘም ላለ ሰዐት መመልከት እንድችል ግን ግዴታ ወጣ ብዬ የክፍሌን ዙርያ ማየት እና ሰው እንደሌለ ማረጋገጥ አለብኝ:: ዛሬ ቤት ማንም ባይኖርም የዘውትር ቅድመ ሁኔታዬ ስለሆነ አረጋግጬ በእግሬ ጣት ቀስስ ብዬ ወደ መቀመጫዬ ተመለስኩ::ቪዲዮውን መመልከት ስጀምር ድንገት ሰውነቴ በክፋት ሲወረር ተሰማኝ:: በሰመመን የክፋትን አለም አሰስኩ::
ይህ ለእኔ ትልቅ ፈተና ነበር::ሰውነቴ በሙሉ አይን አውጥቶ የእርቃነ ስጋቸውን ምስል እየቀረፀ አዕምሮዬ ውስጥ ሲያከማች ይታወቀኛል:: ግማሹ እኔነቴ የማደርገውን ነገር ቢቃወም ግን የማቆሙን ሐይል አጣው:: ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ጨርሼ ከክፍሌ ወጣሁ::በዚች ጥቂት ደቂቃ ውስጥ ግን ብዙ ምስሎችን በጭንቅላቴ ስዬ ነበር።ይህ ምስል ምስል እለት እለት ብዙ ፈተና ያመጣብኝ ነበር።የዛሬው ድርጊቴ የመጀመርያዬ አይደለም። ብዙ ጊዜ ብቻዬን ስሆን ማከናወን የሚቀናኝ ይህ ነው።ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ስቀላቀል ብዙ ነፃነት ተሰማኝ የሁል ጊዜ ተግባሬ ይህን የወሲብ ፊልም ማየትና ራሴን በራሴ ማርካት(masterbation) ሆነ። በዚህ ተግባሬም በጣም ብዙ ፀፀት እሸምት ነበር።
ብዙ ጊዜ ይህን ተግባሬን ለመተው ሞከርኩ ነገር ግን ለምን እንደሆነ አላውቅም ከሳምንት በኋላ ተመልሼ እዛው እገኛለሁ።የእኔ ትልቁ ችግር ፖርኖ ማየት ብቻ ሳይሆን በቪዲዮው ላይ ያሉ አክተሮች አለባበስ አሳሳቅ እና የእያንዳንዷ እንቅስቃሴ ምስል ቀንቀን ት/ቤት ውስጥ የማያቸውን ሴቶች ያለማቋረጥ በመጥፎ እይታ እንድመለከታቸው ማድረጉ ጭምር ነው።አጭር ቀሚስ የለበሰች ሰውነቷን ጥብቅ አድርጎ የሚይዝ ልብስ የለበሰች ሴት ለእኔ እርቃኗን ሆና ነው የምትታየኝ።አይኖቼ ልብሷን አውልቀው መላ አካላቷን ፍንትው አድርገው ውስጤ ያስቀምጣሉ።እነዚህን እህቶች እያሰብኩ ደግሞ ማታ መጥፎ አለም ውስጥ እገባለሁ።
ፀፀት እና እራሴን መጥላት የሁልጊዜ ተግባሬ ነበር።
"ጌታ ሆይ እርዳኝ።"
"ይቅር በለኝ።"
ሁል ጊዜ እላለሁ ነገር ግን ተመልሼ እራሴን እዛው አገኛለሁ።ምክንያቱ ደግሞ ፅኑ የውሳኔ ሰው አለመሆኔ ነበር።
እንደ ዮሴፍ እንድሆን እርዳኝ!!
መፅሐፍ ቅዱስ አንብቤ አላውቅም ነበር።አንድ ቀን ታድያ በምን አይነት አጋጣሚ እንደሆነ ባላውቅም [እውነት ለመናገር ካለሁበት ስቃይ ለመላቀቅ ስል ነው] ከዘፍጥረት ጀምሮ ማንበብ ጀመርኩ።ታድያ በጥልቀት እያጠናው ባልሔድም ስለ ሰው ልጅ ክፋት እና ስለ እግዜአብሔር ምህረት አስተውያለሁ። እንደ ዮሴፍ አይነቱን ታሪክ ማንበቡ አቋሜን ማስተካከል እንዳለብኝ እረድቶኛል። ሴይጣን ደግሶ እና ሁሉንም ነገር አመቻችቶ አቅርቦለት ዮሴፍ እምቢ ብሎ መሸሹ እንደ እኔ አይነቱ ከሰይጣን ጋር አብሮ የመቀበርያውን ጉድጓድ የሚቆፍር ምንኛ ሞኝ እንደሆንን አሳየኝ።
እለት እለት ይህን የዮሴፍን ሽሽት ማሰላሰል ትልቅ ብርታት ሆኖኝ ከነበርኩበት ስቃይ ተላቅቄ አለሁ። ከምንም በላይ ከዚህ አይነት ስቃይ ሊያላቅቅ የሚችል የእግዜአብሔር ፀጋ ብቻ ነው።
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgnjWczaPdu0FwA
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🚀🚀 @sozo_purity 🚻🚻 @sozo_family
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤15👍7👎1
ይህ አባት ለሴት ልጁ የመከረው ምክር ነውና በማስተዋል አንብቡት !
- ወጣት ሴቶች ልጆች እንዲጠነቀቁ
- ወላጆች ሴቶች ልጆቻቸውን እንዲመክሩ ይረዳችኃልና !
ወድ ልጄ በምድር እንድትኖሪበት የተሰጠሽን ሕይወት ዳግመኛ ተመልሰሽ አትኖሪበትም ! የተፈጠርሽበትን ዓላማ ከፈጠረሽ አምላክ ጠይቂ ! በተሰጠሽ ዘመን ለፈጠረሽ አምላክ ፈቃድ ተገዢ !
☞ሴት ልጅ ውድ ነች ርካሽ ብትሆን ለውዷ ቤተክርስቲያን በምሳሌ አትሰየም። በእግዚአብሔር ላንቺ የተመዘነው ዋጋ የክርስቶስ ደም ነው። ራስሽን ማየት ያለብሽ እግዚአብሔር በሚልሽ እንጂ ሰይጣንም፣ ሰውም፣ ሁኔታም፣ በሚገልጽሽ ማንነት አይደለም። በእግዚአብሔር እንተወደደች እንደ ውድ ዕንቁ ሴት ራስሽን ቁጠሪ ፤
☞ እግዚአብሔር በልጁ ሞት ሕይወት የሰጠሽ የከበርሽ ልጁ ነሽ !
☞ እግዚአብሔር በዓላማ ፈጥሮሻል!
☞ ከእግዚአብሔር ሐሳብ ወደ ግራም ወደ ቀኝም እንዳትይ ተጠንቀቂ !
☞ በሰይጣንና በሰው የሚሰጥሽን መደለያ ፈጽሞ አትቀበይ ወጥመድ ነውና !
☞ ክብርሽ ስኬትሽ ደስታሽ ያለው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ነው !
☞ ለገንዘብ ራሳቸውን የሸጡትን ምክር አትስሚ ! ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችይምና ! አምላኬ ገንዘብ ሳይሆን እግዚአብሔር ነው በያቸው !
☞ ሁል ጊዜ ነፍሱን ሰጥቶ ያዳነሽን ጌታ ፍቅር አስቢ !
☞የእግዚአብሔርን የፀጋ ክብር በሙላት ይግባሽ፤
☞ሰይጣን በላከው ተራ ወንድ አትሸወጂ ስላንቺ ያለው እይታ ከቤት ዕቃ አያልፍምና ! (የቤቱን እቃ አሟልቶ አሁን ደግሞ ሚስት ብሎ ከሚያቅድ ነገ እንደ ቁምሳጥን፣አንደ መኪና የቤት እቃ አድርጎ ሊቆጥርሽ ከሚችል እይታው ከጠበበ ወንድ ተጠበቂ)፤
☞እግዚአብሔር ፀጋውንና የክርስቶስን ልብ ሰጠን እንጂ ለእባብ የሚስቅ የሄዋንን ልብ አልሰጠንምና የቀረበሽ ወንድ ሁሉ ያንቺ አይደለምና ተጠንቀቂ።☞ፍቅር የዘኝ ብሎ ለሚፈጥነውም ረጋ በል ብሎ መመርመር ይገባል። ወዲያው አፈቀርኩ አበድኩ ነደድኩ ብሎ የሌለን አለም ታሪክ ዲስኩር ከሚቀድ ወንድ ተጠበቂ ተጠንቀቂ ውድቀትሽን ስብራትሽን ሐዘንሽ ለማፈጠን ከሰይጣን የተላከ የስሜት ፈረስ ጋላቢ ሊሆን ይችላልና።
☞አበድኩ አፈቀርኩ ብሎ ኃላ የጥላቻ ቁንጮ የሆነውን አሲድ ከሚደፋ ወንድ ጋር ህብረት አታድርጊ አሲድ ባይደፋም በእርኩሰቱ ወደ ሲኦል የሚመራሽ ከዚያ ይብሳልና ተጠበቂ !
☞ከማታውቂው መልአክ የምታውቂው ሰይጣን ይሻላል አየተባለ ከሚደሰኮር ተረት ራቂ ለሞትና ለጥፋት የሚያዘጋጅ ነውና።
☞ ይልቅ ለፈጠረሽ አምላክ ለእግዚአብሔርን የተሰጠ እውነተኛ ወንድም ከእግዚአብሔር እጅ ለመቀበል ጸልይ ከአምላክሽ ጋር የጠበቀ ሕብረት ይኑርሽ ! በጸሎት በአምልኮ በቃል ጥናት በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ምሪት የተቃኘ ሕይወት ይኑርሽ !
☞ የተፈጠርሽበትን ዓላማ ለማሳካት ጌታን በሚያስከብር ሕይወት የአገልግሎት ጸጋሽን በመለየት አገልግይ!
☞ የሚገርመው ጌታ በውስጥሽ ያስቀመጠው የሚገርም የተዳፈነ ፀጋ አለሽ በጸሎት በቃሉና በመንፈሱ ሙላት ይገለጣልና ቀድሞ ከነበረሽ ይልቅ በጌታ ፊት ወድቆ የመጮህ ጊዜ ይብዛልሽ ! ☞ጸጋው በተገለጠ ጊዜም ለሰጪው ክብር በማብዛት በስርዓት ወደ መድረክ ይዘሽው ውጪ ለብዙዎች መዳን ምክንያት ትሆኛለሽና !
☞በትንቢት ቃል አትታሰሪ/ትዳር/ አትመስርቺ ለነብይ የነገረው አባትሽ እግዚአብሔር ከሆነ ላንቺ በቀጥታ ይነግርሻል ልጁ ነሽና እንደ ነጎድጓድ የሚነገር ልሳን አትፍሪ አትደንግጪ !
☞አንቺ ልባም ሴት ልጅ ነሽ የክርስቶስ ልብ ያለሸ፤
☞አንቺ ከመውለድ ልጅ ከማሳደግ ንብረት ከመሰብሰብ ያለፈ መለኮታዊ ፕሮግራም ያለብሽ በደሙ የተገዛሽ ዕንቁ ልጁ ነሽ !
☞ የአምላክሽ ዋና ዓላማና ግብ ማግባት ብቻ አይደለም ለዘላለም ሕይወት ክብር በክርስቶስ መመረጥሽ እንጂ ! በምድር ከሚሆንልሽ እና ከሚደረግልሽ ያለፈ ክብር አለሽ !
☞ የሰርጉ ሆታ ጭፈራ እልልታና ሽብሸባ የአንድ ቀን ነው። በክርስቶስ የተዘጋጀው ክብር ግን የዘለዓለም ነው !
☞ በአምላክሽ የታሰበልሽን ግብና የተሰጠሽን ተስፋ አስቢ !
☞በጊዜው የሚመጣ ክብርሽ የሚሆንልሽ የትዳር አጋር ዘውድ የምትሆኚለት ወንድ በእግዚአብሔር እንደተወሰነልሽ አስቢ፤
☞☞☞ይህ ከሆነ በእውነት ልባሟ ሴት አንቺ ነሽ ! ተባረኩልኝ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgnjWczaPdu0FwA
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🚀🚀 @sozo_purity 🚻🚻 @sozo_family
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍22❤13
በአንድ ወዳጄ ላኘቶኘ ላይ ተለጥፎ ያስተዋልኩት የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ብዙ ነገር እንዳስብና ይህን እንድፅፍ አደረገኝ::
"ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ..." ኢዮብ 31:1
ይህ ወዳጄ ብዙ ሰዐታት ብቻውን የኢንተርኔት አገልግሎት ሲጠቀም ብዙም ከእኛ ያልራቁ እና በሴኮንዶች ውስጥ ድረ-ገጾችን አስሰን ልናገኝ የምንችላቸው ምስሎች ምን ያክል ፈታኝ እንደሆኑ እና መፍትሔውን ጭምር ያስተዋለ ይመስለኛል::
ክፍሉ እንዲህ ብሎ ይቀጥላል...
"እንግዲህስ ቈንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ?"
እንደ ብዙዎቻችን ኢዮብ ከሀጢዐት ለመራቅ ከራሱ ጋር ቃልኪዳን የገባ ነው የሚመስኝ::
ኪዳኑን ሲቀጥል ቁ.4 ላይ እንዲህ ይላል!
4፤ መንገዴን አያይምን?
እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?"
ይህን ጥያቄ በሐጢዐት ፈተና ውስጥ ስንሆን አብዛኛዎቻችን አንስተን እናውቃለን::
ይህን እስቲ በማስተዋል እንመልከት!!
" እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።" (ወደ ዕብራውያን 4:13)
ሰው ከሰው በልቡ ብዙ ሚስጢር ሊሸሽግ ይችላል::
ሰው "ሰው አያየኝም" ብሎ ግራና ቀኙን ብቻ አየት አድርጎ ከሰው እይታ ውጪ ነኝ ብሎ ሀጢዐት ሊሰራ ይችላል::
ግን የዕብራውያኑ ፀሀፊ ከሰው ዘንድ አንዳንድ የተሸሸጉ ሚስጢሮች እንደሆኑ ነገር ግን በእግዜአብሔር ዘንድ ሁሉ ነገር የተራቆተ እና የተገለጠ እንደሆነ ይናገራል::
ታድያ ለምን ራሳችንን እናስታለን??
ከምንም እና ከማንም በላይ ለእግዜአብሔር ታማኝ መሆን አለብን::
ከሀጢዐት መራቅ(መሸሽ) ምንኛ መልካም መሰላችሁ!!
ሀጢዐትን በሁለት መንገድ መሸሽ እንችላለን::
1- እንደ ዮሴፍ በአካል መሸሽ(ማምለጥ)
2- እንደ ኢዮብ አቋም እና ኪዳን በመግባት በቃሉ ተሰውሮ መሸሽ(ማምለጥ)
ከዝሙት ለመራቅ የመጀመርያው መንገድ የሚቀድም ይመስለኛል!!
" ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤
ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤" 1ተሰሎ 4:3-5
እስከዛሬ ለራሳችን ቃል ካልገባችሁ እና በእግዜአብሔር ፀጋ ዙፋን ስር ራሳችንን ካላዋረድን አሁኑኑ በርከክ ብለን ጌታ ፊት እንዋረድ!!
በፀጋው እንጂ በራሳችን ብልሀት ፈፅሞ ልናመልጥ አንችልም!!
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgnjWczaPdu0FwA
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🚀🚀 @sozo_purity 🚻🚻 @sozo_family
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤15👍8
"በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ።ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ሆንሁ፥ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ፥ …"(መዝ 39:-1 - 2) አንደበትን መጠበቅ ከብዙ ነገር ያድናል። ከአንደበት የሚፈልቅ ብዙ ቃል አለ :-
1ኛ, መልካም ቃል ! መልካም ቃል ያንጻል ያፅናናል ይጠግናል ያበረታታል……ወዘተርፈ በአንጻሩም
2ኛ, ክፉ ቃል ! ክፉ ቃል ያፈርሳል፣ ይሰብራል፣ ያደክማል፣ያጠፋል፣ ይገላል፣ ያቆስላል……ወዘተ ብዙዎች እንደሚያስቡት ብዙ ማውራት ብዙ ማወቅ አይደለም። አዋቂ ተግባሩ እንጂ ንግግሩ እንዲገልጠው አይፈልግም። አበው "ዝምታ ወርቅ ነው" ሲሉ የዝምታን ጥቅም በመረዳት ነው።
* ቅዱስ ቃሉ ሰው እንደመጣለት መናገር እንደሌለበት አጥብቆ ይናገራል::
* ሰው ቢናገር እንኳ መጠቀም ያለበት:-
የተቀመሙ ቃላቶችን እንደሆነ ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል።
" ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።"( ቆላ 4:-6)
* የተቀመመና በፀጋ የሆነ ንግግር ! በዘይትና በቃሉ እውነት የተለወሰ በጎና መልካም የሆነ የሚያንጽ ቃል ነው ።
" ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።"(ማር 9:49)
* ንግግር በጨው ይቀመማል ?
ጨው የማይገባበት የቅመም አይነት የለም ! ጨው መራራውን ያጣፍጣል!
" እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።"
(ማቴ 5:13)
* ጨው ምንሞ ቅመምን የሚቀምም ቢሆንም አስፈላጊ የሚሆነው ጨውነቱን እስከጠበቀ ጊዜ ድረስ ብቻ ነው !
" ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።"(ማር 9:50)
* ጨው ጨውነቱን ባይጠብቅ ድንጋይ ይሆናል ::
1,ወደ ውጭ ይጣላል !
2, በሰው ይረገጣል !
3, ለምንም የማይጠቅም የሆናል !
ብዙዎች የተቀመመ ንግግር የላቸውም
*ለዚህ ነው አነፅን ሲሉ የሚያፈርሱት !
*ፈወስን ሲሉ የሚያቆስሉት !
* ጠገንን ሲሉ የሚሰብሩት !
* ተከልን ሲሉ የሚነቅሉት ! ኧረ ስንቱ
* አንደበት :- እሳት ነው የፍጥረትን ሩጫ ያቃጥላል ! (ያዕ 3:-5-6)
" እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል።አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።"
*ነጻነት ያለው አንደበት ሰውን በኃጢያት
ያሳድፋል ! ወዳጆችን ይለያያል ! ጥልና ግጭትን ይዘራል ! ያገዳድላል ያጠፋፋል። ሰው በወንድማማች መካከል ጠብ የሚዘራው በአንደበቱ ቃል ነው። " እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤..... በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ። "( ምሳሌ 6:-16,19)
* ልብ በሉ :- አስቴር ሳትነግስ የማንነቷ ወሬ ቢቀድም ሞት የተፈረደባቸውን ህዝቧን ባልታደገች ነበር።
* ሳምሶንም የኃይሉን ሚስጥር በመዘክዘኩ በጠላት እጅ ወደቀ !
" ነገ ር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ፤ ኃጢአተኝነታቸውን ከፊት ይልቅ ይጨምራሉና፥ ቃላቸውም እንደ ጭንቁር ይባላል፤"(2ኛ ጢሞቴዎስ 2:16)
* ብዙዎች ያወቁ እየመሰላቸው እንደ ጭንቁር በሚባላ ቃላቸው ስንቶችን ገደሉ?
* ኢዮብ ለአፅናኞቹ ያላቸውን ተመልከቱ
( ኢዮ ም13:- 5)
"ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ!
ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር።"
አፅናኞች ከሚናገሩት ከንቱ ንግግር ዝምታ እንደሚሻል ይናገራል ! ቅዱስ ቃሉ :- " ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፤ ከከንፈራቸው በታች የእፉኝት መርዝ ነው።"(መዝሙረ ዳዊት 140:3)
*በዚህ መርዝ ስንቱ ተነድፎ ይሆን ?
ለዚህ ነው ! ዳዊት" አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።"ያለው
(መዝ 141:3)
* ስለዚህ በሁሉ አንጻር መጠንቀቁ ይበጃል !
" እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤" (ማቴ 12:36) ስለዚህ እኛስ ምን እናድርግ :-
1ኛ,አንደበት በመጠበቅ የፍጥረት ሩጫ ከማቃጠል እንጠበቅ !
2ኛ,ሞት እና ህይወት በአንደበት ላይ ነው በመሆኑም ሕይወትን እንምረጥ !
3ኛ,አንደበቱን የሚጠበቅ ከተማን ከሚያስተዳድር ይበልጣልና በብልጫ ሕይወት እንኑር !
4ኛ,አንደበቱን እያሳተ የሚያመልክ የሚመስለው የሱ አምልኮ ከንቱ ነውና ከከንቱ አምልኮ እንውጣ !
5ኛ,አንደበትን መጠበቅ ወሳኝ የመንፈሳዊ ሕይወት ምዕራፍ እንደሆነ እንወቅ !
6ኛ, አንደበትን መጠበቅ ከጥፋትና ከፍረድ ይታደገናልና ከአንደበት ለሚወጣ ቃል ትኩረት እንስጥ ቃላትን አንምረጥ !
7ኛ,አንደበትን መጠበቅ እግዚአብሔር ከሚጸየፈው ኃጢያት ይጠብቀናል አብልጠን እንጠንቀቅ !
https://t.me/joinchat/AAAAAEQpgnjWczaPdu0FwA
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🚀🚀 @sozo_purity 🚻🚻 @sozo_family
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍26❤10👎1
ለምን ሁልጊዜ በኃጢአት እወድቃለሁ?
የኃጢአት እና የሱስ ዑደቶችን መስበር
መንፈሳዊ ህይወታችሁን ስታስቡ የኋሊት እየተጓዛችሁ እንዳለ የተሰማችሁ ጊዜ አለ?
ከኃጢአት ለመላቀቅ ትሞክራላችሁ፣ ነገር ግን... BooM! ወዲያውኑ ወደጀመራችሁበት ትመለሳላችሁ። 😔 ብቻችሁን አይደላችሁም። ይህ ብዙዎቻችን የምንጋፈጠው ጦርነት ነው።
እውነቱን ስናወራ ሁሌታው የሚያበሳጭ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ፣ እና አንዳንድ ጊዜ እምነታችንን እንድንጠራጠር የሚያደርግ ነው። ግን እውነቱ ይህ ነው፡ እግዚአብሔር በሽንፈት ዑደት ውስጥ እንድንኖር አይፈልግም። በነጻነት እንድንመላለስ ይፈልጋል! ✨
ታዲያ ለምን መውደቃችንን እንቀጥላለን?
እዚህ ዑደት ላይ እንድንቆይ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች አሉ፡
- ያልተሟሉ ፍላጎቶች፡ ምናልባት በተሳሳተ ቦታዎች ላይ የህይወትን ትርጉም እየፈለግን ሊሆን ይችላል። (ለምሳሌ፡ በማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ የመወደዳችንን ማረጋገጫ. . .)
የምናምናቸው ውሸቶች፡ ጠላት ድርጊታችንን የሚያጸድቁ ውሸቶችን ያሾካሽካል። (ለምሳሌ፡ "ይህ አንድ ጊዜ አይጎዳም፣" "ሌላው ሁሉ እያደረገው ነው።")
ያልተፈወሱ ቁስሎች፡ ያለፉት ህመሞች ጤናማ ወዳልሆኑ የመፈወሻ ዘዴዎች ተጋላጭ ሊያደርጉን ይችላሉ።
ተጠያቂነት ማጣት፡ ድጋፍ በሚያስፈልገን ጊዜ ጦርነቶችን ብቻችንን ለመዋጋት እንሞክራለን።
ቀስቃሾችን ችላ ማለት፡ ወደ ስህተት የሚመሩንን ሁኔታዎች አንለይም ወይም አንርቅም።
ግን የምስራች!! የእግዚአብሔር ጸጋ ከማንኛውም ኃጢአት የበለጠ ኃይለኛ ነው!
📖 የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች፡
1 ዮሐንስ 1:9፡ "ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።"
ሮሜ 6:14፡ "ከጸጋ በታች እንጂ ከህግ በታች ስላልሆናችሁ ኃጢአት አይገዛችሁምና።" "
@sozo_purity

❤21👍4
📢 ጭንቀትን ማሸነፍ፡
ሰላም ቤተሰብ! 👋
- ጭንቀት ብዙዎቻችን ከምንታገላቸው ትልልቅ ችግሮች አንዱ ነው።ጭንቀት ማለቂያ የሌለው የፍርሃትና የጥርጣሬ ማዕበል ሊመስል ይችላል። ግን እውነቱ ይህ ነው፡ እግዚአብሔር በሰላም እንድትኖሩ መንገድ አዘጋጅቷል። ቃሉ ጥንካሬን፣ መጽናናትን እና በጭንቀት ላይ ድልን የሚሰጡ ተስፋዎች የተሞላ ነው።
ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት፣ ወደ እግዚአብሔር እውነት ውስጥ እንገባለን፣ ጭንቀትን በእምነት እንዴት መዋጋት እንደምንችል እንማራለን፣ እና በነጻነት አብረን እንጓዛለን። እንጀምር! 🙏🔥
🔄 https://t.me/sozo_purity
🔄 https://shorturl.at/6uJKY

❤5
"እግዚአብሔር ጭንቀታችን ይገባዋል"
ሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ሆኗል፣ እኔ ግን አሁንም ነቅቻለሁ። አእምሮዬ መሮጡን አላቆመም—ያልተከፈሉ ሂሳቦች፣ እየሳሱ ያሉ ጓደኝነቶች፣ ነገ ምን ሊያመጣ ይችላል የሚለው ፍርሃት። በዚህ ጭንቀት እየሰመጥኩ፣ የማልታይና የተረሳሁ ሆኖ ተሰማኝ።
ይህን ሀሳብ ከመሸሽ ስልኬን ከፍቼ፣ ትኩረቴን ለመቀየር በከንቱ ማሸብለል ጀመርኩ. . . በድንገት አንድ ጥቅስ አየሁ፡-
📖 "እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና፣ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉ።" (1 ጴጥሮስ 5:7)
. . . ደረቴ እየደለቀ ቃላቱን ተመለከትኩ። "እግዚአብሔር ሆይ… በእርግጥ ታስብልኛለህ?" በሹክሹክታ ጠየቅሁ።
ከዚያም እናቴ አንድ ጊዜ የነገረችኝን ነገር አስታወስኩ፡-
"በጭንቀት እየሰመጥክ እንደሆነ ሲሰማህ፣ አትያዘው። ለኢየሱስ ስጠው። እሱ ሊሸከምልህ በቂ ጥንካሬ አለው።"
. . . እንባዎች አይኖቼን ሞሉ። በጥልቅ ተንፍሼ ስልኬን ዘግቼ እጄን በልቤ ላይ አደረግሁ። "እግዚአብሔር ሆይ፣ ዛሬ ፍርሃቴን ሁሉ ላንተ እሰጣለሁ። አንተ እንደምታስብልኝ አምናለሁ።"
በዚያ ቅጽበት፣ አንድ ነገር ሲቀየር ተሰማኝ። ችግሮቼ አልተወገዱም፣ ነገር ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ብቻዬን አልሸከምኳቸውም። ያ ሁሉንም ነገር ለወጠው።
ቁልፍ ነጥቦች፡-
• እግዚአብሔር ጭንቀታችንን ያያል – በችግሮቻችን ውስጥ ብቻችን አይደለንም።
• ጭንቀቶቻችንን ለእርሱ እንስጥ – እነሱን ለመሸከም በቂ ጥንካሬ አለው። (1 ጴጥሮስ 5:7)
• መታመን ሰላምን ያመጣል – ችግሮቻችን ወዲያውኑ ላይጠፉ ይችላሉ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር መገኘት ሁሉንም ነገር ይለውጣል።

❤10👍5
"ጭንቀታችን የሚነግሩን ውሸቶች"
ጭንቀቴ ድምፅ ነበረው እና ለረጅም ጊዜ የሚለኝን እያንዳንዱን ሹክሹክታ አምኜ ነበር።
"ብቻህን ነህ።"
"ይህን መቋቋም አትችልም።"
"ከሁሉ የከፋው ነገር ይከሰታል።"
እነዚህ ሀሳቦች ያለምንም ክልከላ በአእምሮዬ ውስጥ በነፃነት ይመላለሱ ነበር። ወጥመድ ውስጥ እንደገባሁ፣ አቅመ ቢስ እንደሆንኩ ተሰማኝ . . . መጽሐፍ ቅዱሴን ከፍቼ የእግዚአብሔርን እውነት እስክረዳው ድረስ፡-
📖 "አትፍራ፤ ከአንተ ጋር ነኝና፤ አትደንግጥ፤ አምላክህ እኔ ነኝና፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እደግፍሃለሁ።" (ኢሳይያስ 41:10)
📖 "እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።" (መዝሙር 29:11)
📖 "ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም።" (ዮሐንስ 14:27)
. . . እንባዎች አይኖቼን ሞሉ። ጭንቀት ሁልጊዜ ሲዋሸኝ ኖሯል። ብቻዬን አልነበርኩም። አቅመ ቢስ አልነበርኩም። በፍርሃትም መኖር አልነበረብኝም።
በዚያ ምሽት ምርጫ አደረግሁ . . . የጭንቀትን ውሸቶች ማዳመጥ አቁሜ በእግዚአብሔር እውነት ላይ መታመን እጀምራለሁ።
ቁልፍ ነጥቦች፡-
• ጭንቀት ይዋሻል – ብቻህን እንደሆንክ፣ አቅመ ቢስ እንደሆንክ፣ ከሁሉ የከፋው ነገር እንደሚከሰት ይናገራል።
• የእግዚአብሔር እውነት የበለጠ ጠንካራ ነው – መገኘቱን (ኢሳይያስ 41:10)፣ ጥንካሬውን (መዝሙር 29:11) እና ሰላሙን (ዮሐንስ 14:27) ቃል ገብቷል።
• ምርጫ አለህ – የጭንቀትን ውሸቶች ማመን አቁመህ በእግዚአብሔር እውነት ላይ መታመን ጀምር።

❤17👍12🔥1
https://youtu.be/s-fQDGm-2KY?si=AMxiDFJRyRfGJygc
"ነገሮች ማዘግየት ልማድ ብቻ አይደለም—መንፈሳዊ ውጊያ ነው። ጠላት በዘገየ ሁነታ እንድትጣበቅ ይፈልጋል፣ ወደ ጥሪህ በጭራሽ እንዳትገባ። ነገር ግን ዛሬ፣ ያ ዑደት ያበቃል!"
🔔 Subscribe for more faith-filled content!

YouTube
እግዚአብሔር ይህን እንድትመለከት ይፈልጋል—ከእንግዲህ ሰበብ አይሰራም!
"ነገሮች ማዘግየት ልማድ ብቻ አይደለም—መንፈሳዊ ውጊያ ነው። ጠላት በዘገየ ሁነታ እንድትጣበቅ ይፈልጋል፣ ወደ ጥሪህ በጭራሽ እንዳትገባ። ነገር ግን ዛሬ፣ ያ ዑደት ያበቃል! 🚀
📖 ቁልፍ ጥቅሶች፡
መክብብ 11:4 – “ፍጹም ጊዜን” መጠበቅ አቁም
ያዕቆብ 1:5 – ጥበብ እና ተግሣጽ ለማግኘት ጸልይ
ቆላስያስ 3:23 – በሙሉ ልብህ ሥራ
💡 ማዘግየትን ለማሸነፍ 3 ደረጃዎች፡
✅ ጥበብ እና ተግሣጽ ለማግኘት…
📖 ቁልፍ ጥቅሶች፡
መክብብ 11:4 – “ፍጹም ጊዜን” መጠበቅ አቁም
ያዕቆብ 1:5 – ጥበብ እና ተግሣጽ ለማግኘት ጸልይ
ቆላስያስ 3:23 – በሙሉ ልብህ ሥራ
💡 ማዘግየትን ለማሸነፍ 3 ደረጃዎች፡
✅ ጥበብ እና ተግሣጽ ለማግኘት…
❤14👍4🔥3
የኢትዮጵያ የወጣት አገልጋዮች እና የመሪዎች ጉባዔ 2018
በAI ዘመን መምራት እና በሁለንተና ማደግ
ከግንቦት 13-14 2018
ከጠዋቱ 2፡30 -10፡00
በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች፡
📍 ሳርቤት ከኪንግስ ሆቴል ፊት ለፊት
አዘጋጆች
ሪጆይስ አፍሪካ
የኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ
SIM Ethiopia
ተስፋ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ
👉ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👉 https://bit.ly/EYMLS2026
ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ላይ ያገኙናል
Telegram | Facebook | Instagram

❤3