ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
853 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_1
#ፍቅር_ምንድነው_?
ፍቅር እውር ነው ?
አንድ ፈላስፋ ሲናገር ምን አለ በመጀመሪያ ፈጣሪ ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ስሜቶችን ፈጠረ ፍቅር ፣ እብደት ፣ ቅናትና ውሸትን ከዛ ከፈጠራቸው ቡሃላ ተሰወረባቸው ። ስሜቶችም ኩኩሉ መጫወት ጀመሩ ። እብደት ቆጣሪ ነበር ። መጀመሪያ ውሸት ከዛ ቅናት ተያዘ ፍቅር ግን ከፅጌሬዳ አበባ ጀርባ ነበርና የተደበቀው ቢፈልገው ቢፈልገው አጣው ። ከዛ ቅናት ተናደደና ከአበባው ጀርባ እንደተደበቀ ነገረው ። እብደትም ቀስ ብሎ ሊያይ ፅጌሬዳውን ሳብ አርጎ ቢለቀው እሾሁ ሄዶ የፍቅርን አይን ወጋው ።ፍቅርም በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ ፈጣሪም ተገለጠ በተፈጠረው ነገርም አዘነ ። የፍቅር ሁለቱም አይኖቹም እንደ ጠፉ አየ ። ፈጣሪም እብደትን አይኑን አጥፍተኸዋልና ከአሁን ቡሃላ ፍቅርን እጁን ይዘህ ወደ ሚሄድበት ቦታ ትመራዋለህ ብሎ አዘዘው። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ፍቅርን ወደ ሚሄድበት ቦታ እጁን ይዞት የሚመራው እብደት ሆነ። እናማ ይሄ ታውሯል እንዴ ከዚች ጋር ፡ ይቺ አብዳለች እንዴ ከሱ ጋ አትበሉ ። ፍቅር ታውሯል የሚመራውም በእብደት ነውና ይላል ። እኔ ግን ፍቅር እውር ሳይሆን እንደውም ማየት ያለብንን ነገር የሚያሳየን አይናማ ነው እላለው። የፍቅር መገኛውና ምንጩ እግዚአብሔር ሲሆን የህግ ሁሉ ፍፃሜም ነው ።ለዚህ ነው ጳውሎስ የትእዛዝ ፍፃሜ ግን "በንፁህ ልብ ፣ በመልካም ጠባይ ፣ ጥርጥር በሌለበት ሃይማኖት መዋደድ ነው " ። ባለሙያዎች ፍቅር 3 ደረጃዎች አሉት ይላሉ #1ኛ.Relationship ይባላል። relat ማለት መገናኘት ሲሆን ship ደሞ ካርጎ በሚለው እንተርጉመው ። ማንኛውም ሰው የራሱ የሆነ አስተሳሰብ ፀባይና ባህሪ አለው ።ይሄንን ጭነቱን ይዞ ከአንድ ሰው ጋር ሲገናኝ ሲተዋወቅ ሪሌት አደረገ ወይም relationship ጀመረ ይባላል ። #2ኛ.ደረጃው ደሞ Friendship ይባላል። ይሄን ደሞ flow በሚለው እንተርጉመው ። የአንዱ አስተሳሰብ ወደ አንዷ የአንዷ ፀባይ ወደ አንዱ ሲፈስ freindship ይመሰረታል ። #3ኛ.ደረጃው ደሞ Intermacy ይባላል ። ይህም in to see me በሚለው ይተረጎማል ። ሪሌት አርገን ሀሳብ ፍሎው ካደረግን ቡሃላ ወደ ኢንቱ ሲ ሚ ወይም ውስጥን ወደ ማሳየት ያድጋል። አላማችንን ግባችንን የልባችንን ነገር ምናሳየው እዚህ ደረጃ ላይ ስንደርስ ነው ።በዚህ ውስጥ ያለፈ ፍቅር ጠንካራ ይሆናል ግቡም ልብ እንጂ የወሲብ ስሜት አይደለም። ፍፃሜውም በቃልኪዳን የታሰረ ጋብቻ ይሆናል ይላሉ ። #ሊቃውንቶች ደሞ በትዳር ጓደኞች መካከል ሊኖር የሚገባ ፍቅርን በደረጃ መለየት ይከብዳል ። ባልና ሚስት በ1 አካል ላይ ያሉ 2 አይኖች ናቸውና ይላሉ ። ሰው ለ2ቱ አይኖቹ የተለያየ ግምትና የፍቅር ሚዛን እንደማይኖረው ሁሉ በትዳር ጓደኞችም መካከል የሚኖር ፍቅርም ገደብና መጠን የሌለው ፍጹም #ፍቅር ነው ። የክርስቲያናዊ ጋብቻ ፍቅር መሰረቱ #ፍትወት አይደለም ። #ትዳር መሰረቱን ፍቅር ሲያደርግ ትዕግስት ይኖረዋል ፣ አንዱ ለአንዱ እንዲያዝን ያደርጋል ፣ አያቀናናም ፣ አያበሳጭም ፣ መተማመንን ያሰፍናል ፣ ይጸናል። በ1ኛ ቆሮ 13 ላይ ጳውሎስ የፍቅርን ባህርያት ነግሮናል ። "ፍቅር ይታገሳል ቸርነትንም ያደርጋል ፡ ፍቅር አይቀናም ፍቅር አይመካም አይታበይም ፡ የማይገባውን አያደርግም ፡ የራሱንም አይፈልግም ፡አይበሳጭም በደልንም አይቆጥርም ፡ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ አመፃ ደስ አይለውም ፡ ሁሉን ያምናል ፡ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል ፡ በሁሉ ይፀናል ፡ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ፡ ትንቢት ቢሆን ይሻራል ፡ ልሳንም ቢሆን ይቀራል ፡ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ ከነዚህም የሚበልጠው #ፍቅር ነው " ይላል። ም/ቱም ብናምን እግዚአብሔርን ነው ተስፋም ብናደርግ በእግዚአብሔር ነው #ፍቅር ግን እራሱ እግዚአብሔር ነውና ።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret