ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ አቀረበች፡፡

አባቷ የምግብ ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡ ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡

በድስቶቹ ውስጥ ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር በአንዱ ድስት ውስጥ ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት መጠበቅ ጀመረች፡፡

ከ20 ደቂቃ በኀላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡

"ልጄ አሁን ምን ይታይሻል? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ "በቁጣ ስሜት ሁና ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡

"በደንብ ተመልከች፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡

"እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡

በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡

"አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡

አባት ማብራራት ጀመረ፡፡ "ድንቹ፣ እንቁላሉ እንዱሁም የቡናው ዱቄት ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡

ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡

እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡

ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡

አንቺ የትኛው ነሽ?" ችግር ስገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? እንደ ድንቹ መልፈስፈስ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር? አልያም ችግሩን ለአዲስ ነገር መፍጠሪያ መጠቀም?"

በህይወት ውስጥ ነገሮች በአካባቢያችን ይከናወናሉ፤ ነገሮች በእኛ ላይ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ትልቁና ወሳኙ በእኛ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ነው!"

የትኛው ነህ? ነሽ?

አስተማሪ ሆኖ ካገኙት #ላይክ እና #ሼር ያድርጉት
👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
💠 ሳለቅስ በተመለከተችኝ ጊዜ አለቀሰች


እመቤታችን በታላቅ ክብር ባረገችበት ጊዜ ቶማስን አጋንንትን እያወጣ ካለበት ከሕንደኬ መንፈስ ቅዱስ ጠርቶት በደመና ላይ ተጭኖ በሰማይ አግኝቷት ነበር፡፡ ይህንንም ለሐዋርያት ሲተርክ እንዲህ አለ፡-“…እኔ ልናገረው /ልገልጸው/የማይቻለኝ ታላቅ ብርሃንም ከቧት ነበር፡፡ ቶማስ ሆይ ታውቀኛለህን? አለችኝ፡፡ አንችን ማየት አልቻልሁም አልኋት፡፡ያን ጊዜም በፊቷ የነበረው ብርሃን ተወገደ፡፡ያን ጊዜም በግልጽ አየኋት፡፡የልዑል እናት ነሽ አልኋት፡፡ ብዙ ስግደትንም ሰገድሁላት፡፡ምን ሁነሽ ነው አልኋት፡፡ ሁሉንም በየክፍሉ ነገረችኝ፤ እኔም አለቀስሁ፡፡ እሷም ሳለቅስ በተመለከተችኝ ጊዜ አለቀሰች፡፡” (ድርሳነ ማርያም ፣ መ/ር ተስፋ ሚካኤል ታከለ ፣ በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.በሰ.ት.ቤ.ማ.መ.ማኅበረ ቅዱሳን ፣ የካቲት 2003 ዓ.ም. ፣ አዲስ አበባ ፣ ገጽ 128-129)

የእመቤታችንን አዛኚትነትና ርኅርኅትነት በአንደበት ነግሮ መፈጸምአይቻልም፡፡ በተለያየ አነጋገር ፣ በተለያየ ምሳሌ ፣ በረቂቅ ዘይቤ ፣ በመሳጭ ታሪክ ፣ በአበውና በመጻሕፍት ምስክርነት ብንማረውም ፣ ከፍታውን ለማሳየት ከብዙ ፍጡራን ርኅራኄ ጋር ብናነጻጽረውም አሁንም እጅግ ምጡቅ ነው፡፡ከላይ በተጠቀሰው ታሪክ ቶማስን በዕርገቷ ጊዜ ልታነጋግረው ፈቅዳ ከሕንደኬ እንዲመጣ አምላክን የለመነችው እርሷው ነች፡፡ ከቶማስ በላይ ነችና ስለቶማስ በደንብ የምታውቅ ስለሆነች ስሜቱን በደንብ ትረዳዋለች፡፡ በምትነግረው ነገር የሚያለቅስ ቅዱስ ልቡና እንዳለው ታውቃለች፡፡ ነገር ግን ነግራው ሲያለቅስ አብራው አለቀሰች፡፡ እርሱ ከሌሎቹ ሐዋርያት ጋር ያልነበረ በመሆኑ ለእነርሱ የተገለጸ ምሥጢር የቀረበት መስሎት ሲያለቅስ ለሐዋርያት ያልተገለጠው ዕርገቷን እርሱ ብቻ እንዳየው እያወቀች እንኳን አብራው አለቀሰች፡፡ ክብሩን ነግራ ሳታለቅስ ለቅሶውን ማስቆም ስትችል አብራው አለቀሰች፡፡ በዕርገቷ ጊዜ በአስደናቂ ብርሃን ታጅባ ያያት እርሱ ብቻ መሆኑን ነግራ የለቅሶ ዕንባውን ወደ ሐሴት ዕንባነት መለወጥ ስትችል እርሷ ግን አብራው አለቀሰች፡፡ እልፍ አዕላፋት መላእክት አጅበዋት ማረጓን አብሳሪ እርሱ መሆኑን ከመንገርዋ በፊት አብራው አለቀሰች፡፡ ለማስተዛዘን በሚል ፈሊጥ ሳይሆን ስሜቱ ስሜቷ ሆኖ አብራው አለቀሰች፡፡ ሕፃን ልጅ ሲያለቅስ “በቃበቃ” ብለው እንደሚያባብሉት ሳይሆን ከእርሷ ቅድስና አንጻር በጽድቁ ሕፃን የነበረው ቶማስ ሲያለቅስ እርሱን ለማባበል አብራው አለቀሰች፡፡

ድንግል እንዲህ ነች…አብራ አልቅሳ የምታከብረን ውድ ንግሥት ፤ አብራ አልቅሳ የምታማልደን አዛኝት እመቤት ፤ አብራ አልቅሳ የምታበሥረን ቅድስት ፍጥረት ፤ አብራ አልቅሳ የምታባብለን…. ርኅርኅት እናት፡፡

ወዳጄ ሆይ በሕይወትህ ስንት ጊዜ ከልብህ አልቅሰኻል?የምትበላው አጥተህ የምትጠጣው አጥተህ ስንት ጊዜ አልቅሰኻል? ላንተ ምግብንና መጠጥን ከመስጠቷ በፊት ርኀብህን መጠማትህ ተሰምቷት አብራህ አለቀሰች፡፡ሰው አጥተህስ ፣ ብቸኝነት ተሰምቶህ ስንት ጊዜ አልቅሰህ ይኾን? ብቸኝነትህ ተሰምቷት ላንተ ሰው ከመስጠቷ በፊት አብራህ አለቀሰች፡፡ ሥራ አጥተህስ ስንቴ የሐዘን ዕንባህን አውጥተኻል? ላንተ ሥራ ከመስጠቷ በፊት አብራህ አለቀሰች፡፡ ተበድለህና ተገፍተህ ብቻህን የቀረህ መስሎህ ስታለቅስም ይህን ጊዜህን ወደ ደስታ ከመለወጧ በፊት አብራህ አለቀሰች፡፡ ምድር የተደፋችብህና ምንም ተስፋ የሌለህ መስሎህ አቀርቅረህ ስታነባም አብራህ አነባች፡፡ የዓለም መከራ ሁሉ ወደ አንተ የተላከ መስሎህ ስትንሰቀሰቅ ባንተ ስሜት አብራህ ተንሰቀሰቀች፡፡ የሠራኸው ነገር ልክ አለመሆኑን ተረድተህ በጸጸት ዕንባ እየተንገበገብክ ስታለቅስም አብራህ አልቅሳ ዕንባህን አበሰች፡፡ ሰዎች የሰጡህን ተስፋ ሳይፈጽሙልህና ያለህን አጭበርብረው ባዶህን ስትቀር ያነባኸውን ዕንባ አብራህ አነባች፡፡ ኃጢአትህ መሮህ በተነሳሒ ልቡና ስታለቅስም እያለቀሰች አዛኝቱ አብራህ ነበረች፡፡ ምንም እንኳን መከራህና መገፋትህ ፣ ብቸኝነትህና ሮሮህ ጊዜያዊና ባንተ ማስተዋል ችግር ቢያስለቅስህም እርሷ ግን ዕንባህን ስታብስ አብራህ አለቀሰች፡፡

እንዲህ ነች እንግዲህ አዛኝቱ…

ያኔ “ማርያም ፣ ማርያም” የሚል ምግብ የሆነ ቃልን እየሰማሁ ስወለድ አልቅሼ ነበር፡፡ ለቅሶዬን ሐኪሞች የጤንነት ምልክት ብለው ቢደሰቱም ፣ እናቴና አባቴ በሐሴት ጥርስ በጥርስ ሆነው ሊያቅፉኝ ቢጓጉም ፣ የከበቡኝ ሁሉ እልል እያሉ ወደ ምድራቸው መምጣቴንና የጤንነቴን ለቅሶ ቢያጅቡም ፣ ርኅርኅቷ እናቴ ግን “ጨቅላ ነው” ሳትል ፣ “የጤንነት ምልክት ነው” ሳትል…ዐዋቂዎቹ ሳያዩኝ እኔን ከማጫወቷ በፊት ከማኅፀን ስወጣ የተሰማኝ ስሜት ተሰምቷት አብራኝ አለቀሰች፡፡ በልጅነት ዕድሜዬ የሚያስለቅሱኝ ነገሮች በበዙ ቁጥር “ልጅ ነው” ብላ ሳትንቀኝ አብራኝ አልቅሳ ዕንባዬን ታብስ ነበር፡፡ ርኃብ አንጀቴን አጥፎት ይሉኝታ ባስለቀሰኝ ጊዜም አብራኝ አልቅሳለች፡፡ የምፈልጋቸውን አላገኘሁም ብዬ ልጇን በለቅሶ ባማረርኩ ጊዜ እንኳን ዕንባዬን በዕንባዋ አብሳ አካሔዴን አስተካክላለች፡፡ የብቸኝነት ክረምት ውጦኝ ፀሐየ ሰብእን በማጣት አንገቴን ደፍቼ ሳለቅስም ከእኔ ጋር ለማልቀስ እርሷ መች ሰለቸችኝ…?“ ለምን እኔን ” ብዬ ስማጸን የዐይነ ልቡናዬን የሐዘን ፈሳሽ ለማበስ እርሷ መች ተወች? የቀረቡኝን ሳጣቸው ፣ ወንድምነት ትርጉሙ ሲጠፋኝ ፣ እኅትነት ቅኔ ሲሆንብኝ ፣ አባትነት ረቂቅ ፣ እናትነትም ተስፋ ሆነው ቀርተው ሳነባ ውስጠ ውስጠቴን ተረድታ በእኔ ስሜት እኔን ዐውቃ አብራኝ አነባች እንጂ፡፡ ብቻ ለኔ ብቻ የተተወውን ጸጋ ከማየቴ በፊት በጅምላ ሳነባ ጸጋዬን ከማሳየቷ በፊት አብራኝ በጅምላ አነባች - አዛኝቱ ፣ ርኅርኅቱ ፣ ቅድስቲቱ ፣ ንጽህቲቱ ፣ አማላጅቱ…፡፡

እናም ወዳጄ ሆይ…የምታለቅስልህን እያት ፣ የምታመለክትህን ያንተን ብቻ ጸጋ ተመልከትላት ፤ ይህን ካደረክ እንደ ቶማስ ያየኸውን ሔደህ ለወዳጆችህ ትነግራለህ፡፡ “ሳለቅስ በተመለከተችኝ ጊዜ አለቀሰች” ማለት ትችላለህ፡፡ ከዛ በፊት ግን በምልጃዋ ታያት ዘንድ አንቺን ማየት አልቻልኩም በላት፡፡ እርሷም እንድትመለከታት ትገለጽልሀለች፡፡ ከዛም ብዙ ስግደትን ስገድላት፡፡ እርሷም ልብህን የሚኮረኩር ምሥጢር ትነግርሀለች፡፡ አንተም ታለቅሳለህ፡፡ ስታለቅስ በተመለከተች ጊዜም አብራህ ታለቅሳለች፡፡

የአዛኝቱ ክብር ይገለጽልን ዘንድ የቅዱስ ቶማስ ምልጃ አይለየን


#ሼር
__

#share #share ⤵️

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
....... የቀጠለ 👆👆👆

ከዚህ በኋላ ሥዕሏን ከገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባለው ገዳም ወስደው በዘመነ ጽጌ፤ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጧት፡፡ የምትከብርበትንም ቀን ጥቅምት ሦስት እና ሰኔ ስምንት ቀን አደረጉ፡፡ ጽጌ ብርሃንንም ለመዓርገ ምንኩስና አበቁት፡፡ አባ ጽጌ ብርሃን ጽጌ ድንግል የሚለው ቅጽል ስሙ ነው፡፡ አባ ጽጌ ብርሃን/ ጽጌ ድንግል ከመጠመቁ በፊት በአባቶቹ በአይሁድ ሥርዓት እያለ የብሉያት መጻሕፍትን የተማረ ነበር የሐዲሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ ግን የተማረው ከአቡነ ዜና ማርቆስ ነበር በማኅሌት አገልግሎት ጊዜም ታላቁ ፃድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተክርስቲያኒቱንና ሥዕሏን እየዞረ ሲያጥን፤ እመቤታችን የካህናቱን አገልግሎት እነደምትባርክ ካህናቱ በግልፅ ይረዱ ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በተወለዱ በ140 ዓመታቸው ዓርብ ጠዋት ታኅሳስ ሦስት ቀን 1402 ዓ.ም. ዐረፉ፡፡

ከዚህ በኋላ አባ ጽጌ ብርሃን በወሎ ክፍለ ሀገር በወራይሉ አውራጃ፤ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ ለሚባለው ገዳም የሕግ መምህር ሆኖ ከተሾመውና ከጓደኛው ከአባ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ በጎ መዐዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት፤ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሰ፡፡

አባ ጽጌ ድንግል/ጽጌ ብርሃን/ እና አባ ገብረ ማርያም የዘመነ ጽጌን የማኅሌት አገልግሎት በጋራና በፍቅር ያገለግሉ ነበር፡፡ አንዱን ዓመት አባ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በኾነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ አባ ጽጌ ድንግል ካለበት ደብረ ብሥራት ገብቶ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ አገልግሎት በአንድነት ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብረ ሐንታ ይመለሳል፡፡ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ አባ ጽጌ ድንግል ወደ አባ ገብረ ማርያም ይሄዱና በአንድነት በፍቅር ያገለግላሉ፡፡ የአባቶቻችን የአቡነ ዜና ማርቆስ፤ የአባ ጽጌ ብርሃን እና የአባ ገብረ ማርያም ረድዔት ሳይለየን ከዘመነ ጽጌ አገልግሎት በትጋት እንድንሳተፍ ያድርገን! አሜን፡፡

#ምንጭ :- ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ
የማኅሌተ ጽጌ ትርጉምና ታሪክ፤ ሊቀ ጠበብት አስራደ ባያብል

#ሼር
__

#share #share ⤵️ 
  @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
✥ አባቶቻችን እንዲህ አሉ ✥

💦"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

💦"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

💦"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ

💦"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ" አባ ስምዖን

💦"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

💦"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን

💦"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" አባ ቴዎዶር

💦"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

💦"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

💦ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::

💦"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ [ If you don’t forgive, forget heaven]

#ሼር
__

#share #share ⤵️

@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
​​በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

#ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#ሼር
@zekidanemeheret
​​​​በምስሉ ላይ የምታዮት ቅዱስ ያሬድ ይባርክበት የነበረው የእጅ መስቀሉ በ1985 ዓ.ም በሆድ አደር ሌቦች አማካኝነት ተሰርቆ ከሀገር ወጥቶ ነበር።

በፈረንሳይ ሀገር ለጨረታ ቀርቦ በ15 ሚሊዮን ዶላር ተሸጦ ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሰርቆ ከወጣ ከ18 ዓመት በኃላ በ2003 ወደ አገራችን ተመልሶ መጥቷል።

ሊመለስ የቻለውም "ሚስተር ዣክ" የተባሉ በጎ አሳቢ ሰው "...ይህን መስቀል ኢትዮጵያ ውስጥ ጎብኝቼዋለሁ፣ የኢትዮጵያ ንብረት ነው" በማለት ወደ ሀገራችን እንዲመለስ ከሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልጆች ጋር በተደረገ ርብርብ ጨረታውን በ15 ሚሊዮን ዶላር አሸንፈው የአቡነ ያሬድን የእጅ መስቀል ወደ አገራችን መልሰውታል። አምላከ ቅዱስ ያሬድ
ክብር ያድልልን በእውነት!

#ሼር

@zekidanemeheret
ፖርኖግራፊ ምንድነው ?
ክፍል 2
በኤርሚያስ ኪሮስ
የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች
1ኛ.ከፍተኛ ፍላጎት
አንድ ሰው ሱስ ደረጃ ላይ ከደረሰ ለፖርኖግራፊ ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል ። በውስጡ የማያቋርጥ ፍላጎት ይቀጣጠላል ። በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰዓት ፖርኖግራፊን መመልከት ይፈልጋል ። ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከትበትን ጊዜ እየጨመረ ይመጣል ።በሳምንት ያይ የነበረ በቀን ፣ በቀንም አንዴ ያይ የነበረው ሁለቴ ማየት ከጀመረ ፣ በፖርኖግራፊም የሚያጠፋውም ጊዜ እያደገ ከመጣ ፤ በሚመለከትበት ጊዜ የሚሰማው መነቃቃት እና ደስታ በሀፍረት ፤፡ጥፋተኝነት ስሜት እና ፀፀት ሲተካ ነገሩ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል
2ኛ.ለማቆም አለመፈለግ / አለመቻል
ሱስ ውስጥ የገባ አንድ ሰው ፖርኖግራፊ መመልከቱን ማቆም አይፈልግም ።፡ሱስ እንደሆነና ችግር መሆኑን እንኳን መቀበል አይፈልግም ። ይህም የሚሆነው ሱስ ውስጥ ስለገባና ከዛ ህይወት ቢወጣ ሌላ የሚያዝናናው ነገር ሊያገኝ እንደሚችል ስለማያምን ነው ። በሌላ መልኩ ለማቆም እየፈለጉ አለመቻልም የሱሰኝነት ማሳያ ነው ። እዚህ ጋር አንድ ወንድም በድምፅ ባስቀመጠልኝ መልዕክት ውስጥ እኔ ከፖርኖግራፊ ሕይወት ለመውጣት ከ100 ጊዜ በላይ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር ፤ ነገር ግን ተመልሼ እዛው ሕይወት ውስጥ እገኛለው ብሎኛል። ይህ ንግግር የሚያሳየው ከባድ የሆነ ሱስ ውስጥ መግባቱን ሲሆን እየተጸየፍነውም የምናደርገው ነገር ሱስ፡እንደሆነብን ያሳያል ።
3ኛ. በሌላ ነገር ደስታ አለማግኘት
አንድ ሰው ወደዚህ ሱስ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ያስደስቱት የነበሩትን ነገሮች ለምሳሌ ከቤተሰብና ከወዳጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ፤ ወደ ሃይማኖት ስፍራ መሄድ ፣ስፖርት መስራት ፣ ፊልም ማየት ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወ.ዘ.ተ በመተው ደስታውን ሙሉ ለሙሉ በፖርኖግራፊ ላይ ካስቀመጠ ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ እንደገባ ያሳያል ።
4ኛ.ከተፅዕኖው ጋር መቀጠል
በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ ሰው በሱሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣ እያወቀ ፣ ህይወቱ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን እየተረዳ በዛው ከቀጠለ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል ።
5ኛ.ሚስጥራዊነት
በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለ ሰው ህይወቱን አጠገቡ ካሉ እና ከሚወዳቸው ሰዎች ምሥጢር ከማረጉ የተነሳ ድብቅ እና ሁለት ገፅታ ያለው ባይተዋር ሰው እንደሆነ ይሰማዋል ። ምሥጢሩም እንዳይጋለጥ ያያቸውን ድህረ ገፆች በማጥፋት ፣ የት እና ምን ያደርግ እንደ ነበር ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ሰዎችን ይዋሻል ። የሚሰማውንም ሀፍረት ለመሸፈን በማስመሰል ህይወት ውስጥ ይዘፈቃል ።
6ኛ. ኃላፊነትን አለመወጣት
ብዙ ሰዓታትን በፖርኖግራፊ ከማሳለፋ የተነሳ በአግባቡ ስራን አለማከናወን ፣ የቤተሰብ ፣ የማህበራዊና መንፈሳዊ ኃላፊነቶችን መወጣት አለመቻል እና ገለልተኝነት ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል
7ኛ.የፀባይ መቀያየር
በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ በጣም ብስጩ ፣ ቁጡና እና በጥቂት ነገር የሚናደዱ ይሆናሉ ። ከላይ የጠቀስናቸውን ዋና የሚባሉትን የሱስ ምልክቶች የሚታዩባቸው ሰዎች ቆም ብለው ራሳቸውን አይተው ዕርዳታ ካልፈለጉ ለፖርኖግራፊ ሱሶች መዘዞች ይጋለጣሉ
... ይቀጥላል
ብዙ ሰው በዚህ ችግር ተጠቅቷልና በየግሩፑ #ሼር_አርጉት

🕊👉 @zekidanemeheret

https://t.me/zekidanemeheret
ፖርኖግራፊ ምንድነው
ክፍል 5
በኤርሚያስ ኪሮስ
ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጫ መንገዶች

1.እግዚአብሔር እንደሚወዳችሁ አውቃችሁ ንስሐ ግቡ፦

በዚህ ሱስ ውስጥ የገቡ ሰዎች እግዚአብሔር እንደሚጠላቸውና እንደሚፀየፋቸው ያስባሉ ። እንዲህ አይነቱ ሃሳብ ሰዎችን የሱሱ ባሪያ አድርጎ ለማኖር ሰይጣን ይጠቀምበታል ። በፖርኖግራፊ ሀጢአት መውደቅን ተከትሎ ሰይጣን ሁልጊዜ እዛው ተብትቦ ሊያስቀረን ይጥራል ። ይህም ራሳችንን እንድንጠላ ፣ እግዚአብሔር ለእኛ ግድ እንደማይለውና ሩቅ እንደሆነ እንድናስብ እና ተስፋ ቢስነት እንዲሰማን ሀሳባችንን በመያዝ ይተጋል ። ሁሌም ቢሆን ውድቀትን ተከትሎ ዋና ጠላታችን ማን እንደሆነ ማወቁ ተገቢ ነው ። በጥፋታችን ማዘናችን ተገቢ ቢሆንም እንደ ይሁዳ ወደ ከፋ እርምጃ የሚወሰድ መሆን የለበትም (ማቴ 27:4) ራሳችንን በመጥላት ውስጥ ዋዥቀን ራሳችንን የመቅጣት አዝማሚያው ቢኖረንም መውሰድ ያለብን እርምጃ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ዳዊት በንስሃ መደፋት ነው ። (መዝ 51:1) በእኛና በኃጢአታችን መካከል ልዩነት አለ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል ፤ ኃጢአተኛውን ግን ይወዳል እናት የልጅዋ ልብስ ቢቆሽሽ ለልጅዋ ያላት ፍቅር እንደማይቀየር እግዚአብሔርም ለእኛ ያለው ፍቅር አይቀየርም "የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነፃል " (1ዮሐ 1:7) የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለ ዓለም ሁሉ ስለፈሰሰ በእግዚአብሔር ፊት ይቅር የማይባል ኃጢያት የለም። ንስሐ ግቡ!

2.አምናችሁ ጸልዩ

የሰው ልጅ በራሱ ጥረት ከኃጢአት መውጣት አይችልም ። የእግዚአብሔር ፀጋ ሲያግዘው ግን የማይቻለውን ችሎ በቅድስና አሸብርቆ መኖር ይችላል ። እስከ ዛሬ በግል ጥረታችሁ ከዚህ ሱስ መውጣት ስላልቻላችሁ ተስፋ ቆርጣችሁ ሊሆን ይችላል ። ጸጋው ግን ጣልቃ ገብቶ አዲስ ህይወት ሊሰጣችሁ ይችላል ። ይህ ደግሞ የሚሆነው "እኔ ደካማ ስለሆንኩ የሚረዳኝ ጸጋ ይሰጠኝ " ብሎ በጸሎት እግዚአብሔርን በመለመን ነው ። በፀሎት ትጉ (ኤፌ 6:18) መውጣት እንደሚቻል አለማመን በራሱ ሰንሰለት ነው ።፡የእግዚአብሔር ፀጋ ታሪክን እንደሚቀይር ከዚህ ህይወት መውጣት እንደሚቻል እመኑ ። ምክንያቱም ከኀጢአት አውጥቶ ቅዱስ የሚያደርግ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጧልና ። (ቲቶ2:11)

.... ይቀጥላል
#ሼር ይደረግ

🕊👉 @zekidanemeheret

https://t.me/zekidanemeheret
​​​​ጾመገሀድ
በየኔታ ዘለዓለም ሐዲስ

ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት ስለሆኑ ነው።

እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡

ገሀድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሀድና ጋድ፡፡ #ገሀድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል።

በሌላም በኩል #ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡

ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ከመ ይደሉ ንጹም እሎንተ ክልኤተ ዕለታተ ዘእምቅድመ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት እስመ እላ ዕለታት ህየንቴሆሙ ለረቡዕ ወዓርብ ሶበ ይከውን ላዕሌሆሙ በዓለ ልደት ወጥምቀት ወበዝንቱ ይትፌጸም ለነ ክልኤቱ ግብር ግብረ ጾም ወግብረ በዓል ወከመዝ ሥሩዕ ውስተ አብያተ ክርስቲያኖሙ ለግብፃውያን ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ ዐርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት በከመ ተናገርነ ቅድመ ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሀል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ፡፡

ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው በይረሙን (መገለጥ፣ ገሀድ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዓርብ እስከምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ በማለት ይገልጸዋል፡፡

ከላይ እንዳየነው ጥምቀት ወይም ልደት እሑድና ቅዳሜ ከዋሉ ጾሙ መጀመር ያለበት ዓርብ መሆኑን ተመልክተናል ይህንም መነሻ በማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ሰኞ ሲሆን ዓርብ እስከ አንድ ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ስድስት፣ እሑድ እስከ ቅዳሴ መውጫ እስከ ሦስት በመቁጠር የጾሙን ሰዓት 13 ሰዓት ያደርጉታል ይህም ከላይ የተገለጠውን ስንክሳር መነሻ በማድረግ የመሚናገሩት ስለሆነ አክብረን እንቀበለዋለን ቅዳሜ እስከ ስድስት ለመጾሙም ሃይ ምዕ 20 ተጠቃሽ ነው።

በሌላ በኩልም ጋድ አንድ ቀን ነው ሰኞ ሲሆን እሑድን ብቻ ከጥሉላት እንከለከላለን እንጅ ቅዳሜን አይጨምርም በማለት ይህን የሚቃወሙ አሉ ስንክሳር የተናገረውን ምን እናድርገው ተብለው ሲጠየቁም ስንክሳር የታሪክ እንጅ የሥርዓት መጽሐፍ አይደለም የሚል መልስ ነው የሚሰጡት፡፡

ይህ ጥያቄ ወደሌሎች ሊቃውንት ሲቀርብ የሚሰጡት መልስ ደግሞ ስንክሳር ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም የተካተተበት መጽሐፍ መሆኑን ይናገራሉ በእርግጥ ስንክሳር ማለት እስትጉቡእ ስብስብ ማለት ስለሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስተቲያንን ከሠሩ አበው ታሪክ የተሰበሰበ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ከላይም እንዳየነው ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ስለዚህ አባቶቻችን አዘዙን በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጻፉ አበው አዘዙን አለ እንጅ ስንክሳርን የጻፉ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ያንጸባረቁበት አይደለም ስንክሳርም ቢሆን ምንም ቁጥሩ ከአዋልድ መጻሕፍት ቢሆን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነውና ጥምቀትና ልደት ሰኞ ከሆኑ ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት ተከልክለን ቅዳሜንም እስከ ስድስት ሰዓት ጹመን የአበውን ትዕዛዝ ማክበር አለብን፡፡

በሌላም በኩል ጋድ አንድ ነው እሱም የጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው የልደት ዋዜማ የለውም የሚሉም አሉ እንዲህ ለሚሉት መልሱ አጭር ነው ጾመ ነቢያት ስንት ነው የሚል ጥያቄ ማንሣት ነው እንደሚታወቀው ጾመ ነቢያትን ስንጾም ቀናቱ አርባ አራት ናቸው 40 ጾመ ነቢያት፣ 3ቱ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርት የጾሙትና አብርሐም ሦርያዊ ተራራ ያፈለሰበት ጾም፣ አንዱ ጾመ ገሀድ ነው ስለዚህ በበዓለ ልደት ዋዜማ የምንጾመው ገሀድ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡

ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተግሳፁ አንዳስቀመጠው "ስለ ፆም ክርክር በተነሳ ጊዜ ሁሌም ቢሆን ለፆም አድሉ "

"" መልሱ እንዲህ ከምስክር መምህራን ሲሆን ይሻላል፡፡ እኛ ከምንናገረው፡፡

የኔታ ዘለዓለም ሐዲስ ማለት የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ምክትልና የ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ መምህር ናቸው፡፡ (እንዲያው የኔ ብጤ የፌስቡክ አርበኛ እንዳይመስሉህ ብዬ ነው!)

DN YORDANOS ABEBE

❤️ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ❤️

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

#ሼር
Audio
"ቴክስት እና መንፈሳዊ ሕይወት "

የሴቶች ጉዳይ ክፍል 1 በመምህር አቤል ተፈራ

comment @zekidanemeheretbot

🕊👉 @zekidanemeheret

#ሼር አድርጉት።