ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
858 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
🇪🇹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሦስት ቀን ሱባኤ እንዲያዝ መንግሥትን ጠየቀች🇪🇹

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገራችን የተከሠተው በሳይንስ መድኃኒት ያልተገኘለት ኮቪዲ-19 ኮሮና ቫይረስ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእመቤታችን ቃል ኪዳን ከአገራችን እንዲወገድ የነነዌ ሰዎች ከንጉሡ ጀምሮ ከዙፋን ወርደው፣ ሕፃናት ጡት ከመጥባት፣ እንስሳቶች ከእናታቸው ከመገናኘት ተከልክለው ለሦስት ቀን በመጸለያቸው የሚያቃጥል እሳት ከሰማይ ከወረደ በኋላ ከኃጢአት መመለሳቸውን ዓይቶ እንደተመለሰ በአገራችን የተከሠተው ወረርሽኝ እንዲወገድ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጀምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሩን ዘግቶ የሦስት ቀን ሱባኤ እንዲይዝ መንግሥትን ጠየቀች።
#ምንጭ፦ ማህበረ ቅዱሳን

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
....... የቀጠለ 👆👆👆

ከዚህ በኋላ ሥዕሏን ከገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባለው ገዳም ወስደው በዘመነ ጽጌ፤ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጧት፡፡ የምትከብርበትንም ቀን ጥቅምት ሦስት እና ሰኔ ስምንት ቀን አደረጉ፡፡ ጽጌ ብርሃንንም ለመዓርገ ምንኩስና አበቁት፡፡ አባ ጽጌ ብርሃን ጽጌ ድንግል የሚለው ቅጽል ስሙ ነው፡፡ አባ ጽጌ ብርሃን/ ጽጌ ድንግል ከመጠመቁ በፊት በአባቶቹ በአይሁድ ሥርዓት እያለ የብሉያት መጻሕፍትን የተማረ ነበር የሐዲሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ ግን የተማረው ከአቡነ ዜና ማርቆስ ነበር በማኅሌት አገልግሎት ጊዜም ታላቁ ፃድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተክርስቲያኒቱንና ሥዕሏን እየዞረ ሲያጥን፤ እመቤታችን የካህናቱን አገልግሎት እነደምትባርክ ካህናቱ በግልፅ ይረዱ ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በተወለዱ በ140 ዓመታቸው ዓርብ ጠዋት ታኅሳስ ሦስት ቀን 1402 ዓ.ም. ዐረፉ፡፡

ከዚህ በኋላ አባ ጽጌ ብርሃን በወሎ ክፍለ ሀገር በወራይሉ አውራጃ፤ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ ለሚባለው ገዳም የሕግ መምህር ሆኖ ከተሾመውና ከጓደኛው ከአባ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ በጎ መዐዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት፤ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሰ፡፡

አባ ጽጌ ድንግል/ጽጌ ብርሃን/ እና አባ ገብረ ማርያም የዘመነ ጽጌን የማኅሌት አገልግሎት በጋራና በፍቅር ያገለግሉ ነበር፡፡ አንዱን ዓመት አባ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በኾነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ አባ ጽጌ ድንግል ካለበት ደብረ ብሥራት ገብቶ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ አገልግሎት በአንድነት ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብረ ሐንታ ይመለሳል፡፡ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ አባ ጽጌ ድንግል ወደ አባ ገብረ ማርያም ይሄዱና በአንድነት በፍቅር ያገለግላሉ፡፡ የአባቶቻችን የአቡነ ዜና ማርቆስ፤ የአባ ጽጌ ብርሃን እና የአባ ገብረ ማርያም ረድዔት ሳይለየን ከዘመነ ጽጌ አገልግሎት በትጋት እንድንሳተፍ ያድርገን! አሜን፡፡

#ምንጭ :- ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ
የማኅሌተ ጽጌ ትርጉምና ታሪክ፤ ሊቀ ጠበብት አስራደ ባያብል

#ሼር
__

#share #share ⤵️ 
  @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret