ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
ፖርኖግራፊ ምንድነው ?
ክፍል 2
በኤርሚያስ ኪሮስ
የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች
1ኛ.ከፍተኛ ፍላጎት
አንድ ሰው ሱስ ደረጃ ላይ ከደረሰ ለፖርኖግራፊ ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል ። በውስጡ የማያቋርጥ ፍላጎት ይቀጣጠላል ። በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰዓት ፖርኖግራፊን መመልከት ይፈልጋል ። ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከትበትን ጊዜ እየጨመረ ይመጣል ።በሳምንት ያይ የነበረ በቀን ፣ በቀንም አንዴ ያይ የነበረው ሁለቴ ማየት ከጀመረ ፣ በፖርኖግራፊም የሚያጠፋውም ጊዜ እያደገ ከመጣ ፤ በሚመለከትበት ጊዜ የሚሰማው መነቃቃት እና ደስታ በሀፍረት ፤፡ጥፋተኝነት ስሜት እና ፀፀት ሲተካ ነገሩ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል
2ኛ.ለማቆም አለመፈለግ / አለመቻል
ሱስ ውስጥ የገባ አንድ ሰው ፖርኖግራፊ መመልከቱን ማቆም አይፈልግም ።፡ሱስ እንደሆነና ችግር መሆኑን እንኳን መቀበል አይፈልግም ። ይህም የሚሆነው ሱስ ውስጥ ስለገባና ከዛ ህይወት ቢወጣ ሌላ የሚያዝናናው ነገር ሊያገኝ እንደሚችል ስለማያምን ነው ። በሌላ መልኩ ለማቆም እየፈለጉ አለመቻልም የሱሰኝነት ማሳያ ነው ። እዚህ ጋር አንድ ወንድም በድምፅ ባስቀመጠልኝ መልዕክት ውስጥ እኔ ከፖርኖግራፊ ሕይወት ለመውጣት ከ100 ጊዜ በላይ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር ፤ ነገር ግን ተመልሼ እዛው ሕይወት ውስጥ እገኛለው ብሎኛል። ይህ ንግግር የሚያሳየው ከባድ የሆነ ሱስ ውስጥ መግባቱን ሲሆን እየተጸየፍነውም የምናደርገው ነገር ሱስ፡እንደሆነብን ያሳያል ።
3ኛ. በሌላ ነገር ደስታ አለማግኘት
አንድ ሰው ወደዚህ ሱስ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ያስደስቱት የነበሩትን ነገሮች ለምሳሌ ከቤተሰብና ከወዳጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ፤ ወደ ሃይማኖት ስፍራ መሄድ ፣ስፖርት መስራት ፣ ፊልም ማየት ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወ.ዘ.ተ በመተው ደስታውን ሙሉ ለሙሉ በፖርኖግራፊ ላይ ካስቀመጠ ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ እንደገባ ያሳያል ።
4ኛ.ከተፅዕኖው ጋር መቀጠል
በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ ሰው በሱሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣ እያወቀ ፣ ህይወቱ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን እየተረዳ በዛው ከቀጠለ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል ።
5ኛ.ሚስጥራዊነት
በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለ ሰው ህይወቱን አጠገቡ ካሉ እና ከሚወዳቸው ሰዎች ምሥጢር ከማረጉ የተነሳ ድብቅ እና ሁለት ገፅታ ያለው ባይተዋር ሰው እንደሆነ ይሰማዋል ። ምሥጢሩም እንዳይጋለጥ ያያቸውን ድህረ ገፆች በማጥፋት ፣ የት እና ምን ያደርግ እንደ ነበር ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ሰዎችን ይዋሻል ። የሚሰማውንም ሀፍረት ለመሸፈን በማስመሰል ህይወት ውስጥ ይዘፈቃል ።
6ኛ. ኃላፊነትን አለመወጣት
ብዙ ሰዓታትን በፖርኖግራፊ ከማሳለፋ የተነሳ በአግባቡ ስራን አለማከናወን ፣ የቤተሰብ ፣ የማህበራዊና መንፈሳዊ ኃላፊነቶችን መወጣት አለመቻል እና ገለልተኝነት ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል
7ኛ.የፀባይ መቀያየር
በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ በጣም ብስጩ ፣ ቁጡና እና በጥቂት ነገር የሚናደዱ ይሆናሉ ። ከላይ የጠቀስናቸውን ዋና የሚባሉትን የሱስ ምልክቶች የሚታዩባቸው ሰዎች ቆም ብለው ራሳቸውን አይተው ዕርዳታ ካልፈለጉ ለፖርኖግራፊ ሱሶች መዘዞች ይጋለጣሉ
... ይቀጥላል
ብዙ ሰው በዚህ ችግር ተጠቅቷልና በየግሩፑ #ሼር_አርጉት

🕊👉 @zekidanemeheret

https://t.me/zekidanemeheret