#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_1
#የካቶሊክና_የኦርቶዶክስ_ተዋህዶ#ልዩነት
ካቶሊክ ማለት ሁሉ ለሁሉ ማለት ነው ። 1ኛ.በካቶሊኮች ዘንድ ከአንገት በላይ መጠመቅ በቂ ነው ብለው ያምናሉ ። አዋቂዎችም ልብሳቸውን እንዲያወልቁ አይገደዱም ። ፨ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግን የምትቀበለው ልብስን አውልቆ ሙሉ ጥምቀትን ነው ።እኛ ኦርቶዶክሶች ጥምቀትን ስንጠመቅ በመረጨት ወይም ውሃ በማፍሰስ ሳይሆን ሰውነትን እስኪያጠልም ድረስ በመነከር በሥላሴ ስም 3 ጊዜ ከውሃ ብቅ ጥልቅ በማድረግ የሚፈፀም አገልግሎት ነው ። 2ኛ.የካቶሊክ ቄስ ሚስት አያገባም ። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ የካቶሊክ ካህን ድንግላዊ ሆኖ መኖር አለበት ፣ ሚስት አያገባም ። የኦርቶዶክስ ቄስ ግን ሚስት ማግባት ወይም አለማግባት ይችላል ።ሚስት ካገባ ግን ሚስቲቱ ቀድማ አግብታ ባሏን የፈታች መሆን የለባትም ። 3ኛ.ፆምን በተመለከተ በካቶሊክ ዘንድ ስጋ ከመብላት መቆጠብ ነው ።እንደ ኦርቶዶክስ ከሆነ ግን ወተትና እንቁላል ክልክል ነው ።ካቶሊኮች እሮብና አርብን አይፆሙም ። የሚፆሙት ቅዳሜ ነው ። ፆምን በገንዘብ እንቀይራለን እያሉ ገንዘብ በመስጠት ፆምን ችላ ይላሉ ። እኛ እሮብን የምንፆመው የአይሁድ ሸንጎ ጌታን አርብ እለት ለመስቀል ምክረ ሞቱን የፈጸሙበት እለት ነው ።አርብ ደሞ ጌታ የተሰቀለበት በስጋ የሞተበት ብዙ ዘመን ሲጠበቅ የነበረው ተስፉ የተፈፀመበት ቅዱስ እለት ስለሆነ ነው ።4ኛ.ካቶሊኮች ለምዕመናን የሚያቀብሉት ስጋውን ብቻ ነው ።ይህን ለማለት ያስቻላቸው ምክንያት ስጋው ደም አለው የሚል አስተሳሰብ ስላላቸው ነው ።በኦርቶዶክስ አመለካከት ግን ስጋውና ደሙ መለያየት የለበትም ። " እንካችሁ ይህ ስጋዬ ነው ፤ እንካችሁ ይህ ደሜ ነው " ብሎ ስጋውንና ደሙን ለይቶ ሰጥቷቸዋልና "።5ኛ.ካቶሊኮች የሚቆርቡት ከምግብ በሁዋላ ነው ።ኦርቶዶክስ ግን ከመቁረባችን በፊት 18 ሰዓት ድረስ እንፆማለን ። 6ኛ.ካቶሊኮች ፓፓውን /ጳጳሱን/ አይሳሳቱም ይላሉ ።የሮማ ጳጳስ በምድር ላይ የክርስቶስ እንደራሴ ነው ። ባለ ሙሉ ስልጣንም ተደርጎ ይቆጠራል ። እንዲሁም የክርስቲያኖች ማእከል መዲና ኢየሩሳሌም ሳትሆን ሮማ ቫቲካን ናት ይላሉ ። በእኛ በኦርቶዶክሶች ግን ፓትሪያሪኩ ሰው ነው ይሳሳታል ። ስለዚህ ከባድ ውሳኔዎች በመንፈሳዊ ጉባኤ (ሲኖዶስ) ይወሰናሉ ። 7ኛ.ካቶሊኮች ድንግል ማርያምን ከአዳም የተወረሰ ሀጥያት የለባትም የሰው ወገን የአዳም ዘር ሳትሆን ከጠፈር የተገኘች ሃይለ አርያማዊት (ሰማያዊት) ናት ይሏታል ።ኦርቶዶክስ ግን ድንግል ማርያም ለምክንያተ ድሂን ወደ እዚህ አለም የመጣች የቅ/ኢያቄምና ሐና ልጅ ናት ። 8ኛ.ካቶሊኮች መንፈስቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ይሰርፃል ይላሉ ። በኦርቶዶክስ ግን መንፈስቅዱስ ከአብ ሰረፀ እንላለን ። "ለእናንተ የምልከው ከአብ ዘንድ የእውነት መንፈስ ከአብ የሰረፀ "(ዮሀ 15:26) 9ኛ.ካቶሊኮች አንድ አካል ሁለት ባህሪ ነው ይላሉ ።የአብ ልጅ ሌላ የማርያም ልጅ ሌላ ብለው ነጥለው ያምናሉ ። ተዓምር ሲያደርግ እውር ሲያበራ ሙት ሲያስነሳ የአብ ልጅ ነው ሲፈራ ሲራብ ሲፀልይ ደሞ የማርያም ልጅ ነው ብለው ነጣጥለው ያምናሉ ። ኦርቶዶክስ ግን በፍፁም ተዋህዶ የከበረ ነው እንላለን ።ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህሪ አንድ ባህሪ ብለን እናምናለን ። 10ኛ.ካቶሊኮች ታቦት /ጽላት/ የላቸውም ። ታቦት ህጉ ጽላተ ኪዳኑ የላቸውም ። እነሱ ያላቸው "ሜንሳ"( mensa) የሚባል ነው ። ጠረጴዛ ማለት ነው ። 11ኛ.ካቶሊኮች ኃጢያት ማስተስረያ ካርድ አላቸው ። እንደነሱ እምነት ይህንን ካርድ የገዛ ከማንኛውም ኃጢአት ነፃ ነው የሚል አመለካከት አላቸው ። በኦርቶዶክስ ግን ሀጢያት የሚያስተሰርየው ከድንግል ማርያም የተወለደውን ኢየሱስን አምኖ ንስሀ መግባት ሲቻል ነው ። 12ኛ..ካቶሊኮች በገሃነም (በእሳት መንጵሄ) "Purgatory" ያምናሉ ። ይህም ማለት ቀኖናዋን ሳትጨርስ የተለየች ነብስ በገሃነመ እሳት ገብታ ከተቃጠች በሁዋላ ኃጢያቷን ስትጨርስ መንግስተ ሰማያት ትገባለች ። የዚህን የስቃይ ዘመን ለማሳጠር ደግሞ ገንዘብ በመክፈል ቤተክርስቲያን እንድትፀልይለት ማድረግ ይቻላል ። 13ኛ.ካቶሊኮች አዳም ጸጋውን አልተለውም በጥንተ አብሶ ባህሪው ጎሰቆለ እንጂ ይላሉ ። 14ኛና የመጨረሻው የሚገለገሉበት የጎርጎርዮስ ካላንደር ነው ።እኛ መስከረም 1 ስንል እነሱ መስከረም 8 ይላሉ ። ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ምንጭ= ኰኲሕ ሐይማኖት
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret

#ክፍል_2
#ፕሮቴስታንት /ጴንጤ /
ፕሮቴስታንት ተቃዋሚ ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል የተወሰደ ነው ። ይህም ሊሆን የቻለው የካቶሊክ ፓፓ የነበረው አቡነ ሊዎ አስረኛ የቅ/ጴጥሮስን ትልቅ ቤተክርስቲያን ለማሰራት በማሰቡ መንግስተ ሰማያት መግቢያ ብሎ ካርድ መሸጥ ጀመረ ። ማርቲን ሉተር ግን መንግስተ ሰማያት በክርስቶስ እንጂ በካርድ አይገባም ብሎ ተነሳ ።ይባስ ብሎም 90 ነጥቦችን ነቅሶ አውጥቶ ለጠፈላቸው ። ተቃዋሚ ሲሉትም ፕሮቴስት አሉት እሱን የተከተሉትን ደግሞ ፕሮቴስታንት አሏቸው ። አሁን ደሞ እስቲ ልዩነታችንን እንያቸው #1ኛ.ፕሮቴስታንት የንስሀ አባት አያስፈልግም ይላሉ ። ኦርቶዶክስ ግን ከ7ቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ በመሆኑ ከታላቅ አክብሮት ጋር ትገለገልበታለች ። ጌታችን በወንጌል "ኃጢያቱን የተዋቹለት ቀረችለት ፡ "የያዛችሁበትም ተያዘችበት " በማለት አስተምሯልና ። (ዮሀ 20:23 ማቴ 16:19)። ደሞ በፕሮቴስታንት ሴቶች ስልጣነ ክህነት ሊኖራቸው ይችላል ። በኦርቶዶክስ ግን አይቻልም ። ጌታ የመረጣቸውና ስልጣነ ክህነትን የሰጣቸው ለወንዶች እንጂ ለሴቶች አይደለም ። #2ኛ. ፕሮቴስታንቶች የእምነት መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ይላሉ ። ይህም ማለት በቤተክርስቲያን ሊቃውንት መፃህፍትና ሲወርድ በመጣው ቤተክርስቲያናዊ ትውፊትና አዋልድ መፃህፍት ላይ እምነት የላቸውም #3ኛ.ፕሮቴስታንቶች የቅዱሳን አማላጅነት አያስፈልግም ይላሉ ። ኦርቶዶክስ ግን ቅዱሳንን በተሰጣቸው ቃልኪዳን መሰረት ያማልዳሉ ብላ ታምናለች ። #4ኛ.ፕሮቴስታንቶች ጥምቀት እግዚአብሔርን ለማምለክ ምልክት እንጂ ድኀነት አያስገኝም ይላሉ ። በኦርቶዶክስ ግን በክርስቲያናዊ ህይወት የመጀመሪያ መግቢያ በር በመሆኑ ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባትና ሚስጥራትን ለመካፈል አስፈላጊ መሆኑን ታምናለች #5ኛ.ፕሮቴስታንቶች ቁርባን መታሰቢያ እንጂ የክርስቶስ ሥጋና ደም አይደለም ይላሉ ።ኦርቶዶክስ ግን መለኮት የተዋሀደው ነብስ የተለየው ቁርባን አማናዊ የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው ትላለች #6ኛ.ፕሮቴስታንቶች ለመዳን ማመን ብቻ በቂ ነው ስራ አያስፈልግም ይላሉ ።ኦርቶዶክስ ግን እምነትና ምግባርን ነጣጥላ አትመለከትም ። ስራ የሌለው እምነት ነብስ የተለየው ስጋ ነው የሞተ ነው ትላለች ። #7ኛ.ፕሮቴስታንቶች መፅሀፍ ቅዱስን ሁሉም በሚገባው መልኩ መተርጎም ይችላል ይላሉ ። ኦርቶዶክስ ግን ማንም እንደፈለገውና እንደመሰለው እንዲተረጉም አትፈቅድም ።ወስብሀት ለእግዚአብሔር ። የአባቶቻችን የተባረከች በረከታቸው ፡ ርትዕት ሀይማኖታቸው ፡ ጥርጥር የሌላት ድል የማትነሳ እምነታቸው ከኛ ትሁን ለዘለአለሙ አሜን ።

#ክፍል_3
#የይሖዋ_ምስክሮች /ጆቫ ዊትነስ/ *
የይሖዋ ምስክሮች የተባለው የሃይማኖት ተቋም በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በቻርልስ ራስል የተመሰረተ ሲሆን ራስል ቀደም ባሉት ጊዜያት ክርስቲያን የነበረ ሲሆን በኀለኛው የወጣትነት ዘመኑ በአርዮሳውያን የኑፉቄ ትምህርትና በሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት እንዲሁም በአንዳንድ የክህደት ትምህርት (Atheists) አራማጆች ተፅዕኖ ስር ወደቀ ። እ.ኤ.አ በ1872 አካባቢ ከነዚህ የተበረዙና የተዛቡ አስተምህሮዎች በመነሳት ራስል የራሱን አስተምህሮ (Doctrine) በመቅረፅ በአሜሪካ ውስጥ ለማሳተም ቻለ ።እስቲ ጥቂት እምነታቸውን እንመልከት #1ኛ .ጆቫዎች ቤተክርስቲያንና የአለም መንግስታት ሁሉ የሰይጣን ስራ ውጤቶች ናቸው ብለው ያምናሉ #2ኛ.ዜጎች በወታደራዊ ተቋማት እንዳይገቡ ያደርጋሉ ። ለሰንደቅ አላማ የክብር ሰላምታ መስጠትን እንደ ባዕድ አምልኮ አድርገው ይቆጥሩታል #3ኛ. የሰው ነብስ ትሞታለች ብለው ያምናሉ #4ኛ.የሰው ልጅ ከትንሳኤ ቡሃላ ገነት በምትሆነው ምድር ለዘላለም ይኖራል /ምድር ገነት ትሆናለች/ ብለው ያምናሉ #5ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ክርስቶስን ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ሳይሆን መለኮታዊ ባህሪ ያለው ንዑስ አምላክ ነው ብለው ያምናሉ #6ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ሰብአ ሰገል በቤተልሔም በጌታችን ፊት ያደረጉት ስግደት የማይገባና የመራቸውም ኮከብ ከሰይጣን የተላከ እንደሆነ ያምናሉ ። #7ኛ.ጆቫዎች ክርስቶስ አስቀድሞ በሰማይ ከተፈጠረ በኀላ በዚያው ኗሯል ፡ ወደ ምድር እንዲመጣ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማም ስለ ይሖዋ መንግስት ለመመስከር ነው ይላሉ ። #8ኛ.የይሖዋ ምስክሮች የዳግም ልደቱ መጀመሪያ በሚሆነው ጥምቀቱ ለእግዚአብሔር ልጅነት የተሾመ ነው በዚህም የአብ መንፈሳዊ ልጅ በመሆን የይሖዋ መንግስት ገዢ /ንጉስ/ ሆኗል ብለው ያምናሉ ። #9ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ መላዕክት ሚካኤል ነው ብለውም ያምናሉ ። #10ኛ.የይሖዋ ምስክሮች የሰው ልጅ በስጋ ሲሞት ነፍሱም አብራ ትሞታለች። ዘላለማዊነት የይሖዋ ብቻ የተለየ ባህሪ ነው ብለው ያምናሉ ። #11ኛ. የይሖዋ ምስክሮች ኃጢያተኞች ከፃድቃን ተለይተው እንደሚጠፉ እንጂ በሲኦል የሚሰቃዩ መሆናቸውን አይቀበሉም ። ሌላው ቀርቶ ሰይጣን ይጠፉል እንጂ አይሰቃይም አባታችን አዳምም አንዴ ስለሞተ ትንሳኤ አያገኝም ይላሉ ። #12ኛ .መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አንዱ አካል ሳይሆን የይሖዋ ሀይል ነው ብለው ያምናሉ ። #13ኛ. በብዙ ትንሳኤ ያምናሉ ።ማለትም የታናሽ መንጋ ትንሳኤ ፣ምድራዊ ትንሳኤ ፣ የይሖዋ ምስክሮች አባል ላልሆኑትና ፃድቅ ለሆኑት የሚደረግ ትንሳኤ ብለው ትንሳኤን ከፉፍለው ያምናሉ። ወስብሀት ለእግዚአብሔር ።የአብ ፀጋ ፡ የወልድ ቸርነት የመንፈስቅዱስ ህብረት አንድነት ከኛ ጋር ይሁን ለዘለአለሙ አሜን

#ክፍል_4
#ማስተማር_የማን_ተግባር_ነው ?
ዛሬ በፕሮቴስታንት ሐይማኖት ውስጥ የሴት ምህራን ወይም ሰባኪያን እያየን ነው ። ግን ማስተማር #የሐዋርያት ተግባር ነበር ። ከዚያም የእነርሱ ደቀመዛሙርት ለሆኑ ፣ ጳጳሳት ዲያቆናት ተግባር ሆነ ነገር ግን ምእመናን አስተምረው አያውቁም ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይህንኑ ሲያረጋግጥልን "እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዝኀችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ #እያስተማሯችኀቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ። ( ማቴ 28:19) እንደገናም "ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ #ስበኩ ። (ማር 16:15) ብሏል ። ጌታችን #ማስተማርን ለሐዋርያት ሥራ አድርጎ ሰጠ እንጂ ይህንን ሥልጣን ለማንም አልሰጠም ። ሐዋርያት ቃሉን ሊሰብኩ ሊያስተምሩ ፣ ሊያገለግሉና እምነቱን ለሌሎች ሊያስተምሩ ተመርጠው ነበር ። ሰባቱን ዲያቆናት በካኑበት ጊዜ ሐዋርያው "እኛ ግን ለጸሎትና #ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን " ብሏል ። ስለ ጌታም ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ "በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን አሁን ግን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቷል ። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ #ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም #አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት ወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋት ወደ ብርሃን አውጥቷል ። (2ኛ ጢሞ 11) በመሆኑም ሐዋርያት ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት እያስተማሩና እየሰበኩ ኖሩ ።
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የማስተማርና የስበከት ተግባር ለደቀመዛሙርቱ አደራ ሲሰጥ ለጢሞቲዎስ " #ቃሉን ስበክ በጊዜውም አለጊዜውም ፅና ፈፅመህ እየታገስህና እያስተማርህ ዝለፍና ገስፅ ምከርም " (2ጢሞ ዠ4:2) አለው ።
በተጨማሪም ለደቀ መዝሙሩ ለቲቶም "ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገስጽም ማንም አይናቅህ " (ቲቶ 2:15) አለው ። ካህናት በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ስለሚያስተምሩ ወይም ስለሚቀድሱ ብቻ አይደለም ። ነገር ግን በንስሐና በመሳሰሉት ሁሉ መንፈሳዊ እንደራሴዎች ስለሆኑ ጭምር መምህራን ሊሆኑ ይገባቸዋል ። ምዕመናን ደግሞ ሁልጊዜ በተማሪዎች ቦታ ሆነው ሊማሩ ይገባል። እምነት ፣ ሥርዓትና ትውፊት በመንፈስቅዱስ የሚተረጎሙ የቤተክርስቲያን ሕይወት ናቸው ። ሰባኪያን በእምነትና በባህል ሃይማኖት ሽፋን የራሳቸውን አመለካከት ሊያስተምሩ አይገባም ። በመሆኑም ካሁን ቡሃላ በተከታታይ በእኛ እና በፕሮቴስታንት መካከል ስላለው ልዩነት በሰፊው እናያለን።
#ሼር

#ክፍል_5
#በጥምቀት_ላይ_ያለ_ልዩነት
#የጥምቀት_ጥቅሙ_ምንድነው ?
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በጥምቀት ድህነትን ፣ መንጻትን ፣ ፍትህን ፣ አዲስ ሕይወትንና በክርስቶስ ክርስቲያን መሆንን ያስገኛልን ? ወይስ እንደ ፕሮቴስታንት እምነት እነዚህ ሁሉ በማመን ብቻ ይገኛሉ ? በማመን ብቻስ ከሆነ ለምን መጠመቅ ያስፈልጋል ? #ማጥመቅ_የሚችለው_ማነው ?
በኦርቶዶክስ ማጥመቅ የካህናት ተግባር ነው ። ነገር ግን በፕሮቴስታንቶች ዘንድ በ ክህነት ጨርሶ አይታመንም ። ስለዚህ በቤተክርስቲያናቸውም ጥምቀት በተራ ሰው እንጂ በካህናት ፈፅሞ አይደረግም ። አጥማቂው ሴትም ወንድም ሊሆን ይችላል ። እኛ ግን #ጥምቀትን ከሚስጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው ብለን እናምናለን። ፕሮቴስታንቶች ግን ይህንን አያምኑም ። እኛ ውሃ ውስጥ እናጠምቃለን እነርሱ ግን በመርጨት ያጠምቃሉ ።እኛ ህፃናትን ስለቤተሰቦቻቸው እምነት እናጠምቃለን ፡ ፕሮቴስታንቶች ግን ሕፃናትን በማጥመቅ አያምኑም ። ምክንያት ሲሰጡም "ከጥምቀት ማመን መቅደም አለበት "ይላሉ። #የጥምቀት_ጥቅሞች
መዳን በጥምቀት የተሟላ ይሆናል ። ጌታችን "ያመነ የተጠመቀም ይድናል " ብሎ አስተምሮናል ። /ማር 16:16/ ጌታችን ያመነ ይድናል አላለም ነገር ግን ከማመን ጎን ለጎን የመጠመቅንም ነገር አስቀመጠ እንጂ ። #በጥምቀት ከውሃና ከመንፈስ የሆነውን ሁለተኛውን ልደት እናገኛለን ። #ጥምቀት ኃጢያትን ያስወግዳል ። "አሁንስ ለምን ትዘገያለህ ተነሳና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኀጢአትም ታጠብ ። " አለው ። (ሐዋ 22-16) ከዚህ እንደምናየው የመጠመቅ አንዱ ውጤት ከኀጢአት መታጠብ ነው ። #ጥምቀት ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብሮ መሞትና አብሮ መነሳት ነው ።መፅሐፍ "ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን ? (ሮሜ 6:3) አለ። በቆላስያስ መልእክቱ "በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀብራቹ በጥምቀት ደግሞ ከሙታን ባስነሳው በእግዚአብሔር አሰራር በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሳችሁ ። /ቆላ.2:12/
ሌላው የጥምቀት ጥቅም #በጥምቀት ክርስቶስን ለብሰነዋል/መስለነዋል ። ጳውሎስ "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኀልና " /ገላ3:27/ የጥምቀትን ታላቅ ጥቅም ሊገልፅ የሚችል ከዚህ የተሻለ ቃል አለን ? በጥምቀት በደሙ የሆነውን ክርስቶስን ለበስነው ፤ ጽድቁንም በጥምቀቱ የተሰጠንን ድኀነትንም እንዲሁ ለበስነው ። "ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር " /ዘፍ 1:26/ ብሎ በቀደመ በደላችን ያጣነውን እግዚአብሔርን መምሰልን ተላበስን ። በቀጣይ ደሞ ለምን#በ40እናበ80ቀን እንጠመቃለን የሚለውን እናያለን ።

#ክፍል_6
#የ40ቀንና_የ80ቀን_ጥምቀት
አብዛኛውን ጊዜ በፕሮቴስታንቶች በኩል ጥምቀት ላይ የሚያነሷቸው ሁለት ነገሮች ናቸው ። #አንደኛ ፦ ሕፃናት መጠመቅ የለባቸውም የሚል ሲሆን #ሁለተኛው ደሞ እምነት እንጂ ጥምቀት አያድንም የሚል ነው ። በማር 16:16 ላይ ያለውን በመጥቀስ አንድ ሰው አምኖ መጠመቅ አለበት እንጂ ሳያምን ፣ ሳያውቅ ቢጠመቅ ምን ይረባዋል ? ይላሉ ። በመሰረቱ " ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል "የሚለው ይህ ቃል ላመኑት ሳይሆን ላላመኑት የተነገረ ነው ። በተለይም ወደ ዓለም በሚሄዱበት ሰዓት ሐዋርያት አገልግሎታቸው የቀና ይሆን ዘንድ ያላመኑት ማመን ስለሚያስፈልጋቸው ነው ። ለቃሉ መነሻ የሆነው ጥቅስ እንዲህ ይነበባል "... ተነስቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውን የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ " (ማር 16:16) አለማመናቸውን ለመንቀፍ ጌታ የተናገረውን ቃል ሕፃናትን መጠመቅ የለባቸውም ብሎ ከሚያምን ቤተሰብ የተገኙትን ህፃናት ላይ እንዳይጠመቁ መፍረድ ክፋ ሀጥያት ነው ። እንደውም መፅሐፍ ቅዱስ ጥምቀተ ሕፃናትን አይቃወምም እንደውም ይደግፈዋል። ለዚህም ማረጋገጫችን ጌታችን " ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው " ብሏል ። /ማቴ19:14/ ታዲያ ይህን እውነት ይዘን ስንጓዝ ወደ ብሉይ ኪዳን መለስ ብለን እናስተውለዋለን ። ይህም በዘሌ 12 ላይ ከቁ 1 - 8 ስናነብ ይህንኑ የወንድ ልጅና የሴት ልጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ የሚገባቸውን ጊዜ እንዲህ በማለት ገልፆታል ። "ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት። በስምንተኛው ቀን ከሥጋው ሸለፈት ይገረዝ ከደምዋም እስክትነፃ 33 ቀን ትቀመጥ ይላል ። 7 እና 33 ስንደምራቸው #40 ቀን ይሆናል ። #ለወንድ ልጅ ይህንን ብሏል ። #ለሴት ልጅ ደሞ 2 ሳምንት ያህል የረከሰች ናት ከደምዋም እስክትነፃ ድረስ 66 ቀን ትቀመጥ ይላል ።14 እና 66 ስንደምራቸው #80 ቀን ይሆናል ። በመፅሐፈ ኩፋሌ 4:9 ላይ ደሞ "እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረው በ40 ቀኑ ሔዋንን በፈጠራት በ80 ቀኗ መላዕክት ዕፁብ ዕፁብ እያሉ ገነት እንዳስገቧቸው ይናገራል ። ቤተክርስቲያን ይሄን ምክንያት በማድረግ ወንድ በ40 ቀን ሴት በ80 ቀን ታጠምቃለች ። ነገር ከ40 ቀን በተለያየ ችግር ምክንያት ቢያልፍ መጠመቅ አይችልም ማለት አይደለም ። ከዛ በፊትም የከፋ ለሞት የሚያደርስ ህመም ቢያጋጥመው እንዲጠመቅ ፍትሐ ነገስት ያዛል ።
#የአጠማመቅ_ሥርዓታችንና_ፍቺው
ዲያቆኑ ሕፃኑን ይዞ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ እክህደከ ሰይጣን በማለት 3 ጊዜ ይናገራል ። ይህም ሰይጣንን እክደዋለው ማለት ነው ።
እንደገና ፊቱን ወደ ምስራቅ ሕፃኑን እንደያዘ ይመልስና አአምን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ በማለት 3 ጊዜ ከተናገረ በኀላ ወደማጥመቂያው ያቀርበዋል። ይህም በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አምናለው ማለት ነው ። "በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጥምቁ " ብሎ እንዳዘዘው ነው ። (ማቴ 28:19)
ምንጭ ። ኰኲሕ ሐይማኖት
ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
ኢዮአታም