#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር
#ክፍል_5
#3የሰንበትን_ቀን_ትቀድሰው_ዘንድ_አስብ
🖊 የቃሉ ትርጉም አቆመ አረፈ ማለት ነው ። ይህ ማለት የሰው ልጅ ከጌታ ጋር የሚቀራረብበት መገናኛ መንገድ ነው ። ከማንኛውም ስጋዊ ተግባር የምናርፍበት ፣ ትርጓሜው የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናስታውስ የሚያደርግበት ቀን ነው ።
🖊 #ሰንበት የመንግስተ ሰማይ ምሳሌ ነች። የሰው ልጅ በዓለም ሠርቶ ወርዶ በመልካም ሥራው የሚያርፍበት ቦታ ናት ።
🖊ሰው ዕረፍት ያስፈልገዋል የሰንበት ቀን የተፈጠረውም ለዚህ ነው ። የሰንበት ቀን የዕረፍት ቀን ስለሆነ የሚከተሉትን ሁለት ነገሮች ያሳስበናል ።
#፩ኛ ሰው በኀጢአት ከመውደቁ በፊት ከአምላኩ ጋር ያለውን ግንኙነት የነበረውን ዕረፍት
#፪ኛ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን ዘላለማዊ የነፍስ እረፍት ።
🖊በሐዲስ ኪዳን ሰንበት ሁለት ናቸው #ቅዳሜና_እሁድ ። #ቅዳሜ ማለት የበፊቷ የቀደመችው ማለት ነው ። #እሑድ ማለት ደግሞ መጀመሪያ 🖊ስለሆነ ከዚህ ጀምረን ስንቆጥር ቅዳሜ ሰባተኛ ቀን ይሆናል ። በ፫ኛው ትዕዛዝ እንዲከበር የታዘዘው ይህ ቀን ነው ። ፈሪሳውያን በሰንበት ቀን እግር ከዘረጉ አያጥፉም ፣ ከአጠፉም አይዘረጉም መልካምም ሥራ ቢሆን አይሰሩም ።
#እሑድ ሥነፍጥረት የጀመረበት ፣ ኀላም ጌታ የተነሳበት፣ መንፈስቅዱስ የወረደበት እንዲሁም ጌታ የሚመጣበት ዕለት ነው ። ስለዚህ እናከብረዋለን ። በቤተክርስቲያን ታሪክ ደግሞ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ቀን ስለሆነች ሥራ እንዳይሰራ በ፫፻፳፩ ዓ-ም በሕገመንግስቱ አፅድቆ እንዳወጀና እንደወሰነ ይነገራል ። ስለዚህ ሰንበት የእረፍት ቀን ነው ስለተባለ ሥራ ፈተን መዋል የለብንም ። በእግዚአብሔር ቤት በመገኘት ማስቀደስ ፣ ቃሉን መማር ፣ መዘመርና ማመስገን አለብን ። ከዚህም ሌላ ጌታ በሰንበት መልካም ሥራ ማድረግ ተፈቅዷል ስላለ የታመመና የታሰረ መጠየቅ ፣ የተጣላ ማስታረቅ ፣ ያዘነ ማፅናናት ፣ ለተቸገረ ደግሞ ምፅዋት መመፅወት አለብን ። እንግዲህ በክርስትና ሰንበት የሚከበረው እንዲህ ነው ።
🇪🇹ሠንበትን ለምን እናከብራለን
፩ ፦ከቀናት ሁሉ ተለይታ ለበረከት ለቅድስና ለማመስገን ትሆን የተፈጠረች ነች
፪ ፦ሰውን ስለ ወደደ ለዕረፍት የሠራት ቀን ናት
፫ ፦በእግዚአብሔር ና በህዝብ መካከል ምልክት ናት
፬ ፦የሚያምን ከማያምን መለየት ኩፋ ፫÷፭-፱
፭ ፦እግዚአብሔር አምላክ ለህዝቡ የሠጠው የመጀመሪያው ህግ ናት ዘፍ፲፮÷፳፫
ይቀጥላል...
Share👇share👇share
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret