#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_5
#በጥምቀት_ላይ_ያለ_ልዩነት
#የጥምቀት_ጥቅሙ_ምንድነው ?
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በጥምቀት ድህነትን ፣ መንጻትን ፣ ፍትህን ፣ አዲስ ሕይወትንና በክርስቶስ ክርስቲያን መሆንን ያስገኛልን ? ወይስ እንደ ፕሮቴስታንት እምነት እነዚህ ሁሉ በማመን ብቻ ይገኛሉ ? በማመን ብቻስ ከሆነ ለምን መጠመቅ ያስፈልጋል ? #ማጥመቅ_የሚችለው_ማነው ?
በኦርቶዶክስ ማጥመቅ የካህናት ተግባር ነው ። ነገር ግን በፕሮቴስታንቶች ዘንድ በ ክህነት ጨርሶ አይታመንም ። ስለዚህ በቤተክርስቲያናቸውም ጥምቀት በተራ ሰው እንጂ በካህናት ፈፅሞ አይደረግም ። አጥማቂው ሴትም ወንድም ሊሆን ይችላል ። እኛ ግን #ጥምቀትን ከሚስጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው ብለን እናምናለን። ፕሮቴስታንቶች ግን ይህንን አያምኑም ። እኛ ውሃ ውስጥ እናጠምቃለን እነርሱ ግን በመርጨት ያጠምቃሉ ።እኛ ህፃናትን ስለቤተሰቦቻቸው እምነት እናጠምቃለን ፡ ፕሮቴስታንቶች ግን ሕፃናትን በማጥመቅ አያምኑም ። ምክንያት ሲሰጡም "ከጥምቀት ማመን መቅደም አለበት "ይላሉ። #የጥምቀት_ጥቅሞች
መዳን በጥምቀት የተሟላ ይሆናል ። ጌታችን "ያመነ የተጠመቀም ይድናል " ብሎ አስተምሮናል ። /ማር 16:16/ ጌታችን ያመነ ይድናል አላለም ነገር ግን ከማመን ጎን ለጎን የመጠመቅንም ነገር አስቀመጠ እንጂ ። #በጥምቀት ከውሃና ከመንፈስ የሆነውን ሁለተኛውን ልደት እናገኛለን ። #ጥምቀት ኃጢያትን ያስወግዳል ። "አሁንስ ለምን ትዘገያለህ ተነሳና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኀጢአትም ታጠብ ። " አለው ። (ሐዋ 22-16) ከዚህ እንደምናየው የመጠመቅ አንዱ ውጤት ከኀጢአት መታጠብ ነው ። #ጥምቀት ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብሮ መሞትና አብሮ መነሳት ነው ።መፅሐፍ "ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን ? (ሮሜ 6:3) አለ። በቆላስያስ መልእክቱ "በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀብራቹ በጥምቀት ደግሞ ከሙታን ባስነሳው በእግዚአብሔር አሰራር በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሳችሁ ። /ቆላ.2:12/
ሌላው የጥምቀት ጥቅም #በጥምቀት ክርስቶስን ለብሰነዋል/መስለነዋል ። ጳውሎስ "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኀልና " /ገላ3:27/ የጥምቀትን ታላቅ ጥቅም ሊገልፅ የሚችል ከዚህ የተሻለ ቃል አለን ? በጥምቀት በደሙ የሆነውን ክርስቶስን ለበስነው ፤ ጽድቁንም በጥምቀቱ የተሰጠንን ድኀነትንም እንዲሁ ለበስነው ። "ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር " /ዘፍ 1:26/ ብሎ በቀደመ በደላችን ያጣነውን እግዚአብሔርን መምሰልን ተላበስን ። በቀጣይ ደሞ ለምን#በ40እናበ80ቀን እንጠመቃለን የሚለውን እናያለን ።
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret