ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
825 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ዳግም_ትንሣኤ

ዳግም ትንሣኤ ሲባል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሞቶ፣ ተቀብሮ፣ ተነሳ ሳይሆን በድጋሜ ቅዱስ ቶማስ ባለበት ልክ በመጀመሪያ እንደተገለጠላቸው ሆኖ ስለታያቸው ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአስሩ ሐዋርያት ሲገለጥላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልነበረምና መጥቶ በተገናኛቸው ጊዜ እነሱም ጌታችን እንደተነሳና ተገልጦ ሰላምታ እንደሰጣቸው ሲነግሩት የተቸነከረውን እጁን እና እግሩን በጦር የተወጋ ጎኑን ካላየሁ አላምንም በማለቱ (ዮሐ 20፥25) እንደገና ተገልጦላቸዋል።

ቶማስ ይሄንን ሊል የቻለው የተጠራው ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉት ከማያምኑት ከሰዱቃውያን ወገን ነበርና ነው። አንድም ሌሎች ሐዋርያት ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ አየነው እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብዬ ላስተምር ነው ብሎ ነው። ጌታም የቶማስን ጥርጣሬ ያስወግድለት ዘንድ በተነሳ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ቶማስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ሳለ እንደገና በትንሣኤ እንደታያቸው ሆኖ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ሐዋርያው ቶማስን ለይቶ "ቶማስ ቶማስ ና በችንካር የተቸነከሩ እጆቼን እይ እንዲሁም እጅሀን አምጥተሀ በጦር ወደ ተወጋው ጎኔ አግብተሀ ዳሰኝ ያመንክ እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን ባለው ጊዜ ቶማስም በችንካር የተቸነከሩ እጆቹን በጦር የተወጋ ጎኑን በእጆቹ በዳሰሰ ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ኩምትርትር ሲል "ጌታዬ አምላኬ" አለ። መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤ ማቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ” አለ አምላክነቱንም መሰከረ፡፡ ጌታም  አንተ አይተኽ አምነሃል ነገር ግን" ሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን ናቸው"ብሎ ፈውሶታል (ዮሐ. 20፥29)። (እስከ ዛሬም ይህቺ ጌታን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ እጅ በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ትገኛለች)

በሌላ በኩል ዳግም ትንሣኤ የተባለበት በአከባበር፣ በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡ የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤ በሙሉ በዚህ ቀን ይባላል፡፡

ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም “#ፈጸምነ እና #አግብዖተ_ግብር” ይባላል፡፡ "ፈጸምነ" የተባለበት የሰሙነ ትንሣኤን በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ "አግብዖተ ግብር" የተባለበትም ጌታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ "አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" "እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ" ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ (ዮሐ.17፥4)

https://t.me/zekidanemeheret