ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
798 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
እንኳን ለጾመ ሐዋርያት አደረሳችሁ አደረሰን።

ጦምን ለመሻር ጥቅስ አያስፈልግም

☞አንዳንድ ሰዎች ሕግን ለመጣስ: ጦምን ለመሻር: ሥርዓቱንም ለማፍረስ ሲፈልጉ "ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ አያረክስም . . ." ዓይነት ያልተረዱትን ጥቅስ ይጠቅሳሉ:: ወይም ደግሞ ለጾም "የሽማግሌ": "የቄስ": "የመነኮስ": "የሕጻን" . . . የሚል ስምን ይለጥፋሉ::

+ግንኮ! . . . ሕግን ለመጣስ ከሕግ መጽሐፍ ባልተገባ መንገድ መጥቀስ አያስፈልግም:: ጦመንም ለመሻር የማታለያ ምክንያቶችን መደርደር ግብዝ (አላዋቂ) ቢያሰኝ እንጂ ሌላ ትርፍ አይኖረውም::

ለምሳሌ:-

☞አንድ ሰው ሒሳብ (Mathematics) ትምሕርት "ይከብደኛል: አልችለውም . . ." ከፈለገም "አልማርም" ሊል መብቱ አለው:: "የሒሳብ ትምሕርት አያስፈልግም: አይጠቅምም" ሊል ግን ፍጹም አይችልም:: (ቢልም አላዋቂነቱን ይገልጣል)

+እንደዚሁም ሁሉ አንድ ሰው "መጾም ይከብደኛል: አልችልም . . ." ከፈለገም "አልጾምም" ሊል ይችላል:: (እንዲህ ብሎ ክርስቲያን መሆን ባይችልም)

+ምክንያቱም እንኩዋን ምግባራት አምልኮም ቢሆን በፈቃድ (በነጻነት) የሚፈጸም ጉዳይ ነውና:: #እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ነውና ማንንም አያስገድድም::

+ነገር ግን . . . ያ ሰው "ጾም ይከብደኛል: አልጾምም . . ." ለማለት መብቱ ቢኖረውም "ጾም አያስፈልግም" ሊል ግን መብቱ ሊኖረው አይችልም:: (ቢልም የሰይጣን የግብር ልጅ ከመሆን ሌላ ትርፍ አይኖረውም)

+ሰው (በተለይም #ክርስቲያን) ለድኅነት: ለበጐነትና #ለቅድስና ይጠቅሳል: ምክንያትንም ይፈጥራል እንጂ #ቅዱስ_ቃሉን እያጣመመ የጥፋትን መንገድ አይጠርግም::

+እኛ ግን:-
¤#ነቢያትን (ዘጸ. 24:18, ዘዳ. 9:9, 1ነገ. 19:8, ዳን. 10:2, መዝ. 108, 109:24)
¤#ሐዋርያትን (ሐዋ. 13:2)
¤#ጻድቃን_ሰማዕታትን: #ደናግል_መነኮሳትን (#ገድላተ_ቅዱሳን) . . . አብነት አድርገን ለድኅነት እንጦማለን::

+ይልቁኑ ግን ከክብር ባለቤት #ከመድኃኒታችን_ክርስቶስ አብነትን ነስተን (ማቴ. 4:1): ትምሕርቱን ሰምተን: ለሕይወት እንጦማለን:: "ስትጦሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ" እንዳ ለጌታችን:: (ማቴ. 6:16)

=>#ቸር_አምላከ_ቅዱሳን መዋዕለ ጦሙን #የበረከትና_የአኮቴት ያድርግልን::

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>