፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
2.19K subscribers
2.76K photos
41 videos
355 files
163 links
ይህ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ህጋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official Channel of 6 kilo Gibi Gubae.
በግቢ ጉባኤው ላይ ያለዎትን አስተያየት ወይም ጥያቄ በ @fesehatsion12 ወይም @Hoping7 ላይ ይላኩልን።
Download Telegram
"ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ" መዝ 118÷25
እንኳን ደስ አላችሁ።
እነሆ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ለ2011 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ልዩ መርሐግብር አዘጋጅቷል።
በመርሐግብሩም
1. ሙሉ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ ተማሪዎች የጋራ የፎቶ ፕሮግራም
2. ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች በማይመረቁ ተማሪዎች የተዘጋጀ የፍቅር ማዕድ(አጋፔ)
3.ሥነ ጽሑፍ
4. የስጦታ እና በግቢ ውስጥ አብረውን የቆዩ ወንድምና እህቶቻችንን የምናመሰግበት መርሐግብር እና ሌሎች ተካተውበታል

ቀን ፦ሰኔ 2/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30-6:30
ቦታ፦በቅ/ማርቆስ መጠለያ
ዋጋ፦ የእአፔ፣ ለሁሉም ተማሪ በጋራ የተነሳ አንድ ማስታወሻ ፎቶ ማሳጠብያ እንዲሁም የስጦታን ጨምሮ 30 ብር ብቻ

✴️ማሳሰብያ፥ ኩፖኑን #የማይመረቁም ተማሪዎች #መግዛት_ይችላሉ
👉ፎቶ የምንሰጠው ኩፖኑን ለያዘ ተማሪ ብቻ ስለሆነ በመርሐግብሩ ኩፖን ይዘው መምጣት እንዳይረሱ
👉ትኬቱ የሚሸጠው እስከ #ቅዳሜ (ሰኔ 1/2011) ድረስ ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0946349322/0913850267
"ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ" መዝ 118÷25
እንኳን ደስ አላችሁ።
እነሆ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ለ2011 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ልዩ መርሐግብር አዘጋጅቷል።
በመርሐግብሩም
1. ሙሉ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ ተማሪዎች የጋራ የፎቶ ፕሮግራም
2. ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች በማይመረቁ ተማሪዎች የተዘጋጀ የፍቅር ማዕድ(አጋፔ)
3.ሥነ ጽሑፍ
4. የስጦታ እና በግቢ ውስጥ አብረውን የቆዩ ወንድምና እህቶቻችንን የምናመሰግበት መርሐግብር እና ሌሎች ተካተውበታል

ቀን ፦ሰኔ 2/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30-6:30
ቦታ፦በቅ/ማርቆስ መጠለያ
ዋጋ፦ የአጋፔ፣ ለሁሉም ተማሪ በጋራ የተነሳ አንድ ማስታወሻ ፎቶ ማሳጠብያ እንዲሁም የስጦታን ጨምሮ 30 ብር ብቻ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የአደራ ልጆች እንደምን አላችሁ?
✝️ ይህ ዘወትር ማክሰኞ በዚህ ሰዓት ወደ እናንተ የሚደርሰው "እናስተዋዉቃችሁ" የተሰኘ ዓምዳችን ነው፡፡
✝️ ዓምዳችን በየሳምንቱ ስለተለያዩ ገዳማትና አድባራት አንዲሁም ስለቅዱሳን አበውና እማት አስተማሪ ጽሑፎችን ይዞ ይቀርባል፡፡ ባለፈው ሳምንት ወታደርና መነኩሴ ስለነበረው የደብረ ሊባኖስ ቅዱስ አባት አባ ገብረ እንድርያስ አጭር ጽሑፍ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡
✝️ ዛሬም ግቢ ጉባኤያችን በሚቀጥለው #ቅዳሜ/እሑድ (በ 27/28-03-2012 ዓ.ም) ወደ #ደብረ_ሊባኖስ የሚያደርገውን ጉዞ በማስመልከት ይህን ታላቅ ገዳም በአጭሩ ልናስቃኛችሁ ወደድን፡፡ መልካም ቆይታ፡፡
✝️ደብረ ሊባኖስ
ደብረ ሊባኖስ በጥንቱ ግራርያ አውራጃ (በአሁን ስሙ ሰላሌ ) ሸዋ የሚገኝ ጥንታዊ ገዳም ነው። ገዳሙ በመጀመሪያ ደብረ አስቦ ሲባል የአሁን ስሙን የያዘው በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ አነሳሽነት በ፲፬፳፮ ዓ.ም ነው።
👉ስለገዳሙ ምሥረታ
ደበረ ሊባኖስ ገዳም ከሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ አንስቶ ድንቅ ድንቅ ተዓምራት የሚደረጉበት ታሪካዊ ገዳም ነው፡፡ ጌታችን ከእናቱ ጋር በተሰደደበት ጊዜ በኢትዮጵያ መጥተው በቆዩበት ጊዜ ከባረኳቸውና ከቀደሷቸው ቦታዎች መካከል ይህ ቦታ አንዱ ነው፡፡ ወደዚህ ቦታ የመጡት በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ሲሆን በቆይታቸው ጊዜ አዕዋፋት ይመግቧቸው እንደነበር ገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት ይናገራል፡፡ ጌታም በዚህ ቦታ እንደ ኤልያስ ጻድቅ የሆነ ሰው ይኖርበታል ብሎ ስለአቡነ ተክለሃይማኖት ለእመቤታችን ነግሯታል፡፡
✝️ በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን አባ ሊባኖስ የተባሉ ጻድቅ ወደዚህ ገዳም በመምጣት ደብረ አሰቦ ዋሻን ገድመው ለ፵ ዓመታት ከቆዩ በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ይህ ቦታ ከአንተ በኋላ ለሚነሳው አቡነ ተክለሃይማኖት ነውና አንተ ወደ ትግራይ ተመለስ የገዳሙ ስም ግን ፵ ዓመት ተጋድለህበታልና በስምህ ሲጠራ ይኖራል ብሏቸው ወደ ትግራይ ተመልሰዋል፡፡
✝️ በ፲፪፻፷፯ ዓ.ም አቡነ ተክለሃይማኖት ወደዚህ ገዳም በመምጣት ገዳሙን ገድመው ለ፳፱ ዓመታት ከጸለዩ በሗላ ነሐሴ ፳፬ / ፲፪፻፺፮ ዓ.ም አርፈዋል፡፡ በዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት በ፲፬፻፳፮ ዓ.ም በንጉሱ ትዕዛዝ ደብረ ሊባኖስ ተብሎ ተሠይሟል፡፡
✝️ የገዳሙ መነኮሳት ግራኝ ቤተ ክርስቲያኑንና ገዳሙን ባቃጠለ ጊዜ በሃይማኖታዊ ስሜት ከእሳቱ እየገቡ ተቃጥለዋል፡፡ ጣሊያንን ሀገራችንን በወረረችበት ወቅት በ፲፱፻፳፱ ዓ/ም ግንቦት ፲፫ ቀን መነኮሳቱን ከገዳሙ በማውጣት ሽንኩርት በተባለ ቦታ በመትረየስ በግፍ አልቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔርም ለአቡነ ተክለሃይማኖት በሰጣቸው ቃል ኪዳን መሠረት ልጆቻቸውን እንደሰማይ ከዋክብት እንደ ባህር አሸዋ በማብዛት እስካሁን ድረስ ገዳሙን በማክበርና በመጠበቅ ለመላው ኢትዮጵያ ብርሀን በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
✝️ ከገዳሙ ተግባር ቤት ዳቤ፣ንፍሮ፣ወጥና ጠላ የሚዘጋጁ ሲሆን የሚዘጋጁትም የተለያየ ትሩፋት ባላቸው አባቶችና ወንድሞች ዕለት በተቆረጠ የአጋምና ቀጋ እርጥብ ቅጠል ነው፡፡ ሕሙማንም ዳቤውን በመብላት የንፍሮ ውሀውን በመጠጣት ጢሱን በመታጠን ከተለያዩ በሽታዎች ይፈወሳሉ፡፡
✝️ የቀድሞ ስሞች
👉 ኤላሞ ፡ የንጽሕና መገለጫ የድርገት መዉረጃ ምስራቃዊ ወይም ብርሀናዊ ቦታ ማለት ነው፡፡
👉 ግራርያ ፡ ይህን ስም ያወጣችው እመቤታችን ስትሆን ትርጉሙም ግራር የበዛበት ቦታ ማለት ነው፡፡
👉 ደብረ አሰቦ ፡ ተራራማ የድካም መቀበያ ቦታ ማለት ነው፡፡

✝️ የገዳሙን ዋና ሕንፃ ከኢትዮጵያ ነገሥታት ብዙዎቹ ያማረ በመሰላቸው፤ ጊዜያቸው በፈቀደላቸው ጥበብ ሕንፃውን አሠርተዋል። የመጀመሪያውን ሕንፃ ያሳነፁት በ ፲፪፻፷ የነገሡት አጼ ይኩኖ አምላክ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ በ፲፬፻፭
ዓ/ም የነገሡት አጼ ይስሐቅ ነበሩ። እንዲሁም በ ፲፰፻፬ ዓ/ም በ ወሰን ሰገድ ፣ በ ፲፰፻፸፮ ዓ/ም አጼ ዮሐንስ፣ በ፲፱፻ ዓ/ም በ ዳግማዊ ምኒልክ እንደገና ታንጿል፡፡ በመጨረሻ፣ በ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን፣ ከጥልቅ የግንባታ ጥናት በኋላ ተሠርቶ ኅዳር ፱ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ ተመረቀ። ከቅዳሴው በሗላ ፳፬ መድፍ ተተኩሷል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ
#ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማክሰኞ
#ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ
#አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ
#አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ
#ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ
ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ
#ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡