፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
2.19K subscribers
2.75K photos
41 videos
355 files
163 links
ይህ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ህጋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official Channel of 6 kilo Gibi Gubae.
በግቢ ጉባኤው ላይ ያለዎትን አስተያየት ወይም ጥያቄ በ @fesehatsion12 ወይም @Hoping7 ላይ ይላኩልን።
Download Telegram
Forwarded from ♥ ወይኩን ፈቃድከ♥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር
መዝ. 118፥26

🎓🎓🎓🎓እንኳን ደስ አላችሁ🎓🎓🎓🎓

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ማዕከል በአራዳ ጉለሌ ወረዳ ማዕከል ግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል ስር ሲማሩ የነበሩ የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን እሁድ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ላይ ከጠዋቱ ከ2:30 - 7:00 ሰዓት ያስመርቃል። እርስዋም በዕለቱ የመርሐ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

በዕለቱ
➡️ ጸሎተ ወንጌል
➡️ ትምህርት ወንጌል
➡️ የበገና ዝማሬ በተመራቂ ተማሪዎች
➡️ ወረብ በተመራቂ ተማሪዎች
➡️ ቅኔ በተመራቂ ተማሪዎች
➡️ የአደራ መስቀል ለተመራቂ ተማሪዎች

ቦታ: ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል
ቀን: እሑድ ሰኔ 30 ጠዋት 2:30 ጀምሮ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

©አራዳ ጉለሌ ወረዳ ማዕከል
!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር
መዝ. 118፥26

🎓🎓🎓🎓እንኳን ደስ አላችሁ🎓🎓🎓🎓

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ማዕከል በአራዳ ጉለሌ ወረዳ ማዕከል ግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል ስር ሲማሩ የነበሩ የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን እሁድ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ላይ ከጠዋቱ ከ2:30 - 7:00 ሰዓት ያስመርቃል። እርስዋም በዕለቱ የመርሐ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

በዕለቱ
➡️ ጸሎተ ወንጌል
➡️ ትምህርት ወንጌል
➡️ የበገና ዝማሬ በተመራቂ ተማሪዎች
➡️ ወረብ በተመራቂ ተማሪዎች
➡️ ቅኔ በተመራቂ ተማሪዎች
➡️ የአደራ መስቀል ለተመራቂ ተማሪዎች

ቦታ: ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል
ቀን: እሑድ ሰኔ 30 ጠዋት 2:30 ጀምሮ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

©አራዳ ጉለሌ ወረዳ ማዕከል
!
Forwarded from ♥ ወይኩን ፈቃድከ♥
"ዘወትር በንፁሕ ሕሊና እየሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።" መ.ቀሌሜንጦስ 12:22

የአንድነት ጸሎት

🌿የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዘወትር ዓርብ ተሰብስበን የአንድነት ጸሎት የምናደርስበት መርሐግብራችን ነገም እንደተጠበቀ ነው‼️

🌿ስለዚህም ሁላችንም ከጓደኞቻችን ጋር ተቀሳቀሰን በመገኘት የጸሎት መርሐግብሩ ተሳታፊዎች እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃዱ ይሁንልን!

👥ቦታ: ቅዱስ ማርቆስ ወሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
ሰዓት: ጠዋት 12: 00

፮ ኪሎ ጊቢ ጉባኤ
፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! "ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር መዝ. 118፥26 🎓🎓🎓🎓እንኳን ደስ አላችሁ።🎓🎓🎓🎓 በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ማዕከል በአራዳ ጉለሌ ወረዳ ማዕከል ግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል ስር ሲማሩ የነበሩ የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን እሁድ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን…
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️

"የቦታ ለውጥ መኖሩን ስለማሳወቅ"

ለመላው የ2016 ዓ.ም የስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤ ምሩቃን በሙሉ እንኳን በጉጉት ለምንጠብቃት የምርቃት ቀን በሰላም አደረሳችሁ እያልን ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን የሚያዘጋጀው የምርቃት መርሐ ግብር በቦተ ጥበት ምክንያት ወደ ቅዱስ ማርቆስ ወሚካኤል ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት እሑድ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:30 የተዛወረ  መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ/CONGRATULATIONS

የስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤ
Forwarded from ዲ.ን ባህሩ ገመቹ
ሰላም ለክሙ
ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።
             መዝ 118:26

🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
ውድ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
እቺ ቀን ታላቅ ቀን ናት !!ለዚህችን ቀን ለበቃችሁ እህት ወንድሞቻችን እግዚያብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን

እስካሁን በቡዙ ፈተና እና በቡዙ ድካም በእግዚአብሔር ቸርነት ለዚህ በቅታችኅል።
ደስታችሁ ደስታችን ነው!!!
▬▬▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
በግቢ ጉባኤ ሆነን የእግዚአብሔርን ቃል ተመግበን የመንፈስ መጠጥ ጠጥተን በፍቅር ተረዳድተን በአገልግሎት ተግተን በጸሎት ፀንተን በቃሉ ተሰብስበን ኖረን ይኸው ዛሬ ላይ ደርሰናል እናንተም(ተመራቂዎች) ልባችሁ ውስጥ የፃፋችሁትን ፍቅር ይዘናል ያለፈ ሳይሆን ህያው ትዝታንም በልባችን አትመናል!
ከዚህም በኅላ ባለው መንገዳችሁ ሁሌም የሚያስብልን ፈጣርያችን ከናንተ ጋር ይሁን
የወላዲተ አምላክ ምልጃ እና በረከቷ አይለያችሁ/አይለየን
ፍፃሜውን ያሳምርላችሁ!!
በአንዲት ቤ/ክ ውስጥ ብንሆንም በመንፈስ ባንራራቅም በአካል ግን ልንለያይ ነውና ዳግም እግዚአብሔር ፈቅዶ እስክንገናኝ "ሰላም ሁኑ" እንባባል!
🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓


       
  ፮ ኪሎ ጊቢ ጉባኤ
" የምርቃት ክብረ በዓል"
በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ እና
ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ

በአባቶች ቡራኬ



ያስመርቃል!

ታዲያ እርስዎ ቤተሰብዎንና ወዳጅ ዘመዶችዎን በመጋበዝ በደስታዎ ቀን እንዲታደሙ ተጋብዘዋል።

አዘጋጅ:-በማኅበረ ቅዱሳን አራዳ ጉለሌ ወረዳ ማእከል
እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱሰ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ  ዮሐንስ ምልጃና ጸሎቱ ለዘለዓለሙ ከሕዝብ ክርስቲያኑ ጋር ይሁን 
አሜን🙏
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላት፡

መስከረም 26፡ በዓለ ጽንሰቱ
ሰኔ 30፡ በዓለ ልደቱ
መስከረም 2፡ ራሱ የተቆረጠበት
መስከረም 15፡ ነፍሱ ከራሱ የወጣችበት
የካቲት 30፡ ራሱ የተገኘችበት
ሰኔ 2፡ ራሱ በኤልሳዕ መቃብር የተቀበረበት
መስከረም 1፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ
የበረከት በ0ል ያድርግልን
Forwarded from Addisu Teshome
የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለደግ ሚድዋይፍሪ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤያት ያስተማራቸውን 1088 ተማሪዎች አስመረቀ።

በውብሸት መገርሳ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል በአራዳ ጉለሌ ወረዳ ማእከሉ ስር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4ኪሎ፣ 5ኪሎ፣ 6ኪሎ እንዲሁም የማታ እና ለደግ ሚድዋይፍሪ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤያት ያስተማራቸውን 1088 የግቢ ጉባኤ አባላት በዛሬው ዕለት በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤ/ክ አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቆይታቸው በግቢ ጉባኤ የሚሰጡትን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሚገባ የተከታተሉ መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን ከ1088ቱ ተማሪዎች ውስጥ 59ኙ የማዕረግ ተማሪዎች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በምረቃት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ እና የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
@mahibere kidusan Broadcast service
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ውድ የግቢ ጉባኤያችን ልጆች እንዴት ናችሁ?🙏🙏

ግቢ ጉባኤያችን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን በክረምቱ ቤተሰብ መሄድ ለማይፈልጉ(አዲስ አበባ መቆየት ለሚፈልጉ) ተማሪዎች ልዩ የሆነ እድል አዘጋጅቷል::
እድሎችም

👉 አብነት ትምህርት ማስተማር ለምትችሉ
👉 ስነ ምግባር ማስተማር ለምትችሉ (የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር……
👉 መዝሙር ማስጠናት ለምትችሉ

ከላይ👆 በተዘረዘሩት በእያንዳንዳቸው ሶስት(3) ሰው ይፈልጋል

‼️‼️የሚያስፈልጉ ነገሮችና የስራ ሁኔታ
👉 የስራ ጊዜ:- ክረምቱን
👉ሲገቡ interview ይኖረዋል
👉ከአገልግሎት በተጨማሪ የተወሰነ ክፍያ ይኖረዋል
👉 የምዝገባ ቦታ:- ማህበረ ቅዱሳን 4ኛ ፎቅ የልማት ተቋማት/አዲስ አበባ ማዕከል ጽ/ቤት
👉 የምዝገባ ቀን ከ03/11/2016 ጀምሮ እስከ 05/11/2016

ሌሎች መረጃዎች በቦታው ተገኝታችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ

ቀድሞ ለሚመዘገብ እድሉ ሰፊ ስለሆነ ቀድሞ መመዝገብን አትዘንጉ!!!

©፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
🌹እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ለሆኑበት ዕለት በሰላም አደረሰን!🌹
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ

ልደቱ በገሊላ ባሕር ዳር በቤተሳይዳ ሲሆን አባቱ ከሮቤል ነገድ የሆነ ዮና የሚባል ሰው ነው። ሪዛምና በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ የነበረ ይህ ሰው የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ይባላል፣ ይህም በእናቱ ነገድ ስም የወጣለት ነው። በጐልማሳነቱ እድሜም ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሳ በማሥገር ያሳልፍ ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀንም በገሊላ ባሕር አጠገብ ዓሳ በማጥመድ ላይ ሳሉ ጌታችን "ሰው አጥማጆች አደርጋቹ ዘንድ ተከተሉኝ" አላቸው። እነሱም መረባቸውን ትተው፣ ታንኳቸውን ጥለው ተከተሉት [ማቴ ፬ ÷ ፲፰]። በዚህ ጊዜ ስምዖን እድሜው ፶፭  ነበር።

ስምዖን በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን "ማን ትሉኛላችሁ?" ብሎ በጠየቀ ጊዜ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ አለው፣ ይህም በግሪክ ቋንቋ ዐለት ማለት ሲሆን፤ በአርማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል [ማቴ ፲፮ ÷ ፱፰]።

ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ/የምሥጢር ሐዋርያት አንዱ ነው። ይህ ሐዋርያ «ከደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ አለው፣ እንዲሁ ሐዋርያቱንም ወክሎ ይናገር ነበርና» የሐዋርያት አፈጉባኤ ተባለ [ማቴ ፲፬፥፳፪-፴፫ ፣ ዮሐ ፮፥፷፮-፷፰ ]። «መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ የባሕርይ ልጁ መሆኑን መስክሯልና» የመንግስተ ሰማይ ቁልፍ ተሰጠው

ቅዱስ ጴጥሮስ በአራቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ በተቀመጡት የሐዋርያት ዝርዝር ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል። ይህም፤ በሽምግልና አባትነቱ፣ ጌታ በቂሳርያ በሰጠው ቃል ኪዳን፣ የሐዋርያት አፈ ጉባዔ ሆኖ ይናገር ስለነበር፣ በጥብርያዶስ ባሕር በተሰጠው ቃል መሠረት ነው። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መሠረት ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጥኤም፣ በሶርያ፣ በጳንጦን፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በቢታንያ እና በሮሜ ሰብኳል። እንዲሁም ሁለት መልእክታትንም ጽፏል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ

የኪልቂያ ዋና ከተማ በሆነች በጠርሴስ፣ ከዕብራዊያን ዘር፣ ከብንያም ነገድ ተወለደ። የመጀመርያ ስሙ ሳውል ነው። በአባቱ ሮማዊም ነበር [አባቱ የሮም ሰራተኛ ሲሆን፣ ሮማውያን ደግሞ ለሚሰሩላቸው ዜግነትን ይሰጡ ነበርና]። በወጣትነቱም በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀው የገማልያል ትምህርት ቤት ገብቶ፣ የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ጠንቅቆ ተምሯል። በዚህም በ፴ ዓመቱ የአይሁድ ሸንጎ አካል ሆነ። ለኦሪት ከነበረው ቅናት ይተነሳ ክርስቲያኖቸን እጅግ አምርሮ ይጠላ፣ ያሳድዳቸውም ነበር።

በ፴፪ ዓመቱ ከሊቀ ካህናቱ እጅ ክርስቲያኖቸን ሊያጠፋ የሚያስችለውን ደብዳቤ ተቀብሎ፣ ወደ ደማስቆ በመሄድ ሳለ በታላቅ ብርሃን ተመታ። መድኃኒታችንም በብርሃኑ መሃል ተገልጦለት "...አንተ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" ብሎ ተናገረው [ሐዋ ፱፥፩]። በዚያም የሐዋርያው ዓይኖች ማየት ስላልቻሉ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ። በሶስተኛው ቀን ሐናንያ የሚባል ደቀ መዝሙር በጌታ ትዕዛዝ ወደሱ መጥቶ ዐይኑን ፈወሰው፣ አጠመቀውም። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት የጌታን ስም ይሸከም ዘንድ የተመረጠ ዕቃ» ሆነ [ሐዋ ፱፥15]። ብረሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የኦሪትም የወንጌልም ሊቅ የነበር፣ ምድርን ሙሉ ዞሮ ወንጌልን የሰበከ፣ እስከ ሶስተኛው ሰማይ መነጠቅ የቻለ፣ ዐስራ አራት መልእክታትን የጻፈ ድንቅ ሐዋርያ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ነው።
ዕረፍታቸው

በ ፶፬ ዓ.ም ኔሮን በሮም ነገሠ። በ፷፬ ዓ.ም ይህ ንጉስ በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሠየፍ፣ መታረድ እጣ ፈንታው ሆነ። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሰዓት በእሥር ነበርና ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም ተሠይፎ ዐረፈ። ይህን የሰሙት የአግቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች "አንተ ትረፍልን" ብለው ቅዱስ ጴጥሮስ ሮማን ለቅቆ እንዲወጣ አደረጉት። ቅዱስ ጴጥሮስ በመንገዱ እያዘገመ ሳለ አንድ ጐልማሳ መስቀል ተሸክሞ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ። እየቀረበ ሲመጣ ጌታችን መሆኑን ተረዳ። እርሱም "ጌታዬ ወዴት እየተጓዝክ ነው?" አለና ጠየቀው። "ዳግም በሮም ልሰቀል" አለው። በዚህ ሰዓት ቅዱስ ጴጥሮስ አዘነና እንደገና ወደ ሮማ ተመለሰ። በዚያም እኔ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም በማለት ቁልቁል ተሰቅሎ ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም ዐርፈ።

የአባቶቻችን ረድኤት እና በረከት ይደርብን🙏

፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ 
              የተሰጠ መግለጫ

‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ 
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ አበክሮ ይነግረናል፡፡
በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡
ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Forwarded from Ayni ጌታ ሆይ እኔን ከእኔ ጠብቀኝ..አባ አትናቲዮስ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከምሁር እየሱስ ገዳም 1:30 ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው የነጎጀ ( የነጌጃ) ደብረ ምሕረት ወዳጆች ሁላችሁ አደራ አለብን በተለይ ጊቢያት 6,5,4 ኪሎ ጊቢ ጉባኤ ወዳጆቼ ከአባታችን ጎን ሆነን የኛን ትንሽ ( ጥቂት) ሀላፊነት እንወጣ promotion በተለያዩ የ Social Media በመጠቀም ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ተደራሽ በማድረግ ከታሪክ ተወቃሽነት እንዳን ትኬት ለመግዛት 📞0913850267 ይደውሉ
Online ይቁረጡ