፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
2.18K subscribers
2.73K photos
39 videos
354 files
161 links
ይህ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ህጋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official Channel of 6 kilo Gibi Gubae.
በግቢ ጉባኤው ላይ ያለዎትን አስተያየት ወይም ጥያቄ በ @fesehatsion12 ወይም @Hoping7 ላይ ይላኩልን።
Download Telegram
ወየው ወየው ወየው

❖  "አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ

❖  በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ

❖ በአዳም ፊት የህይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋራ የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ ፡ #ወዮ

የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቅር ጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፡ ህሊናም ይመታል ፡ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ፡ ስጋም ይደክማል፡፡

የማይሞተው ሞተ ፡ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ፡ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ ፤ የምትወዱት ሰወች ፈፅሞ አልቅሱለት ፤

❖ ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡

❖ ወየው ወየው ወየው መድሃኒታችን ኢየሱስ ፤

❖ወየው ወየው ወየው ንጉሳችን ክርስቶስ ፤

❖ ወየው ወየው ወየው ፃድቃን ከእንጨት አወረዱት ስጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንፁህ በፍታን አመጡ፡፡

ሞተም ተቀበረም ፤ ሙስና ሳይኖርበት ከሙታን ተለይቶ ፈፅሞ ተነሳ ፤ ከሃጢአት ቀንበርም ነፃ አደረገን ፤ በዚያች ስጋ በመለኮት ሃይል ወደ ሰማይ ወደ ቀደመ አኗኗሩ አረገ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንጋፋው ግቢ ጉባኤያችን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል በታላቅ ድምቀት በትንሳኤ ዋዜማ ሚያዝያ 26 በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።

በመርሐግብሩም ላይ

ሰባኪያነ ወንጌል

፩. ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ
፪. ቀሲስ ዐብይ ሙሉቀን

ዘማርያን

፩. ዘማሪ ሀብታሙ
፪. ዘማሪት ወርቅነሽ ተፈራ

እንዲሁም የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ያከብራል

በዕለቱ የሚኖሩን መርሃ ግብሮች

፩. ፀሎተ ወንጌል በቅዱስ ማርቆስ አባቶች እና በግቢው ዲያቆናት

፪. መዝሙር በተጋባዥ ዘማርያን

፫. ትምህርተ ወንጌል

፬. ስነ ፅሁፍ

፭. ወረብ በማኅበረ ካህናት እና በመዝሙር ክፍል

፮. ቅኔ

፯. ጭውውት

፰. ቃለምዕዳ

በዕለቱም የሚወጣ እጣ ያዘጋጀ ሲሆን እጣውን በመቁረት ግቢ ጉባኤያችሁንም እንድትደግፉ ከበረከቱም ተሳታፊ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን!

1ኛ    በገና                        
2ኛ    Smart phone
3ኛ    Air pod                     
4ኛ    ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል
5ኛ    ነጠላ
                  
በተጨማሪም

ማስተዛዘኛ ለ 5 ሰው ወርሃዊ Voice package
             
ይሄ ሁሉ በ20ብር ብቻ 

ቦታ:- በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ

ሰዓት ⌚️ ከቀኑ 10:00 - 4:30

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
ሰላም ለኩልክሙ

ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ።
በመስቀሉ ሰላምን አደረገ

ትኩረት የሚሻ መልዕክት

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው ዋይዜማ  በሰላም አደረሳችሁ

እግዚአብሔር ቢፈቅድ የትንሣኤው መርሐግብራችን ለማክበር አጭር 
ሰዓታት ቀሩን። 

የዘንድሮው መርሐግብራች ከሌላው ዓመት በተለየ ቀደም ተብሎ 
ከቀኑ 10:30 ላይ የሚጀመር !


ይህም የሆነበት ምክንያት መርሐግብራችንን ቶሎ ጨርሰን ወደ አገልግሎት  ለመግባት እና ቅዳሴ ለማስቀደስ በሚል እሳቤ ነው።

ቦታ:መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ አዳራሽ
ሰዓት:10:30  ( አደራ ሰዓት ይከበር  የሚጀመረው ontime ነው።) ለሚመለከተው ሁሉ share አድርጉ! እና ተቀሳቅሳችሁ ተገኙ!

፮  ኪሎ ግቢ ጉባኤ
✥✥ መቃብሩን አትክፈቱ❗️❗️❗️❗️ ✥✥✥

👉 በብዛት የክርስቶስን ትንሣኤ ለመግለጽ የሚሣሉ ሥዕላት መቃብሩን ከፍቶ(ፈንቅሎ) ሲነሣ ወይም መላእክት የመቃብሩን ደጃፍ ከፍተውለት ሲነሣ ኣድርገው ነው የሚሣሉት ይህ በመጽሓፍ ቅዱስ ከተገለጸው ጋር የሚጋጭ ነው።

👉 ጌታችን የተነሣው መግነዝ ፍቱልኝ፥ መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ነው።

➛ ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ እንደገለጸልን እሑድ በማለዳ ወደ ጌታ መቃብር ሽቱ ለመቀባት የሄዱት ሴቶች «ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?» የሚል ጥያቄ ኣሳስቧቸው እንደነበር ይገልጽልናል።

➛ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት “ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ” በማለት የጥያቄያቸው መነሻ የሆነውን ምክንያት ያስረዳናል። {ማር ፲፮÷፩-፮፡፡}

➛ የእነዚህ ቅዱሳን ኣንስት (ሴቶች) ላሳሰባቸውን ጥያቄ መፍትሔ እንዴት እንዳገኘ ሌላኛው ወንጌላዊ ማቴዎስ በወንጌሉ እንዲህ ባለ መልኩ ይገልጽልናል፦

➛ «በሰንበትም መጨረሻ ( ሰንበት ያለው ቅዳሜን ነው) የመጀመሪያው ቀን (የመጀመሪያ ቀን ያለው የሥነፍጥረት መጀመሪያ የሆነች እሁድ ነው) ሲነጋ፥ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡ እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን ኣንከባሎ በላዩ ተቀመጠ፡፡ መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፡፡ ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ፡፡ እንደ ሞቱም ሆኑ፡፡ መልኣኩም መልሶ ሴቶቹን ኣላቸው፥ እናንተስ አኣትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ ኣውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። » {ማቴ ፳፰÷፩-፮፡፡}

➛ ጌታችን መቃብሩ ከፍቶ ተነስቶ ቢሆንስ ኖሮ መልኣኩ ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ውስጥ እንዲመለከቱ መቃብሩን ከፈተው ባልተባለ ነበር። ጌታችን በዝግ መቃብር ከተነሣ በኋላ ባዶ የነበረውን መቃብር የከፈተው ይህ የጌታ መልአክ ነው፡፡

➛ መልኣኩ መቃብሩን ለምን ከፈተው ቢሉ፦ የመጡ እነዚህ ሴቶች የጌታችንን መነሣት እንዲያውቁ እና ትንሣኤውን እንዳይጠራጠሩ ነው፡፡ ኋላም ደቀ መዛሙርቱ ትንሣኤውን ያመኑት መልኣኩ ወደ ከፈተው መቃብር ገብተው መግነዙን ካዩ በኋላ ነው። ዮሐ ፳፥፯።

➛ ጌታችን መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ለምን ተነሣ ቢሉ፦ ሞቱ በፈቃዱ እንደሆነ ትንሣኤውም በሥልጣኑ መሆንን ለማስረዳት ነው።

ኣንድም፦ ሥግው ቃልን በርቀቱ ቢያጸናው ነው። ይኸውም በኅቱም ድንግልና መወለዱ፣ በባህር ላይ መራመዱ፣ በተዘጋ ደጃፍ ሳይከፈት መግባቱ፣ መቃብርም ክፈቱልኝ ሳይል መነሣቱ ጌታ ምንም እንኳን ግዝፍ የሆነ ሥጋን ቢነሣም በመለኮትነቱ ግን ረቂቅ ነው በተዋሕዶ የቃል ርቀቱ ለሥጋ ገንዘቡ በመሆኑ (ሥግው ቃልን በርቀቱ ቢያጸናው ) በድንግልና ለመወለድ የማይከልክለው፣ ባህር የማያሰጥመው፣ ደጃፍ ለመግባት የማይከለክለው፣ ለትንሣኤውም መቃብር መክፈት የማያስፈልገው መሆኑን ኣስረዳ።

👉 ስለዚህ ቅዱሳን ሥዕላት በመሣል ቤተክርስቲያንን የምታገለግሉ ይህንን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ትምህርትን መሠረት ኣድጋች ብትሥሉ (መቃብሩን ኣትክፈቱ)፤ ምዕመናንም ይህን በመረዳት በቤታችንም ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን የምናመጣቸውን ሥዕላትን ትክክለኛ መልእክት የሚያስተላልፍ ከቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር የማይጋጭ መሆኑን በማገናዘብ ቢሆን ፤ እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ የምናቀርባቸው ሥዕላትንም ይህን ያማከለ ሊሆን ይገባል። ይቆየን

መልካም በዓል ይሁንላችሁ ❗️❗️❗️
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፡
በዓቢይ ኃይል ወስልጣን ።
አሰሮ ለሰይጣን፡ አግዓዞ ለአዳም ።
ሰላም፡ እምይእዜሰ ።
ኮነ ፡ፍስሐ ወሰላም፡፡
እነሆ ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩር ሆኖ ከሙታን ተነስቷል፡1ኛ ቆሮ 15÷20።

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የትንሳኤ ሎተሪ ትናንት ምሽት በይፋ መውጣቱ የታወሳል። በስፍራው ተገኝተው መካታተል ላልቻሉ አባላትም እድለኛ ቁጥሮችን እነሆ ብለናል።

1ኛ እጣ 1143 በገና
2ኛ እጣ 0265 Smart phone
3ኛ እጣ 3565 Air pode
4ኛ እጣ 1303 ድርሳነ ሚካኤል
5ኛ እጣ 0112 ነጠላ
የማስተዛዘኛ እጣዎቸ
6ኛ እጣ 0697
7ኛ እጣ 4026
8ኛ እጣ 0141
9ኛ እጣ 2286
10ኛ እጣ 0650

ከ6-10 ያሉት ሁሉም የወርሃዊ የድምጽ ጥቅል እድለኞች ናቸው።

እድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ።
@Mi121919 ላይ በማሳወቅ ሽልማቱን መቀበል ትችላላችሁ።

ትኬቱን በመሸጥና እና በመግዛት ለመርኃ ግብሩ መሳካት ላበረከታችሁች ተሳትፎ በግቢ ጉባኤው ስም ከልብ እናመሰግናለን።

የ2016 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ


https://t.me/SidistKiloGibiGubae
https://t.me/SidistKiloGibiGubae
https://t.me/SidistKiloGibiGubae
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ
#ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማክሰኞ
#ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ
#አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ
#አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ
#ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ
ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ
#ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
የእመቤታችንን ልደት  ከግቢ ጉባኤያችን ጋር 

  ልደተ እግዝእትነ ማርያም

መዝ. 86፥1
“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር 
ቅዱሳን" መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው

ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ 
ለማርያም   |በእመቤታችን ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ|


ውድ የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች በመጀመሪያ ​​እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን  የእናታችንን በዓለ ልደት በማሰብ ነገ በዕለተ ሐሙስ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በመንበረ ልዑል ቅዱሰ ማርቆሰ ወሚካኤል ቤተክርሰቲያን አውደምህረት እናት ግቢ ጉባኤያችን  መርሐ ግብር አዘጋጅታ ልጆቸ ኑ  እያለች መልዕክቷን ታሰተላልፋች።

ልደትሽ ልደታችን ነው!

ሰዓት ፡ 11:00 ጀምሮ
ቦታ : መንበረ ልዑል ቅዱሰ ማርቆሰ ወሚካኤል  አውደምህረት

የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባዔ
Forwarded from ወይኩን ፈቃድከ
"ዘወትር በንፁሕ ሕሊና እየሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።" መ.ቀሌሜንጦስ 12:25

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዘወትር ዓርብ በጋራ ተሰብስበን የአንድነት ጸሎት የምናደርስበት መርሐግብራችን ነገም እንደተጠበቀ ነው‼️

ስለዚህም ሁላችንም ከጓደኞቻችን ጋር ተቀሳቀሰን በመገኘት የጸሎት መርሐግብሩ ተሳታፊሆች እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃዱ ይሁንልን!

👥ቦታ: ቅዱስ ማርቆስ ወሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
ሰዓት: ጠዋት 11:50

፮ ኪሎ ጊቢ ጉባኤ
ሰላም የ6ኪሎ ግቢ ጉባዔ ተማሪዎች

እንደሚታወቀው ይህ ጥንታዊ የሆነ ግቢ ጉባዔ የራሱ የሆነ የ YouTube channel መክፈቱን በይፋ ገልጿል። ስለሆነም ለጓደኞቻችሁ ፣ ለምታቁት ሰው ሊንኩን በመላክ #SUBSCRIBE እንዲያደርጉ ንገሯቸው። ይህንንም በማረግ ያሳደገችንን ግቢ ጉባዔ እናግዛት።

📌ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ወንጌሎችን፣
📌የበዓላት ወረቦችን፣
📌ዝማሬዎችን፣
📌ምክረ አበውን እንዲሁም ሌሎች በስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤ የሚዘጋጁ ምስል ወ ድምፆችን ያገኙበታል።

ስለዚህ YouTube ላይ ገብታችሁ @6kilogbigubae ብላችሁ Search ማድረግ ወይም ደሞ ይህንን https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR መጠቀም ትችላላችሁ።

፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
                   
@SidistKiloGibiGubae
                   
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፪ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሰን!

"ግቢ ጉባኤያት የአገልግሎት መሠረት" በሚል መሪ ቃል እሑድ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከ7፡00 ሰዓት ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በመገኘት የማኅበራችንን የምሥረታ በዓል በጋራ እናክብር።
መቅረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
"ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም"
           ቅ/ያሬድ

እንኳን አደረሳችሁ?

ዓመታዊ የእመቤታችንን ልደት በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ስለሆነም ሁላችሁም ማግሰኞ ግንቦት 6 ቀን ምሽት 11፡00 ላይ በቅ/ሥላሴ ካቴደራል ትልቁ አዳራሽ እንድትገኙ ስንል አደራ እንላለን!!

ቀኑን ግንቦት 6 ያደረግነው ክፍለ ሃገር በዓል ለማክበር የሄዳችሁ ሰዎች ተመልሳችሁ በዓሉ ላይ እንድትገኙ ብለን ስለሆነ ሁላችሁም በዕለቱ እንድትገኙ ስንል አደራ እንላለን!!

፬ ኪሎ ጊቢ ጉባኤ
Forwarded from J𝑒𝑟𝑒𝑚𝑖𝑎h
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!"

የ2ኛ ዓመት ኮርስ
ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!
ነገ ረቡዕ ግንቦት 7, 2016 ዓ.ም የ2ኛ ዓመት ኮርስ አለ!

⛪️ቦታ: ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መጠለያ
ሰዓት: ምሽት 1:00
📚ኮርስ: ነገረ ማርያም

ሁላችንም በሰዓቱ እንገኝ!

©፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ
🌹🙏🌹ምክረ አበው🙏
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ጸጋ ቢሰጥህ  በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ " (ማር ይስሃቅ)
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለናል ።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹
‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏
‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏
‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏
‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏
‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏
‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏
‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› 
/ቅዱስ እንጦስ/
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏


   
ረድኤተ እግዚአብሔር  አይለየን
!
በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል መዝ 94(95)፥2

ዝክረ ቅዱስ ያሬድ
እንኳን አደረሳችሁ?


ዓመታዊ የዝክረ ቅዱስ ያሬድ በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ስለሆነም ሁላችሁም ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን ምሽት 11፡00 ላይ ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል እንድትገኙ ስንል አደራ እንላለን!!

በዕለቱ የሚኖሩ መርኃ ግብራት
➡️ትምህርተ ወንጌል
➡️ያሬዳዊ ወረብ
➡️ተውኔት እንዲሁም
➡️የቀጣይ ዓመት የሥራ አስፈፃሚዎች ዕጣ ማውጣት ስለሚኖር ሁላችሁም በሰዓቱ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።

፮ ኪሎ ግቢ ጉባዔ

📲Join & Share👥
                   👇👇👇
  Telegram @SidistKiloGibiGubae
  YouTube https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR
"ዘወትር በንፁሕ ሕሊና እየሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።" መ.ቀሌሜንጦስ 12:25

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዘወትር ዓርብ በጋራ ተሰብስበን የአንድነት ጸሎት የምናደርስበት መርሐግብራችን ነገም እንደተጠበቀ ነው‼️

ስለዚህም ሁላችንም ከጓደኞቻችን ጋር ተቀሳቀሰን በመገኘት የጸሎት መርሐግብሩ ተሳታፊዎች እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃዱ ይሁንልን!

👥ቦታ: ቅዱስ ማርቆስ ወሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
ሰዓት: ጠዋት 11:50

፮ ኪሎ ጊቢ ጉባኤ