𝚂𝚎𝚢𝚏𝚎𝚕𝙸𝚜𝚕𝚊𝚖 ሰይፈል ኢስላም!
375 subscribers
1.44K photos
150 videos
9 files
329 links
قال ابن تيمية -رحمه الله-:
{قوام الدين كتاب يهدي وسيف ينصر وكفى بربك هادياونصيرا}
مجموع الفتاوى [10/13]
Download Telegram
#የኢስራኤልናፍልስጤምግጭት_መቼ_እና_እንደት_ጀመረ??
#ታሪካዊዳራ___ክፍል③
"ኢስራኤል በተ/መ/ድ እንደ ሃገር እውቅና ካገኘችበት እ.ኤ.አ.1947 ጀምሮ እስከ ዘመነ ትራምፕ ድረስ ያለው ሁኔታ!!"
________
#የ1947ቱ የተ/መ/ድ የፀጥታው ምክርቤት #ኢፍትሐዊ ውሳኔ፣በርካታ ፍልስጤማዊያንን ክፉኛ ያስቀየመ ከመሆኑም ባሻገር በርካቶችን ተወልደው ካደጉባቸው መንደሮች እንድፈናቀሉ ምክናየት ሆነ።
ይህ ኢፍትሐዊ ውሳኔ የተላለፈበትን ቀን ፍልስጤማውያን በየአመቱ “በናክባ ቀን”አስበውት ይውላሉ።ይህም “ጥፋት” ለሚለው የአረብኛ ቃል የተሰየመ ሲሆን ፍልስጤማውያን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱባቸውን ቤቶች ቁልፍ በማመልከት #አሁንም_ተመልሰው_እንደሚኖሩባቸው_ተስፋ_ያልቆረጡባቸውን_ግዛቶች ለመዘከር የታሰበ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤማውያን “ #ወደቤታቸው_ተመልሰው_ከአይሁድ_ጎረቤቶቻቸውጋር_በሰላም_ለመኖር_የሚፈልጉሁሉ_በተቻለፍጥነት_ይህን_የማድረግመብት_ሊኖራቸው_እንደሚገባ” በመገንዘብ #ውሳኔ194ን አፀደቀ ፡፡ እስራኤል ምንም እንኳን ይህ በሃይልና በዙልም ከመኖሪያ ቤታቸው ያስለቀቋቸው ነባር ፍልስጤማውያን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸውና ከቀያቸው አስለቅቀው የራሳቸውን መንግስት ከመሰረቱ መጤ አይሁዶች ጋር በጉርብትና እንድኖሩ በሚል ተ/መ/ድ ያወጣውን ውሳኔ፣አድሱ የኢስራኤል መንግስት በቅፅበት ፈቃጅና ከልካይ ሁና" #የፍልስጤሞች_ወደዚህ_መመለስ_ለአዲሱ_የአይሁድ_መንግስት_ተፈጥሮአዊስጋት ነው!"በሚል ሀሳብ ውሳኔውን ላለመቀበልም ዳዳት!
ከአንድ ዓመት በኋላ ለተፈናቀሉ"ፍልስጤማውያን" ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት በቅርብ ምስራቅ የሚገኙ የፍልስጤም ስደተኞች #የተባበሩትመንግስታት_የእርዳታ_ስራዎች_ኤጄንሲ( #UNRWA)ተቋቋመ።
በእነዚያ ሁለት ክስተቶች መካከል ባለው ጊዜ እስራኤል #ከአጎራባች አረብ አገሮች ማለትም ከሊባኖስ፣ከሶሪያ ፣ከጆርዳን እና ከግብፅ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነቶችን ተፈራረመች።
ከዚያም እ.ኤ.አ.በ1950 ዮርዳኖስ የዌስት ባንክ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ስትወስድ፣ግብፅ ደግሞ ጋዛን እንድትወስድ ተደረገ።
ይህ ስምምነት እስራኤል እነዚህን ግዛቶች ከዮርዳኖስና ከግብፅ አስለቅቃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ እስከጀመረችበትና በዚህም #የ6ቀኑ_የአረብ_ኢስራኤል_ጦርነት እስከተጀመረበት ግዜ ድረስ ቆየ።
(የ6ቱን ቀን የአረብ-እስራኤል ጦርነት ሂደት በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ ኢንሻ አሏህ)
ከዚያ በፊትም ብጥብጡ አልፎ አልፎ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን፣በ1956 በቃልኪሊያ፣በኩፍርቃሲም እና በሃን ዩኒስ መንደሮች ውስጥ፣እንድሁም በ1966 አስሳሙ በተባሉ ቦታዎች እልቂቶች ተከስተዋል።
#በ1964 #የፍልስጤም_ነፃ_አውጪ _ድርጅት(PLO)ካይሮ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፣ከሰላማዊ ትግል ይልቅ በትጥቅ አብዮት “ፍልስጤም ነፃ ለማውጣት”የተመሰረተ ነበር።እስራኤልናአሜሪካ ድርጅቱን በአሸባሪነት ቢፈርጁትም፣የፍልስጤም ህዝብ ብቸኛ ተወካይ መሆኑን የአረብሊግ በ1974 እውቅና ሰጠው።
የእስራኤል ወታደራዊ ጦር በጋዛ ሰርጥ፣ በዌስትባንክ፣በጎላን ከፍተኛቦታዎች እና በግብፅ ሲናይ በረሃ፣በ1967 ከፍተኛ ደም መፋሰስ ያስከተለ ሲሆን፣የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በሃይል ተይዘዋል ብለው ካሰቡዋቸው ግዛቶች እስራኤል ጦሯን እንድታወጣ በማዘዝ #ውሳኔ242 ቢያፀድቅም፣እስራኤል ከቆብ አልቆጠረችውም ነበር።
እስራኤል በ1970 በዮርዳኖስ ውስጥ ከፍልስጤማውያን ወታደሮች ጋር በጥቁሯመስከረም(Black September)ተጨማሪ ውጊያ ማድረጓን ተከትሎ፣"የፀጥታው¡"ምክርቤት የተኩስ አቁም ጥሪ በማቅረብ እና እስራኤል ከ 1967ቱ ወረራ እንድትመለስ በመጠየቅ #ውሳኔ338 አስተላለፈ።
አሁንም እስራኤል እምቢ አለች!
በፍልስጤማውያን"የመሬትቀን"ተብሎ የሚዘከርበት፣ማርች30ቀን1976፣ የእስራኤልን የመሬት ወረራ በመቃወም ከገሊላ ባህር እስከ ኔጌቭ ድረስ ባሉ ከተሞች አመጽ፣አድማ እና ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎችን አስከተለ።
እ.ኤ.አ.መስከረም17ቀን 1978፣የእስራኤሉ ጠ/ሚ #ሜናም_ቤገን ከግብፁፕሬዝዳንት #አንዋር_ሳዳት ጋር በፕሬዚዳንት በጂሚ ካርተር ማረፊያ የካምፕ ዴቪድ ስምምነቶችን ለመፈራረም ተገናኙ። ስምምነቱ በሁለቱ ሃገሮች(እስራኤልናግብፅ)መካከል ግንኙነታቸውን ያጠናከረና #የሰላምኖቬል_ሽልማት ያስገኘላቸውሲሆን፣በሌላ በኩል ግን ስምምነቱ የባለጉዳዮቹ ፍልስጤማውያን ውክልና የሌለበት በመሆኑ፣ግጭቱን ከማባባስ የዘለለ የፈየደው አንዳችም ነገር አልነበረም።
የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚገኙ 4 ሲቪል ፍልስጤማዊያንን በግፍ በመግደሉ ምክናየት፣December 8, 1987 በፍልስጤምግዛቶች ውስጥ በአይነቱየመጀመሪያ የሆነ ከባድሁከት( #The_First_Intifada)ተነስቶ እስከ መስከረም13,1993 ድረስ ቆየ።
በ1993 #የኦስሎI_ስምምነት(Oslo1) በእስራኤል ጠ/ሚ #ይስሃቅ ራቢንና የ PLO ሊቀመንበር #ያሲር_አራፋት የተፈረመ ሲሆን፣የፍልስጤም ጊዜያዊ የራስገዝ አስተዳደር እንድመሰረትና የእስራኤል ጦር ከተ/መ/ድ እውቅና ውጭ በሃይል ከያዛቸው ቀጠናዎች እንዲወጣ ተደረገ፡፡ነገር ግን ኢስራኤል ስምምነቱን በማፍረሷ
#ሁለተኛው_የኦስሎ_ስምምነት(Oslo2)እ.ኤ.አ.በ1995 ተደረገ።በዚህም በተወሰኑ የዌስትባንክ እና የጋዛ አካባቢዎች የፍልስጤም የራስ ገዝ አስተዳደርን እውቅና ቢሰጥም፣የፍልስጤምን ሉኣላዊ ሃገርነት ግን አሁንም አላፀደቀም ነበር።
በመስከረም28,2000 #ሁለተኛውከባድ አመፅ( #the second Intifada)የተቀሰቀሰ።ዋነኛ ምክናየቱ የእስራኤል ጠ/ሚ #አርኤል_ሻሮን #በአልአቅሷ መስጅድ ጉብኝት ማድረጉ ነበር።
በ2002 እስራኤል ዌስትባንክን ወረረች።ይህም #በ2004_ከያሲር_አራፋት_ሞት ጋር ተዳምሮ ፍልስጤማውያንን ክፉኛ ጎዳቸው።
በ2006 በፍልስጤም በተካሄደ ምርጫ #ሃማስ አብላጫ ድምፅ በመያዝ አሸነፈ።ሆኖም በምርጫ የተሸነፈው ፋታህ(PLO)ውጤቱን ባለመቀበሉ ሃማስናፋታህ #የርስበርስ_ጦርነት አደረጉ።በመጨረሻም ሃማስ ጋዛን ሲቆጣጠር፣ፋታህ ደግሞ ዌስትባንክን ያዘ።
በ2006 እስራኤል በሊባኖስ በሚገኘው"ሂዝቦላህ"የተባለ ቡድን ላይ ጦርነት አወጀች።
አስከትላም በጋዛ በሚገኘው ጅሃድስት ቡድን(ሃማስ)ላይ፣ኦፕሬሽን ካስት ሊድ(2008)፣ኦፕሬሽን የመከላከያ ዓምድ(2012) እና የኦፕሬሽን መከላከያ ጠርዝ(2014)ን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች፡፡ ይህ ሳያንሳት በ2017 እና በ20018፣ፍልስጤማውያን የናክባ ቀን በሚያስቡበት እለት፣በተ/መ/ድ #የጦርወንጀሎች_ምርመራ የሚያስጠይቅ የሆነ ከባድጥቃት አደረሰች።
በ2017በአሜሪካ በተደረገው ምርጫ #ዶናልድ_ትራምፕ መመረጥ ሁኔታውን ዳግም አገረሸው።ለዚህም ዋነኛ ማሳያ ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ #ከቴልአቪቭ_ወደ_ኢየሩሳሌም ማዘወሩ ነበር፡፡ትራምፕ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ፣ #የጎላን ከፍተኛቦታዎችን የእስራኤል መሆናቸውንም አፀደቀ።
ይህም አልበቃ ብሎት አሜሪካ ለUNRWA የምትመድበውን የገንዘብ ድጋፍም አቋረጠ።🔚
የዚህን ፅሁፍ ክፍል①እና②ለማግኘት👉t.me/Abdelaziz_Bin_Muhammed ይጎብኙ።
የመረጃ ምንጮቸ
#አልጀዚራ #ቢቢሲ #ዊኪፔድያ
#ኢንሳይክሎፔድያብሪታኒካ #ዘጋርድያን #ሂስትሪዶትኮም እና ሌሎችም ናቸው።
ጥያቄ/አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ በቴሌግራም t.me/ServantOf_Almighty ላይ ይፃፉልኝ።

t.me/Seyfel_Islam
#የኢስራኤልናፍልስጤምግጭት_መቼ_እና_እንደት_ጀመረ??
#ታሪካዊዳራ___ክፍል③
"ኢስራኤል በተ/መ/ድ እንደ ሃገር እውቅና ካገኘችበት  እ.ኤ.አ.1947 ጀምሮ እስከ ዘመነ ትራምፕ ድረስ ያለው ሁኔታ!!"
____
#የ1947ቱ የተ/መ/ድ የፀጥታው ምክርቤት #ኢፍትሐዊ ውሳኔ፣በርካታ ፍልስጤማዊያንን ክፉኛ ያስቀየመ ከመሆኑም ባሻገር በርካቶችን ተወልደው ካደጉባቸው መንደሮች እንድፈናቀሉ ምክናየት ሆነ።
ይህ ኢፍትሐዊ ውሳኔ የተላለፈበትን ቀን ፍልስጤማውያን በየአመቱ “በናክባ ቀን”አስበውት ይውላሉ።ይህም “ጥፋት” ለሚለው የአረብኛ ቃል የተሰየመ ሲሆን ፍልስጤማውያን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱባቸውን ቤቶች ቁልፍ  በማመልከት #አሁንም_ተመልሰው_እንደሚኖሩባቸው_ተስፋ_ያልቆረጡባቸውን_ግዛቶች ለመዘከር የታሰበ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤማውያን “ #ወደቤታቸው_ተመልሰው_ከአይሁድ_ጎረቤቶቻቸውጋር_በሰላም_ለመኖር_የሚፈልጉሁሉ_በተቻለፍጥነት_ይህን_የማድረግመብት_ሊኖራቸው_እንደሚገባ” በመገንዘብ #ውሳኔ194ን አፀደቀ ፡፡  እስራኤል ምንም እንኳን ይህ በሃይልና በዙልም ከመኖሪያ ቤታቸው ያስለቀቋቸው ነባር ፍልስጤማውያን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸውና ከቀያቸው አስለቅቀው የራሳቸውን መንግስት ከመሰረቱ መጤ አይሁዶች ጋር በጉርብትና እንድኖሩ በሚል ተ/መ/ድ ያወጣውን ውሳኔ፣አድሱ የኢስራኤል መንግስት በቅፅበት ፈቃጅና ከልካይ ሁና" #የፍልስጤሞች_ወደዚህ_መመለሾ_ለአዲሱ_የአይሁድ_መንግስት_ተፈጥሮአዊስጋት ነው!"በሚል ሀሳብ ውሳኔውን ላለመቀበልም ዳዳት!
ከአንድ ዓመት በኋላ ለተፈናቀሉ"ፍልስጤማውያን" ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት በቅርብ ምስራቅ የሚገኙ የፍልስጤም ስደተኞች #የተባበሩትመንግስታት_የእርዳታ_ስራዎች_ኤጄንሲ( #UNRWA)ተቋቋመ።
በእነዚያ ሁለት ክስተቶች መካከል ባለው ጊዜ እስራኤል #ከአጎራባች አረብ አገሮች ማለትም ከሊባኖስ፣ከሶሪያ ፣ከጆርዳን እና ከግብፅ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነቶችን ተፈራረመች።
ከዚያም እ.ኤ.አ.በ1950 ዮርዳኖስ የዌስት ባንክ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ስትወስድ፣ግብፅ ደግሞ ጋዛን እንድትወስድ ተደረገ።
ይህ ስምምነት እስራኤል እነዚህን ግዛቶች ከዮርዳኖስና ከግብፅ አስለቅቃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ እስከጀመረችበትና በዚህም #የ6ቀኑ_የአረብ_ኢስራኤል_ጦርነት እስከተጀመረበት ግዜ ድረስ ቆየ።
(የ6ቱን ቀን የአረብ-እስራኤል ጦርነት ሂደት በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ ኢንሻ አሏህ)
ከዚያ በፊትም ብጥብጡ አልፎ አልፎ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን፣በ1956 በቃልኪሊያ፣በኩፍርቃሲም እና በሃን ዩኒስ መንደሮች ውስጥ፣እንድሁም በ1966 አስሳሙ በተባሉ ቦታዎች እልቂቶች ተከስተዋል።
#በ1964 #የፍልስጤም_ነፃ_አውጪ _ድርጅት(PLO)ካይሮ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፣ከሰላማዊ ትግል ይልቅ በትጥቅ አብዮት “ፍልስጤም ነፃ ለማውጣት”የተመሰረተ ነበር።እስራኤልናአሜሪካ ድርጅቱን በአሸባሪነት ቢፈርጁትም፣የፍልስጤም ህዝብ ብቸኛ ተወካይ መሆኑን የአረብሊግ በ1974 እውቅና ሰጠው።
የእስራኤል ወታደራዊ ጦር በጋዛ ሰርጥ፣ በዌስትባንክ፣በጎላን ከፍተኛቦታዎች እና በግብፅ ሲናይ በረሃ፣በ1967 ከፍተኛ ደም መፋሰስ ያስከተለ ሲሆን፣የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በሃይል ተይዘዋል ብለው ካሰቡዋቸው ግዛቶች እስራኤል ጦሯን እንድታወጣ በማዘዝ #ውሳኔ242 ቢያፀድቅም፣እስራኤል ከቆብ አልቆጠረችውም ነበር።
እስራኤል በ1970 በዮርዳኖስ ውስጥ ከፍልስጤማውያን ወታደሮች ጋር በጥቁሯመስከረም(Black September)ተጨማሪ ውጊያ ማድረጓን ተከትሎ፣"የፀጥታው¡"ምክርቤት የተኩስ አቁም ጥሪ በማቅረብ እና እስራኤል ከ 1967ቱ ወረራ እንድትመለስ በመጠየቅ #ውሳኔ338 አስተላለፈ።
አሁንም እስራኤል እምቢ አለች!
በፍልስጤማውያን"የመሬትቀን"ተብሎ የሚዘከርበት፣ማርች30ቀን1976፣ የእስራኤልን የመሬት ወረራ በመቃወም ከገሊላ ባህር እስከ ኔጌቭ ድረስ ባሉ ከተሞች አመጽ፣አድማ እና ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎችን አስከተለ።
እ.ኤ.አ.መስከረም17ቀን 1978፣የእስራኤሉ ጠ/ሚ #ሜናም_ቤገን ከግብፁፕሬዝዳንት #አንዋር_ሳዳት ጋር በፕሬዚዳንት በጂሚ ካርተር ማረፊያ የካምፕ ዴቪድ ስምምነቶችን ለመፈራረም ተገናኙ። ስምምነቱ በሁለቱ ሃገሮች(እስራኤልናግብፅ)መካከል ግንኙነታቸውን ያጠናከረና #የሰላምኖቬል_ሽልማት ያስገኘላቸውሲሆን፣በሌላ በኩል ግን ስምምነቱ የባለጉዳዮቹ ፍልስጤማውያን ውክልና የሌለበት በመሆኑ፣ግጭቱን ከማባባስ የዘለለ የፈየደው አንዳችም ነገር አልነበረም።
የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚገኙ 4 ሲቪል ፍልስጤማዊያንን በግፍ በመግደሉ ምክናየት፣December 8, 1987 በፍልስጤምግዛቶች ውስጥ በአይነቱየመጀመሪያ የሆነ ከባድሁከት( #The_First_Intifada)ተነስቶ እስከ መስከረም13,1993 ድረስ ቆየ።
በ1993 #የኦስሎI_ስምምነት(Oslo1) በእስራኤል ጠ/ሚ #ይስሃቅ ራቢንና የ PLO ሊቀመንበር #ያሲር_አራፋት የተፈረመ ሲሆን፣የፍልስጤም ጊዜያዊ የራስገዝ አስተዳደር እንድመሰረትና  የእስራኤል ጦር ከተ/መ/ድ እውቅና ውጭ በሃይል ከያዛቸው ቀጠናዎች እንዲወጣ ተደረገ፡፡ነገር ግን ኢስራኤል ስምምነቱን በማፍረሷ
#ሁለተኛው_የኦስሎ_ስምምነት(Oslo2)እ.ኤ.አ.በ1995 ተደረገ።በዚህም በተወሰኑ የዌስትባንክ እና የጋዛ አካባቢዎች የፍልስጤም የራስ ገዝ አስተዳደርን እውቅና ቢሰጥም፣የፍልስጤምን ሉኣላዊ ሃገርነት ግን አሁንም አላፀደቀም ነበር።
በመስከረም28,2000 #ሁለተኛውከባድ አመፅ( #the second Intifada)የተቀሰቀሰ።ዋነኛ ምክናየቱ የእስራኤል ጠ/ሚ #አርኤል_ሻሮን #በአልአቅሷ መስጅድ ጉብኝት ማድረጉ ነበር።
በ2002 እስራኤል ዌስትባንክን ወረረች።ይህም #በ2004_ከያሲር_አራፋት_ሞት ጋር ተዳምሮ ፍልስጤማውያንን ክፉኛ ጎዳቸው።
በ2006 በፍልስጤም በተካሄደ ምርጫ #ሃማስ አብላጫ ድምፅ በመያዝ አሸነፈ።ሆኖም በምርጫ የተሸነፈው ፋታህ(PLO)ውጤቱን ባለመቀበሉ ሃማስናፋታህ #የርስበርስ_ጦርነት አደረጉ።በመጨረሻም ሃማስ ጋዛን ሲቆጣጠር፣ፋታህ ደግሞ ዌስትባንክን ያዘ።
በ2006 እስራኤል በሊባኖስ በሚገኘው"ሂዝቦላህ"የተባለ ቡድን ላይ ጦርነት አወጀች።
አስከትላም  በጋዛ በሚገኘው ጅሃድስት ቡድን(ሃማስ)ላይ፣ኦፕሬሽን ካስት ሊድ(2008)፣ኦፕሬሽን የመከላከያ ዓምድ(2012) እና የኦፕሬሽን መከላከያ ጠርዝ(2014)ን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች፡፡  ይህ ሳያንሳት በ2017 እና በ20018፣ፍልስጤማውያን የናክባ ቀን በሚያስቡበት እለት፣በተ/መ/ድ #የጦርወንጀሎች_ምርመራ የሚያስጠይቅ የሆነ ከባድጥቃት አደረሰች።
በ2017በአሜሪካ በተደረገው ምርጫ #ዶናልድ_ትራምፕ መመረጥ ሁኔታውን ዳግም አገረሸው።ለዚህም ዋነኛ ማሳያ ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ #ከቴልአቪቭ_ወደ_ኢየሩሳሌም ማዘወሩ ነበር፡፡ትራምፕ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ፣ #የጎላን ከፍተኛቦታዎችን የእስራኤል መሆናቸውንም አፀደቀ።
ይህም አልበቃ ብሎት አሜሪካ ለUNRWA የምትመድበውን የገንዘብ ድጋፍም አቋረጠ።🔚
የመረጃ ምንጮቼ:
#አልጀዚራ #ቢቢሲ #ዊኪፔድያ
#ኢንሳይክሎፔድያብሪታኒካ #ዘጋርድያን #ሂስትሪዶትኮም እና ሌሎችም ናቸው።
ጥያቄ/አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ በቴሌግራም t.me/ServantOf_Almighty ላይ ይፃፉልኝ።

t.me/Seyfel_Islam
👌የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ “በጋዛ አፋጣኝ እርምጃዎችን ለመውሰድ የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ሙሉ፣ፈጣን እና ውጤታማ ትግበራ እንጠብቃለን!”ብሏል።
👌በሌላ ዜና ደግሞ በርከት ያሉ የፈረንሳይ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ለመጠየቅ በየካቲት4 ወደ ግብፅ ራፋህ እንደሚያመሩ አስታውቀዋል።
የዛሬውን የአለምአቀፍ የፍትህ ፍርድቤት ውሳኔ በደስታ እንቀበላለን በማለት ሀሳብ ከሰጡ ሃገራት መካከል ኳታር፣ሳዑዲአረቢያ፣ግብፅ፣ቱርክ፣ፓኪስታን፣ኢራንና ጆርዳን ይጠቀሳሉ።
⏺አሁን ደግሞ የጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች የሆኑት የፍልስጢን ተዋጊዎች፣ወራሪዋ እስራኤልና አስወራሪዋ አሜሪካ በዛሬው ውሳኔ ዙሪያ የሰጡትን እንመልከት።

👌 #ሃማስ “ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ወራሪውን በዘር ማጥፋት ወንጀል የከሰሰበትን ውሳኔ በደስታ እንቀበላለን!”ሲል፣
👌ኢስላሚክ ጂሃድ ንቅናቄ በበኩሉ “የፍትህ ፍ/ቤት ውሳኔዎች ግድያው እንዲቆምና ህዝባችንን ከጥፋት እንዲከላከል በተጠየቀው ደረጃ ላይ #ያልደረሰ ሲሆን ይህም ጠላት የፈለገውን ለማድረግ ሊጠቀምበት ይችላል!”በማለት ስጋቱን ሀልፇል።በማስከተልም
“ፍ/ቤቱ የዘር ማጥፋት ወንጀልን በተዘዋዋሪ ቢቀበልም የጽዮናውያን ጠላት ተኩስ እንዲያቆም ለማስገደድ ግልጽ ውሳኔ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን እናወግዛለን!”በማለት ውሳኔውን ተቃውሟል።
የኢስላሚክ ጅሃድ ንቅናቄው የፍርድቤቱን ውሳኔ ይቃወም እንጅ
“የደቡብ አፍሪካ መንግስት የጽዮናውያንን ወንጀል ለማጋለጥ እና በህዝባችን ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ጦርነት አስመልክቶ አለም አቀፍ ዝምታን ለመስበር ያደረገውን ጥረት እናደንቃለን!”ብሏል።

👌የጅምላ ጭፍጨፋው #ዋነኛአጋርና_ተሳታፊ የሆነችው #የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ “አሜሪካ አሁንም በእስራኤል ላይ የቀረበው የዘር ማጥፋት ወንጀል #መሠረተቢስ ነው ብሎ ያምናል!”ሲል
የስቴት ዲፓርትመንቱ ደግሞ “የፍትህ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከዋሽንግተን እይታ ጋር የሚስማማ ነው።እስራኤል የጥቅምት 7 ጥቃቶች እንዳይደገሙ እርምጃዎችን የመውሰድ መብት አላት የሚል ነው!”ብሏል።

👌ይህ በእንድህ እያለ የዛሬው የፍርድቤት ውሳኔ ከተሰማ በኋላ ለራሳቸው የፖለቲካ ሚዛን በእነ አሜሪካና ብሪታንያ ከየሀገሩ ተለቃቅመው በፍልስጢኖች የርስት ሀገር ላይ እንድሰፍሩ ከተደረጉ በኋላ ባሰፈሯቸው ሀገራት ያላሰለሰ እርዳታ በአጋጣሚ ዛሬ ላይ የጀት እና የታንክ ባለቤት ሆነው ገና ከሰፈሩ የአንድ አዛውንት እድሜ እንኳን ሳይሆናቸው ባስጠለሏቸው ህዝቦች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ እያደረጉ የሚገኙት እጅግ ቆሻሻ ሰዎች ፕሬዝዳንት የሆነው እብሪተኛው #ኔታንያሁ “ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመወያየት ፍቃደኛ መሆናቸው ከትውልድ እስከ ትውልድ የማይጠፋ ውርደት ነው።ዓለም አቀፍ ህግን እየተከተልን ራሳችንን እና ዜጎቻችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን።”በማለት የፍርድቤቱን ውሳኔ ለማክበር ፈቃደኛ እንዳልሆነ አቻ የሌለው ቀሽምነቱን ለማሳወቅ ግዜ አልወሰደበትም!

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Seyfel_Islam
#Breaking
#የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #ሚካሂል_ቦግዳኖቭ #ከፋታህ እና #ሃማስ መሪዎች ጋር #በሞስኮ የፍልስጤም ስብሰባ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በስልክ ተወያዩ።
ሚኒስትሩ  ከፋታህ እና ሃማስ መሪዎች ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት በሞስኮ የፍልስጤም ስብሰባ ሊካሄድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
የፋታህ ፕሬዝዳንት ማህሙድ ዐባስ ሩሲያ የፍልስጤም ቡድኖች ውይይት እንዲያደርጉ እና መከፋፈላቸውን ትተው በጋራ እንድሰሩ ያቀረበችውን ግብዣ በደስታ ተቀብለዋል።
የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ “በፍልስጤም በኩል አነሳሽነት የቴሌፎን ውይይቶች ተካሂደዋል፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ የሩስያ ፕሬዚደንት ልኡክ የሩሲያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካሂል ቦግዳኖቭ ከ ፋታህ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጋር ተወያይተዋል ያለ ሲሆን የፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት(ፋታህ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል #ዐዛሙልአህመድ እና የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ምክትል ኃላፊ #ሙሳ_አቡመርዙቅ ጋር ተወያይተዋል።
“የንግግሩ ዋናው ትኩረቱ የፍልስጤም እና የእስራኤል ግጭት ያስከተለውን ውጤት እና በጋዛ ሰርጥ እየጨመረ ያለው የሰብአዊ አደጋዎች ላይ ነበር።”ያለው መግለጫው፣በማስከተልም
“በንግግሮቹ ወቅት በየካቲት ወር መጨረሻ - መጋቢት መጀመሪያ ላይ በሞስኮ በሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የምስራቃዊ ጥናት ተቋም ውስጥ የፍልስጤም ስብሰባ ለማዘጋጀት በተዘጋጁ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር የሃሳብ ልውውጥ ተካሂዷል!”ብሏል።

ምንጭ፡ ኖቮስቲ
#RT እንደዘገበው።

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Seyfel_Islam
#Palestine

ዛሬ አይርላንድ ፣ ኖርዌይ እንዲሁም ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አስታወቁ።

" የዛሬው ቀን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ ቀን ነው " ተብሏል።

የአየርላንድ ጠ/ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ " ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና ሰጥተናል። ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዳችን ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " #በሚቀጥሉት_ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ይህን ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ እርግጠኛ ነኝ " ሲሉ አክለዋል።

የአይርላንድ መንግሥት ይህ የሀገርነት እውቅና የሁለት ሀገር መፍትሄን እንደሚደግፍና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል።

የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ " ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን #ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም " ብለዋል።

የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር በበኩላቸው ፥ " እውቅና ከሌለ (የፍልስጤም) በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር አይችልም " ብለዋል።

" ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው። " ሲሉ አክለዋል።

" ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ መብት አላት " ብለዋል።

የፍልስጤም #የነጻ_ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #በኖርዌይ እና #በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል።

ሚኒስትሩ፤ " የዛሬው ውሳኔ ሽብርተኝነት እንደሚከፍል ለፍልስጤማውያን እና ለዓለም መልእክት ያስተላለፈ ነው " ብለዋል።

መረጃው የስካይ ኒውስ ነው።
ŠTikvah
https://t.me/Seyfel_Islam