ቄራ ሰላም መስጂድ kera Selam Mesjid
771 subscribers
370 photos
52 videos
9 files
117 links
አህለን

       ይህ የቄራ ሰላም መስጂድ ቻናል ነው

🔸ስለ መስጂዱ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች መረጃ
🔸መልዕክት አዘል አጫጭር ፅሁፎች
🔸የተለያዩ የድምፅና የምስል ፕሮግራሞች


          💎ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን💎
Download Telegram
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ.pdf
1.9 MB
ባለ 15 ገፁ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለት አዲሱ ረቂቅ አዋጅ!

ትናንት ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት አጋርቻችሁ ነበር። በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708

ነገር ግን ይህ ረቂቅ አዋጅ አንዳንድ ሃሳቦቹ ከቀረበው ጥናት በተቃራኒ የሰፈሩ አዋጆችን አካቷል። ለምሳሌ፦ አንቀፅ 17 በግልፅ ሶላትን ለመከልከል የታሰበበት ሸፍጥ ያለው ሲሆን፣ አንቀፅ 19 ደግሞ በደፈናው የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ ከሌላው ጋር በማነፃፀር ኒቃብ መልበስን «ማንነትን ለመለየት የማያስችል» በሚል ሽፋን ለመከልከል ታልሞበት ነው። ምክንያታቸው ሙስሊም ጠልነት ስለሆነ እንጂ የእውነት ማንነትን መለየት ቢሆን ኖሮ፤ ልክ ባንክና መሰል ቢዝነስ ላይ በሴት ጥበቃ ማንነትን እንደሚፈትሹት መለየት ይችሉ ነበር።

ይህ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት ሁሉም ሙስሊም እንዲስተካከል ማድረግ አለበት። እስከዛሬ ባልተጻፈ ህግ የጨቆኑን አንሶ፤ ዛሬ ጽፈው ሊጨቁኑን ሲመክሩ ዝም ብለን መመልከት የለብንም። ለነገው ትውልድ ነፃነትን እንጂ በኛ ዘመን የተመሰረተን ጭቆና አናወርስም።

ሲቀጥል ገና ከረቂቅ አዋጁ ጥናት ጀምሮ ከ50% በላይ የሆነውን የሃገሪቱን ሙስሊም የወከለው አንድ ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ ሃሳብ ቢያቀርብ እንኳ «በድምፅ ብልጫ» በሚሉት የዙልም ፍርድ ሃሳቡን ውድቅ ያደርጉበታል። ከ10 በላይ የአዋጁ ጥናት አዘጋጆች መካከል 50%+ ህዝብ ውክልናው 10% ብቻ ነበር። ይህ እጅግ አሳፋሪና በተደጋጋሚ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የምናስተውለው ነው።

ልክ እንደዚሁ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽንም በወረዳ ደረጃ ሳይቀር ተወካዮችን ሲመርጥ፤ የሙስሊሙን ቁጥር ታሳቢ ባላደረገ መልኩ ነው። ታዲያ እንዲህ ሆኖ ምን የተሻለ ውጤት ይመጣል?
📌 የዱንያ ፈተና

🎙 በኡስታዝ ማህሙድ ሀሰን

🗓 ሀሙስ/ ግንቦት 9/2016 🗓

🕌 በቄራ ሰላም መስጂድ 🕌
የ2016 በጀት ዓመት 4ተኛ ዙር መደበኛ
የምግብ ድጋፍ ተደረገ

🟧🟨🟩🟦🟪⬛️⬜️                   
▪️ የምግብ ዘርፍ 
🟧🟨🟩🟦🟪⬛️⬜️
              
💰215,000.00ብር ወጪ በማድረግ ለ136 የቲም ቤተሰቦች ፣ ለ25 አካል ጉዳተኞችና ምስኪኖች የምግብ ድጋፍ ተደረገ።

ውድ አህለል ኸይሮች በዚህ በተከበረው ዙልቅዕዳህ ወር የቲሞችን ለመርዳት ፤ ሰደቃ ለመስጠት በሚከተለው አካውንት ገቢ ማድረግ ይችላሉ👇
🟪🟪🟪🟪🟪🟪🟪🟪🟪🟪🟪🟪
1000315884229 ንግድ ባንክ
ሰላም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህፃናት…
🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩

ለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።
جزاكم الله خيرا    🎁🎁                     

https://t.me/keraSelamMesjideYetimochBiro              
ቄራ ሰላም መስጂድ የቲሞች ቢሮ 
🗓8/9/2016
 1445  ذُو الْقَعْدَةِ    ግንቦት 8|2016
ቄራ ሰላም መስጂድ

መስጂዱ ያፈራቸው የህክምና ባለሙያዎች እና የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር የፊታችን እሁድ 18/09/16 አ፡ል ከጠዋት 3፡00 እስከ 6፡30 የነፃ የህክምና ማማከር አግልግሎት ለመስጠት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ እርሶን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

አገልግሎቱ የእድሜ ገደብ የለውም ከጨቅላ ህፃናት እስከ አረጋዊያን ያካተተ ነው።

መስጂዱም የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ከወዲሁ ጥሪውን እያስተላለፈ ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትመዘገቡ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

የመመዝገበያ አድራሻዎች፡ ቄራ ሰላም መስጂድ አስተዳደር ቢሮ በአካል አልያም በስልክ ቁጥር 0913695980//0913550963
📌 የአላህ ሀያልነት

🎙 በኡስታዝ ማህሙድ ሀሰን

🗓 ሀሙስ/ ግንቦት 15/2016 🗓

🕌 በቄራ ሰላም መስጂድ 🕌
Forwarded from Fethiya Abdul Hamid
የነገ ዝግጅት
Forwarded from Fethiya Abdul Hamid
በስራ ላይ
Forwarded from Fethiya Abdul Hamid
Forwarded from Fethiya Abdul Hamid
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የወንድማችን ሙባረክ ኽይሩ ወይም የዳሩሰላም የዳእዋ አስተባባሪ (አስተዋዋቂ) እናት ለተከታታይ ወራት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኺራ ሂደዋል
ቀብር ዝዋይ ከተማ ላይ የሚሆን ሲሆን መሄድ የምንችል ስዎች በጊዜ ብንነሳ
Forwarded from ቄራ ሰላም መስጂድ ዳሩሰላም ዛሬ በእግርህ ስትሄድ ከከበደህ ወደ መስጂድ መምጣት ነገ በ 4 ሰዉ ጀናዛ ተብለህ ትመጣለህ
''እኔ ለመስጅዴ ፅዳትና ውበት ባለቤት ነኝ'' በሚል የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

በዛሬው ቀን ግንቦት 18/2016 ዓ/ል ከፈጅር ሰላት በኋላ በዳሩ ሰላም ዳዕዋ ተቋም አስተባባሪነት የመስጅዱን ግቢ የማፅዳት ስራ ተከናውኗል። ይህንንም የፅዳት ዘመቻ በየወሩ ለማስቀጠል ተቋሙ ስራውን በዛሬው እለት ጀምሯል።

ስለሆነም የመስጅዱን ውስጣዊና ውጫዊ ፅዳቱን ለማስቀጠል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንዲሳተፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ግንቦት 18/2016 ዓ/ል
ዳሩ ሰላም ዳዕዋ ተቋም
ቄራ ሰላም መስጅድ