የብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ሰነድ ወለድ ከግሽበት እና ፖሊሲ ምጣኔ በላይ መሆኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ሰነዶች (Tbills) የወለድ ምጣኔ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱንና ለመጀመሪያ ጊዜ ከፖሊሲ ምጣኔ በላይ መሆኑን አስታውቋል፣ ይህም አዎንታዊ ምጣኔን ያመለክታል ነው የተባለው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የካቲት 6፤2017 ዓ.ም. ባሳተመው አጭር ሪፖርት መሠረት የአንድ ዓመት የግምጃ ቤት ሰነዶች የወለድ ምጣኔ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ57 በመቶ ጨምሯል።
በሐምሌ ወር 10 በመቶ የነበረው ምጣኔ በስድስት ወራት ውስጥ ወደ 15.7 በመቶ ከፍ ብሏል፣ ይህም ጥር ላይ ከተመዘገበው የ15.5 በመቶ የዋጋ ግሽበት እና የ15 በመቶ የፖሊሲ ምጣኔ አንጻር ከፍተኛው መጠን ሆኖ እንዲቀመጥ ያደረገ ነው።
በቲ-ቢል ምጣኔዎች ላይ የቅርብ ጊዜ ጭማሪ የአለም አቀፋዊ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ ) የሚሰጠውን ምክር ተከትሎ የመጣ ሲሆን፣ ይህም ማዕከላዊ ባንክ ተጨማሪ ተጫራቾችን ለመሳብ እና ሀብት ለማሰባሰብ የሚረዳ መሆኑ ነው አይኤምኤፍ ሲገለጽ የቆየው፡፡
አሁን ላይ የተቀማጭ ወለድ ከግሽበት አንጻር በከፍተኛ መጠን ቅናሽ ያለው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ በተመሳሳይ የመግስት የግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ላይ ማእከላዊ ባንኩ የሚቀበለው የወለድ ምጣኔ ከ10 በመቶ አይበልጥም ነበር፡፡
በመሆኑም ከፍ ያለ ወለድ የሚጠይቁ ተጫራቾች በጨረታው አያሸንፉም ነበር፡፡ ሆኖም ባለፉት ጥቂት ወራት ባንኩ ከፍ ያሉ የወለድ መጠኖችን እየተቀበለ መምጣቱ ነው የሚነገረው፡፡ #Capital
@PatternFin

👍1
አሊባባ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ ከነገ ጀምሮ መቀበል ሊጀም መሆኑን አሳወቀ
አለም አቀፉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም አሊባባ፣ ከሰኞ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀመር አሳዉቋል።
ይህ እርምጃ ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ በቀላሉና በአገር ውስጥ ገንዘባቸው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል።
አሊባባ ይህን ውሳኔ የወሰነው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች ይበልጥ ተደራሽ ለመሆንና በዓለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ በማሰብ ነው ተብሏል። ይህ እርምጃ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ምክንያት ለአፍሪካውያን ትልቅ እንቅፋት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ መሆኑም ተሰምቷል።
ይህም ማለት አሁን ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ በብር ገንዘባቸው ክፍያ መፈጸም ይችላሉ። አሊባባ ይህን ለማሳካት በኢትዮጵያ ካሉ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ትብብር መፍጠሩን አስታውቋል። #Capital

ብሔራዊ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 135 ብር ዋጋ መሸጡን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት መሰረት፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 135 ነጥብ 6185 ብር መሆኑን ይፋ አደረገ።
በዚህ ጨረታ 27 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳትፎ መኖሩን ገልጿል። ባንኩ አክሎም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና ከዋጋና ከውጭ ምንዛሪ መረጋጋት ጋር በሚስማማ መልኩ ተጨማሪ ጨረታዎችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ይህ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የገንዘብ ገበያውን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሪ ተገኝነትን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ትግበራ ከገባ ካለፈው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም አንስቶ የአሁን የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጨረታ ሲወጣ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል ።
በዚህም በመጀመሪያዉ ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን እና 27 ባንኮች በጨረታው ላይ መሳተፋቸውን ገልፆ ነበር። #Capital

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዲስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾመ
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የዳይሬክተሮች ቦርድ አቶ መርጊያ ባይሳን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል።
አቶ መርጊያ በተቋሙ ውስጥ ከምስረታው ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን፣ ለሰባት ዓመታትም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደነበሩ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ቦርዱ ወ/ሪት ቅድስት ስጦታውን በገበያና ግብይት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም አቶ ታምራት ተሰማን በመጋዘንና ጥራት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል።
#Capital

NBE to modernize Treasury Bill Market
The National Bank of Ethiopia (NBE) has announced plans to introduce a modernized system for government treasury bills (T-bills), aiming to make these financial instruments more accessible to citizens and investors. This initiative is part of the central bank’s broader efforts to enhance transparency, efficiency, and competitiveness in Ethiopia’s financial markets.
The announcement was made during a ceremony where the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) granted licenses to five new capital market service companies. #Capital

ኢትዮጵያ በሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሆን ተወስኗል።
በሞምባሳ የተጠናቀቀው ይህ ስምምነት የንግድ ሂደቶችን በማቅለል የድንበር ማህበረሰቦችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ ነው።
በስምምነቱ የኢትዮጵያ የድንበር ንግድ ዞን ከሞያሌ በ50 ኪሎ ሜትር እንዲሁም የኬንያ ደግሞ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚወሰን ሲሆን ነጋዴዎችም በጋራ በተስማሙበት የምርት ዝርዝር መሰረት እስከ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የንግድ ልውውጥ በወር እስከ አራት ጊዜ ድረስ ማካሄድ ይችላሉ ተብሏል።
ይህ ስምምነት የንግድ ዋጋ ጣሪያዎችን፣ የጉዞ ድግግሞሽን እና የድንበር ንግድ ዞኖችን የመሳሰሉ ጉዳዮችን በመዳሰስ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር የተገኘ ውጤት ነው።
በኬንያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ጠቀሜታ የሚያሳዩ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እ.ኤ.አ በ 2023 ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ለኬንያ ትልቁ የኤክስፖርት መዳረሻ ነበረች።
ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ በላከቻቸው ሸቀጦች 86.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የገቡት ምርቶች በዋናነት ቡና፣ ሻይ፣ ህይወት ያላቸው እንስሳት እና የዘይት እህሎች ሲሆኑ መጠናቸው 36.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱ ይታወቃል። #Capital

👍4
የአፍሪካ ልማት ባንክ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ዋስትና ለዳሽን ባንክ ሰጠ
የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን ንግድ ለማሳደግ ዳሸን ባንክን የሚያግዝ የ40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ስምምነት ተፈራርሟል።
ይህ የዋስትና መስጫ ዳሸን ባንክ የማስመጣት እና የመላክ ንግድ ፋይናንስ ፍላጎቶችን እንዲያመቻች በማስቻል የባንኩን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወሳኝ ዘርፎች የመደገፍ አቅም ያሳድጋል።
እንዲሁም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) አጀንዳን በመደገፍ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ንግድ ያበረታታል ተብሏል።
የአፍዴብ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሊአንድሬ ባሶል ይህ ታሪካዊ ግብይት ዳሸን ባንክ የንግድ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እና የአገር ውስጥ ኩባንያዎችን በፋይናንስ በመደገፍ ረገድ ያለውን መልካም ስም የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለ የግል ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ መሆኑ ለመረዳት ተችሏል።
ይህ የዋስትና መስጫ በተለይም እንደ ማዳበሪያ፣ መድኃኒት እና የእርሻ መሣሪያዎች ያሉ አስፈላጊ ዕቃዎችን ለማስገባት ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። #Capital

ኢትዮጵያ አባል በሆነችው ብሪክስ የንግድ ልውውጥ ከዶላር እየራቀ 65 በመቶ በብሔራዊ ገንዘቦች ተከናወነ
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያን ጨምሮ አባል የሆኑት የብሪክስ አገራት (ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች) በንግድ ልውውጣቸው ከአሜሪካ ዶላር እየራቁ ሲሆን ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ንግድ አሁን በአባል አገራቱ ብሔራዊ ገንዘቦች እየተከናወነ ነው።
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በብራዚል በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ በሰጡት መግለጫ ሲሆን፣ ይህ አዝማሚያ ቡድኑ በፋይናንስ ረገድ ያለውን ነፃነት ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
ላቭሮቭ አክለውም "BRICS Pay" የተባለ ገለልተኛ የክፍያ ስርዓት ለመመስረት የሚደረጉ ውይይቶች እየተሻሻሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በተጨማሪም የBRICS የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች በካዛን ጉባኤ በተሰጠው መመሪያ መሠረት በጋራ ንግድ ውስጥ ብሔራዊ ገንዘቦችን በንቃት ለመጠቀም ተስማምተዋል።
ይህ እርምጃ ብሪክስ በምዕራባውያን የገንዘብ ስርዓቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የፋይናንስ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያደርገውን የጋራ ጥረት ያሳያል።
በቅርቡ ኢትዮጵያ ለአዲሱ የልማት ባንክ (ቀደም ሲል የብሪክስ ልማት ባንክ በመባል ይታወቅ የነበረው) በይፋ አባልነት ለመቀላቀል ማመልከቻ ማስገባቷና የዚህ ሂደት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ገልፃ እንደነበር ይታወሳል። #Capital

Wegagen Bank forms strategic alliance with IFC to boost global competitiveness
Wegagen Bank, one of Ethiopia’s leading private financial institutions, has signed a landmark cooperative agreement with the International Finance Corporation (IFC), marking a significant step in its strategy to modernize operations and expand its international footprint.
The agreement was formalized during the prestigious African CEO Forum 2025, held in Abidjan, Côte d’Ivoire, an annual summit that brings together influential leaders to address Africa’s pressing economic and financial challenges. #Capital

ማዕከላዊ ባንክ ባንኮች የማገገሚያ እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አወጣ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ከባድ የገንዘብ ችግር ሲያጋጥማቸው ራሳቸውን እንዲያገግሙ የሚያስችል ዝርዝር እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ ቁጥር SBB/93/2025 አውጥቷል። ይህ መመሪያ የባንኮችን የገንዘብ መረጋጋት ለማረጋገጥ እና ቀውስ ከመከሰቱ በፊት ዝግጁ እንዲሆኑ ለመርዳት ያለመ ነው።
በአዲሱ መመሪያ መሰረት፣ ሁሉም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ባንኮች አጠቃላይ እና አስተማማኝ የማገገሚያ እቅድ ማዘጋጀት አለባቸው። ይህ እቅድ አስፈጻሚ ማጠቃለያ፣ ስትራቴጂካዊና የአመራር ትንተና፣ የማገገሚያ አማራጮችን፣ የአሰራር የአደጋ ጊዜ እቅድ እንዲሁም የግንኙነትና ይፋ የማድረግ እቅድን ማካተት ይኖርበታል።
የብሔራዊ ባንክ ዋና ዓላማ ባንኮች የገንዘብ ቀውስ ሲገጥማቸው ከብሔራዊ ባንክ ወይም ከመንግስት ልዩ ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው የማገገም አቅም እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ገልጿል።
ካፒታል ከመመሪያው እንደተመለከተው ፣ ባንኮች በቂ እና የተለያዩ የማገገሚያ አማራጮችን ማካተት አለባቸው። እነዚህ አማራጮች የካፒታል እና ስጋትን መቀነስ፣ በቂና የተለያየ የገንዘብ ምንጮችን ማግኘት፣ እንዲሁም እዳዎችን እንደገና ማዋቀርን የመሳሰሉ እርምጃዎችን ያካትታሉ። #Capital

Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
Photo
በስምንተኛው ዙር የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 136 ብር ደረሰ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው 8ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት መሰረት፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ 136.6286 ብር መሆኑን አስታወቀ።
50 ሚሊዮን ዶላር በቀረበበበት ጨረታ ላይ 11 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል አግኝተዋል።
ይህ አሁን ይፋ የተደረገው የምንዛሪ ተመን፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው 7ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ከተመዘገበው 134.95 ብር የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር፣ የብር የመግዛት አቅም በ1.6786 ብር መቀነሱን ያሳያል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎችን የሚያካሂደው በሀገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማቃለል እና የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማሟላት መሆኑ መግለፁ ይታወቃል። #Capital

የቻይና ማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ አዲስ የገንዘብ ሥርዓት ዶላርን እንደሚገዳደር ገለጹ
የአሜሪካ ዶላር ለአስርት ዓመታት ከዘለቀው የበላይነት በኋላ አዲስ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ሥርዓት እንደሚፈጠርና የቻይናው ገንዘብ ዩዋን “ባለ ብዙ ምሰሶ ባለው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ሥርዓት” ውስጥ ተወዳዳሪ እንደሚሆን የቻይናው ማዕከላዊ ባንክ አስታወቀ።
የባንኩ ገዥ ፓን ጎንግሼንግ፣ በሻንጋይ በተካሄደው የቻይና የፋይናንስ መድረክ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ የአሜሪካ ዶላር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ “በላይነቱን እንዳረጋገጠ” እና “እስካሁንም ክብሩን እንደጠበቀ” ተናግረዋል። ሆኖም፣ በአንድ ምንዛሪ ላይ “ከመጠን ያለፈ ጥገኛ መሆን” አደገኛ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
“ወደፊት ዓለም አቀፉ የገንዘብ ሥርዓት ጥቂት ሉዓላዊ ምንዛሪዎች አብረው የሚኖሩበት፣ እርስ በርስ የሚወዳደሩበት፣ እንዲሁም እርስ በርስ የሚተጋገሩበት ሁኔታ ሊቀጥል ይችላል” ያሉት ፓን፣ የዩዋን ሚና እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል። #Capital

Inflation
የኢትዮጵያ ወርሃዊ የዋጋ ግሽበት ሳይቀየር 14.4 በመቶ ሆኖ ቀጥሏል
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት በግንቦት ወር 2017 ላይ ሳይቀየር በ14.4 በመቶ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ መረጃ አመልክቷል።
ይህ አሃዝ ከሚያዝያ ወር የዋጋ ግሽበት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን መረጃው ያሳያል።
በወሩ ከተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ውስጥ የምግብ ነክ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት 12.1 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 17.8 በመቶ መመዝገቡ ታውቋል። ይህ የሚያሳየው ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ ያለው የዋጋ ጭማሪ ከምግብ ነክ ምርቶች በበለጠ ፍጥነት መጨመሩን ነው። #Capital

የነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ ተነሳ
መንግስት ላለፉት አራት ዓመታት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታወቀ።
ይህ ውሳኔ የተሰጠው በአለም አቀፍ የገበያ ዋጋ መሠረት የነዳጅ ምርቶች ዋጋ እንዲወሰን ለማድረግ ሲሆን፣ በቅርቡ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች የነዳጅ ማደያዎች ላይ አላስፈላጊ ወረፋ እንዲፈጠር ማድረጋቸውንም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።
መንግስት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገር ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ጥቅል ድጎማ በሂደት በመቀነስ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ከድጎማ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ለመውጣት አቅዶ እንደነበር አስታዉሷል።
ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ እንዳይጎዳ በሚል፣ መንግስት ከሐምሌ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እንደገና ጥቅል ድጎማ ማድረግ ጀምሮ ነበር። ይሁን እንጂ፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ልዩነት ከፍተኛ በመሆኑ ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ግብይት እንዲስፋፋ ከማድረጉም በላይ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑ ሚኒስትሩ ጠቁሟል።
በዚህም መሰረት ቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅ ከግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ፣ እንዲሁም ነጭ ናፍጣና ሌሎች የነዳጅ ውጤቶች ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ጥቅል ድጎማው እንዲቀር ተደርጎ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መሠረት እንዲወሰን ተደርጓል ብሏል።

Rammis Bank launches mobile application, card banking services to enhance digital banking experience
Rammis Bank has officially unveiled its new Rammis Mobile Application and Card Banking services, marking a significant milestone in the bank’s commitment to advancing digital banking solutions in Ethiopia. The launch event took place at the Grand Eliana Hotel and was attended by the Bank’s Board Chairman, Chief Executive Officer, senior management, and distinguished guests.
Despite being operational for just two years, Rammis Bank has demonstrated rapid growth and a strong focus on technological innovation. In their remarks, Board Chairman Rabi Hussein and CEO Ali Ahmed Ali emphasized the bank’s dedication to expanding its digital offerings and enhancing customer satisfaction through cutting-edge technology. #Capital

❤1
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
ISSUANCE OF DIRECTIVE NO. MFAD/TBOND/002/2025 | A DIRECTIVE TO REPEAL THE TREASURY BOND PURCHASE DIRECTIVE NO. MFAD/TRBO/001/2022 @PatternFin
ንግድ ባንኮች የግምጃ ቤት ቦንዶችን እንዲገዙ ያስገድድ የነበረው መመሪያ ተሰረዘ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ ያስገድድ የነበረውን መመሪያ ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ መሻሩን አስታውቋል።
ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የተወሰነ መጠን ያለው የረዥም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ ያስገድድ የነበረውን መመሪያ መሰረዙን ገልጿል።
ይህ ውሳኔ በ"የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ (የመሻሪያ) መመሪያ ቁጥር MFAD/TRBO/002/2025" የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ስራ ላይ ውሏል።
የተሻረው መመሪያ (ቁጥር MFAD/TRBO/001/2022) ባንኮች በየወሩ ከሚሰጡት አዳዲስ ብድሮች እና ቅድሚያ ክፍያዎች መጠን ላይ ተመስርቶ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ ያስገድድ ነበር።
ምንም እንኳን መመሪያው ቢሻርም፣ አንዳንድ የሽግግር ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል። በሰኔ 2017 ዓ.ም. ያልተገዙ እና በቀድሞው መመሪያ መሠረት የተመደቡ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥዎች በሥራ ላይ ይቆያሉ፣ እና ባንኮች እነዚህን ግዥዎች እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ማጠናቀቅ አለባቸው።
በተጨማሪም፣ አዲሱ መመሪያ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የወጡ ወይም በሽግግር ድንጋጌው መሠረት የተፈጸሙ የግምጃ ቤት ቦንዶች እንደ አስፈላጊነቱ በቀድሞው መመሪያ ድንጋጌዎች የሚተዳደሩ ይሆናል ተብሏል። #Capital

የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 13.9 በመቶ ዝቅ አለ
የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲክስ መረጃ ያመለክታል ። ይህ አሃዝ ከግንቦት ወር 14.4 በመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።
በሰኔ ወር ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ውስጥ የምግብ ነክ ዕቃዎች ድርሻ 11.7 በመቶ ሲሆን፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 17.3 በመቶ ደርሷል። #Capital

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 135.3 ሚሊዮን ደረሰ
የተባበሩት መንግሥታት የስነ-ሕዝብ ፈንድ (ዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ) በ2025 የዓለም ሕዝብ ቁጥር ሪፖርት ባወጣው መረጃ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ወደ 135.3 ሚሊዮን ደርሷል። ይህ አኃዝ የመጣው ኢትዮጵያ በ1985 ዓ.ም. ከጸደቀ ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ አዲስ ብሔራዊ የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ባለችበት ወሳኝ ወቅት ነው። #Capital

ኢትዮጵያ የስጋ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በካርጎ፤ ቡናና ጥራጥሬን በየብስ ወደ አፍሪካ መላክ ልትጀምር ነው
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) ተከትሎ ወደ አፍሪካ ሀገራት የምታደርገውን የኤክስፖርት ንግድ በሁለት ዋና ዋና የትራንስፖርት ሞዳሊቲዎች ልትጀምር መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ንግዱን በይፋ ለማስጀመር ለሚደረገው የሐሙስ ዕለት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም. መርሃ ግብር ከ40 በላይ ላኪዎች ተሳታፊ ሆነው ሰፊ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
የስጋና የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በዋናነት በካርጎ አገልግሎት አማካኝነት የሚላኩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Ethiopian Airlines) ካርጎ ሰርቪስ ለአፍሪካ ሀገራት በሚመጥን መልኩ ሰፋፊ መዳረሻዎችን ታሳቢ በማድረግ በቅርበት እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል እንደ ቡና፣ ጥራጥሬ የደረቅ ምርቶች ደግሞ በ የብስ ጭነት ወደ አፍሪካ ሀገራት የሚሄዱ ይሆናሉ ተብሏል። #Capital

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት የ1.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ፈታኝ በሆነው የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም የላቀ የፋይናንስና የአሠራር ውጤት በማስመዝገብ፣ ከግብር በፊት 1.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።
ይህ ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ94% ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ ባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡ በ23% በማደግ 44.0 ቢሊዮን ብር እንደደረሰና ጠቅላላ ብድርና ቅድሚያ ክፍያው ደግሞ በ19% ጨምሮ 36.2 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል።
የባለአክሲዮኖችን 21ኛዉ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ያደረገው አንበሳ ባንክ፣ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል የቅርንጫፍ መረቡን በ35 አዳዲስ መውጫዎች በማስፋፋት ጠቅላላ 341 ቅርንጫፎች ያደረሰ ሲሆን፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ ላይም ሰፊ ዕድገት አስመዝግቧል።
በዚህ አፈጻጸም የተነሳ፣ የባንኩ ጠቅላላ ንብረቶች በ25% አድገው 54 ቢሊዮን ብር ሲደርሱ፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ በ21% በማደግ 3.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን በዓመታዊ ሪፖርቱ አስታዉቋል። #Capital

❤2👍1