Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
417 subscribers
590 photos
6 videos
51 files
34 links
Banking & FInance, Stock market, forex, Fintec and e-commerce
Download Telegram
የዳታ ጥበቃና የግለኝነት መብት ነገር...

ትላንት ከወዳጆቼ ጋር መጪውን የጾም ወር ለመቀበል ምሳ ለመብላት ቀጠሮ ያዝን። የተቀጣጠርንበት ቤት የፍየል ስጋ የሚሸጥበት ሬስቶራንት ነው።

የሆድ የሆዳችንን እያወራን ምሳችንን ከበላን በኋላ ቢል ቀረበልን። ምሳ ጋባዥ ተረኛው እኔ በመሆኔ ከTelebirr ሒሳቤ ወደ XXX ባንክ ቢል ከፈዬ ተያይዘን ከሬስቶራንቱ ተያይዘን ወጣን።

ይሁንና ከደቂቃዎች በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ቡና እየጠጣን ከአንድ አንጋፋ ባንክ ስልክ ተደወለልኝ።

"አቶ ጥላሁን?!"

"አዎ ነኝ"

"ከXXX ባንክ፣ yyy ቅርንጫፍ ነው የምንደውልልህ። የቅርንጫፋችን ደንበኛ ከሆነው ZZZ ሬስቶራንት ምሳ በልተው ሒሳብ ሲከፍሉ በስህተት ሳይከፍሉት የቀረ ሒሳብ እንዳለ ነግረውን እንዲከፍሏቸው ለመጠየቅ ነው የደወልነው"

"What?! እኔ ሒሳብ የከፈልኩት በቴሌብር ነው በምን መንገድ ነው ስልኬን ያገኛችሁት?! በደንበኞች ግብይት ውስጥ ባንኩ ጣልቃ የመግባት መብት አለው? እንዴት የግለኝነት መብቴን ጥሳችሁ ከፈቃዴ ውጪ ሒሳቤን በርብራችሁ ልትደውሉልኝ ቻላችሁ? ዛሬ ላይ ሒሳብ አልከፈለም ብላችሁ መረጃዬን አውጥታችሁ ከደወላችሁ ነገ ለሽፍታ ሰጥታችሁ እንደማታስፍኑኝና እንደማታስዘርፉኝ ምን ማረጋገጫ አለኝ?" (በነገራችን እኔም የእዚሁ ቅርንጫፍ ደንበኛ ነኝ)

ከደወለልኝ የባንክ ሰራተኛ በቂ ምላሽ አላገኘሁም። ጭራሽ ደንበኛቸው በሌላ ጊዜ ተመሳሳይ ሲገጥማቸው በእዚህ መንገድ እንደሚረዷቸው ነገረኝ፣ የሰማሁትን ለማመን አልቻልኩም።

"የሬስቶራንቱ ሥራ አስኪያጅ አጠገባችን ናቸው። ፈቃደኛ ከሆኑ ያናግሯቸው"

የሬስቶራንቱን ሥራ አስኪያጅ በስልክ አወራኋቸው ችግሩ የእኔ እንዳልሆነና የአስተናጋጇ እንደነበረ፣ ሳይከፈል የቀረ ቢል እንዳለ አስረዱኝ። ከእሳቸው ጋር ጉንጭ መላፋት ስላልፈለግኩ ቀረ የተባለውን ሒሳብ ከፈልኩ። ተመሳሳይ ችግር ሲፈጠር እንዴት ሊፈታ እንደሚችል ሂደቱን ባላውቅም በጭራሽ ከፈቃዴ ውጪ ከባንክ ሊደወልልኝ እንደማይገባ ግን ጠንቅቄ አውቃለሁ።

በመቀጠል ያደረግሁት ነገር ባንኩ ለደንበኞች አስተያየት ወደ ከፈተው ነጻ የስልክ መስመር መደወል ነበር። ስልኩን ያነሳው ኦፊሰር ጉዳዬን በጥሞና ከሰማ በኋላ "ከቴሌ ብር የከፈሉትን ሒሳብ በምን መንገድ ስልክዎን ሊያገኝ ቻለ?!" ሲል ጠየቀኝ። "ያ የእኔም ጥያቄ ነው" ስል መለስኩ።

"ይህ ጉዳይ በጣም serious ስለሆነ ወደ በላይ አለቃ ላስተላልፍዎ" ሲል ከአለቃው ጋር አገናኘኝ። እኔም ከላይ የጻፍኩትን ኩነት በሙሉ አብራራሁ። አለቃው ክሴን በሙሉ መስማታቸውንና ማቀረጹን በቅርቡም አስፈላጊውን ምርመራ አድርገው እንደሚደውሉልኝ ቃል ገብተውልኝ ተለያየን። (በነገራችን ላይ ባንኩ በሚወስደው እርምጃ ካልረካሁ ሁነኛ ጠበቃ ፈልጌ በግለኝነት መብቴ ላይ ባደረሰብኝ ጥቃት ክስ የምመሰርት ይሆናል)

ደንበኛ ለባንክ ምስጢሩን የሚሰጠው ከገንዘብ እኩል እንደውም በላይ የግለኝነት ምስጢሬን ይጠብቅልኛል ብሎ በማመን ነው። ባንኮች ለፍርድ ቤት እና ሌሎች ስልጣን ከተሰጣቸው አካላት ውጪ የደንበኛ ምስጢር ለሥጋ ቤት አሳልፈው ይሰጣሉ ተብሎ አይታሰብም። ይሄንን ለማወቅ የባንክ ሰራተኛ ሳይሆን ሰው መሆን በቂ ነው።

ባንኮች ለሰራተኞቻችሁ ተገቢውን ስልጠና ብትሰጡ ከተመሳሳይ ችግርና የደንበኛ ትምምን እጦት እራሳችሁን ትጠብቃላችሁ ብዬ ጽሁፌን እደመድማለሁ።

መልካም ቀን
(Tilahun Girma)
👍4
Pattern Finance and Investment - ፋይናንስ
Photo
ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛው በተጨማሪ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ግቦቹን ለማሳካትና በገበያው ውስጥ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ለማርካት የሚውል የ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከመደበኛው የየሁለት ሳምንት ጨረታ በተጨማሪ ልዩ የጨረታ ሽያጭ ነገ ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ይህ ከፍተኛ የሆነው የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ፣ ባንኩ ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓትን ለመደገፍና የጥሬ ገንዘብ የገበያ ውስጥ ዝውውርን ለመቆጣጠር ከሚጠቀምባቸው ስልቶች አንዱ ነው።

በቅርቡ በተደረጉ የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎች ላይ ከፍተኛ የባንኮች ፍላጎት የታየ ሲሆን፣ ገበያውም ተወዳዳሪ እየሆነ መምጣቱ ይነገራል።

ይህ የ500 ሚሊዮን ዶላር የገበያ ጣልቃ ገብነት፣ በግል ዘርፉ ለሚታየው የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ ፍላጎት ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥና የብርን የመግዛት አቅም ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

ባንኩ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም የ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከመደበኛው በተጨማሪ ልዩ የጨረታ ሽያጭ ማካሄዱ እና የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 154.81 ብር መድረሱ ይታወቃል።
ባንኩ ባሳለፍነው ማክሰኞ 31 ባንኮች በተሳተፉበት የመደበኛ ልዩ ጨረታ 70 ሚሊየን ዶላር ለ21 ባንኮች መሸጡ የሚታወስ ነው፡፡
2
Best images about life...!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ብሔራዊ ባንክ የRTGS የሥራ ሰዓት እንዲራዘም ወሰነ።

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ ባንኮች መካከል የሚደረገውን ፈጣን የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት (RTGS) የሥራ ሰዓት እንዲራዘም መወሰኑን ለሁሉም የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል።

በዚህም አሁን ላይ በሳምንት 6 ቀን በቀን 9 ሰዓት ይሰራ የነበረው ሥርዓት በቀን ለሁለት ተጨማሪ ሰዓታት እንዲራዘም በማድረግ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጥ ተወስኗል።

ከፊታችን መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ የብሔራዊ ባንክ ውሳኔ የዘርፉ ተዋናዮች በተራዘመው ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ወደ ባንኮች የሚገቡና የሚወጡ የገንዘብ ዝውውሮችን ያለምንም መስተጓጎል እንዲያከናወኑ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ/ም

Via @tikvahethmagazine