✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
27.7K subscribers
90 photos
7 videos
49 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
​​​​ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
Photo
የፆመ ኢየሱስ ሦስተኛ ሳምንት #ምኩራብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ፆም ፀሎታችንን ይቀበልልን

👉 #ጌታ_ክርስቶስ ለደካሞች እጅግ ያዝን ነበር ከተናቁት ጋር መአድ ላይ ቀርቦ ተመልክተነዋል ከተጠሉት ጋር አብሮ መቀመጡንም አልጠላም ለደካሞች ቃሉን አያጠነክርም የቁጣ ጅራፉን አያነሳም

👉 #ምኩራብ በገባ ጊዜ ምን እንዳደረገ ለአፍታ እናስታውስ አይሁድ የጸሎት ቤተ የተሰኘውን ምኩራብ ሲሸጡበት ሲለውጡበት ተመለከተ ጅራፍ አበጅቶም ገበያቸውን ፈታባቸው ለሁሉ ጅራፉን ሲያነሳ ርግቦች ላይ ግን ከማንሳት ወደ ኋላ አለ ምክንያቱም  ርግብና መሰል እንስሳት አካላቸው ዱላ አይችሉም ለሞት ይሆናሉ

👉 #ጌታ_ክርስቶስ ምን እንዳደረገ ተመልከቱ ለቤቱ ቢቀናም ደካሞችን ሊጎዳ  ጅራፍ ሊያነሳባቸው አልወደደም ሲሸጡ ሲለውጡ የነበሩት ላይ ቢሆን ይህን ያደረገው ለትምህርት እንዲሆናቸው እንጂ ሊጎዳቸው አልነበረምና ሊያጠፋቸው ቢወድ በአንድ ቃል ምድር ተከፍታ በዋጠቻቸው ነበር

👉እርሱ ግን ቁጣው #ለትምህርት እንዲሆናቸው ብቻ ወደደ የኛ ቁም ነገር ግን ይህ ነው በአማኞች መካከል እንደ ርግብ የዋህ የሆኑ አሉ በጠንካራ ቃላቶች የሚደነግጡ ብዙ ናቸው በጥቂቶች በደል የተያዙ ገር አማኞች በየስፍራው ይገኛሉ

👉ጅራፍ ስናነሳ ምናሳርፈው ማን ላይ ነው አንድ አንድ ወቅቶች አሉ #ለቤተክርስቲያን ቀንተን ምናወጣቸው ቃላቶች ከሩቅ ያሉ አማኞችን ያስደነግጣል ዘለፋዎቻችን ያደክማቸዋል

👉በትጋት ያሉትን ሳየቀር ያስደነግጣል #መቅናታችን የዋሀኑን እንዳይጎዳ በማሰብ ቢሆን እንዴት መልካም ነው ቅጣታችን በጥቂቶች ኃጢአት የተያዙ ሃይማኖታዊ ሰውነታቸው ስስ የሆነባቸውን አማኞች እንዳይጎዳ እናስተውል አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከሰንበት ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​መጋቢት 22/2016 #የፆመ_ኢየሱስ ፬ኛ ሳምንት #መፃጉዕ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና ፀሎት ለምንማፀንበት ለ4ተኛ የፆም ሳምንት #መፃጉዕ በሰላም አደረሰን

👉 #መፃጉዕ ማለት የወደቀ የተጨበጠ የሰለለ መነሣት መቀመጥ የማይችል ሽባ ጎባጣ ሕመምተኛ ማለት ነው በዚህ ሳምንት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 የተዘገበውን ታሪክ የሚታሰብበት ነዉ

👉ለ38 ዓመታት የደዌ ዳኛ የአልጋ ቁራኛ ኹኖ የሚኖር አንድ ሰው ነበር በመጠመቂያ ስፍራ ሕመምተኞች በዚያ ተሰልፈው በዓመት 1 ጊዜ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሲነካው ቀድሞ የገባ ይፈወስ ነበር በዚህ ኹኔታ ሕመምተኞች ባሕሩ ከበው ሲጠብቁ አስታማሚ ያለው ቀድሞ በመጠመቅ ይፈወስ ነበር

👉ይህ #መጻጉዕ በዚህ ኹኔታ አሰታማሚ ዐጥቶ ለ38 ዓመት ኖረ ጌታ ቀርቦ ልትድን ትወዳለኽ አለው አዎ ጌታዬ ሰው የለኝም ውሃው ሲታወክ ወደ ጥምቀት የሚያገባኝ በማጣቴ አለው፡፡

👉 #መጻጉዕ ጌታን ሲያየው የ30 ዓመት ወጣት ነውና አንስቶ ተሸክሞ ይወሰደኛል ብሎ አስቦ ነበር ነገር ግን ባልጠበቀው ልትድን ተወዳለህ ብሎ ጠየቀው አዎን አለ እንግዲያው ተነሥና አልጋኽን ተሸክመኽ ኺድ ብሎ በቃሉ ተናግሮ ከበሽታው አዳነዉ ፈወሰዉ

👉አይሁድ ግን ለምን በሰንበት አልጋህን ትሸከማል በሚል ክስ አቀረቡበት ታሞ የተነሣ ፈጣሪውን ረሳ እንዲሉ #የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ማድነቅና መመስከር ሲገባው መፃጉዕም ያደነኝ ተሸከም አለኝ በማለት ከአይሁድ ጎራ ተሰልፏል በዕለተ ዐርብም የጌታን ፊት በመምታት በሰንበት ቀን አድኖኛል ብሎ ለአይሁድ እንደመሰከረ ይነገራል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሣምንቱን በሠላም በጤና ያስፈፅመን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​መጋቢት 29/2016 #በዐለ_ደብረ_ዘይት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የዘንድሮው #ዘመነ_ዮሐንስ መጋቢት 29 አምስት በአላት አንድ ላይ ዉለዋል

1ኛ ዕለተ ሰንበት
2ኛ ደብረ ዘይት ዕለተ ምፅዓት
3ኛ በዓለ ፅንሰት
4ኛ ዓለም የተፈጠረበት
5ኛ ጥንተ ትንሣኤ

👉ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን #ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም ማቴ፤24፣36)

👉 ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማንም አያውቅም ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ፣ዕለቱ ዕለተ እሑድ፣
ሰዓቱ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ቢታወቅም ብዙ ዘመነ ዮሐንስ፣ ብዙ ዕለተ እሑድ፣ብዙ መንፈቀ ሌሊት አለና ስለዚህ አይታወቅም የሰማይ #መላእክትም አያውቁትም

👉ልጅም አያውቀውም ማለቱ ልጅ ያለው ማንን ነው ከተባለ ፍጥረታትን ሁሉ ማለቱ ነው ኦሪት ዘልደት ሲል ኦሪት ዘፍጥረት ማለት እንደሆነ ሁሉ ልጅም ቢሆን አያውቅም የሚለው ቃል #መላእክትም ሌሎች ፍጥረታትም አያውቁም ማለት ነው

👉 #ከአብ በቀር የሚያውቃት የለም ማለቱ "በቀር" የሚለው ቃል ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም ይህን የመሰለ አገላለፅ 1ኛ ጢሞ፤1፣17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘለዓለም ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘለዓለም ድረስ ይሁን አሜን የሚል ቃል አለ

👉በዚህ አገላለፅ "ብቻውን" ስላለ አምላክ "አብ" ብቻ ሊመስለን ይችላል ነገር ግን ብቻውን የሚለው ከፍጥረታት ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል ምክንያቱ #ሥላሴ በአብ፤ልብነት ያስባሉ በወልድ፤ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ፤እስትንፋስነት ለዘለዓለም ይኖራሉ

👉 #አጋዕዝተ_ዓለም_ሥላሴ ፤የአለምን መጨረሻ በአብ ልብነት ያውቃሉ፤ በወልድ ቃልነት የሚነገርበት ጊዜ ሲደርስ ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ጊዜው ሲደርስ ዓለምን ያሳልፋሉ ማለት ነው።

👉ሞት በሰዎች ትከሻ ላይ የተሰየመ ነውና ምጽዓተ ክርስቶስን ብቻ አንጠብቅ ሞት ለሰው ልጅ ዕለተ ምጽዓት ነው ምክንያቱም ከሞት በኋላ ጽድቅ ሥራ መሥራት፣መፆም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ ንስሐ መግባት፣ አይቻልምና ስለዚህ ሁል ጊዜ ከኃጢአት ርቀን ሕጉን ጠብቀን ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ለመኖር ጌታችን ይርዳን

👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት ለእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ #ገብርኤል የጌታን መፀነስ የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል

👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው

👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍፁም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና

👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #መጋቢት_ሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 6/2016 #ፆመ_ኢየሱስ_6ኛ_ሳምንት_ገብርሄር

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የአብይ ፆም 6ኛ ሳምንት #ገብርሔር :- ገብር ማለት አገልጋይ፣ሔር ማለት ቸር ማለት ነው

👉በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 25 እንደተገለጸው ቸሩ ፈጣሪ እራሱን እንደ ባለፀጋ ሰይሞ ለሶስት ሰዎች #መክሊት ፀጋና በረከት እንደሰጣቸውና አንድ መክሊት የተሰጠው አንተ ያልዘራኸውን የምታጭድ ጨካኝ መሆንህን ስለማውቅ ደብቄ ያቆየሁትን መክሊትህን እንካ አለው

👉የተሰጠንን ፀጋ በተለይ ካህናት አብዝተን ለጌታ መመለስ እንደሚገባን ሲያስተምረን አንተ በትንሽ ያልታመንክ እንደሌሎቹ አብዝተህ እንኳን ልትሰጠኝ ባትችል ለለዋጮች አደራ ሰጥተህ ልታተርፈው ትችል ነበር አለው  ስለዚህ #መክሊቱን ውሰዱበት  አስር መክሊትም ላለው ስጡት ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታልና

👉ምዕመናን ከዚህ ምን እንማራለን #እግዚአብሔር በሰጠን ፀጋ ጤንነትና እውቀት ተጠቅመን በዚህ ዐቢይ ፆም የሰራዊት ጌታ የሚወደውን መልካም በጎ ምግባር ብቻ አብዝተን በመስራት ፈጣሪን ማስደሰት እንደሚገባን ያስተምረናል

👉እርሱ የሚያተርፈው ይህን ጊዜ ብቻ ነው ሌላውማ ምን ቸግሮት ስለሆነም በአንቃድዎ ልቦናና በሰቂለ ህሊና ትኩረታችንን ወደ ጌታ መልሰንና በንስሐ ታጥበን ሁል ጊዜ ልንፀልይና ልንሰግድ ይገባናል  ቸሩ አንድ አምላክ ለሰው ዘር በሙሉ ምህረቱንና ረድኤቱን ይላክልን እኛም የተሰጠንን #መክሊት አትርፈንበት ታማኝ አገልጋይ ተብለን በጌታችን ታምነን የክብሩ ወራሾች እንድንሆን አምላካችን ይፍቀድልን "አሜን"

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 13/2016 #የፆመ_ኢየሱስ_7ኛ_ሳምንት_ኒቆዲሞስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለፆሙ 7ኛ ሳምንት #ለኒቆዲሞስ መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

"ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል"

1ኛ.ኢትዮጵያዊ በተወለደበት መንደሩና አፉን በፈታበት ቋንቋው እየተፈረጀ አንተ ከየት ነህ እየተባለ በሚፈናቀልበትና በሚገደልበት ባለሥልጣን የሆናችሁት አለቆች

2ኛ.በሰው ሠራሽ ችግር ብዙ ወገን ትናንት ሰጪ ዛሬ ለማኝ በሆነባት፤ ወደ ሀብት ተጉዛችሁ ሳይሆን እሱ ራሱ ሀብት ድንገት ደርሶባችሁ በድንገቴ ሀብታም የሆናችሁ ባለፀጎች

3ኛ.ያለ ጥም ቆራጭ እውቀታችሁ ራሳችሁን አዋቂና ምሁር ስታደርጉበት ሕዝቡ ምሁራን እያለ የሚጠራችሁ የሀገሬ ምሁራን ሁላችሁ

👉በዛሬው ዕለተ #ሰንበት_ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል ወደ እሱ ባትመጡ እንኳን እስኪ እንደው አንድ ጊዜ ባላችሁበት ሁኑና ስሙት

👉እኔ ሦስት ነገሮች የተስማሙልኝ ሰው ነበርኩ ሀብት ሥልጣን ዕውቀት ይሁን እንጂ ጎዶሎ ነበርኩ

👉ጎዶሎዬም #እግዚአብሔር ነበር እሱን የምሞላበት ጊዜ ስፈልግ የራሴን ጊዜ የምተኛበትን እረፍተ ሥጋ የምወስድበትን ጊዜ አገኘሁ እናም ይኼንን ጊዜ ሰዋሁና በጨለማ በሌሊት ከጌታዬ እግር ሥር ቁጭ ብዬ ጎዶሎዬን ሞላሁት

👉ይገርማል ወደ #እግዚአብሔር ስንቀርብ ያለን ምድራዊ ሀብት ሥልጣንና ዕውቀት ሁሉ የሚወሰድብን ይመስለናል ግን እንደምናስበው አይደለም

👉እኔ ራሴ ሦስቱን ምድራዊና ጊዜያዊ ነገሮች ይዤ መጥቼ ሦስት ዘላለማዊና ሰማያዊ ስጦታዎችን ነው ይዤ የተመለስኩት

1ኛ. ምድራዊ ሥልጣን ነበረኝ የሥላሴ ልጅ የመሆን ሥልጣን ገንዘብ አደረኩኝ፤ የጌታዬን ቅዱስ ሥጋ ለመገነዝም በቃሁ

2ኛ. ምድራዊ ሀብት ነበረኝ ሰማያዊዉን የፀጋ ልጅነት ሀብት ርስተ መንግሥተ ሰማያትን የማግኘት ሀብት የዘላለማዊ ሕይወት ሀብት አግኝቼ ተመለስኩ

3ኛ. ምድራዊ ዕውቀት ነበረኝ ያውም የብሉይ ኪዳን ወደ ጌታዬ ስመጣ ግን ምሁረ ሐዲስ ሆንኩኝ #ምሥጢረ_ሥላሴን ምሥጢረ ጥምቀትን ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን የማወቅ ፀጋ ተጨመረልኝ ይላችኋል

መልካም ዕለተ ሰንበት
❖ ኒቆዲሞስ ❖

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 20/2016 #የፆመ_ኢየሱስ 8ኛ ሳምንት #ሆሣዕና

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንና መድኃኒታችንን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ስምንተኛ ሳምንት በአለ #ሆሣዕና እንኳን አደረሰን

👉 #ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም

👉 #ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው

👉 #ሆሣዕና ከጌታችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው

👉ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከኢየሩሳሌም ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት በፈለገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ፊታችሁ ባለው ሀገር ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው አምጡልኝ ምን ያደርግላችኋል የሚላችው ሰው ካለ #ጌታቸው ይፈልጋቸዋል በሉ ብሎ ላካቸው

👉ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው ሂደው ፈተው አመጡለት በዚያም የተሰበሰቡት ሁሉ #በአህዮቹ ላይ ልብሳቸውን ጎዘጎዙለት ጌታችንም በሁለቱ አህዮች ላይ ተቀመጠ ከሌሎቹ እንስሳት አህዮችን መርጦ በአህዮች ተቀምጧል

👉 #አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች ዘኁ 22 እስከ 28 ጌታችን በተወለደ ጊዜ #አህዮች_ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል

👉 #የሆሣዕና_አህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል ለምን የተዋረዱት አህዮችን መረጠ?

1 ትሕትናን ለማስተማር

👉የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ ደመና አዞ ነፋስ ጠቅሶ በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ነው ነገር ግን የመጣው #ለሰው_ልጅ ትህትናን ሊያስተምር ነውና በአህያ ተቀመጠ

2 ትንቢቱን ለመፈፀም

👉ትንቢት አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ #በእህያም_በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈፀም ነው
ዘካ፣9፥1

3 ምሳሌውን ለመግለጽ

👉ምሳሌ ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና #ጌታችንም_ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል

4 ምሥጢሩን ለመግለፅ

👉ምሥጢር በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል #በአህያይቱ ላይ ተቀምጧል

👉ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ሕግ ናትና በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም #ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው

👉ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ነው 14ቱን ምዕራፍ በእግሩ ሂዶ ሁለቱን ምዕራፍ #በአህያይቱ ሂዷል #በውርጭላይቱ ሆኖ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሱን ዙሯል 14 ምዕራፍ የአስርቱ ትእዛዛትና የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ አስሩ ምዕራፍ የአስርቱ ትአዛዛት አራቱ ምዕራፍ የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ ነው

👉 #አራቱ_ኪዳናት የሚባሉት እነዚህ ናቸው ኪዳነ ኖህ፣ ክህነተ መልከ ጼዴቅ፣ ግዝረተ አብርሀምና ጥምቀተ ዮሐንስ ናቸው

👉 #በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ
በአህያዋ ላይ ኮርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ህግ ሰራህልን ሲሉ ነው

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዘወረደ ብለን ጀምረን ሆሣእና ብለን ሱባኤያችንን እንድንፈፅም ስለረዳኸን እናመሰግንሃለን #ሰሙነ_ህማማቱንም በሠላም አስፈፅመህ #ለብርሃነ_ትንሣኤህ በሠላም አድርሰን የተባረከ #እለተ_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸ ሥርዓቶች

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ።
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
  አሰሮ ለሰይጣን፤
   አግዐዞ ለአዳም፤
   ሠላም፤
   እምይዕዜሰ፤
    ኮነ፤ 
  ፍስሐ ወሰላም፡፡
መልካም የትንሣኤ በዓል!❤️👏

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✞ የሠርግ ዝማሬ || ቃና ዘገሊላ ✞

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

       ቃና ዘገሊላ (፪)
በዚያ በሠርግ ቤት ተገኝተሻል ድንግል
ከልጅሽ ጋራ ተገኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ

እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ አልቆበት
ድንግል እናታችን ቤዛዊተ ዓለም
አንች ደረስሽለት ሆንሽው አማላጅ
       አዝ = = = = = =
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላቸው
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ
ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ
      አዝ = = = = = =
የጌታን አምላክነት የተገለፀበት
ምንኛ ታደለ የነዶኪማስ ቤት
ዛሬም ይሄው በሰርገኞቹቤት
በረከት ፈሰሰ በአምላክ ቸርነት
     አዝ = = = = = =
ውሃው ተለውጦ ወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ዘገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን
ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን

"በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበር
      የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች …"
                   ዮሐ ፪፥፩-፲፪

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
#መንፈሳዊ ጥያቄ
------------------------------------

1️⃣ "ሚካኤል" ማለት ምን ማለት ነው?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM