✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
27.8K subscribers
92 photos
7 videos
50 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
​​መጋቢት 22/2016 #የፆመ_ኢየሱስ ፬ኛ ሳምንት #መፃጉዕ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና ፀሎት ለምንማፀንበት ለ4ተኛ የፆም ሳምንት #መፃጉዕ በሰላም አደረሰን

👉 #መፃጉዕ ማለት የወደቀ የተጨበጠ የሰለለ መነሣት መቀመጥ የማይችል ሽባ ጎባጣ ሕመምተኛ ማለት ነው በዚህ ሳምንት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 የተዘገበውን ታሪክ የሚታሰብበት ነዉ

👉ለ38 ዓመታት የደዌ ዳኛ የአልጋ ቁራኛ ኹኖ የሚኖር አንድ ሰው ነበር በመጠመቂያ ስፍራ ሕመምተኞች በዚያ ተሰልፈው በዓመት 1 ጊዜ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሲነካው ቀድሞ የገባ ይፈወስ ነበር በዚህ ኹኔታ ሕመምተኞች ባሕሩ ከበው ሲጠብቁ አስታማሚ ያለው ቀድሞ በመጠመቅ ይፈወስ ነበር

👉ይህ #መጻጉዕ በዚህ ኹኔታ አሰታማሚ ዐጥቶ ለ38 ዓመት ኖረ ጌታ ቀርቦ ልትድን ትወዳለኽ አለው አዎ ጌታዬ ሰው የለኝም ውሃው ሲታወክ ወደ ጥምቀት የሚያገባኝ በማጣቴ አለው፡፡

👉 #መጻጉዕ ጌታን ሲያየው የ30 ዓመት ወጣት ነውና አንስቶ ተሸክሞ ይወሰደኛል ብሎ አስቦ ነበር ነገር ግን ባልጠበቀው ልትድን ተወዳለህ ብሎ ጠየቀው አዎን አለ እንግዲያው ተነሥና አልጋኽን ተሸክመኽ ኺድ ብሎ በቃሉ ተናግሮ ከበሽታው አዳነዉ ፈወሰዉ

👉አይሁድ ግን ለምን በሰንበት አልጋህን ትሸከማል በሚል ክስ አቀረቡበት ታሞ የተነሣ ፈጣሪውን ረሳ እንዲሉ #የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ማድነቅና መመስከር ሲገባው መፃጉዕም ያደነኝ ተሸከም አለኝ በማለት ከአይሁድ ጎራ ተሰልፏል በዕለተ ዐርብም የጌታን ፊት በመምታት በሰንበት ቀን አድኖኛል ብሎ ለአይሁድ እንደመሰከረ ይነገራል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሣምንቱን በሠላም በጤና ያስፈፅመን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 13/2016 #የፆመ_ኢየሱስ_7ኛ_ሳምንት_ኒቆዲሞስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለፆሙ 7ኛ ሳምንት #ለኒቆዲሞስ መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

"ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል"

1ኛ.ኢትዮጵያዊ በተወለደበት መንደሩና አፉን በፈታበት ቋንቋው እየተፈረጀ አንተ ከየት ነህ እየተባለ በሚፈናቀልበትና በሚገደልበት ባለሥልጣን የሆናችሁት አለቆች

2ኛ.በሰው ሠራሽ ችግር ብዙ ወገን ትናንት ሰጪ ዛሬ ለማኝ በሆነባት፤ ወደ ሀብት ተጉዛችሁ ሳይሆን እሱ ራሱ ሀብት ድንገት ደርሶባችሁ በድንገቴ ሀብታም የሆናችሁ ባለፀጎች

3ኛ.ያለ ጥም ቆራጭ እውቀታችሁ ራሳችሁን አዋቂና ምሁር ስታደርጉበት ሕዝቡ ምሁራን እያለ የሚጠራችሁ የሀገሬ ምሁራን ሁላችሁ

👉በዛሬው ዕለተ #ሰንበት_ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል ወደ እሱ ባትመጡ እንኳን እስኪ እንደው አንድ ጊዜ ባላችሁበት ሁኑና ስሙት

👉እኔ ሦስት ነገሮች የተስማሙልኝ ሰው ነበርኩ ሀብት ሥልጣን ዕውቀት ይሁን እንጂ ጎዶሎ ነበርኩ

👉ጎዶሎዬም #እግዚአብሔር ነበር እሱን የምሞላበት ጊዜ ስፈልግ የራሴን ጊዜ የምተኛበትን እረፍተ ሥጋ የምወስድበትን ጊዜ አገኘሁ እናም ይኼንን ጊዜ ሰዋሁና በጨለማ በሌሊት ከጌታዬ እግር ሥር ቁጭ ብዬ ጎዶሎዬን ሞላሁት

👉ይገርማል ወደ #እግዚአብሔር ስንቀርብ ያለን ምድራዊ ሀብት ሥልጣንና ዕውቀት ሁሉ የሚወሰድብን ይመስለናል ግን እንደምናስበው አይደለም

👉እኔ ራሴ ሦስቱን ምድራዊና ጊዜያዊ ነገሮች ይዤ መጥቼ ሦስት ዘላለማዊና ሰማያዊ ስጦታዎችን ነው ይዤ የተመለስኩት

1ኛ. ምድራዊ ሥልጣን ነበረኝ የሥላሴ ልጅ የመሆን ሥልጣን ገንዘብ አደረኩኝ፤ የጌታዬን ቅዱስ ሥጋ ለመገነዝም በቃሁ

2ኛ. ምድራዊ ሀብት ነበረኝ ሰማያዊዉን የፀጋ ልጅነት ሀብት ርስተ መንግሥተ ሰማያትን የማግኘት ሀብት የዘላለማዊ ሕይወት ሀብት አግኝቼ ተመለስኩ

3ኛ. ምድራዊ ዕውቀት ነበረኝ ያውም የብሉይ ኪዳን ወደ ጌታዬ ስመጣ ግን ምሁረ ሐዲስ ሆንኩኝ #ምሥጢረ_ሥላሴን ምሥጢረ ጥምቀትን ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን የማወቅ ፀጋ ተጨመረልኝ ይላችኋል

መልካም ዕለተ ሰንበት
❖ ኒቆዲሞስ ❖

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 20/2016 #የፆመ_ኢየሱስ 8ኛ ሳምንት #ሆሣዕና

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንና መድኃኒታችንን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ስምንተኛ ሳምንት በአለ #ሆሣዕና እንኳን አደረሰን

👉 #ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም

👉 #ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው

👉 #ሆሣዕና ከጌታችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው

👉ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከኢየሩሳሌም ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት በፈለገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ፊታችሁ ባለው ሀገር ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው አምጡልኝ ምን ያደርግላችኋል የሚላችው ሰው ካለ #ጌታቸው ይፈልጋቸዋል በሉ ብሎ ላካቸው

👉ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው ሂደው ፈተው አመጡለት በዚያም የተሰበሰቡት ሁሉ #በአህዮቹ ላይ ልብሳቸውን ጎዘጎዙለት ጌታችንም በሁለቱ አህዮች ላይ ተቀመጠ ከሌሎቹ እንስሳት አህዮችን መርጦ በአህዮች ተቀምጧል

👉 #አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች ዘኁ 22 እስከ 28 ጌታችን በተወለደ ጊዜ #አህዮች_ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል

👉 #የሆሣዕና_አህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል ለምን የተዋረዱት አህዮችን መረጠ?

1 ትሕትናን ለማስተማር

👉የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ ደመና አዞ ነፋስ ጠቅሶ በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ነው ነገር ግን የመጣው #ለሰው_ልጅ ትህትናን ሊያስተምር ነውና በአህያ ተቀመጠ

2 ትንቢቱን ለመፈፀም

👉ትንቢት አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ #በእህያም_በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈፀም ነው
ዘካ፣9፥1

3 ምሳሌውን ለመግለጽ

👉ምሳሌ ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና #ጌታችንም_ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል

4 ምሥጢሩን ለመግለፅ

👉ምሥጢር በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል #በአህያይቱ ላይ ተቀምጧል

👉ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ሕግ ናትና በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም #ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው

👉ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ነው 14ቱን ምዕራፍ በእግሩ ሂዶ ሁለቱን ምዕራፍ #በአህያይቱ ሂዷል #በውርጭላይቱ ሆኖ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሱን ዙሯል 14 ምዕራፍ የአስርቱ ትእዛዛትና የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ አስሩ ምዕራፍ የአስርቱ ትአዛዛት አራቱ ምዕራፍ የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ ነው

👉 #አራቱ_ኪዳናት የሚባሉት እነዚህ ናቸው ኪዳነ ኖህ፣ ክህነተ መልከ ጼዴቅ፣ ግዝረተ አብርሀምና ጥምቀተ ዮሐንስ ናቸው

👉 #በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ
በአህያዋ ላይ ኮርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ህግ ሰራህልን ሲሉ ነው

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዘወረደ ብለን ጀምረን ሆሣእና ብለን ሱባኤያችንን እንድንፈፅም ስለረዳኸን እናመሰግንሃለን #ሰሙነ_ህማማቱንም በሠላም አስፈፅመህ #ለብርሃነ_ትንሣኤህ በሠላም አድርሰን የተባረከ #እለተ_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥