✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
27.8K subscribers
92 photos
7 videos
51 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
​​መጋቢት 29/2016 #በዐለ_ደብረ_ዘይት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የዘንድሮው #ዘመነ_ዮሐንስ መጋቢት 29 አምስት በአላት አንድ ላይ ዉለዋል

1ኛ ዕለተ ሰንበት
2ኛ ደብረ ዘይት ዕለተ ምፅዓት
3ኛ በዓለ ፅንሰት
4ኛ ዓለም የተፈጠረበት
5ኛ ጥንተ ትንሣኤ

👉ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን #ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም ማቴ፤24፣36)

👉 ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማንም አያውቅም ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ፣ዕለቱ ዕለተ እሑድ፣
ሰዓቱ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ቢታወቅም ብዙ ዘመነ ዮሐንስ፣ ብዙ ዕለተ እሑድ፣ብዙ መንፈቀ ሌሊት አለና ስለዚህ አይታወቅም የሰማይ #መላእክትም አያውቁትም

👉ልጅም አያውቀውም ማለቱ ልጅ ያለው ማንን ነው ከተባለ ፍጥረታትን ሁሉ ማለቱ ነው ኦሪት ዘልደት ሲል ኦሪት ዘፍጥረት ማለት እንደሆነ ሁሉ ልጅም ቢሆን አያውቅም የሚለው ቃል #መላእክትም ሌሎች ፍጥረታትም አያውቁም ማለት ነው

👉 #ከአብ በቀር የሚያውቃት የለም ማለቱ "በቀር" የሚለው ቃል ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም ይህን የመሰለ አገላለፅ 1ኛ ጢሞ፤1፣17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘለዓለም ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘለዓለም ድረስ ይሁን አሜን የሚል ቃል አለ

👉በዚህ አገላለፅ "ብቻውን" ስላለ አምላክ "አብ" ብቻ ሊመስለን ይችላል ነገር ግን ብቻውን የሚለው ከፍጥረታት ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል ምክንያቱ #ሥላሴ በአብ፤ልብነት ያስባሉ በወልድ፤ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ፤እስትንፋስነት ለዘለዓለም ይኖራሉ

👉 #አጋዕዝተ_ዓለም_ሥላሴ ፤የአለምን መጨረሻ በአብ ልብነት ያውቃሉ፤ በወልድ ቃልነት የሚነገርበት ጊዜ ሲደርስ ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ጊዜው ሲደርስ ዓለምን ያሳልፋሉ ማለት ነው።

👉ሞት በሰዎች ትከሻ ላይ የተሰየመ ነውና ምጽዓተ ክርስቶስን ብቻ አንጠብቅ ሞት ለሰው ልጅ ዕለተ ምጽዓት ነው ምክንያቱም ከሞት በኋላ ጽድቅ ሥራ መሥራት፣መፆም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ ንስሐ መግባት፣ አይቻልምና ስለዚህ ሁል ጊዜ ከኃጢአት ርቀን ሕጉን ጠብቀን ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ለመኖር ጌታችን ይርዳን

👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት ለእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ #ገብርኤል የጌታን መፀነስ የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል

👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው

👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍፁም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና

👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #መጋቢት_ሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥