Nigat Media
133 subscribers
520 photos
22 videos
277 links
Nigat Media ያልተዛባ መረጃን በተለየ አቀራረብ!
👉 https://www.nigatmedia.com
👉 https://www.am.nigatmedia.com
👉 https://www.facebook.com/nigatmedia1
👉 https://www.youtube.com/nigatmedia
Download Telegram
አሁናዊ የግንባር መረጃ

#Nigat_Media | #ንጋት ሚዲያ

አዲርቃይ ግንባር

በአዲ አርቃይ ግንባር አዲ_አረጋይ እና ጀማ በተባሉ አካባቢዎች ቀኑን ሙሉ ውጊያ ሲካሄድ ውሏል። ከመሸ ደግሞ የከባድ መሳሪያ ድምፅ መሰማት መጀመሩ ነው የተሰማው።

@nigat_media1 | @nigat_media1
@nigat_media1 | @nigat_media1
ዛሬ ከ8:00 ሰዓት መከላከያ በቆቦ ከተማ  ጀምሮ መድፍ መተኮስ መጀመሩን ነዋሪዎች ገለጹ።

ቆቦ ከተማና ዙሪያዋን እስከ ትላንት ምሽት ድረስ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ጋብ ብሎ የዋለ ሲሆን አሁን መድፍ እየተተኮሰ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፣ እስካሁን #ሶስት ጊዜ ተተኩሷል ሲሉ ጨምረዋል።

#ንጋት ሚድያ

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
* ቴሌግራም  @nigat_media1
#ሙጃ!!

በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ  ሙጃ ከተማ ዙሪያ በተለይም ደግሞ ዙሮ በር ላይ ከምሳ ሰዓት ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል። 

የተኩሱ መነሻ የወረዳው ፖሊሶች የፋኖ አባላት ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ሲሆን፣ በሰዎች ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንደሰለቀረ ምንጮች ገልጸዋል።

ከሳምንታት በፊት በተመሳሳይ የወረዳው ፋኖዎች የብ/ጄነራል አሳምነው ፅጌን 4ኛ አመት መታሰቢያ አክበርው በሚመለሱበት ወቅት ፖሊሶች ትንኮሳ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ የፖሊስ  አባላት ላይ ሞትና ጉዳት መከሰቱ ይታወሳል።

#ንጋት ሚድያ

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
* ቴሌግራም  @nigat_media1
ኮማንደር ምንውየለት ባልታዎቁ ሰዎች ተገደሉ

የሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሀን ከተማ ፖሊሰ አዛዥ ኮማንደር ምንውየለት ጭንቅሎ በዛሬው ዕለት ባልታዎቁ ኃይሎች መገደላቸው ተገለፀ።

#ንጋት ሚድያ

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
* ቴሌግራም  @nigat_media1
ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ አንባ ጊዮርጊስ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል በካንፑ ውስጥ ባስራቸው የከተማዋ ወጣቶች  ላይ ግድያ እየፈፀመ መሆኑን የአይን እማኞች ለ #ንጋት ሚድያ ገለፁ።

በዛሬው እለትም አንድ ወጣትልጅን በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸኑን የገለፁት ምንጮች፣ የወረዳውና የከተማው አመራሮችም ተባባሪ ሆነው ወጣቱን እያስቀጡት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
#ሰበር_መረጃ
ቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ጥሪ አስተላለፈ!!

"በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

#ንጋት_ሚድያ

ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያኗ የገጠማት ፈተና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ አስቸኳይ  ምልዓተ ጉባኤ መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ በተለያየ ምክንያት #እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ ተብሏል።

ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤው እንዲገኙ በድጋሜ ጥሪ ተለልፏል።

በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ  አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳስቧል።

መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት / EOTC TV ነው።
#ድሮን

በአማራ ክልል ኢንተርኔት የዘጋው መንግስት የድሮን ጥቃት መፈጸም ጀምሯል‼️

#ንጋት_ሚድያ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ
👇👇👇
@nigat_media1
#ሰበር_መረጃ #መረጃ

#መርጦለማሪያም ከብልፅግና መዋቅር ውጪ ሆናለች!

የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ የምስራቅ ጎጃሟን ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማ የሆነችዉን መረጦ ለማሪያም ከተማን ተቆጣጥሯል።

በተመሳሳይ ህዝባዊ ሃይሉ ሸበልበረንታ ወረዳንም መቆጣጠሩ ሲሰማ፣ የወረዳው የመሳሪያ ግምጃ ቤተም ሙሉ በሙሉ በፋኖ ስር ሆኗል።


#ንጋት_ሚድያ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ
👇👇👇

@nigat_media1