Nigat Media
211 subscribers
534 photos
22 videos
1 file
285 links
Nigat Media ያልተዛባ መረጃን በተለየ አቀራረብ!
👉 https://www.nigatmedia.com
👉 https://www.am.nigatmedia.com
👉 https://www.facebook.com/nigatmedia1
👉 https://www.youtube.com/nigatmedia
Download Telegram
#ሰበር_መረጃ
ቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ጥሪ አስተላለፈ!!

"በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

#ንጋት_ሚድያ

ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያኗ የገጠማት ፈተና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ አስቸኳይ  ምልዓተ ጉባኤ መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ በተለያየ ምክንያት #እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ ተብሏል።

ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤው እንዲገኙ በድጋሜ ጥሪ ተለልፏል።

በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ  አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳስቧል።

መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት / EOTC TV ነው።