Nigat Media
174 subscribers
520 photos
22 videos
277 links
Nigat Media ያልተዛባ መረጃን በተለየ አቀራረብ!
👉 https://www.nigatmedia.com
👉 https://www.am.nigatmedia.com
👉 https://www.facebook.com/nigatmedia1
👉 https://www.youtube.com/nigatmedia
Download Telegram
#ሰበር ዜና

⚡️በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጓይ ቀበሌ ህዝቡ ከፋኖ ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት ከ 15 በላይ ትጥቅ ማረከ። ትጥቁን የማረኩት ከአካባቢው ሚሊሻ እና ፖሊስ መሆኑ ታውቋል።

⚡️ዛሬ ከቀኑ 7 ላይ 3 ኦራል እና አንድ ታታ አውቶብስ መከላከያ ወደ ደብረኤልያስ ገብቶ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን፣ ወደ ወረዳው የገባውን ሠራዊት እየመሩ ንፁሃንን እና ፋኖን ለማስመታት መንገድ ለመምራት ተዘጋጅተው ይጠብቁ ከነበሩ የአካባቢው ታጣቂዎች ነው ትጥቁ የተወሰደው።
ከነዚህ ሰይጣን አይሻልም ታዲያ? 💯

⚡️የትግራይ ክልል ቤተክህነት የኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቆ፣ ፓትሪያክ ቢልክም፣ ይቅርታው የረፈደ ነው በማለት እንዲህ የቤተክርስቲያንን በር በፓትሪያኩ ላይ ዘግተዋል። ለታሪክ ይቀመጥ።

⚡️የሰሜን እዝን በማጥቃት ጦርነት የከፈተውን ወያኔ የተቃወመ አንድም የሀይማኖት አባት አልነበረም ከትግራይ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እንወርዳለን ሲሉ የተቃወመ አልነበረም።

⚡️ ጅራፍ ገርፎ ይጮሀል ሆኖ ይህ አሳዛኝ ነገር ተከስቷል። መዝግቦ ማለፍ ነው። አሁንም ከነዚህ እፉኝቶች ሰይጣን ይሻላል!! 💯
ዛሬ ከ8:00 ሰዓት መከላከያ በቆቦ ከተማ  ጀምሮ መድፍ መተኮስ መጀመሩን ነዋሪዎች ገለጹ።

ቆቦ ከተማና ዙሪያዋን እስከ ትላንት ምሽት ድረስ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ጋብ ብሎ የዋለ ሲሆን አሁን መድፍ እየተተኮሰ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፣ እስካሁን #ሶስት ጊዜ ተተኩሷል ሲሉ ጨምረዋል።

#ንጋት ሚድያ

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
* ቴሌግራም  @nigat_media1
#ሙጃ!!

በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ  ሙጃ ከተማ ዙሪያ በተለይም ደግሞ ዙሮ በር ላይ ከምሳ ሰዓት ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል። 

የተኩሱ መነሻ የወረዳው ፖሊሶች የፋኖ አባላት ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ሲሆን፣ በሰዎች ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንደሰለቀረ ምንጮች ገልጸዋል።

ከሳምንታት በፊት በተመሳሳይ የወረዳው ፋኖዎች የብ/ጄነራል አሳምነው ፅጌን 4ኛ አመት መታሰቢያ አክበርው በሚመለሱበት ወቅት ፖሊሶች ትንኮሳ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ የፖሊስ  አባላት ላይ ሞትና ጉዳት መከሰቱ ይታወሳል።

#ንጋት ሚድያ

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
* ቴሌግራም  @nigat_media1
#ሙጃ

⚡️ሙጃ ላይ በፋኖና በመከላከያ መካከል እስካሁን ድረስ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ሲሆን የደረሰውን ጉዳት ማወቅም ሆነ ከሁለቱም አካል ቁስለኞችን እና የተጎዱ ሰዎችን ማንሳት አልተቻለም።

⚡️ ነገር ግን ከ #ድልብ ወደ ሙጃ ተጨማሪ የመከላከያ ሀይል እየገባ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም አካባቢውን በተደጋጋሚ የጦር ጀቶች እያንዣበቡበት እንደሆነ ከቦታው መረጃ ደርሶናል።
ኮማንደር ምንውየለት ባልታዎቁ ሰዎች ተገደሉ

የሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሀን ከተማ ፖሊሰ አዛዥ ኮማንደር ምንውየለት ጭንቅሎ በዛሬው ዕለት ባልታዎቁ ኃይሎች መገደላቸው ተገለፀ።

#ንጋት ሚድያ

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
* ቴሌግራም  @nigat_media1
[ መቸም የእኛ ቅሌት ማለቂያ የለውም ]
ከወላይታ ሶዶ የተሰማ ዜና ነው..!!

በወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ የሆነ የፖሊስ አባል፣ ውሻ የማስሮጥ ቁማር ወይንም የVirtual Betting ሱስ አለበት። እናም፣ ይህን ሱስ ለማርካት ሲል፣ በተደጋጋሚ ቁማሩን ይጫወታል።

ዛሬ ግን አልቀናውም፤ በቁማሩ ገንዘቡን ተበላ። በዚሁ ንዴት ተገፋፍቶ ከተማዋ ውስጥ አዲሱ የመምሕራን ሕንጻ ጀርባ ሄዶ በገዛ ሽጉጡ፣ ጭንቅላቱ ላይ ተኩሶ ራሱን አጥፍቷል
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት ነው

⚡️እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት መወሰኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) ገልፀዋል።

⚡️ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ የገለፁት ፕሬዘዳንቱ ፥ በዕለቱ ለተወዳጇ አርቲስት እጅጋየው ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

⚡️ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ ፥ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬቱ እንደሚበረከትላት ነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የተናገሩት።

ምንጭ - ፋና ቢ ሲ
ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ አንባ ጊዮርጊስ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል በካንፑ ውስጥ ባስራቸው የከተማዋ ወጣቶች  ላይ ግድያ እየፈፀመ መሆኑን የአይን እማኞች ለ #ንጋት ሚድያ ገለፁ።

በዛሬው እለትም አንድ ወጣትልጅን በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸኑን የገለፁት ምንጮች፣ የወረዳውና የከተማው አመራሮችም ተባባሪ ሆነው ወጣቱን እያስቀጡት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ሰበር ዜና!

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤት በቦንብ ተደበደበ‼️

⚡️የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤት በቦንብ መደብደቡን የአይን እማኞች ለእዮሃ ቲቪ ገለፀዋል።

⚡️የዋና አስተዳዳሪውን ቤት በቦንብ የደበደቡት አካላት ማንነት ያለታወቀወ ሲሆን፣ በቦንብ ፍንዳታው ምክንያት በሰው ላይ ጉዳት አልመድረሱን ተናግረዋል።

⚡️አሁን ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤትን በመከላከያ ወታደሮች እየተጠበቀ መሆኑንም ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።

⚡️ከሳምንት በፊት የደበር ብርሃን ከተማ ፖሊስ አዛዥ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው


➤ 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 :-@nigat_media1
#ሰበር

አሳዛኝ በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ በዚህ ሰዓት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ አለ።
የምስራቅ አማራ ፋኖ አሳመነው ብርጌድ የላስታ አውራጃ "አስ ከተማ" የተባለችውን ከተማ ሲቆጣጠር፣ የከተማው ህዝብ በሚገርም ሁኔታ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇👇👇
   @nigat_media1
#ሰበር_መረጃ
ቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ጥሪ አስተላለፈ!!

"በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

#ንጋት_ሚድያ

ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያኗ የገጠማት ፈተና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ አስቸኳይ  ምልዓተ ጉባኤ መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ በተለያየ ምክንያት #እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ ተብሏል።

ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤው እንዲገኙ በድጋሜ ጥሪ ተለልፏል።

በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ  አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳስቧል።

መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት / EOTC TV ነው።
#ጀግና ተዋወቁ . . .
አሰከተማ፣ ጋሸና እና መቄትን የተቆጣጠረው የምስራቅ አማራ ፋኖ አሳምነው ብርጌድ ላስታ አውራጃ ኮማንደር  . . . ይሄ ነበልባል ፋኖ እስራኤል ድረስ ሄዶ የኮማንዶ ስልጠናን በብቃት የተወጣ ባለ ቀይ ቦኔት ኮማንዶ ነው።
የዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራና የንፁኃን ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም እያሳሰብሁ፤ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች መንግስት የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት ጭምር በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ታግዞ በንፁኃን ዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እንድታወግዙና አገዛዙ ላይ ጫና እንድታሳድሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

©የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ
#ድሮን

በአማራ ክልል ኢንተርኔት የዘጋው መንግስት የድሮን ጥቃት መፈጸም ጀምሯል‼️

#ንጋት_ሚድያ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ
👇👇👇
@nigat_media1
#ሰበር_መረጃ #መረጃ

#መርጦለማሪያም ከብልፅግና መዋቅር ውጪ ሆናለች!

የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ የምስራቅ ጎጃሟን ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማ የሆነችዉን መረጦ ለማሪያም ከተማን ተቆጣጥሯል።

በተመሳሳይ ህዝባዊ ሃይሉ ሸበልበረንታ ወረዳንም መቆጣጠሩ ሲሰማ፣ የወረዳው የመሳሪያ ግምጃ ቤተም ሙሉ በሙሉ በፋኖ ስር ሆኗል።


#ንጋት_ሚድያ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ
👇👇👇

@nigat_media1
ከ50 በላይ ኤርትራውያን ጉዳት ደረሰባቸው!!

በስዊድኗ መዲና ስቶክሆልም በኤርትራ የባሕል ፌስቲቫል ላይ በተከሰተ ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን አሶሲዬትድ ፕሬስ (ኤፒ) ዘገበ።

የስዊድን ፖሊስ ቃል አቀባይ ዳንኤል ዊክዳሀል እንዳሉት ከክስተቱ ጋር በተያያዘ ከ100 እስከ 200 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ኤፒ የአገሪቱን መገናኛ ብዙኃን ጠቅሶ እንደዘገበው በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል በተከሰተው ግጭት በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

ፌስቲቫሉ እንዳይካሄድ የተቃወሙ አንድ ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ወደ ፌስቲቫሉ ስፍራ በኃይል በመግባት ድንኳኖች እና ተሽከርካሪዎችን በእሳት አያይዘዋል።

ፌስቲቫሉን በኃይል ለመበተን ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የመጡ ናቸው የተባሉት ተቃዋሚዎች ድንጋይ እና ዱላ በመጠቀም የፖሊስ ፍተሻ ጣቢያዎችን በኃይል አልፈዋል ሲል 'ኤክስፕረሰን' የተባለ የአገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።

ግጭቱን ተከትሎ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መኪኖች ሲነዱ እና ደንኳኖች ፈራርሰው አሳይተዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ መሸሻቸው ተሰምቷል። ርዕሰ መስተዳድሩ ከባህር ዳር ከተማ ሸሽተው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ አንድ ወር እንዳለፋቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ከሌሎች የክልሉ አመራሮች ጋር እንዳይገናኙ ሆነው ከጥቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሚሰጣቸውን መመሪያ እና መግለጫ እንዲያስተላልፉ ተደርገዋል ነው የተባለው።

በትላንትናው እለት በዶ/ር ይልቃል ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤም ከአዲስ አበባ ርዕሰ ምስተደሰድር ቢሮ ተዘጋጅቶ የወጣ መሆኑም ነው የተነገረው።