STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ኮምቦልቻ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤት ወስጥ የነበሩ በርካታ ቁሳቁሶች በህወሃት የሽብር ቡድን ማውደማቸውን የትምህርት ቤቱ ዕርሰ መምህር ለኢትዮዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን ገለፁ

የህወህት የሽብር ብድኑ በኮምቦልቻ ከተማ በነበረበት ወቅት ትምህርት ቤቱን የሽብር ቡድኑ አባላት የመመልመያ እና ማስልጠኛ በማድረግ ሲገለገልበት ከቆይ በሆላ በውስጡ የነበሩ ትምህርት ቤቱ በተለያዩ አካላት እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለ41 ዓመታት ያፈራቸውን ውድ እና ጠቃሚ ንብረቶችን የሚችለውን ጭኖ ያልቻለውን ደግሞ ከጥቅም ወጭ አድርጓ ትምህርት ቤቷን ለከፍተኛ ኪሳራ ደርጓታል ነው ያሉት ርዕሰ መምህር በቀለ ወርቁ።

በመጨረሻም ትውልድ የማስተማርና የመቅረጽ ስራ በማንኛውም ሁኔታ የሚቆም ስላልሆነ የመማር ማስተማር ስራውን ትምህርት ቤቷ ከነበረበት ደረጃ ዝቅ ብሉ ለመጀመር ዝግጂት እያደረገ መሆኑን ገልጠው ሁሉም የሚመለከተው አካል ትምህርት ቤቷ ከጉዳት እንዲገግም የድርሻውን እንዲወጣ ሲሉ ጥሪ አቀርበዋል።

#EETV


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

የወሎ ዩንቨርስቲ በሚቀጥሉት 90 ቀናት ለተማሪዎች ጥሪ ለማድረግ እየሰራሁ ነው አለ።

የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለኢትዮዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን እንደገለፁት በወሎ ዩንቨርስቲ ወስጥ የነበሩ ከፈተኛ ወጭ የወጣባቸው ከ30ሺ በላይ ተማሪዎች የመማሪያ አግልግሎት እየሰጡ የነበሩ ግምታቸው ከ15 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆኑ ንብረቶች መውደማቸውን ገልጸው ዩንቨርስቲውን መልሶ ትምህርት ለማስጀመር ዘረፈ ብዙ ስራዎችን እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይ ሁለትና ሶስት ወራት ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በተያያዘ መረጃም የወሎ ዩንቨርስቲ ያጋጠመውን ዘርፍ ብዙ ችግሮች ለማስተካከል የዩንቨርስቲው አመራሮች የሚመሩት ቡድን ተቋቁሞ ዩንቨርስቲው ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለመመለስና የወደሙ ንብረቶችን ለመተካት እየተሰራ እንደሚገኝ ለኢትዮዮጵያ ትምህርት ቴለቭዥን የገለፁት ደግሞ የወሎ ዩንቨርስቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ብርሀን አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው።

በመጨረሻም የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ተሾመ አየነ (ዶ/ር) ዩንቨርስቲው ለሚያደረገው የመልሶ ግንባታ ስራ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። #EETV

@NATIONALEXAMSRESULT