STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
አምቦ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ ትምህርት ማዕከል አስመረቀ።

በዩኒቨርሲቲው ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው የሚማሩበት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ ትምህርት ማዕከል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ብዙነሽ ሚደክሳ (ዶ/ር)፤ ማዕከሉ የዩኒቨርሲቲውን የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው የፈጠራ ዝንባሌያቸውን አውጥተው ለውጤት እንዲያበቁ እገዛ እንደሚያደረግ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የስቴም ፓወር ዋና ዳይሬክተር ቅድስት ገብረአምላክ በበኩላቸው ማዕከሉ ተማሪዎች የፈጠራ ስራቸውን አሻሽለው ወደ ገንዘብ በመቀየር ራሳቸውንና ሀገራቸውን ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡

የማዕከሉን ሙሉ የላብራቶሪ ዕቃዎች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከውጭ ሀገር ገዝቶ ያደራጀው ድርጅቱ ፤ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ማዕከሉን ለማገዝ ስምምነት አድርጓል።

ማዕከሉ የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው 175 ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል፡፡ #አምቦዩኒቨርሲቲ #ኢፕድ
የትምህርት ቤት የመመዝገቢያ ዋጋ ፦

የትምህርት ቤት የመመዝገቢያ ዋጋ ከወርሀዊ ክፍያ ከ25 በመቶ በላይ እንዳይበልጥ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ በሰጡት መግለጫ ትምህርት ቤቶችን ለምዝገባ ከወርሀዊ ክፍያቸው በላይ እንዳያስከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ብቻ ከክፍያቸው በላይ እያስከፈሉ በማስቸገራቸው ምክንያት አሰራሩን መፈተሽ እንዳስፈለገ የጠቆሙት ዋና ስራ አስኪያጇ አዲሱ አሰራር ግን ለዚህ መፍትሄ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

እንደ ወይዘሮ ሸዊት ገለፃ፤ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሬን በሚመለከት ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በሚደረግ ስምምነት መሠረት እንደሚሆን ገልፀዋል። #ኢፕድ

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#AddisAbaba

" ከ75 ሺ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚኒስትሪ ፈተና ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተማሪዎችን ለማስፈተን የዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋቃ።

የቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠጡት ቃል ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ በግል እና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።

- ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ተማሪዎቹን ለፈተና የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

- ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና ከመፈተናቸው አስቀድሞ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞዴል ፈተናዎችን በማዘጋጀት በወሩ እንዲወስዱ ተደርጓል። ለፈተናው የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትንም አንብበው እንዲዘጋጁ እና እንዲፈተኑ እየተደረገ ነው።

- በአማርኛ ቋንቋ የሚፈተኑ አራት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የሚፈተኑ አምስት የትምህርት ዓይነት ፈተናዎች የሚወስዱ ይሆናል። በዚህ መሠረትም ፦
👉 የሒሳብ፣
👉 የአካባቢ ሳይንስ፣
👉 አማርኛ፣
👉 አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ።

- ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን ሲሆን የተመዘገቡ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን የስም እና ዕድሜ ስህተት እንዳይኖር ማረጋገጥ እና ማስተካከል ይችላሉ።

- በየክላስተሩ ላሉ ትምህርት ቤቶች ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና በመስጠት ትምህርት ቤቶች ራሳቸው ፈተናዎችን እንዲያወጡ እና እንዲፈተኑ ይደርጋል።

- በአዲሱ ሥርዓት ትምህርት በየምዕራፉ ማጠናቀቂያ ላይ ለተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። ለዚህም አንደኛ ምዕራፍ የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛ ምዕራፍ የሚባለው ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ነው።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያጠናቅቁት ስድስተኛ ክፍል ላይ ስለሆነ የሚኒስትሪ ፈተናው ተማሪዎች ከታች ጀምረው ራሳቸውን እያነጹ እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም አለው።

- የመማሪያ መጽሐፍት በሚፈለገው ልክ ሀገር ውስጥ አለመገኘት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ የሚመጡ መጽሐፍት የመዘግየት ሁኔታ አለ።

- የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት የሚወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም እንደ ቢሮ #ከሰኔ አጋማሽ በኋላ ለመስጠት ዝግጁ ነን።

#ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ቦንጋ

ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ትምህርት መስክ የተማሩ ተማሪዎች ሊመረቁ ነው።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን በ " ቡና ሳይንስ " የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርት ኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት ሸቀጥ በመሆኑ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ 37 ተማሪዎችን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ ይመረቃሉ ብሏል።

ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ያበረከተች ሀገር ብትሆንም እስካሁን ድረስ የቡና ትምህርት መስክ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት አዳጋች ሆኖ ነበር ያለው ተቋሙ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቡና ሳይንስ ትምህርት ክፍል እራሱን ችሎ በ2012 ዓ.ም እንዲከፈት ማድረጉን አስታውሷል ።

በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመርመር ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ቡናን በትምህርትና ምርምር አስደግፎ ለመምራት ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የቡና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል በማቋቋም ነው ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኘው።

በሚቀጥለው ዓመት በሁለተኛ ዲግሪ በቡና ሳይንስ ተማሪዎች የሚመረቁ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ጊዜትም የቡና ሳይንስ ትምህርት መስክን በዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ ማስተማር እንደሚጀምር ዶክተር ጴጥሮስ ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ካለው 200 ሄክታር መሬት ውስጥ በ150 ሄክታሩ ላይ የግብርና ምርቶችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

#ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆንና አስተዳደራዊ ነፃነት

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆናቸው አስተዳደራዊ ነፃነት
እንዲኖራቸው ያደርጋል ሲሉ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ገለጹ።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ አደረጃጀታቸው የምርምር እና የመማር ማስተማር ሂደቱን በነፃነት እንዲያከናውኑ የሚረዳቸው እንደሚሆን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ራስ ገዝ ከሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ከአስተዳደራዊ ነፃነት በተጨማሪ የአካዳሚክ ነፃነት እንደሚሰጥ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ራስ ገዝ ለመሆን ዝግጅት እያደረጉ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካካል አንዱ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ካሪኩለምን ጨምሮ አስተዳደራዊ አደረጃጀት ላይ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ሃብት ማመንጨት ላይ ለመስራት የተቋማቱን ኢንተርፕራይዞች በተገቢው መልክ እያደራጁ መሆኑን ጠቁመዋል። #ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
180 ሺህ የሚጠጉ ዕጩ ተመራቂዎች በቀጣይ ወር የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና መዘጋጀቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና፣ ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወቃል፡፡

"የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል" ያሉት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱንም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። #ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠውን አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወንደወሰን ኢየሱስወርቅ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ከተመዘገቡት ውስጥ 503,812 ተማሪዎች የሶሻል ሳይንስ እና 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30/2015 ዓ.ም በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ #ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

“ኬኖ” ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመሰጠቱ ተገለጸ


“ኬኖ” ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመስጠቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ቤቲንግ ቤቶችና ሌሎችም ቁጥር በማስገመት ለሚያጫወቱት “ኬኖ” አስተዳደሩ ፈቃድ ያልሰጠ ሲሆን፣ ይህን ጨዋታ በሚያጫውቱ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

በቀጣይም ጨዋታውን ሲያጫውቱ በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

#ኢፕድ እንዳጣራው “ኬኖ” ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች እያዘወተሩት የሚገኝና በብዛት ብራቸውን የሚከስሩበት የቁማር ዓይነት ነው፡፡

(ኢ ፕ ድ)
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እየተቀበለ ነው


ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐ-ግብር የሚማሩ ስድስት ሺህ ተማሪዎቹን እየተቀበለ መሆኑን አስታወቀ:: የተማሪዎች ቅበላ ጥር ስድስት ቀን 2016 ዓ.ም መጀመሩ ተመላክቷል::

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ብርሃን ደጀን ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በክልሉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም በመጠቀም ዩኒቨርሲቲው ከጥር ስድስት ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

በክልሉ በነበረው የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት በመደበኛው የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዳልቻለ አስታውሰው፤ አሁን ላይ በአማራ ክልል ያለውን አንጻራዊ ሰላም በመጠቀም ዩኒቨርሲቲው ስድስት ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት እያደረገ ነው ብለዋል።

#ኢፕድ
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot