STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#WolloUniversity

የወሎ ዩንቨርስቲ በሚቀጥሉት 90 ቀናት ለተማሪዎች ጥሪ ለማድረግ እየሰራሁ ነው አለ።

የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለኢትዮዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን እንደገለፁት በወሎ ዩንቨርስቲ ወስጥ የነበሩ ከፈተኛ ወጭ የወጣባቸው ከ30ሺ በላይ ተማሪዎች የመማሪያ አግልግሎት እየሰጡ የነበሩ ግምታቸው ከ15 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆኑ ንብረቶች መውደማቸውን ገልጸው ዩንቨርስቲውን መልሶ ትምህርት ለማስጀመር ዘረፈ ብዙ ስራዎችን እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይ ሁለትና ሶስት ወራት ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በተያያዘ መረጃም የወሎ ዩንቨርስቲ ያጋጠመውን ዘርፍ ብዙ ችግሮች ለማስተካከል የዩንቨርስቲው አመራሮች የሚመሩት ቡድን ተቋቁሞ ዩንቨርስቲው ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለመመለስና የወደሙ ንብረቶችን ለመተካት እየተሰራ እንደሚገኝ ለኢትዮዮጵያ ትምህርት ቴለቭዥን የገለፁት ደግሞ የወሎ ዩንቨርስቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ብርሀን አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው።

በመጨረሻም የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ተሾመ አየነ (ዶ/ር) ዩንቨርስቲው ለሚያደረገው የመልሶ ግንባታ ስራ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። #EETV

@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ለ2014 ዓ.ም ነባርና አዲስ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ኤክስቴሽን ተማሪዎች በሙሉ

ተቋርጦ የነበረው የ2014 ዓ.ም የ1ኛ ሴሚስተር የኤክስቴንሽን ት/ት ከየካቲት 05/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቀጥል የተወሰነ በመሆኑ ካሁን በፊት የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የተመዘገባችሁበትን ስሊፕ በመያዝ በግንባር ቀርባችሁ እንድታረጋግጡ፡ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 28-29/2014 ድረስ ያለ ቅጣት ምዝገባ የሚካሄድ በመሆኑ በተጠቀሰው ቀን ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ርቀትና ተከታታይ ትምህርት ዳይሬክቶሬት


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT