STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
መንግስት የሴት ተማሪዎች ወሊድ ፈቃድ ረቂቅ መመሪያን እንዲሰርዝ ተጠየቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎች ምዘናና የክፍል ዝውውር ረቂቅ መመርያ ማዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ከአንድ ሳምንት በፊት ባወጣው ዘገባ የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪ ከ15 ቀናት በላይ በወሊድ ምክንያት ከትምህርቷ የምትቀር ከሆነ በዚያው የትምህርት ዘመን ትምህርቷን መቀጠል እንደማትችል የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

በዚህ ረቂቅ መመሪያ መሰረትም ተማሪዋ ለ15 ተከታታይ ቀናት በወሊድ ምክንያት የምታርፍ ከሆነ ትምህርቷን መቀጠል አትችልም፡፡ ተማሪዋ ለ16 ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ቀናት የምትቀር ከሆነ በዚያ ዓመት ስትከታተል ከነበረው ትምህርት የምትታገድ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ሆኖም ተማሪዋ በቀጣዩ ዓመት ትምህርቷን መቀጠል የምትፈልግ ከሆነ፣ ‹‹ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ›› መቀጠል እንደምትችል ይፈቅዳል ሲል በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ይህን ረቂቅ መመሪያ የተቃወመ ሲሆን መመሪያው ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ሴቶች የወሊድ ፈቃድ መብትን በእጅጉ የሚገድብ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ይህ ረቂቅ ሕግ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን አወንታዊ የድርጊት ድንጋጌዎች የሚንድ ብቻ ሳይሆን የሴቶችን መሠረታዊ የመማር መብቶችም በግልጽ የሚነፍግ ስለሆነ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቋሙን እንደገና እንዲያጤነው ሲል ጠይቋል፡፡


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ሀዋሳዩኒቨርሲቲ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በፈተና አወጣጥና የተማሪ ምዘና ዘዴዎች ላይ ለመምህራኑ ስልጠና ሰጠ።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በስልጠናው መርሃግብር መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት መምህራን በጉዳዩ ዙሪያ ምንም እንኳ ልምድና ዕውቀት ቢኖራቸውም ወቅቱን ያገናዘበ የመነቃቅያ ስልጠና አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ስልጠናውን ማዘጋጀታቸን አስረድተዋል።

ስልጠናው የተዘጋጀው ከመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ጋር በተደረገ ውይይት በተለይም በወጣት መምህራን ዘንድ የትምህርት አሰጣጥና የፈተና አዘገጃጀት ላይ ክፈተት መኖሩን በተማሪዎች ከተሰጠ ጥቆማ በመነሳት እንደሆነ ገልፀው ዓላማውም መምህራን በዒላማና መሠረታዊ የትምህርት ይዘትና ዝግጅት ላይ የተመሠረተ የሥነ-ማስተማር እና ምዘና ዘዴዎችን በመከተል ተማሪዎቻቸውን በሀገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አጋዥ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ለማስቻል መሆኑን አብራርተዋል።

በኮሌጁ የጥራት ማሻሻያ ኃላፊና የሰልጠናው አስተባባሪ ዶ/ር በየነ ተክሉ በበኩላቸው ጥራት የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን ጠቁመው የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በመከተል ከተማሪዎችና የኮሌጁ ማኅበረሰብ ጋር በመወያየት መጠነ ሰፊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ኮሌጁ ተማሪዎቹን በማሳለፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ቢሆንም ውጤቱን አስጠብቆ ለመቀጠል የመምህራን የሙያ ክህሎት ስልጠና አጋዥ መሆኑ ስለታመነበት ስልጠናው መዘጋጀቱንም ኃላፊው አብራርተዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ማስታወቂያ
**
ኅዳር 20 ቀን 2016 ዓም

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች  እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ነባር የሬሜዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 08-09/2016 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች - በዋናው ግቢ 
ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች - በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ
======
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

• የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒውን፣
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒውን
• አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ፣ የስፖርት ትጥቅ

ከላይ ተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
     
ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

                        ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
                        ሁሌም ለልህቀት!
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DambiDolloUniversity

በ2015 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታትላችሁና የማለፊያ ነጥብ ያመጣቹ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችው አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 10 እና 11/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

፨ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ ነገሮችን ከማስታወቂያው ያንብቡ‼️


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ በላይ አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱን አስታወቀ
*

መቐለ
ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን ከ1 ሺህ በላይ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ትካቦ ገብረስላሴ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከህዳር 28 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት አድርጓል።

“ዩኒቨርሲቲው አዲሀቂን ጨምሮ በሁለት ጊቢዎቹ ተማሪዎቹን በመቀበል በማህበራዊና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች ለማስተማር ተዘጋጅቷል” ብለዋል።

የመማሪያ፣ መመገቢያና ማደሪያ ክፍሎች ጨምሮ በጊቢ ጽዳትና በአረንጓዴ ስፍራዎች ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።

የተገኘው ሰላም የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አሁን ላይ ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን አመልክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፈው ሳምንት 2ሺህ 35 ተማሪዎችን በአንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ማስመረቁን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolaitaSodoUniversity

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስዳቹህ ማለፊያ ነጥብ በማምጣት ወደ ወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ የተመደባቹህ አዲስ ተማሪዎች፣በ2015ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተር ጀምራቹህ በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal የሞላቹህ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ(Remedial) ትምህርት ተከታትላቹህ ማለፊያ ነጥብ ያመጣቹህ ነባር የሪሜዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 03 እስከ 04/2016ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

💥 የድህረ ምረቃ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባም በተመሳሳይ ቀን ነው‼️

[ተጨማሪ መረጃ ከማስታወቂያው ያንብቡ]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2016_SPHMMC_UG_Candidates_Final_compiled_result.pdf
684.4 KB
በቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለ2016 የትምህርት ዘመን የሕክምና ትምህርት ለመከታተል የቃል እና የጽሑፍ ፈተና አልፈው የተመረጡ ተማሪዎች ሥም ዝርዝር


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AASTU

በ2016 ዓ.ም በሁለት ዙር የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) የወስዳችሁና የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመዘገባችሁ የአንደኛ ዓመት የማስተርስ እና የፒ.ኤች.ዲ. ተማሪዎች ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 25/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተቋሙ በመገኘት የምትማሩበት ትምህርት ክፍል በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AmboUniversity

በ2016 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች፤ እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በሪሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም) በዩኒቨርሲቲው ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ዉጤት አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነዉ ታህሳስ 4-5/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋን።

በተጠቀሰው ቀናት ብቻ በማህበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ በዋና ካምፓስ ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ የተመደባችሁ አምቦ ከተማ ሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ተብሏል።

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ስትሄዱ ከ8 -12ተኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃ በሙሉ ዋናውንና ኮፒ፤ 3*4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ ፤ አንሶላ፤ ብርድልብስ፤ እንዲሁም ትራስልብስ ይዛችሁ መሄድ እንዳትዘነጉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2016 ዓ.ም የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመከታተል ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ያመለካታችሁ ወይም በሌላ ዩኒቨርሲቲ ፈተና ወስዳችሁ፥ የድህረ-ምረቃ ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ አመልካቶች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከህዳር 24 እስከ 26/ 2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የድህረ-ምረቃ ፈተና (GAT) በየፕሮግራሙ ያለፉ አመልካቶች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ በሁሉም ፕሮግራም ተማሪ መቀበል አለመቻሉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ በመደበኛው መርሐግብር በ2ኛ ዲግሪ ቁጥራቸው ሦስት እና ከዚያ በላይ በሆነባቸው አምስት ፕሮግራሞች ትምህርት የምንጀምር መሆኑ ተጠቁሟል።

ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር ተማሪ የሚቀበልባቸው የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦

- MSc in Agricultural Economics
- MSC in Information Technology
- MBA General
- MSc in Environmental Health
- MPH in Nutrition

የሚፈለገው ቁጥር ባልተሟላበት ፕሮግራሞች ውስጥ ያላችሁ አመልካቶች የመግቢያ መስፈርቱን ወደምታሟሉበት ፕሮግራም መዟዟር የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ንግድ ባንክ🤔

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ላይ የአገልግሎት በወር 5 ብር መቁረጥ ጀምሯል።

ከትላንት ጀምሮ ለበርካታ ሰዎች የወርሃዊ አገልግሎት በሚል አምስት ብር መቆረጡን የሚያመላክት መልክት እየተላከ ነው።
#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው፡፡

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ህዳር 24 እና 25/2016 ዓ.ም ጥሪ ያደረገው ዩኒቨርሲቲው፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ከአዲስ አበባ መርካቶ እና ቃሊቲ መናኸሪያዎች የትራንስፖርት አገልግሎት በማዘጋጀት ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2016 ዓ.ም በተቋሙ ስልጠና ለመከታተል ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁና ያለፋችሁ አመልካቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

ኢንስቲትዩቲ ለመሰልጠን ያመለከታችሁ ስም ዝርዝራችሁን በተቋሙ የቴሌግራም ገፅ ላይ መመልከት ትችላላችሁ፦ https://t.me/tticommunication

ተመዝግባቸሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ስማችሁ በዝርዝሩ ያልተካተተ ቅሬታችሁን ዛሬ ህዳር 24/2016 ዓ.ም በተቋሙ በመገኘት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MizanTepiUniversity

በ2016 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችው ተማሪዎች፤ የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 03 እና 04/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሚዛን አማን በሚገኘው ዋናው ጊቢ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ጊቢ

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

ከ9ኛ እስከ 2ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
ዘጠኝ 3 x 4 የሆ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
የስፖርት ትጥቅ፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot