STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.1K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ወሎ ዩንቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል በሚል በተለያዩ ግሩፖች የሚዘዋወረው መረጃ ትክክለኛ አይደለም ‼️

ወሎ ዩንቨርሲቲ ከቀናት በፊት የመደበኛ ተማሪዎችን መግቢያ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ከገለፀ በኋላ ዩንቨርሲቲው ምንም ዓይነት አዲስ የጥሪ ማስታወቂያ አላወጣም።

ለግቢው ተማሪዎች ዩንቨርሲቲው በይፋ ጥሪ ሲያደርግ ተከታትለን የምናሳውቃቹህ ይሆናል።

ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሼር ከማድረጋቹህ በፊት የመረጃውን ምንጭ አጣሩ🙏

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#EntranceResult

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤትን ቶሎ ለማድረስ በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ የተማሪዎቹ #ውጤት እስከ መስከረም መጨረሻ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል።

ውጤት በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የሚጠበቅ ቢሆንም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ የዩንቨርሲቲ ምርጫ ፎርም እየተሞላ እንደሆነ ተማሪዎች ገልፀውልናል። ይህ አሰራር የተለመደ ቢሆንም በርካታ ተማሪዎች ግር መሰኘታቸውን ታዝበናል።

ውጤት ከማወቃቹህ በፊት የዩንቨርሲቲ ምርጫ ፎርም ብትሞሉም የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጎ መቁረጫ ነጥብም ይፋ ከተደረገ በኋላ ወደ መንግስት ዩንቨርሲቲዎች የሚያስገባቸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩንቨርስቲ ምርጫቸውን በድጋሚ ይስተካከሉ ዘንድ ሁለተኛ እድል ይሰጣል።( በተለመደው አሰራር መሰረት)

አሁን ላይ የዩንቨርሲቲ ምርጫ ፎርም የምትሞሉ ተማሪዎች የምታስመዘግቡትን ውጤት ገምታቹህ የምትፈልጓቸውን ዩንቨርሲቲዎች በጥንቃቄ ሙሉ። በቅርቡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ውጤት ይፋ ሲደረግና መቁረጫ ነጥብም ሲገለፅ ውጤት የሚመጣላቹህ ተማሪዎች ድጋሚ የማስተካከል እድል እንደሚሰጣቹህ እንጠብቃለን።

⭕️ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሜዲያል ትምህርት ተከታትላቹህ ያለፋቹህ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት በተማራችሁበት የከፍተኛ ተቋም ተመድባቹህ ከ2016 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር ጥሪ ተደርጎላቹህ ፍሬሽማን ኮርስ ትማራላቹህ።

⭕️ በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪሜዲያል ትምህርት ተከታትላቹህ #ያለፋቹህ ተማሪዎች ወደ መንግስት ዩንቨርሲቲዎች የመግባት እድላቹህ እጅግ ጠባብ ቢሆንም ፍሬሽማን በየትኛውም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መማር እንደምትችሉ መገለፁ ይታወሳል።

ውጤትን አስመልክቶ በሰሞኑን በርካታ ያልተረጋገጡ መረጃዎች የሚበዙበት ጊዜ በመሆኑ ታማኝ የመረጃ ምንጮችን ብቻ ተከታተሉ‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
እ.ኤ.አ. እስከ 1956 ድረስ በፈረንሳይ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች ወይን ይቀርብ ነበር።

ወይን መጠጣት በትምህርታቸው ውስጥ ጤናን እና ትኩረትን እንደሚያሻሽል ይታመን ነበር.። ሁሉም ተማሪ በቀን ግማሽ ሊትር ወይን ይጠጣ ነበር ።

ከ 1956 በኋላ ግን ወይን በወተት ተተካ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የ2016 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 28 እና 29/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን አሳውቋል።

የሬሜዲያል ትምህርታችሁን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ እስከሚደርግላችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#TTI

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የነባር መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 01 እና 02/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የነባር የማታ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 22 እስከ 24/2016 ዓ.ም መሆኑም ተገልጿል።

የመደበኛ እንዲሁም የማታ መርሐግብር ተማሪዎች ትምህርት ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

(የኢንስቲትዩቱ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአዲስ መልክ የተደራጀው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምስረታ ማብሰሪያ ስነ-ስርዓት በቀጣይ ሳምንት ያካሒዳል።

ዩኒቨርሲቲው መስከረም 24/2014 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውሳኔ መሠረት “ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ እንዲደራጅ መደረጉ ይታወቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ለተቋሙ ምስረታ የሚሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሷል።

በዚህም መስከረም 23 እና 24/2016 ዓ.ም የምስረታ ማብሰሪያ ስነ-ስርዓት እንደሚያካሒድ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ስያሜዎች ከ60 ዓመታት በላይ የመማር ማስተማር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም በጦርነት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠውና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ያልቻሉ ተማሪዎቹ ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።

በዚህም ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ጥቅምት 05 እና 06/2016 ዓ.ም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ በነበራችሁበት ግቢ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

በ2013 ዓ.ም በአንደኛ ዓመት ተመድባችሁ በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያልጀመራችሁ እንዲሁም አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት ሚኒስቴር በሚያስቀምጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ጥሪ እንደሚደረገ ተገልጿል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolaitaZone

• በዎላይታ ዞን የተመዘገበው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት አስደንጋጭ ነው ተብሏል።

• ፈተናው ከወሰዱት ከ31 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ20 ፐርሰንት በታች የማለፍ ምጣኔ መመዝገቡ ተነግሯል።

በዎላይታ ዞን ፤ የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በተለየ መንገድ መሰጠቱ ዝቅተኛ ዉጤት እንዲመዘገብ ምክኒያት ሆኗል ተባለ።

እንደ ሀገር የገጠመን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ይቻል ዘንድ በሀገር ደረጃ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል።

በተለይም በፈተና ስርአቱ እየታዩ የነበሩ ስህተቶችን ለመቅረፍ በማስብ አዳዲስ የፈተና ስርአቶች ተዘርግተዋል።

ይህን በመከተል የወላይታ ዞን በዚህ አመት የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን በተለዬ መልኩ መፈተኑ ተገልጿል።

የመምሪያዉ የመምህራንና የትምህርት ልማት ዳይሬክተር ቡድን መሪዉ አቶ ኢሳያስ ሀይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት ፤ ተማሪዎችን አጥርቶ ለማሳለፍ የፈተና ጣቢያዉን በመቀየር በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መፈተናቸዉ የመጠነ ማለፉን ዝቅ ማድረጉን ያነሳሉ።

አቶ ኢሳያስ ፤ በዚህ አመት የታየዉ ከ20 ፐርሰንት በታች የማለፍ ምጣኔ መሆኑን ገልጸው ይህ ለብዙዎች አስደንጋጭ መሆኑን አንስተዋል።

ካሁኑ ችግሩን ቀርፎ ጥሩ ዉጤት  ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት መጀመሩን ገልጸዋል።

ከሰላሳ ሶስት እስከ ሰላሳ አምስት ፐርሰንት  የነበረዉ የማለፊያ ዉጤት በዚህ አመት ወደሀምሳ ፐርሰንት ከፍ ማለቱ ያላለፉ ተማሪዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ ትልቅ ምክኒያት መሆኑንም አንስተዋል።

ሀላፊዉ ይህ የማለፊያ ዉጤትና የፈተና አሰጣጥ የሚቀጥል መሆኑን አዉቀዉ ተማሪዎች ካሁኑ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዉል።

መረጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
#ማስታወሻ

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ኢንስቲትዩት- የፈተና ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው ፈተና በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይከናወናል።

ለፈተናው የተመረጡ ተፈታኞች ከመስከረም 21 እስከ 25/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የGAT መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ላይ ምዝገባ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ከመስከረም 23 እስከ 25/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት የሙከራ ፈተና ይሰጣል።

(ለመመዝገብ እና ፈተናውን ለመውሰድ የይለፍ ቲኬት ለማግኘት ሊከተሏቸው የሚገቡ ቅደም-ተከተሎች ከላይ ተያይዟል።)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ ከምሽት አንስቶ ለሶስት ቀናት በክልል ደረጃ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከጥቅምት 2 ጀምሮ የሀዘን ቀን እንደሚታወጅ ይፋ አድርገዋል።

" 3 የብሄራዊ ሀዘን ቀን ይኖሩናል " ያሉት ጄነራል ታደሰ ይህ ሁሉንም ትግራዋይ የሚመለከት ሀዘን ነው ብለዋል።

" ሁሉም ትግራዋይ በትግራይ ውስጥ ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ፤ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኘው ለሰማዕታት ክብር የሚሰጥበት የሃዘን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ጄነራል ታደሰ የሃዘን ቀኑ ጥቅምት 2 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ #ከምሽት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ሰማዕታትን የተመለከቱ መልእክቶች እንደማያስተላልፉ ተነግሯል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር ይህን የሀዘን ሂደት የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#Update

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እየተቀበሉ የሚገኙት ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሸኟቸውን ነባር ተማሪዎቻቸውን ነው።

ወለጋ ፣ አሶሳ ፣ መቱ እና ወ/ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተማሪዎቻቸውን መቀበል ከጀመሩ ተቋማት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የገጽ-ለገጽ ትምህርት መስከረም 23/ 2016 ዓ.ም እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

ከዚህ ከተማሪዎች ጥሪ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ሰላም በራቃቸው የአማራ ክልል ቀጠናዎች ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በክልሉ ያለው ሁኔታ ተማሪዎች በተባለው ቀን እንዲገኙ ላያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር ከወዲሁ በጉዳዩ ላይ እንዲያስብበት መጠየቃቸው ይታወሳል።

ተማሪዎቹ በተከሰተው የፀጥታ ችግር መንገድ የመዘጋጋት፣ የተወሰኑ ቦታዎች ሙሉ ኔትዎርክ አለመስራት፣   የዳታ ኢንተርኔት መዘጋት፣ የደህንነት እጦት፣ የወላጆች ፍራቻና ሌሎችም ችግሮች ተደራርበው ጥሪውን ሰምቶ በተባለው ጊዜ ለመድረስ እንደሚያዳግት ማስገንዘባቸው ይታወሳል።

በተለይ በትግራይ ክልል እንደነበረው ተማሪዎች ከትምህርት እንዳስተጓጎሉ ፍርሃት እንዳላቸው ነው የገለፁት።

ከዚህ ባለፈ በአማራ ክልል ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን አለመጥራታቸው በተመሳሳይ አመት ከሚማሩ አቻ ጓደኞቻቸው ወደኃላ እንዳይቀሩ እንደሚያሰጋቸው በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ተማሪዎች ገልጸዋል። እነዚህም ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበው ነበር።

እስካሁን ተማሪዎች ባነሷቸው ስጋቶች ዙሪያ ምላሽ / ማብራሪያ የሰጠ አካል የለም።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በዘንድሮ ዓመት ከዚህ ቀደም የነበረውን የተዛነፈ የትምህርት ካላደር ለማስተካከል እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ብሄራዊ ፈተና፣ የመውጫ ፈተና ታሳቢ በማድረግ ጭምር የትምህርት ዓመቱ በአግባቡ እንዲሄድ ለማድረግ የተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል።

ፎቶ፦ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ የሚያሳይ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot